Telegram Web Link
እንኳን አደረሳችሁ
ቀዳም ስዑር
26/8/2016
#_____ተነስቷል

እናንተስ አትፍሩ የተሰቀለውን እየሱስን እንድትሹ አውቃለሁና እንደተናገረ ተነስቶአልና በዚህ የለም የተኛበትን ስፍራ ኑና እዩ። ፈጥናችሁም ሂዱና ከሙታን ተነሣ እነሆም ወደ ገሊላ ይቀድማችኋል በዚያም ታዩታላችሁ ብላችሁ ለደቀ መዛሙርቱ ንገሩዋቸው። እነሆም ኢየሱስ ነገርኋችሁ። በፍርሃትና በታላቅ ደስታም ፈጥነው ከመቃብር ሄዱ ለደቀ መዛሙርቱም ሊያወሩ ሮጡ። እነሆም ኢየሱስ አገኛቸውና ደስ ይበላችሁ አላቸው።

ሞት ጠፍቶልናል "ደስ ይበላችሁ። "

◇◇◇ ማቴ 28÷5-9 ◇◇◇

#ለሕዝበ_ክርስቲያን_በሙሉ

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ትንሳኤው አደረሳችሁ::

#መልካም_የትንሣኤ_በዓል_ይሁንልን 🙏⁣⁣

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇

@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
🕊

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡  †

🕊  †  ሚያዝያ ፳፯ [ 27 ] †   🕊

† እንኩዋን ለታላቁ ሰማዕት "ቅዱስ ፊቅጦር" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ †

🕊  ማር ፊቅጦር   🕊

ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በደማቸውና በገድላቸው ያስጌጡ ብዙ ሰማዕታት አሉ:: ነገር ግን ከኮከብም ኮከብ ይበልጣልና ማን እንደ ጊዮርጊስና እስጢፋኖስ !

ከእነርሱ ቀጥለው ከሚጠሩ ሰማዕታት ደግሞ አንዱና ዋነኛው ቤተ ክርስቲያን "ማር" የምትለው ቅዱስ ፊቅጦር ነው:: እስኪ ከበዛው መዓዛ-ገድሉ ጥቂት እንካፈል::

ቅዱስ ፊቅጦር አባቱ ኅርማኖስ ይባላል:: አረማዊና ጨካኝ ነው:: እናቱ ግን የተመሰገች ቅድስት ማርታ ትባላለች:: ልጇን እንደሚገባ አሳድጋው ፳ [20] ዓመት ሲሞላው የአንጾኪያ ንጉሥ የሠራዊት አለቃና በመንግሥቱ ፫ [3] ኛ አድርጐ ሾመው::

የድሮዋ አንጾኪያ [ሮም] እንደ ዛሬዋ አሜሪካ ዓለምን የተቆጣጠረች ሃገር ነበረች:: ቅዱስ ፊቅጦር ደም ግባቱ ያማረ: በጦርነትም ኃይለኛ ስለ ነበር ሁሉ ያከብሩት: ይወዱትም ነበር:: እርሱ ግን ቀን ቀን ሲጾም: ነዳያንን ሲያበላ ይውል ነበር::

ሌሊት ደግሞ እኩሉን ሲጸልይና ሲሰግድ: እኩሉን የእስረኞችን እግር ሲያጥብ ያድር ነበር:: ይህ ሁሉ ሲሆንኮ እርሱ የንጉሡ ፫ [3] ኛ: የሠራዊትም አለቃ ነው:: በዘመኑ የሚያገድፍ ምግብና የወይን ጠጅ በአፉ ዙሮ አያውቅም::

ከነገር ሁሉ በሁዋላ ንጉሡ ዲዮቅልጢያኖስ ካደ:: ዘመነ ሰማዕታትም ጀመረ:: አብያተ ክርስቲያናት ተቃጠሉ:: ከ፵፯ [47] ሚሊየን በላይ ክርስቲያኖች በመንኮራኩር ተፈጩ: በመጋዝ ተተረተሩ: ለአራዊት ተሰጡ: በግፍም ተጨፈጨፉ:: ቀባሪ አጥተውም ወደቁ::

በዚሕ ጊዜ ማር ፊቅጦር እናቱን ቅድስት ማርታን በዕንባ ተሰናብቶ ወደ ንጉሡ ቀርቦ በክርስቶስ ስም ታመነ:: ክፉ አባትም በልጁ ላይ ሞትን መከረ::

ከዚያም ቅዱሱን አፉን በብረት ለጉመው ወደ ምድረ ግብፅ አወረዱት:: መሪያቸው እንዳልነበረ ወታደሮቹ መኳንንቱ ሁሉ ተዘባበቱበት:: እርሱ ከምድራዊ ንግሥና ሰማያዊ መንግስትን: በሰዎች ፊት ከመክበር ስለ ክርስቶስ ሲል መናቅን መርጧልና::

ለቀናት: ለወራትና ለዓመታት መኳንንቱ እየተፈራረቁ አሰቃዩት:: በርሱ ላይ ያልሞከሩት የስቃይ ዓይነት አልነበረም:: አካሉን ቆራርጠዋል: ዓይኖቹን አውጥተዋል: ምላሱንም ቆርጠዋል::

በዚሕች ዕለት ግን በሰይፍ አንገቱን ቆርጠውታል:: ስለዚህም እናት ቤተ ክርስቲያን በታላቅ ማክበር ታከብረዋለች:: እግዚአብሔርም ለቅዱስ ፊቅጦር እንዲህ አለው :-

"እንደ አቅሙ ስምህን የጠራ: መታሠቢያህን ያደረገ: ስምህን ያከበረ: የብርሃን ልብስ አጐናጽፌ ወደ መንግስተ ሰማያት አስገባዋለሁ::"

ቸሩ አምላከ ፊቅጦር ሁላችንም ይማረን:: ከቃል ኪዳኑ አሳትፎ ለርስቱ ያብቃን::

🕊

[ † ሚያዝያ ፳፯ [ 27 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ጽኑዕና ኃያል ማር ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት
፪. ቅድስት ማርታ [የፊቅጦር እናት]
፫. ብጽዕት እስጢፋና [በክርስቶስ ስላመነች ከ፪ [2] ሰንጥቀው የገደሏት የ፲፭ [15] ዓመት ወጣት]
፬. ቅዱሳን ሳሲማና አባ ኖባ [ሰማዕታት]

[ †  ወርኀዊ በዓላት ]

፩. የጌታችንና አምላካችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በዓለ ስቅለት
፪. አቡነ መብዐ ፅዮን ጻድቅ
፫. ቅዱስ መቃርስ [የመነኮሳት ሁሉ አለቃ]
፬. ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ
፭. ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት [ንጉሠ ኢትዮዽያ]
፮. ቅዱስ ቢፋሞን ጻድቅና ሰማዕት

" እግዚአብሔር ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ: እስከ አሁንም ስለምታገለግሏቸው ያደረጋችሁትን ሥራ: ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመጸኛ አይደለምና:: በእምነትና በትእግስትም የተስፋውን ቃል የሚወርሱትን እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞች እንዳትሆኑ ተስፋ እስኪሞላ ድረስ እያንዳንዳችሁ ያን ትጋት እስከ መጨረሻ እንድታሳዩ እንመኛለን። " [ዕብ.፮፥፲-፲፫] (6:10-13)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
                       †                       

🕊  💖  እንኳን  አደረሳችሁ  💖  🕊


🕊 " በሦስተኛውም ቀን ያስነሣናል ! " 🕊

▬▬▬▬▬▬  †  ▬▬▬▬▬▬

"  ኑ ፥ ወደ እግዚአብሔር እንመለስ ፤ እርሱ ሰብሮናልና ፥ እርሱም ይፈውሰናል ፤ እርሱ መትቶናል ፥ እርሱም ይጠግነናል።

ከሁለት ቀን በኋላ ያድነናል ፤ በሦስተኛውም ቀን ያስነሣናል ፥ በፊቱም በሕይወት እንኖራለን። "

[ ትንቢተ ሆሴዕ . ፮ ፥ ፩ ]


†                       †                        †
💖                    🕊                     💖
                       †                       

🕊  💖  እንኳን  አደረሳችሁ  💖  🕊


🕊 " ክርስቶስም ካልተነሣ እምነታችሁ ከንቱ ናት ! " 🕊

▬▬▬▬▬▬  †  ▬▬▬▬▬▬

" ክርስቶስም ካልተነሣ እንግዲያስ ስብከታችን ከንቱ ነው እምነታችሁም ደግሞ ከንቱ ናት፤ ደግሞም። ክርስቶስን አስነሥቶታል ብለን [ በገዛ ሥልጣኑ ተነሥቷል ብለን ] በእግዚአብሔር ላይ ስለ መሰከርን ሐሰተኞች የእግዚአብሔር ምስክሮች ሆነን ተገኝተናል፤ ሙታን ግን የማይነሡ ከሆነ እርሱን አላስነሣውም።

ሙታን የማይነሡ ከሆነ ክርስቶስ አልተነሣማ ፤ ክርስቶስም ካልተነሣ እምነታችሁ ከንቱ ናት ፤ እስከ አሁን ድረስ በኃጢአታችሁ አላችሁ።"

[ ፩ቆሮ.፲፭፥፲፬ ]

▬▬▬▬▬▬  †  ▬▬▬▬▬▬

'' ክርስቶስ ተንስአ እሙታን
▸ በዐቢይ ኃይል ወስልጣን ፤
አሰሮ ለሰይጣን
▸ አግአዞ ለአዳም ፤
ሰላም
▸ እምይእዜሰ ፤
ኮነ
▸ ፍስሐ ወሰላም ''

'' ክርስቶስ በታላቅ በኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሳ ፤ ሰይጣንን አሰረው አዳምንም ነጻ አወጣው ፤ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ ፍፁም ሰላም እና ደስታ ሆነ። ''

🕊

"ሞት ሆይ! መውጊያህ ወዴት አለ? ሲዖል ፥ መቃብርም ሆይ ! ድል መንሣትህ ይዞም ማስቀረትህ ወዴት አለ?
ክርስቶስ ተነሣ ፤ ሞት ሆይ፥ አንተም ጠፋህ!
ክርስቶስ ተነሣ፣ አጋንንትም አዘኑ!
ክርስቶስ ተነሣ፤ መላእክትም ሐሴት አደረጉ!
ክርስቶስ ተነሣ፤ የሰው ሕይወትም ነጻ ወጣች!
ክርስቶስ ተነሣ፤ መቃብርም ባዶ ኾነች!
ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቶ ለአንቀላፉት ኹሉ በኵር ኾኖላቸዋልና፡፡ "

[ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ]

†                       †                        †
💖                    🕊                     💖
🕊      
   

[ " የክርስቶስ ትንሣኤ የክርስትና መሠረት ነው " ]


" ሞት ሆይ ቀስትህ ወዴት አለ ?  አንተ ጠላት ሆይ ማሸነፍህ ወዴት አለ ? ክርስቶስ ከሙታን ተነሳ አንተንም አጠፋህ፡፡ ክርስቶስ ተነሳ አጋንንትን አስወጣቸው፡፡ ክርስቶስ ተነሣ ነፍስም ነጻ ወጣች። ክርስቶስ ተነሣ መላእክትም ደስ አላቸው። ክርስቶስ ተነሳ መቃብርም ከሙታን ባዶ ሆነ ክርስቶስ ከሞት ስለተነሣ፡፡

ወድቀው አንቀላፍተው የነበሩትን መሪና ነጻ አውጪ ሆኖ ወደ ቀደመ ክብራቸው መለሰ:: ይኽች ዕለት አስራኤላውያን ከባርነት ነጻ የወጡባት ቀን ናት፡፡ ክብር ምስጋና ለዘላለሙ ለእርሱ ይሁን፡፡

[   ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ  " ]

----------------------------------------------

ሦስት ቀን ሦስት ሌሊት አምላክ በመቃብር ያደረበት ምስጢር !

💖    ድንቅ ትምህርት   💖


🕊  [  በመምህራነ ቤተክርስቲያን   ]  🕊


የአምላካችን ቅዱስ ስዕል የግብፅ ኮፕቲክ ቤተክርስቲያን ነው።

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
                        👇
                       †                       

🕊  💖  እንኳን  አደረሳችሁ  💖  🕊


🕊 " ክርስቶስም ካልተነሣ እምነታችሁ ከንቱ ናት ! " 🕊

▬▬▬▬▬▬  †  ▬▬▬▬▬▬

" ክርስቶስም ካልተነሣ እንግዲያስ ስብከታችን ከንቱ ነው እምነታችሁም ደግሞ ከንቱ ናት፤ ደግሞም። ክርስቶስን አስነሥቶታል ብለን [ በገዛ ሥልጣኑ ተነሥቷል ብለን ] በእግዚአብሔር ላይ ስለ መሰከርን ሐሰተኞች የእግዚአብሔር ምስክሮች ሆነን ተገኝተናል፤ ሙታን ግን የማይነሡ ከሆነ እርሱን አላስነሣውም።

ሙታን የማይነሡ ከሆነ ክርስቶስ አልተነሣማ ፤ ክርስቶስም ካልተነሣ እምነታችሁ ከንቱ ናት ፤ እስከ አሁን ድረስ በኃጢአታችሁ አላችሁ።"

[ ፩ቆሮ.፲፭፥፲፬ ]

▬▬▬▬▬▬  †  ▬▬▬▬▬▬

💖        ድንቅ ትምህርት        💖

[      በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ      ]

🕊       እንኳን አደረሳችሁ        🕊

†                       †                        †
💖                    🕊                     💖
2024/09/29 11:21:34
Back to Top
HTML Embed Code: