Telegram Web Link
የምትወዱት ሰዎች ፈጽሞ አልቅሱለት፡፡

ወየው ወየው ወየው አማኑኤል አምላካችን፡፡

ወየው ወየው ወየው መድኃኒታችን ኢየሱስ፡፡

ወየው ወየው ወየው መድኃኒታችን ኢየሱስ፡፡

ወየው ወየው ወየው ንጉሣችን ክርስቶስ፡፡

ወየው ወየው ወየው ጻድቁን ከዕንጨት አወረዱት፡፡

ሥጋውንም ለመገነዝ ከርቤ የሚባል የጣፈጠ ሽቱንና ንጹሕ በፍታን አመጡ፡፡

ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው የማይሞት የማይለወጥ፡፡

ከድንግል ማርያም የተወለደ አቤቱ ይቅር በለን፡፡

ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ የማይሞት የማይለወጥ በዮርዳኖስ የተጠመቀ በመስቀልም የተሰቀለ አቤቱ ይቅር በለን፡፡"

#ቅዳሴ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

@Enatachn_mareyam  
@Enatachn_mareyam
                         †                         


“ ሁሉን የያዘውን ያዙት ፣ ሁሉን የሚገዛውን አሠሩት ፣ የሕያው አምላክን ልጅ አሠሩት ፣ በቁጣ ጎተቱት ፣ በፍቅር ተከተላቸው ፣ በሚሸልተው ፊት እንደማይናገር እንደ የዋህ በግ በኋላቸው እየተከተለ ወሰዱት፡፡

ሊቃነ መላእክት በመፍራትና በመንቀጥቀጥ በፊቱ የሚቆሙለትን በአደባባይ አቆሙት ኃጢአትን ይቅር የሚለውን ኃጢአተኛ አሉት ፣ በፈራጆች ላይ በሚፈርደው በእርሱ ላይ ፈረዱበት፡፡ ለሱራፌል ዘውድ የሚያቀዳጃቸውን የእሾኽ ዘውድ አቀዳጁት። ለኪሩቤል የግርማ ልብስ የሚያለብሳቸውን ቀይ ግምጃ አለበሱት። የመላእክት ሠራዊት በፍጹም መደንገጥ ለሚሰግዱለት እየዘበቱበት በፊቱ ተንበረከኩ፡፡

ይህን ያህል ትሕትና እንደምን ያለ ትሕትና ነው?
ይህን ያህል ትዕግሥት እንደምን ያለ ትዕግሥት ነው?
ይህን ያህል ዝምታ እንደምን ያለ ዝምታ ነው?
ይህን ያህል ሰውን ማፍቀር እንደምን ያለ ፍቅር ነው?
ፍቅር የአምላክን ልጅ ከዙፋኑ ሳበው እስከ ሞትም አደረሰው''

[ መጽሐፈ ቅዳሴ ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
                            †                             


[        ኃይሌና አምባዬ መጠጊያዬ       ]


• ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወዕዘዝ እስከ ለዓለም
- [ ለአንተ ኃይል ክብር ጌትነት ገዥነት ለዘለዓለሙ ገንዘብህ ነው ]

• አማኑኤል አምላኪየ ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወዕዘዝ እስከ ዓለም
- [ ፈጣሬዬ አማኑኤል ሆይ ኃይል ክብር ጌትነት ገዥነት ለዘለዓለሙ የአንተ ነው ]

• ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶ ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወዕዘዝ እስከ ለዓለም
- [ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ኃይል ክብር ጌትነት ገዥነት ለአንተ ይገባል ]

• ኃይልየ ወፀወንየ ዉእቱ እግዚእየ እስመ ኮንከኒ ረዳእየ እብል በአኮቴት አቡነ ዘበሰማያት እስከ ይእቲ መንግሥት ኃይል ወስብሐት ለዓለም ዓለም።
- [ ኃይሌና አምባዬ መጠጊያዬ እርሱ ጌታዬ ነው ረዳቴ ሆነህልኛልና በምስጋና እንዲህ እላላው አባታችን ሆይ እስከ ኃይል ክብር ምሥጋና ለዘለዓለሙ አሜን። ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
                         †                         

" እነሆም ፥ በጎና ጻድቅ ሰው የሸንጎ አማካሪም የሆነ ዮሴፍ የሚባል ሰው ነበረ ፤

ይህም በምክራቸውና በሥራቸው አልተባበረም ነበር ፤ አርማትያስም ከምትባል ከአይሁድ ከተማ ሆኖ እርሱ ደግሞ የእግዚአብሔርን መንግሥት ይጠባበቅ ነበር።

ይኸውም ወደ ጲላጦስ ቀርቦ የኢየሱስን ሥጋ ለመነው ፤ አውርዶም በተልባ እግር ልብስ ከፈነው ፥ ማንም ገና ባልተቀበረበት ከዓለትም በተወቀረ መቃብር አኖረው።" [ ሉቃ . ፳፫ ፥ ፶ - ፶፫ ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
ክርስቲያኖች ሁላችሁ ኑ እናፅናናት

#ክርስቲያን_ሁላችሁ ኑ ድንግል ማርያምን #እናፅናናት፤ በልጇ ስቃይ ሆድ ብሷታልና፥ እንባን ከመጠጧ ጋር አመድንም ከምግቧ ጋር ቀላቅላለችና። #የተወደደ_ልጇ_በመስቀል ተሰቅሎ ስታየው አንድ ጊዜ ከእሾህ አንድ ጊዜ ከድንጋይ ላይ እየወደቀች አለቀሰች። ወንድም የሌለው አንድ ልጇ እንዲህ ሲሰቃይ የወለደ አንጀቷ እንደምን ይቻል? ምንስ ብላ ትፅናና? ያፅናኗት ዘንድ ሊቃነ መልአክት በዙሪያዋ መጡ ግን አልተፅናናችም፤ ልጄ እያለ የሚጠራት አባቷ ዳዊትም መጣ ድንግል ግን እርቃኑን የተሰቀለው ልጇን እያየች መሪር #እንባን_አፈሰሰች። ስለ ልጇ ብዙ መከራ አሳልፋለች፥ ያሁኑ የልጇ መከራ ግን ከሀዘኖች ሁሉ የከፋ ሆነባት። አንድ ልጇ እየሞተ ምን ብላ ትፅናና ? የእናቱን አለመፅናናት ያየ ጌታ ኢየሱስ ከሃዘን ብዛት እንዳትሞት ያፅናናት ዘንድ ቁጽረ ገፅ ለተባለው ለዮሐንስ እነኋት እናትህ አለው። በእውነት እነኋት እናታችን በልጇ ስቃይ ሆድ ብሷታልና ክርስቲያን ሁላችሁ ኑ እናፅናናት።"😭😭😭😥😓

@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
                         †                         

🕊    †          ስቅለት        †    🕊

▬▬▬▬▬▬  †  ▬▬▬▬▬▬

[     ላሐ ማርያም [  የማርያም ለቅሶ  ]      ]
------------------------------------------------


የእመቤታችን ለቅሶ ሰማይን ስቅጥጥ ፣ ስቅጥጥ  አደረገው፡፡ ምድርን አንቀጠቀጠ፡፡ ባሕሩን አነቃነቀ ፡፡ ሐዋርያትን ሦስት ቀን አስለቀሰ፡፡ የለቅሶውም ድምጽ ሰውነታቸውን እንደ ሰም አቀለጠ፡፡

--------------------------------------------------

"ልጄ ፡ ሆይ ከዚህ ፡ ካገኘህ ፡ የሞት ፡ ፃዕር ፡ የተነሣ ፡ ግፌን የሚመለከትልኝ ፡ ሹም ፡ ወይም ፡ በሐዘን ፡ የተሰበረውን ፡ ልቤን ፡ አይቶ ፡ በማስተዋል ፡ የሚፈርድልኝ ፡ ዳኛ ፡ አላገኘሁም።

መኰንን ፡ ሆይ ፡ እንደ ፡ ሕጉ ፡ የምትፈርድስ ፡ ቢሆን ፡ ኖሮ ፡ ንጉሥ ፡ ልጄን ፡ እንደራበው ፡ እንደጠማው ፡ የአይሁድ ፡ ወገኖች ፡ ባልሰቀሉትም ፡ ነበር።

አንተም ፡ ሊቀ ፡ ካህናት ፡ በዕውነት ፡ ፈራጅ ፡ ብትሆን ፡ ባርያ ፡ በጌታው ፡ ፈንታ ፡ መሞት ፡ በተገባው ፡ ነበር። በበርባን ፡ ፈንታ ፤

ሹም ፡ ሆይ ፡ በቅን ፡ የምትፈርድ ፡ ብትሆን ፡ ልጄን ፡ ባልሰቀልከውም ፡ ነበር። አንተም ፡ ሊቀ ፡ ካህናት ፡ በዕውነት ፡ የምትፈርድ ፡ ብትሆን ፡ ከልጄ ፡ ይልቅ ፡ ይሁዳ ፡ ለሞት ፡ የተገባው ፡ በሆነ ፡ ነበር። ሹም ፡ ሆይ ፡ ፍርድን ፡ የምታውቅ ፡ ቢሆን ፡ ልጄን ፡ ሥጋውን ፡ አራቁተህ ፡ መስቀል ፡ ባልተገባህም ፡ ነበር።

ሊቀ ፡ ካህናት ፡ ሆይ በቅን ፡ የምትፈርድ ብትሆን ፡ ወንበዴውን ፡ አድነህ ፡ ጻድቁን ባልገደልከውም ፡ ነበር።

ዳኛ ፡ ሆይ ፡ መልካም ፡ ፍርድን ፡ የምታውቅ ብትሆን ፡ ኑሮ ፡ ጦሮች ፡ በላይህ ላይ ሲያንዣብቡ ፡ ጽኑዕ ፡ የሆነውን ፡ ባልገደልከውም ነበር።

አንተም ፡ ሊቀ ፡ ካህናት ፡ በቅን ፡ የምትፈርድ ብትሆን ፡ የጌታህን ፡ ፊት ፡ ባፈርክ ነበር። እኔ ፡ ስለጦርነት ፡ ሰልፍ ፡ ስሰማ ፡ የንጉሥ ፡ ልጅ ፡ በጦርነቱ ፡ ውስጥ ፡ የተያዘ ፡ እንደሆን ፡ እንዳይሞት ፡ ስለእርሱ ፡ እጅግ ፡ በርትተው ፡ እየተዋጉ ፡ ወደ ፡ አባቱ፡ በፍጹም ፡ ጌትነትና ፡ ክብር ፡ እስከ ፡ አደረሱት ፡ ድረስ ፡ ይጠብቁታል።

ሊቀ ፡ ካህናት ፡ ሆይ ፡ ለምን ፡ እንዲህ ፡ ሆነ ፡ በጠየቅኸው ፡ ጊዜ ፡ ዕውነቱን ፡ አስረዳህ ፡ ግን ፡ በአንተ ፡ ዘንድ ፡ የተጠላ ፡ ሆነ ፡ ሐሰትን ፡ ወደድክ ፤ እምነትህንም ፡ በሐሰቱ ፡ ላይ ፡ አጸናህ ፤ እንግዲህ ፡ ከእውነተኛው ፡ ከእርሱ ፡ በቀር ፡ ማንን ፡ ትጠይቃለህ። በፊትህ ፡ የቆመው ፡ እርሱ ፡ እውነተኛ ፡ እንደሆነ ፡ አታውቅምን ፡ እርሱም ፡ በዕውነት ፡ ሕይወት ፡ ነው።

ንጽሕት ፡ ድንግል ፡ ሆይ ፡ በኢየሩሳሌም ፡ ከተማ ፡ በዚች ፡ ትውልድ ፡ መካከል የሆነውን ፡ ታላቅ ፡ ግፍ ፡ እዪ ፣ እነሆ ፡ ከእነርሱ በሚበልጠው ፡ ላይ ፡ ተሰብስበው ፡ ስም ለሞት ፍርድ ፡ ሰጥተውታልና።

ከዚህ ፡ ሁሉ ፡ በኋላ ፡ ክርስቶስ ፡ በመስቀል ላይ ፡ እንደሆነ ፡ ነበር ፣ የመቶ ፡ አለቃውን በዕውነት ፡ ይህ ፡ ሰው ፡ የእግዚአብሔር ልጅ ነው ፡ ብሎ ፡ አመነ ፤ እሊህ ፡ ተአምራቶቹ በሁሉ ፡ ዘንድ ፡ ታመኑ። በዕንጨት ፡ መስቀል ፡ ላይ ፡ ሳለ ምዕመናን ሁሉ ፡ በአንድነት ፡ አለቀሱለት።

ላሐ ማርያም [  የማርያም ለቅሶ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
🕊

[     ፫. በማርያም እሙ    ]  ፦

†                     †                       †

. . . ሶበ ሰማዕኪ ማርያም ዘነገሩኪ በቃል ፤
ዘውኅዘ እምአዕይንትኪ ፥ ከመ ማየ ክረምት ዘይፈለፍል ፤
ድንግል ድንግል ፥ ወላዲተ አምላክ ቃል ፤
ቤዛ ይኲነነ ፥ ማየ አንብዕኪ እምኃጉል !

- የልጅሽን መከራ በነገሩሽ ጊዜ ፤
እንደ ክረምት ዝናም ከዐይኖችሽ የፈሰሰው እንባ ፤
የአካላዊ ቃል እናቱ ድንግል ሆይ ፤
ከጥፋት እንድንድን ቤዛ ይሁነን !

እንኳን አደረሰን !

በዕጸ መስቀሉ ቤዛነት ያዳነን ቸሩ መድኃኔዓለም ፥ በምድር በመቅሠፍት ፥ በሰማይ በገሃነመ እሳት አያጥፋን !

አሜን  !

[  ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ    ]


               †       †       †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💖                    🕊                     💖
#እውነት__ተሰቀለ


እውነት ተገኝታ አታውቅም ነበር። ሰዎች ለእውነት ያላቸውን ጥላቻ በእውነተኞች ላይ ይፈጽሙት ነበር። በመጋዝ በመሰንጠቅ ፣ በፍላት በመቀቀል፣ በእሳት በመቃጠል፣ ለተራቡ አንበሶች በመሰጠት፣ ደጋግ አበው፣ ቡሩካን ነቢያት፣ ጣዕመ ዓለምን የናቁ ፈላስፎች እውነት ብትገኝ የሚገጥማትን ጉዳት ተቀብለዋል። ዛሬ ግን እውነተኛ ሳይሆን ራሱ እውነት ተገኝቷል። ላይማሩበት ስለ እውነት ሰዎች ይጠይቃሉ። አንገታቸውን ይነቀንቃሉ፣ ሕይወታቸው ግን ከወላዋይነት ንቅንቅ አይልም። ከተቃዋሚዎች በላይ መሐል ሰፋሪዎች እውነትን ተፋልመዋል። ተቃዋሚዎች ላመኑበት ይሞታሉ፣ ወላዋዮች ግን የሚኖሩለት ነገር የላቸውምና የሚሞቱለት ነገር አይኖራቸውም። ወላዋዮች በጆሮ እየሰሙ በኑሮ ግን ይቃወማሉ። ተቃዋሚዎች ግን አንሰማም የሚሉት ከሰሙት እንደሚኖሩለት ስለሚያውቁ ነው። ብዙ ሰው ቀድሞ ለሰማው እንጂ ለእውነት አልታመነምና ያሳዝናል።

ለመቀላቀል 👇👇👇👇
@Enatachn_mareyam  
@Enatachn_mareyam
2024/09/30 17:16:23
Back to Top
HTML Embed Code: