Telegram Web Link
Forwarded from አብሰራ ገብርኤል ለማርያም (ባሕራን)
🕊

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡

[ † ግንቦት ፲፫ [ 13 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት † ]


†   🕊 ቅዱስ አርሳኒ   🕊   

ቅድስት ሃይማኖት እዚህ ዛሬ እኛ ጋር የደረሰችው በበርካታ ሰማዕታትና ጻድቃን ደም ነው:: ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ግድግዳዎቿ እንጨትና ድንጋይ እንዳይመስሏችሁ:: አጽመ ቅዱሳን ነው እንጂ::

ቅዱሳን ልዑለ ባሕርይ ክርስቶስን እንደ እኔ እና እንደ ዘመኑ ትውልድ በከንፈራቸው የሚሸነግሉ አልነበሩም:: እነርሱ በፍጹም ልባቸው ስለ ፍቅሩ ሕይወታቸውን አሳልፈው ሰጡ እንጂ:: በቅድስናቸው ከተመሰከረላቸው ቀደምት ቅዱሳን አንዱ ደግም ቅዱስ አርሳንዮስ ነው::

ቅዱሱ የተወለደው በ፫፻፵፭ [ 345 ] ዓ/ም ሮም ውስጥ ነው:: በወጣትነቱ ይሕ ቀረህ የማይሉት የጥበብና የፍልስፍና ሰው ነበር:: በተለይ በትልቁ የሮም ቄሳር ቴዎዶስዮስ ዘመን በቤተ መንግስት አካባቢ የተከበረና የንጉሡ ልጆች መምሕር ነበር:: አኖሬዎስና አርቃዴዎስን ቀጥቶ ያሳደጋቸውም እርሱ ነበር::

በድንግልና እስከ ፵ [ 40 ] ዓመቱ ድረስ ሮም ውስጥ ቆየ:: ከዚህ በኋላ ግን ስለ ሰማያዊ ነገሮች ሲያስብ መልዐኩ በሕልም ወደ ግብፅ ሒድ አለው:: በመጀመሪያ ወደ እስክንድርያ ቀጥሎ ወደ ገዳመ አስቄጥስ ሒዶ መነኮሰ:: በቆይታ ግን ብሕትውና ምርጫው ሆነ::

ቅዱስ አርሳኒ በእነዚሕ ነገሮቹ ይታወቃል :-

፩. በምንም ምክንያት ከማንም ጋር አያወራም:: [ለ፷ [60] ዓመታት በአርምሞ ኑሯል]

፪. በቤተ መቅደሱ ግድግዳ ተጠግቶ እንባውን ሲያፈስ የርሱን አካል አርሶ በመሬት ላይ ሲፈስ ይታይ ነበር:: ከእንባው ብዛት ቅንድቦቹ ተላልጠው አልቀው ነበር::

፫. በርካታ ድርሳናትን ደርሷል:: ብዙዎቹ ዛሬም ግብጽ ውስጥ አሉ::

፬. ሸንጎበቱን ወደ ደረቱ አዘንብሎ ስለሚቆም ማንንም ቀና ብሎ አያይም ነበር::

፭. ለጸሎት አመሻሽ ፲፩ ሰዓት [11:00] አካባቢ ላይ ይቆምና ጸሎቱን የሚጨርስ ፀሐይ ግንባሩን ስትመታው ነው::

፮. ሁል ጊዜ ራሱን "አንተ ሰነፍ [ሐካይ] እያለ ይገስጽ ነበር::

፯. በገዳማውያን ታሪክ የርሱን ያሕል በቁመቱ ረዥም አልተገኘም ይባላል:: የራሱ ጸጉር በጀርባው የወረደ ሲሆን ጽሕሙን በስዕሉ ላይ እንደምታዩት ነጭና እስከ መታጠቂያው የወረደ ነበር::

እነዚህ ግን በጣም ጥቂቶቹ ናቸው::

ቅዱስ አርሳንዮስ አካሉ በተጋድሎ ደቆ: ለ፷ [60] ዓመታት በግሩም መንፈሳዊነት ኑሮ በ፻ [100] ዓመቱ በዚሕች ዕለት ዐርፏል::

አምላካችን እግዚአብሔር ከታላቁ የቅድስና ሰው አርሳኒ በረከት አይለየን::

🕊

[ †  ግንቦት ፲፫ [ 13 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ አርሳንዮስ - አርሳኒ [ጠቢብ ገዳማዊ]

[ †  ወርኀዊ በዓላት ]

፩. እግዚአብሔር አብ
፪. ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላዕክት
፫. ፺፱ "99ኙ" ነገደ መላዕክት
፬. ቅዱስ አስከናፍር
፭. ፲፫ " 13ቱ " ግኁሳን አባቶች
፮. አቡነ ዘርዐ ቡሩክ

" የፍጥረት ወገን ሁሉ በሰው ይገራል:: ደግሞ ተገርቷል:: ነገር ግን አንደበትን ሊገራ ማንም ሰው አይችልም:: የሚገድል መርዝ የሞላበት ወላዋይ ክፋት ነው:: በእርሱ ጌታንና አብን እንባርካለን:: በእርሱም እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠሩትን ሰዎች እንረግማለን:: ከአንድ አፍ በረከትና መርገም ይወጣሉ:: ወንድሞቼ ሆይ ይህ እንዲህ ሊሆን አይገባም:: " [ያዕ.፫፥፯-፲፩] (3:7-11)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
#እግዚአብሔርን_ተስፋ አድርግ ለመንጋው ሁሉ በጎ እንደሚመኝ እንደ መልካም እረኛ
#እግዚአብሔርም በፍጥረታቱ በሙሉ ያለምንም ጥርጥር በዝምታ ይሠራል። ይሁን እንጂ ሰዎች በመከራ ውስጥ ሆነው #የእግዚአብሔር መልስ ከዘገየባቸው እንደማይሰራ አድርገው ያስባሉ፡ እነርሱ #እግዚአብሔር አይሰራም በሚያስቡበት ሰዓት ሁሉ እርሱ ግን ለእነርሱ በጥልቅ እየሰራ ነው፡ ሰዎች ይህንን ስለማይገነዘቡ #የእግዚአብሔርን ሥራና የስራውን ውጤት ፈጥነው ለማየት ይፈልጋሉ። እነዚህ ሰዎች ግን በእምነታቸው ያመኑትን በዓይነቻቸው እስኪመለከቱ ድረስ ሊቆዩ ይገባቸዋል፡" #እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ በርታ ልብህም ይጽና #እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፡፡"
መዝ 26 € 14::
አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ


#መልካም__ቀን🙏

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇

@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
Forwarded from አብሰራ ገብርኤል ለማርያም (ባሕራን)
                        †                        

🕊  💖        ሰ ላ ም ታ        💖  🕊

❝ ክርስቶስ ተንስአ እሙታን
▸ በዐቢይ ኃይል ወስልጣን ፤
አሠሮ ለሰጣን
▸ አግዐዞ ለአዳም ፤
ሰላም
▸ እምይእዜሰ ፤
ኮነ
▸ ፍስሐ ወሰላም ❞

🕊

❝ ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሳ ፤ ሰይጣንን አሰረው ፤ አዳምንም ነጻ አወጣው ፤ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ ፍፁም ሰላም እና ደስታ ሆነ። ❞

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

  እግዚአብሔርም ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ ፥ የወይን ስካር እንደ ተወው እንደ ኃያልም ሰው ፤

ጠላቶቹንም በኋላቸው መታ ፤ የዘላለምን ኀሣር ሰጣቸው። ❞

[    መዝ . ፸፰ ፥ ፷፭   ]


†                       †                         †
💖                    🕊                     💖
Forwarded from አብሰራ ገብርኤል ለማርያም (ባሕራን)
                        †                        

🕊  💖                     💖  🕊

[  መልካም ምግባርና የዋህነት !  ]

🕊

                        †                        

[    የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ !   ]

❝  ስለዚህ ርኵሰትን ሁሉ የክፋትንም ትርፍ አስወግዳችሁ ፥ ነፍሳችሁን ማዳን የሚችለውን በውስጣችሁም የተተከለውን ቃል በየዋህነት ተቀበሉ።

ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ ራሳችሁን እያሳታችሁ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ። ❞

[  ያዕ . ፩ ፥ ፳፩   ]


💖  ም ግ ባ ር ና የ ዋ ህ ነ ት 💖 ]
                   ]      [

     🕊    ምክረ ቅዱሳን   🕊

🕊 [ ከቅዱሳን አባቶቻችን አንደበት ]


†                       †                        †
💖                    🕊                     💖
Forwarded from አብሰራ ገብርኤል ለማርያም (ባሕራን)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
                       †                       

[ ❝ በርታ ፥ ልብህም ይጽና ! ❞ ]

🕊

❝ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ ፤ በርታ ፥ ልብህም ይጽና ፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ። ❞ [ መዝ.፳፯ ፥ ፲፬ ]

በሌላ ስፍራም

❝ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ ፤ አበረታሃለሁ ፥ እረዳህማለሁ ❞ [ ኢሳ.፵፩ ፥፲ ]


†                       †                        †
💖                    🕊                     💖
Forwarded from አብሰራ ገብርኤል ለማርያም (ባሕራን)
                        †                        

[ ባለ ውለታችን ታመዋል ! ]

❤️‍🩹

ኑ በመልካም እንተባበር
ለባለ ውለታችን ውለታ እንመልስ !

ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ ወ/ቂርቆስ መታመማቸውን እና ለህክምና ብር እንደሚያስፈልግ ሰምተናል።

ሊቀ መዘምራን በብዙ ውጣ ውረድ ውስጥ አልፈዋል። እናም ብንተባበር ከህክምናም በላይ ለአባታችን ብዙ ማድረግ እንችላለን።

Account [ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ]
1000481007287
KINETIBEB W/KIRKOS W/MESKEL
CBE

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
Forwarded from አብሰራ ገብርኤል ለማርያም (ባሕራን)
🕊

[ † እንኩዋን የመነኮሳት አባት ለተባለው "ቅዱስ ዻኩሚስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ † ]


🕊  ቅዱስ ዻኩሚስ [ አባ ባኹም ]  🕊

ዛሬን አያድርገውና ምንኩስና ማለት መላእክትን መስሎ የሚኖርበት ሕይወት ነበር:: ምንኩስና በእግዚአብሔር ፈቃድ በአባ እንጦንስ ቢመሠረትም ሕይወቱን በማስፋፋት ደረጃ የቅዱስ ዻኩሚስን ያሕል የደከመና የተሳካለት ግን የለም::

ቅዱሱ በትውልዱ ግብፃዊ እንደሆነ የሚነገር ሲሆን ከቀደመ ሕይወቱ ጋር በተያያዘ የሚተረክ ነገር በመጽሐፈ ገድሉ ላይ አለ:: ዻኩሚስ ወደ ምንኩስናው ዓለም የመጣ በታላቁ አባ ዸላሞን አማካኝነት ነው:: ለተወሰነ ጊዜም መንፈሳዊ አባቱን እየረዳ ሕይወተ መነኮሳትን አጥንቷል::

በመንፈሳዊ ሕይወቱና በተጋድሎ እየበረታና እየደረጀ ሲሔድ ከአባ ዸላሞን ተለይቶ : ማሕበር መስርቶ ለመኖር አምላኩን ጠይቆ ፈቃድ በማግኘቱ በሕግ የሚመራ የመጀመሪያውን ገዳም መሥርቷል::

ቅዱስ ዻኩሚስ ጸሎቱ አጋንንትን ከአካባቢው አያስቀርባቸውም ነበር:: አካሉ አልቆ በአጥንቶቹ እስኪቆም ድረስ ጾሟል:: ዓርብ ዓርብ የጌታችንን ሕማማት እያሰበ ከእንባ ጋር ይሰግዳል:: እንባውና ላበቱ ከፊቱ እየወረደ አካባቢው ጭቃ ይሆን ነበር:: ጌታችንም መስቀል ተሸክሞ ይታየው ነበር::

ስለ ክብሩም መላእክት ወደ ሰማይ ወስደው ገነትና ሲዖልን አሳይተውታል:: አባታችን ቅዱስ ዻኩሚስ ከርሕራሔው የተነሳ አጋንንት ያደሩባቸውን ሰዎች ሲያገኝ በቀጥታ ከመፈወስ ይልቅ ደዌውን : ርኩሳን መናፍስቱንም ወደ እርሱ እንዲገለበጡ ያዛቸው ነበር::

ከዚያም በጾም : በጸሎትና በስግደት ያማስናቸዋል:: ያኔ በግዳቸው እየጮሁ ሲወጡ ደጉ አባት "ምነው ትንሽ ቆዩ እንጂ" ይላቸዋል::

አጋንንቱም እያደነቁ "ከገነት ካስወጣነው ከአዳም በቀር እንዲህ ዓይነት ፍጡርስ ዓይተን አናውቅም" ብለው እንደ ጢስ በነዋል:: አጋንንት ስለሚፈሩት "አርበኛው መነኩሴ" ይሉታል::

"  የቅዱስ ዻኩሚስ ፍሬዎች   "

፩. በግብፅ በርካታ ገዳማትን አቁዋቁሟል::

፪. ለሁሉም ገዳማት አበ ምኔቶችን ሹሞ እየዞረ ይጠብቃቸው ነበር::

፫. የመጀመሪያውን ሥርዓተ መነኮሳት አዘጋጅቷል::

፬. መነኮሳት ሥጋዊም ሆነ መንፈሳዊ ሹመት እንዳይሾሙ ከልክሏል::

፭. መነኮሳት ከገዳማቸው በፍፁም እንዳይወጡ ከልክሏል::

፮. ከግብፅ ውጪ ምንኩስናን ያስፋፉ አባቶችን አስተምሮ አመንኩሷል:: [ለምሳሌ በኢትዮዽያ ምንኩስናን ያስፋፉት አቡነ አረጋዊ የዚህ አባት ደቀ መዝሙር ናቸው]

ከዚሕም ባለፈ በርካታ ሥራዎችን ሠርቷል:: ቅዱስ ዻኩሚስ ጫማ ሳይጫማ: እሾህን ሳይሰቀቅ ይረግጥም ነበር:: የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ እጥፍ ሆኖ የበዛለት ቅዱሱ መነኮስ ወደ ወደደው እግዚአብሔር በዚህች ቀን ሔዷል::

የጻድቁ መነኮስ ጸጋና በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን::

🕊

[ †  ግንቦት ፲፬ [ 14 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ አባ ዻኩሚስ [አበ መነኮሳት ሣልሳዊ]
፪. አባ ሲማኮስ ሰማዕት

[ †  ወርሐዊ በዓላት ]

፩. አቡነ አረጋዊ [ዘሚካኤል]
፪. ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ መርዓዊ
፫. ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ
፬. ቅዱስ ሙሴ [የእግዚአብሔር ሰው]
፭. አባ ስምዖን ገዳማዊ
፮. አባ ዮሐንስ ጻድቅ
፯. እናታችን ቅድስት ነሣሒት

" ይህ ነገር ለተሰጣቸው ነው እንጂ ለሁሉ አይደለም:: በእናት ማሕጸን ጃንደረቦች ሆነው የተወለዱ አሉ:: ሰውም የሰለባቸው ጃንደረቦች አሉ:: ስለ መንግስተ ሰማያትም ራሳቸውን የሰለቡ ጃንደረቦች አሉ:: ሊቀበለው የሚችል ይቀበለው:: " [ማቴ.፲፱፥፲፩] (19:11)

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
2024/09/28 23:18:07
Back to Top
HTML Embed Code: