Telegram Web Link
#በቸርነትህ_ዓመታትን_ታቀዳጃለህ
መዝ 65፥11

ስለሁሉ እግዚአብሔር ይመስገን እንደ ኃጥአታችን ያይደለ እንደቸርነቱ የንስሃ ጊዜ የፍሬ ጊዜ ሰጥቶናልና እናመሰግነው ዘንድ ይገባናል፡፡ ምስጋናችንም ይህን የተወዳጅ ሐዋርያ የቅዱስ ጳውሎስን ቃል በመተግበር እንግለፅ፡፡

“ፊተኛ ኑሮአችሁን እያሰባችሁ እንደሚያታልል ምኞት የሚጠፋውን አሮጌውን ሰው አስወግዱ፥ በአእምሮአችሁም መንፈስ ታደሱ፥ ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ።” ኤፌ 4፥22


🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼 #መልካም_አዲስ_አመት🙏 🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

ለመቀላቀል 👇👇👇👇
@Enatachn_mareyam  
@Enatachn_mareyam
Forwarded from አብሰራ ገብርኤል ለማርያም (♱ ባሕራን ♱)
                          †                          

🌼 [ አዲስ ዓመት ማክበር ማለት ! ] 🌼

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊
       
" ለእግዚአብሔር ክብር ብሎ ሰውን መውቀስ ... "
.........

" ለእግዚአብሔር ክብር ብሎ ሰውን መውቀስም አለ፡፡ ከእናንተ መካከል ፦ " እንዴት ሆኖ ?  እርግጥ ነው ብዙውን ጊዜ ሠራተኞቻችንን እንወቅሳለን ለእግዚአብሔር ክብር ብሎ መውቀስስ እንደምን ያለ ነው ? " የሚል ሊኖር ይችላል፡፡

አዎ ! የሚሰክር ወይም የሚሰርቅ ሠራተኛ ወይም ጓደኛ ብንመለከት ወይም ከዘመዳችን አንዱ ወደ ተውኔት ቤት ፣ ወይም ለነፍሱ ምንም ረብሕ [ ጥቅም ] ወደማያገኝበት ሥፍራ ሲሮጥ ፣ በከንቱ ሲምል ፣ የሐሰት ምስክርነትን ሲሰጥ ፣ ወይም ሲዋሽ ፣ ወይም ሲቆጣ ብናየው ጀርባችንን ብንሰጠውና ብንገስፀው ወቀሳችን ለእግዚአብሔር ክብር የተደረገ ነው ይባላል፡፡

ዳግመኛም አንድ ሰው ቢበድለን ፣ እርሱ ራሱ የሠራውን ጥፋት በእኛ ቢያመካኝ ስለ እግዚአብሔር ብለን ይቅር ልንለው ይገባል፡፡ ብዙዎቻችን ግን ለጓደኞቻችን ፣ ለሰራተኞቻችን የዚህ ተቃራኒውን ነው የምናደርገው፡፡

ጓደኞቻችን ወይም ሠራተኞቻችን ቢበድሉን እናንባርቃለን ፤ ይቅርታ የሌለው ፍርድም እንፈርድባቸዋለን፡፡ እኛው ራሳችን እግዚአብሔርን በገቢር ስናስቀይም አንድም ስናሰድብ ወይም ነፍሳችንን ስንጎዳ ግን እንደበደልን አንቆጥረውም፡፡

ይህ ግን በአዲሱ ዓመት ልናስተካክለው የሚገባ ነገር ነው፡፡ ዕለት ዕለትም ልንለማመደው የሚገባ ነገር ነው፡፡ "

🕊

[ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ]


†                       †                        †
🌼                    🍒                     🌼
Forwarded from አብሰራ ገብርኤል ለማርያም (♱ ባሕራን ♱)
🕊                    💖                   🕊

[ 🌼  ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ  🌼 ]

                        🕊                       

🕊                   

እንኳን ለቅዱስ እና ታማኝ ሐዋርያ ዮሐንስ ወንጌላዊ የልደቱ መታሰቢያ አደረሳችሁ።

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

[ መስከረም ፬ [ 4 ] ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ልደቱ ]

ካህናቱ በሰዓታት ምስጋናቸው የአምደ ሃይማኖት አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫን ቃል አንደበታቸው በማድረግ እንዲህ ያመሰግኑታል።

🕯

[ ዮሐንስ እንደ መላእክት ንጹሕ ነው ፤ ድንግል ዮሐንስ የቅዱሳን መመኪያ ነው ፤ ዮሐንስ በብርሃን መጎናጸፊያ ሐር የተጌጠ ነው ፤ ዮሐንስ የቤተክርስቲያን አርጋኖን ነው በኤፌሶን የአዋጅ ነጋሪ ዮሐንስ ኃጥአን ለምንሆን ለእኛ ይቅርታን ይለምንልን።]

[ መከራ ተቀብሎ በመስቀል ላይ ደሙ በፈሰሰ ጊዜ ዮሐንስ ፍቅሩን አላጎደለም። ]

[ በወዳጁህ በዮሐንስ ድንግልና በንጽሐ ሥጋውም አቤቱ ይቅር በለን።]

🕊

† በዚህች ዕለት ቅዱሱ ሐዋርያ ከእናቱ ማርያም ባውፍልያ: ከአባቱ ዘብዴዎስ መወለዱን ቤተ ክርስቲያን ታስተምራለች::

የግፍና የመከራ ጽዋዕ በመላባት ዓለማችን… ትዕግሥቱ ፤ ጥላቻና መገፋፋት በነገሠባት ምድራችን… ፍቅሩ ፤ ኃጢአትና መተላለፍ በሠለጠነባት ሕይወታችን… በረከቱ ፤ እርሱ በተወለደባት በዚህች ዕለት በእኛም ልቡና ይወለድ ዘንድ ምልጃው አይለየን።

†                       †                        †
🌼                    🍒                     🌼
🕊

✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞ 

[  ✞  🌼  እንኩዋን ለብርሃነ መስቀሉ እና ለቅዱሳኑ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ  🌼 ✞  ]


🕊  ✞ ቅዱስ ዕፀ መስቀል ✞  🕊

ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና ቸር አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን ከሰማያዊ ክብሩ ወደ ምድር ወርዶ: በማሕጸነ ማርያም እግዝእት በኪነ ጥበቡ ተጸንሶ: በኅቱም ድንግልና ተወልዶ: በፈቃዱ መከራ መስቀልን ተቀብሎ:
¤ ከግራ ቁመት:
¤ ከገሃነመ እሳት:
¤ ከሰይጣን ባርነት:
¤ ከኃጢአት ቁራኝነትም አድኖናል::

" እምእቶነ እሳት ዘይነድድ አንገፈነ " እንዳለ ሊቁ::

ምንም መስቀል በብሉይ የወንጀለኞች መቅጫ ሆኖ ቢቆይም እግዚአብሔር ለዓለም መዳኛነት የመረጠው ነውና ሕብረ ትንቢቶች ሲነገሩለት: በብዙ ሕብረ አምሳልም ሲመሰል ኑሯል:: ከተፈጥሯችን ጀምሮ ዓለም ራሷ አርአያ ትዕምርተ መስቀል ናት::

እግዚአብሔር ለቃየን እንዳይገድሉት ከሰጠው ምልክት [ዘፍ.፬፥፲፭]  ጀምሮ

¤ ይስሐቅ ሊሰዋ የተሸከመው እንጨት [ዘፍ.፳፪፥፮]
¤ ቅዱስ ያዕቆብ ያያት የወርቅ መሰላል [ዘፍ.፳፰፥፲፪]
¤ ያዕቆብ የዮሴፍን ልጆች የባረከበት መንገድ [ዘፍ.፵፰፥፲፬]
¤ ባሕረ ኤርትራን የከፈለችው የሙሴ_በትር [ዘጸ.፲፬፥፲፭]
¤ የናሱ ዕባብ የተሰቀለበት እንጨት [ዘኁ.፳፩፥፰]  ጨምሮ በርካታ ምሳሌዎች ለቅዱስ መስቀሉ መኖራቸውን መተርጉማን ተናግረዋል::

ቅዱስ ዳዊትን የመሰሉ ነቢያት ደግሞ "ለሚፈሩሕ ከቀስት ያመልጡ ዘንድ ምልክትን ሰጠሃቸው" እያሉ መስቀሉን ከርቀት ተመልክተዋል:: [መዝ.፶፱፥፬]

በሐዲስ ኪዳን ግን ምሳሌው ገሃድ ሆኖ: ጌታ በዕፀ መስቀል ላይ ተሰቅሎ ሥጋውን ቆረሰበት: ደሙን አፈሰሰበት: ዓለምንም አዳነበት:: ስለዚህም "መስቀል ብርሃን ለኩሉ ዓለም: መሠረተ ቤተ ክርስቲያን" ተብሎ የሚመሰገን ሆኗል::

ቅዱስ_ያሬድ ሊቁ አክሎ "መስቀል መልዕልተ ኩሉ ነገር: ያድኅነነ እምጸር" ብሎ ጠላትን ማሳፈሪያ መሆኑን ይነግረናል:: ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ዻውሎስም ስለ መስቀሉ አምልቶ አጉልቶ አስተምሯል:: መመኪያችን ነውና:: [፩ቆሮ.፩፥፲፰  ገላ.፮፥፲፬]

አንዳንዶቹ እኛን 'የተሰቀለውን ትታቹሃል' ይሉናል:: የተሰቀለውማ የጌቶች ጌታ: የነገሥታት ንጉሥ: የአማልክት አምላክ: ሁሉ በእጁ የተያዘ: ኢየሱስ ክርስቶስ ነውና ከኦርቶዶክስ በላይ የሚያመልክ በወዴት አለና::

ነገር ግን መስቀሉን ንቆ የተሰቀለውን ማክበር አይቻልምና እኛ ለመስቀሉ የጸጋ ስግደትን እንሰግዳለን: እናመሰግነዋለን: እናከብረዋለን: ቤዛ: ጽንዕ: መድኃኒት: ኃይል እያልንም እንጠራዋለን:: አባቶቻችን በመስቀሉ ምርኩዝነት ማዕበለ ኃጢአትን: ባሕረ እሳትን ተሻግረዋል::

በመስቀሉ ቢመኩ አጋንንትን ድል ነስተዋል:: ጠላትንም አሳፍረዋል:: እኛም በመስቀሉ አምነን ከብረን: ገነን እንኖራለን:: ተጠቅመንበታልና ከራሳችን ሕይወት በላይ ምስክርን አንፈልግም::


†  🕊   በዓለ መስቀል  🕊  †

መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ካረገ ከዓመታት በሁዋላ አይሁድ በአንድ ነገር ተቸገሩ:: የክርስቶስን ሐዋርያት እያሳደዱ ቢገድሉም ከመስቀሉና ሥጋ ክርስቶስ አርፎበት ከነበረው ጐልጐታ ላይ የሚደረገውን ተአምር ግን መግታት አልተቻላቸውም::

መቼም ለተንኮል አያርፉምና ቅዱስ መስቀሉን ሽፍቶቹ ከተሰቀሉባቸው ጋር ደርበው አርቀው ቀበሩት:: አካባቢው የጉድፍ መጣያ እንዲሆንም አዋጅ ነገሩ:: ለክፋት ሲሆን ተባባሪው ብዙ ነውና ለ፪፻፸ ዓመታት ያህል ቆሻሻ ቢጥሉበት ተራራ ሆነ::

ከዚህ ሁሉ ነገር በሁዋላ እናታችን ቅድስት እሌኒ [ሔለና] በመንፈስ ቅዱስ አነሳሽነት: በቅዱስ ኪራኮስ መሪነት: በቅዱስ ሚካኤል ረዳትነት ደመራ አስደምራ: እጣን አጢሳ መካነ መስቀሉን አገኘች::

መስከረም ፲፯ ቀን የተጀመረው ቁፋሮ መጋቢት ፲ ቀን ተጠናቆ: ንጹሕ መስቀሉ ወጥቶ ብርሃን በርቷል: ሙታን ተነስተዋል:: ከ፲ ዓመት በሁዋላም የመስቀሉ ቤተ መቅደስ ታንጾ መስከረም ፲፯ ቀን ተቀድሷል::

ይህ ቅዱስ ዕፀ መስቀልም በደጉ አፄ ዳዊት ዘመን ወደ ሃገራችን መጥቶ: በጻድቁ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ አማካኝነት በደብረ ከርቤ [ግሸን ማርያም] ተለብጦ ተቀምጧል::


†  🕊 ቅዱስ አውዶኪስ ቀሲስ  🕊 † 

ይህ ቅዱስ ሰው ለቅዱስ መስቀሉ ከነበረው ፍቅር የተነሳ በብዙ ድካም ወደ ኢየሩሳሌም በእግሩ ተጉዞ ነበር:: ከብዙ መንገደኞች ጋር በጐዳና ላይ ሳሉ ታዲያ አንድ አይሁዳዊ [ሰማርያዊ] ተቀላቀላቸው:: በወሬ በወሬ የት እንደሚሔዱ ሲጠይቃቸው "መካነ መስቀሉን ለመሳለም ወደ ጐልጐታ ነን" አሉት::

እሱ ግን ከት ብሎ ስቆ "እንዴት እንጨት ትሳለማላችሁ" በሚል አፌዘባቸው:: የፀሐዩ ሐሩር እጅግ ጠንቶ ነበርና ቅዱስ አውዶኪስ ኃይለ መስቀሉን ሊያሳይ ወደደ:: በመንገድም መርዝነት ያለው ውሃ ነበርና ቅዱሱ ቀርቦ ጸልዮ በመስቀሉ ባረከውና ፈጥኖ ወደ ጣፋጭነት ተቀየረ::

ምዕመናኑ ደስ ብሏቸው ሲጠጡ ያ አይሁዳዊ 'እጠጣለሁ' ብሎ ቢቀርብ ወደ ነበረው ተመለሰበት:: 'በኮዳ የያዝኩትን እማልጠጣ' ብሎ ቢከፍተው ደግሞ ተልቶ አገኘው:: እጅግ ደንግጦ አለቀሰ:: በጣም ጠማው: ግን ምኑን ይጠጣ!

አማራጭ ሲያጣ ወደ ቅዱስ አውዶኪስ ሒዶ እግሩ ላይ ወድቆ አለቀሰ:: በመስቀሉ ቢማጸን መራራው ጣፈጠለት:: በዚህ ምክንያትም ወደ ክርስትና ተመልሷል:: ቅዱሱ በመልካም ሽምግልና ሲያርፍ ውሃው የተቀየረበት ቦታ ላይ ቤተ መቅደስ ታንጾ በዚህ ቀን ተቀድሷል::


†  🕊  ቅድስት ታኦግንስጣ  🕊   †

በ፭ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበረችው ሮማዊቷ እናት መንገድ ላይ ቁማ ወንጌል ስታነብ በንጉሥ ወታደሮች ተማርካ ወደ ሕንድ ተወስዳለች:: በዚያም በመስቀል አማትባ ሙት በማስነሳቷ የሃገሩ ሰው ወደ ክርስትና ከነ ንጉሡ ተመልሰዋል:: እርሷም ገዳም አንጻ: ደናግሉን ሰብስባ በንጽሕና ኑራለች:: በዚህ ቀን ዐርፋ ሲቀብሯት የብርሃን መስቀል መቃብሯ ላይ ተተክሏል::

አምላከ ቅዱሳን በኃይለ መስቀሉ: በሞገሰ መስቀሉ ይጠብቀን:: ከበረከቱ አሳትፎ በዓሉን የሰላም ያድርግልን::

🕊

[  †  መስከረም ፲፯ [ 17 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት   ]

፩. ቅዱስ ዕፀ መስቀል
፪. ቅድስት እሌኒ ንግስት
፫. ቅዱስ ኪራኮስ አረጋዊ
፬. ቅዱስ መቃርስ ሊቀ ዻዻስ
፭. ቅዱስ አውዶኪስ ቀሲስ
፮. ብጽዕት ታኦግንስጣ ሮማዊት
፯. ቅዱስ ዲዮናስዮስ ሊቀ ዻዻሳት

[   †  ወርኀዊ በዓላት  ]

፩. ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት [ቀዳሜ ሰማዕት]
፪. ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ [ወልደ ዘብዴዎስ]
፫. ቅዱሳን አበው መክሲሞስና ዱማቴዎስ
፬. አባ ገሪማ ዘመደራ
፭. አባ ዸላሞን ፈላሢ
፮. አባ ለትጹን የዋህ
፯. ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ሊቅ [ዘደሴተ ቆዽሮስ]

" የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና . . . መቼም አይሁድ ምልክትን ይለምናሉ:: የግሪክ ሰዎችም ጥበብን ይሻሉ:: እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን:: " [፩ቆሮ.፩፥፲፰-፳፫]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
                           †                           

🌼  [     እንኳን አደረሳችሁ !     ]  🌼

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

❝ አንብር መስቀልዬ በዲበ መስቀል ❞

[  ግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም   ]

🕊

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡


ግሸን ደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት በአምባሰል ወረዳ ከደሴ ከተማ ፹፪ ኪ/ሜ ርቃ ከፍ ብሎ በሚታይ መስቀለኛ ተራራ ላይ ትገኛለች። በተለይ አቡነ ሚካኤል ጳጳስ ዘጎንደር መንፈሳዊ መናኝ በመባል የሚታወቁት ደገኛ አባት ባሠሩት ከቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ሆነው የተራራውን ተፈጥሮአዊ አቀማመጥ ሲመለከቱ አንድ ጥሩ አናጢ ከጥሩ እንጨት ባማረ ጌጥ ጠርቦ የሠራውን ግሩም የእጅ መስቀል ይመስላል።

በአቅራቢያዋም ከሚገኙ በርካታ ታሪካውያንና ጥንታውያን መካናት መካከልም ፦ ጥንታዊው የደብረ ሐይቅ አቡነ ኢየሱስ ሞዓ ገዳም ፣ የድጓ ምስክር የነበረው ደብረ እግዚአብሔር ፣ የቅኔ ትምህርት ምንጭ የሆነው ዋድላ/ደላንታ ፣ የ፲፱ ኛው ክፍለ ዘመን የሃይማኖት ውሳኔ የተደረገበት የቦሩ ሜዳ ሥላሴ ፣ የውጫሌ ውል የተፈረመበት የውጫሌ ከተማ ፣ የመቅደላ አምባ ፣ የበሽሎ ወንዝ ሸለቆና ሌሎችም ናቸው።

ግሸን ደብረ ከርቤ የሚለውን ስያሜ ከማግኘቷ በፊት በልዩ ልዩ ታሪካዊና ምሥጢራዊ ምክንያቶች ደበረ ነገሥት ፣ ደብረ ነጎድጓድ ፣ ደብረ እግዚአብሔር በሚባሉ ስሞች ትጠራ ነበር፡፡ ግሸን ደብረ ከርቤ መጀመሪያ የተመሰረተችው በዘመነ አክሱም በዐፄ ካሌብ ዘመነ መንግሥት ነበር፡፡

ዐፄ ካሌብ በየመን በሩ ክርስቲያኖች እየደረሰባቸው ከነበረው መከራ ለመታደግ ወደ ናግራን ዘምተው ድል አድርገው መንግሥት አጽንተው ሲመለሱ በዚያ ይኖሩ የነበሩ አባ ፈቃደ ክርስቶስ የሚባሉት መነኰስ አብረው ተመልሰዋል።

አባ ፈቃደ ክርስቶስም ከናግራን ሲመለሱ ሁለት ጽላቶችን ወደ ኢትዮጵያ በማምጣት የበሽሎ ወንዝን ተሻግረው ወደ ግሸን ተራራ ጫፍ ለመውጣት የአምባውን ዙሪያ ሲመለከቱ በገደሉ ላይ ንብ ሰፎ ማሩ ሲንጠባጠብ አይተው የአምላክን ስጦታ ለማድነቅ በጥንታውያን ግእዝና ዓረብኛ ቋንቋዎች ቦታውን "አምባ " "አሰል " [ አምባሰል ] ብለው ጠሩት። ትርጉሙም "የማር አምባ " ማለት ነው እስከ አሁንም አካባቢው አምባሰል እየተባለ ይጠራል።


አባ ፈቃደ ክርስቶስም ይዘዋቸው የመጡትን ሁለት ጽላቶች ወደ አምባው በማስገባት ሁለት ቤተ ክርስቲያን ሠርተው ደብሩን መሥርተዋል። ይኽንኑ ታሪክ በመከተልም ይመስላል በጉዲት ጦርነት የስደት ዘመን የአክሱሙ ንጉሥ ድል ነዓድ በዘጠነኛው ክፍለ ዘመን ከአምባሰል ባሻገር ከሐይቅ ባሕር አጠገብ ባለው ተራራ ላይ ደብረ እግዚአብሔርን መሥርቶ ኖሯል።

ከዚህም በኋላ መንግሥት ከደብረ እግዚአብሔር በመራ ተክለሃይማኖት አማካኝነት ወደ ላስታ ሲሻገር የደብረ ከርቤ ክብር በላስታ ዘመንም አልተቋረጠም፡፡ በቅዱስ ላልይበላል ዘመን እንደተፈለፈሉ የሚነገርላቸው ጅምር ዋሻዎች አሁንም በደብረ ከርቤ ግሸን ማርያም ይገኛሉ። በዚህ ዘመንም ደብረ ከርቤ የነገሥታት መናኸሪያ የሊቃውንት መገኛ የቤተ ክርስቲያን የሐዲስ ኪዳን ሥርዓት መፈጸሚያ ቅድስት ቦታ ነበረች።

በመጨረሻም በዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመነ መንግሥት የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ መስቀል መቀመጫ ሆናለች። ፲፬፻፵፮ ዓ/ም መስከረም ፳፩ ዓፄ ዘርአ ያዕቆብ ግማደ መስቀሉንና ሌሎች ብዙ የቤተ ክርስቲያን ንዋያተ ቅድሳትን አምጥተው በግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም አስቀመጡ፡፡

የግማደ መስቀል በረከት የእመቤታችን ምልጃና ጸሎት ከሁላችን ጋር ይሁን !

አምላካችን በኃይለ መስቀሉ ሀገራችንና ሕዝባችንን ይጠብቅልን።

†                       †                        †
🌼                    🍒                     🌼
2024/11/17 12:42:00
Back to Top
HTML Embed Code: