Telegram Web Link
#መስከረም 1 - ርዕሰ አውደ ዓመት

#ዕንቁጣጣሽ ተብሎ የሚጠራበት ምክንያት ነው፡፡ በዚህ ዙሪያ የተለያዩ አስተያየቶች ይሰነዘራሉና ተራ በተራ እንያቸው፡፡

አንደኛው በኖህ እና በልጆቹ ዙሪያ የሚያጠነጥን፡፡ ሴም፣ ካምና ያፌት ሶስቱ የኖህ ልጆች ናቸው፡፡ ኖህ አህጉራትን ለሶስቱ ልጆች አከፋፍሎ ሲሰጥ ለካም አፍሪካ ደረሰው፡፡ ካም ወደ አፍሪካ የገባው እና መጀመሪያ የረገጠው #ኢትዮጵያን ሲሆን ወሩም ምድሪቱ #በአደይ_አበባ ያሸበረቀችበት #የመስከረም ወር ነበር፡፡ በምድሪቱ ውበት በመደመሙና ይህ ዕጣም ለእሱ ስለደረሰው ተደስቶ “ዕንቁ ዕጣ ወጣልኝ” አለ፡፡ እንግዲህ እንቁጣጣሽ ለሚለው ቃል አንዱ የየት መጣ ሀሳብ /#Etymology/ እንዲህ የሚል ነው፡፡

ሁለተኛው ምድሪቱ በአደይ ፈክታ ሲመለከት #ዕንቁ_ዕፅ_አወጣሽ ከሚል ነው #እንቁጣጣሽ የሚለው ስያሜ የመጣ የሚል ነው፡፡

በዚህኛው አካሄድ “ዕንቁ” ከኦይስተር ቅርፊት /pearl/ ውስጥ የሚገኝ ትንሽ ድቡልቡል፤ ጠንካራ አንጸባራቂ፤ ነጭ ውድ ጌጥ/ ለጌጥነት የሚያገለግል ነገር/ ሲሆን “ዕፅ” ደግሞ በግዕዝ የአማርኛው “ተክል” አቻ ነው፡፡ ስለዚህ የተክሉን መልክ ከዕንቁ ጋር በማነጻጸር የምድሪቱን ውበት ለመግለጽ የተጠቀሙበት ነው፡፡

ሶስተኛው ደግሞ #የቀዳማዊ_ምኒሊክ እናት ንግስት ሳባ ሰሎሞንን ለመጎብኘት በሄደችበት ጊዜ ንጉሱ “ዕንቁ ለጣትሽ ጌጥ ይሁንልሽ” ብሎ መስጠቱን መሰረት አድርጎ የሚነሳ ሃሳብ ሲሆን ወሩም ወርሃ #መስከረም ነበር።

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼 #መልካም_አዲስ_አመት🙏 🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

ለመቀላቀል 👇👇👇👇
@Enatachn_mareyam  
@Enatachn_mareyam
Forwarded from አብሰራ ገብርኤል ለማርያም (♱ ባሕራን ♱)
                          †                          

🌼     [    አዲስ ዓመት  !   ]     🌼

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🌼

"በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ ፥ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል። የምድረ በዳ ተራሮች ይረካሉ ፥ ኮረብቶችም በደስታ ይታጠቃሉ። ማሰማርያዎች መንጎችን ለበሱ ፥ ሸለቆችም በእህል ተሸፈኑ ፤ በደስታ ይጮኻሉ ይዘምራሉም።"

[ መዝ.፷፭፥፲፩ ]

🕊
         
እንኳን ከዘመነ ቅዱስ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ቅዱስ ማቴዎስ በሰላምና በጤና አሸጋገራችሁ፡፡ አሸጋገረን፡፡ ዘመኑን የንስሃና የፍሬ ያድርግልን፡፡

[ 🕊 እንኳን አደረሳችሁ 🕊 ]


†                       †                        †
🌼                     🕊                   🌼
Forwarded from አብሰራ ገብርኤል ለማርያም (♱ ባሕራን ♱)
                          †                          

      🕊   [  መስከረም ፪  [ 2  ]    🕊

     ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊  ምትረተ ርዕሱ ለዮሐንስ መጥምቅ  🕊

🕊

" እውነት እላችኋለሁ ፥ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም፡፡ " [ ማቴ.፲፩፥፲፩ ]
                   
💖   እንኳን አደረሰን     💖
     
†  🕊 የመጥምቁ ዮሐንስ ስሞች  🕊  †

+ ነቢይ
+ ሐዋርያ
+ ሰማዕት
+ ጻድቅ
+ ካሕን
+ ባሕታዊ / ገዳማዊ
+ መጥምቀ መለኮት
+ ጸያሔ ፍኖት [ መንገድ ጠራጊ ]
+ ድንግል
+ ተንከተም [ የብሉይና የሐዲስ መገናኛ ድልድይ ]
+ ቃለ አዋዲ [ አዋጅ ነጋሪ ]
+ መምሕር ወመገሥጽ
+ ዘየዐቢ እምኩሉ [ ከሁሉ የሚበልጥ ]
                            
🕊

የቅዱስ ዮሐንስ የጸሎቱ ኃይል የምልጃዉ በረከት ዘወትር በምንማጸነዉ ልጆቹ ላይ አድሮና ጸንቶ ይኑር ለዘለዓለሙ አሜን።
               
†                       †                        †
🌼                     🕊                   🌼
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
Forwarded from አብሰራ ገብርኤል ለማርያም (♱ ባሕራን ♱)
🕊

[  † እንኳን ለታላቁ ነቢይና ሰማዕት ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †  ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †

†  🕊 ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ  🕊  †

† ቅዱስ ወንጌል ላይ ከእመቤታችን ቀጥሎ የነ ዘካርያስን ቤተሰብ ያህል ክብሩ የተገለጠለት ፍጡር ይኖራል ብሎ መናገሩ ይከብዳል:: ቅዱስ ሉቃስ ወንጌሉን የጀመረው በዚህ ቅዱስ ቤተሰብ ነውና መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ሲል አጽፎታል::
"ዘካርያስ ካህኑና ቅድስት ኤልሳቤጥ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ" ይላቸዋል:: [ሉቃ.፩፥፮] (1:6)

የሰውን እንተወውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ መኖር ምን ይረቅ? ለዚህ አንክሮ [አድናቆት] ይገባል! እሊህ ቅዱሳን ባልና ሚስት ግን መካኖች በመሆናቸው ልጅ ሳይወልዱ ዘመናቸው አልፎ ነበር:: እንደ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ዕድሜአቸው የኤልሳቤጥ ፺ [90] የዘካርያስ ደግሞ ፻ [100] ደርሶ ነበር::

ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ ግን በስተ እርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ: ትንቢት ለብቻው የተነገረለት [ኢሳ.፵፥፫] (40:3), ሚል.፫፥፩] (3:1) ታላቅ ነቢይን ይሰጣቸው ዘንድ መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው::

ቅዱስ ዘካርያስ ሰው ነውና ከደስታ ብዛት በመከራከሩ ድዳ ሆነ:: ቅድስቲቷ ግን መስከረም ፳፮ [26] ቀን ታላቁን ሰው ጸንሳ ለ፮ [6] ወራት ራሷን ሠወረች:: በ፮ [6] ኛው ወር የፍጥረት ሁሉ ጌታ በተጸነሰ ጊዜ የአርያም ንግሥት ድንግል እመቤታችን ደጋ ደጋውን ወደ ኤልሳቤጥ መጣች:: ሁለቱ ቅዱሳት የእህትማማች ልጆች ናቸው::

የአምላክ እናቱ ስትደርስና "ሰላም" ስትላቸው መንፈስ ቅዱስ በእናትና ልጅ ወርዶ ኤልሳቤጥ በምስጋና: ዮሐንስ ደግሞ ገና በማሕጸን ሳለ በደስታ ዘለለ [ሰገደ]:: ከዚህ በሁዋላ ሰኔ ፴ [30] ተወልዶ: አባቱ ዘካርያስ "ዮሐንስ" ሲለው አንደበቱ ተፈትቶለታል::

ቅዱስ ዮሐንስ ከተወለደ ፪ [2] ዓመት ከ፮ [6] ወር በሆነው ጊዜ ሰብአ ሰገል በመምጣታቸው በእሥራኤል ምድር የሚገኙ ሕጻናትን ሔሮድስ ቁዝ አስፈጀ:: ትንሽ ቆይቶም አይሁድ ለሔሮድስ ስለ ቅዱሱ ሕጻን ነገሩት:: "ሲጸነስ የአባቱን አንደበት የዘጋ: ሲወለድ ደግሞ የከፈተ 'ዮሐንስ' የሚባል ሕጻን አለና እሱንም ግደል" አሉ::

እናቱ ቅድስት ኤልሳቤጥ ይዛው ስትሸሽ ካህኑን ዘካርያስን ግን በቤተ መቅደስ መካከል ገድለውታል:: አረጋይት ኤልሳቤጥም ሕጻኑን እያሳደገች በገዳመ ዚፋታ ለ ፫ [3] ፭ [5] ዓመታት ቆይታለች:: ቅዱስ ዮሐንስ ፭ [5] ፯ [7] ዓመት ሲሞላው ግን እዚያው በበርሃ እናቱ ዐረፈች:: ከሰማይ ዘካርያስና ስምዖን ወርደው ቀበሯት::

ሕጻኑ ዮሐንስ ሲያለቅስ ድንግል ማርያም ስንት አገር አልፋ ሰማችው:: እርሷም ስደት ላይ ነበረችና:: ከጌታ ጋር በደመና ሒደው ድንግል አቅፋ አጽናናችው:: ጌታንም "እንውሰደው ይሆን?" አለችው:: ጌታችን ግን "ለአገልግሎት እስክጠራው እዚህ ይቆይ" አላት:: ባርካው: አጽናንታውም ተለያዩ::

ቅዱስ ዮሐንስ ከዚህ በሁዋላ በዚያ ቆላ የግመል ጠጉር ለብሶ: ጠፍር ታጥቆ ተባሕትዎውን ቀጠለ:: ለ፳፭ [25] ፳፫ [23] ዓመታትም በንጽሕና ሲኖር ከምድር አራዊትና ከሰማይ መላእክት በቀር ማንንም አላየም:: ይሕችን ዐመጸኛ ዓለምም አልቀመሳትም::

ከዚህ በሁዋላ ፴ [30] ዘመን ሲሞላው እግዚአብሔር ከሰማይ ተናገረው:: "ሒድ! የልጄን ጐዳና ጥረግ" አለው:: ነቢያት ስለዚህ ነገር ተናግረው ነበርና:: [ኢሳ.፵፥፫] (40:3), [ሚል.፫፥፩] (3:1) አባቱ ዘካርያስም "ወአንተኒ ሕጻን ነቢየ ልዑል ትሰመይ: እስመ ተሐውር ቅድመ እግዚአብሔር ከመ ትጺሕ ፍኖቶ" [ሉቃ.፩፥፸፮] (1:76) ብሎ መንገድ ጠራጊነቱን ተናግሮ ነበርና::

ቅዱስ ዮሐንስ በዚያ ጊዜ በኃይለ መንፈስ ቅዱስ እየገሰገሰ ከበርሃ ወደ ይሁዳ መጣ:: ያዩት ሁሉ ፈሩት: አከበሩት:: ቁመቱ ቀጥ ያለ: ጽሕሙ እንደ ተፈተለ ሐር የወረደ: ጸጉሩ የቁራ ያህል የጠቆረ: መልኩ የተሟላ: ግርማው የሚያስፈራ ገዳማዊ ነውና::

ፈጥኖም ሕዝቡን ለንስሃ ሰበከ: ለንስሃም በርካቶችን አጠመቃቸው:: በዚህ አገልግሎት ለ6 ወራት ቆይቶ ጌታችን ወደ እርሱ ዘንድ መጣ:: ዮሐንስ ሰማይን ከነግሱ: ምድርን ከነልብሱ የያዘ ፈጣሪ "አጥምቀኝ" ብሎ ሲመጣ ደነገጠ:: የሚገባበትም ጠፋው::

"እንቢ ጌታየ! አንተ አጥምቀኝ" አለው:: ጌታ ግን "ፈቅጄልሃለሁ" አለው: አጠመቀው:: በዚህ ምክንያት ይሔው እስከ ዛሬም "መጥምቀ መለኮት" ሲባል ይኖራል:: ቅዱስ ዮሐንስ በመጨረሻ ሔሮድስን ገሰጸው:: ንጉሡም ተቀይሞ ለ7 ቀናት አሠረው::

ልደቱን ባከበረ ጊዜ ወለተ ሔሮድያዳ በዘፈን አጥምዳ አስማለችው:: እርሱም የታላቁን ነቢይ ራስ አስቆርጦ በወጪት አድርጐ ሰጣት:: አበው "እምሔሶ ለሔሮድስ ይብላዕ መሐላሁ - ሔሮድስ መሐላውን በበላ በተሻለው ነበር" ይላሉ:: የቅዱስ ዮሐንስ ራሱ በርራ ስትሔድ አካሉን ግን ደቀ መዛሙርቱ ቀብረውታል:: [ማቴ.፫፥፩] (3:1), ማር.፮፥፲፬ (6:14), [ሉቃ.፫፥፩] (3:1), [ዮሐ.፩፥፮] (1:6)*ርጉም ሔሮድስ አንገቱን ካስቆረጠው በሁዋላ የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ራሱ የጸጋ ክንፍ ተሰጥቷት ጌታችን ወዳለበት ደብረ ዘይት ሔዳ በፊቱ ሰገደች:: ቅዱሳን ሐዋርያት በአዩት ነገር ተገርመው ራሱን እጅ ነሷት::

ከዚሕ በሁዋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱስ ዮሐንስ ራስ የማስተማር ስልጣን ሰጥቶ አሰናበታት:: በመላው ዓለም ለ፲፭ [15] ዓመታት ስትሰብክ ኑራ ዓረቢያ ውስጥ ዓርፋለች::

††† አስማተ-ዮሐንስ መጥምቅ [የመጥምቁ ዮሐንስ ስሞች]

፩. ነቢይ
፪. ሐዋርያ
፫. ሰማዕት
፬. ጻድቅ
፭. ካሕን
፮. ባሕታዊ/ገዳማዊ
፯. መጥምቀ መለኮት
፰. ጸያሔ ፍኖት [መንገድ ጠራጊ]
፱. ድንግል
፲. ተንከተም [የብሉይና የሐዲስ መገናኛ ድልድይ]
፲፩. ቃለ አዋዲ [አዋጅ ነጋሪ]
፲፪. መምሕር ወመገሥጽ
፲፫. ዘየዐቢ እምኩሉ [ከሁሉ የሚበልጥ]

††† ጌታችን መድኃኔ ዓለም መጥምቁ ዮሐንስን አስቦ ይቅር ይበለን:: ጸጋውን: በረከቱንና ክብሩንም ያሳድርብን::

🕊

[  † መስከረም ፪ [ 2 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ]

፩. ቅዱስ ዮሐንስ ነቢይ [መጥምቀ መለኮት]
፪. ቅዱስ ዳስያ ሰማዕት
፫. ቅዱስ ዲዲሞስ ሰማዕት
፬. ቅድስት መሪና

[   † ወርኀዊ በዓላት   ]

፩. ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ [ከ፲፪ቱ ሐዋርያት]
፪. ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ ተአጋሲ
፫. ቅዱስ አቤል ጻድቅ
፬. ቅዱስ አባ ዻውሊ ገዳማዊ [ታላቁ]
፭. ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ
፮. አባ ሕርያቆስ ዘሃገረ ብሕንሳ

" ጌታ ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ ዮሐንስ ሊናገር ጀመረ . . . ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይን? አዎን እላችሁአለሁ ከነቢይም የሚበልጠውን . . . እውነት እላቹሃለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሳም . . . ነቢያት ሁሉና ሕጉ እስከ ዮሐንስ ድረስ ትንቢት ተናገሩ:: ልትቀበሉትስ ብትወዱ ይመጣ ዘንድ ያለው ኤልያስ ይሕ ነው:: የሚሰማ ጀሮ ያለው ይስማ::" [ማቴ.፲፩፥፯]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
እንኳን ለመጥመቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሰን አደረሳችሁ!!!። አሜን።

#ዕለቱ_መስከረም ፪ ነው። (“የቅዱሳኑ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው።” መዝ.115/116፡15 እንዲል ወንጌል በዚህ ዕለት መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ አንገቱ የተሰየፈበት ዕለት መታሰቢያ ክብረ በዓል ነው።)

#ከመጥምቁም_ከዮሐንስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ መንግሥተ ሰማያት ትገፋለች፥ ግፈኞችም ይናጠቋታል። ነቢያት ሁሉና ሕጉ እስከ ዮሐንስ ድረስ ትንቢት ተናገሩ፤ ልትቀበሉትስ ብትወዱ፥ ይመጣ ዘንድ ያለው ኤልያስ ይህ ነው። የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ። “ ማቴ. ፲፩፡፲፪-፲፭ (ማቴ.11 ፡12-15)

“በዚያም ወራት መጥምቁ ዮሐንስ መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ ብሎ በይሁዳ ምድረ በዳ እየሰበከ መጣ። በነቢዩ በኢሳይያስ። የጌታን መንገድ አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረ በዳ የሚጮህ ሰው ድምፅ የተባለለት ይህ ነውና። ራሱም ዮሐንስ የግመል ጠጉር ልብስ ነበረው፥ በወገቡም ጠፍር ይታጠቅ ነበር፤ ምግቡም አንበጣና የበረሀ ማር ነበረ።” ዮሐ.፫፡፩-፬

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼 #መልካም_አዲስ_አመት🙏 🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

ለመቀላቀል 👇👇👇👇
@Enatachn_mareyam  
@Enatachn_mareyam
Forwarded from አብሰራ ገብርኤል ለማርያም (♱ ባሕራን ♱)
🕊                    💖                   🕊

[  ግፉዕ ወቅቱል ንጹሕ ወቅዱስ  !  ]

                        🕊                       

❝ ሰላም ለዮሐንስ ግፉዕ ወቅቱል ንጹሕ ወቅዱስ  ወስቡሕ ላእከ ወነቢይ ወሰማዕት ድንግል ካህን ጸያሒ ወሰባኪ መጥምቀ እግዚኡ ❞

[ ጌታውን ያጠመቀና ሰባኪ ፤ መንገድ ጠራጊ ፤ ካህን ድንግል ሰማዕት ፣ ነቢይና አገልጋይ ፤ ምስጉን ቅዱስና ንጹሕ ፤ ተገፍቶ የተገደለ ለኾነ ዮሐንስ ሰላምታ ይገባል። ]

[ በጣፋጭ አንደበቱ ወንጌልን የሚሰብክ ፣ ቀኙ የሚያቃጥል መለኮትን የዳሰሰች ፣ ጀርባው በግመል ጸጉር የተሸፈነ ፣ የዮሐንስን ደግነት ፈጽመን እንናገራለን ]

[ አቤቱ ስላጠመቀኽ ስለ ዮሐንስ ብለኽ በምሕረትኽ ዐስበኝ ፤ ከታናሽነቴ ዠምሮ እስከ ዛሬ አንተን የበደልኹኽን ኅጢአቴን ስለ ርሱ ብለኽ እኔን አገልጋይኽን አንጻኝ አሜን። ]

[   ተአምኆ ቅዱሳን   ]

🕊

የቅዱስ ዮሐንስ የጸሎቱ ኃይል የምልጃዉ በረከት ዘወትር በምንማጸነዉ ልጆቹ ላይ አድሮና ጸንቶ ይኑር ለዘለዓለሙ አሜን።

🕊 [ ምትረተ ርዕሱ ለዮሐንስ መጥምቅ ]  🕊

[      🕊   እንኳን አደረሳችሁ   🕊      ]


🕊                        💖                       🕊
2024/11/17 09:47:28
Back to Top
HTML Embed Code: