💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
🕊 ዐቢይ ጾም [ ጾመ እግዚእ ] 🕊
▷ " ከ ጨ ለ ማ መ ው ጣ ት ! "
[ 💖 በብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ 💖 ]
[ 🕊 ]
----------------------------------------------------
" መብራትንም አብርተው ከዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል።
መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።" [ ማቴ.፭፥፲፭ ]
" ሁላችሁ የብርሃን ልጆች የቀንም ልጆች ናችሁና። እኛ ከሌሊት ወይም ከጨለማ አይደለንም"
[ ፩ ተሰሎ.፭፥፭ ]
🕊 💖 🕊

🕊
[ † እንኳን ለጥንተ በዓለ ምሴተ ሐሙስ እና ኢዮጰራቅስያ ድንግል ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †
🕊 † ምሴተ ሐሙስ † 🕊
† ስም አጠራሩ ከፍ ከፍ ይበልና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰባ ስምንት [1978] ዓመታት በፊት "ምሴተ ሐሙስ" በምትባለው በዚሕች ዕለት :-
፩. በወዳጁ በዓልዓዛር ቤት የዓለማት ፈጣሪ ሲሆን በትሕትና ዝቅ ብሎ የደቀ መዛሙርቱን እግር አጥቧል::
፪. ለእኛ ድኅነት ይሆነን ዘንድ ቅዱስ ሥጋውን : ክቡር ደሙን ለመጀመሪያ ጊዜ ሰጥቷል::
፫. በጌቴሴማኒ ላበቱ እንደ ደም እየተንጠፈጠፈ ጸልዮ "ወደ ፈተና እንዳትገቡ ጸልዩ" ሲል አስተምሯል::
፬. ምሽት ፫ (3) ሰዓት አካባቢ ይሁዳ ሊቃነ ካህናቱን አስከትሎ መጥቶ ለ30 ብር አሳልፎ ሰጥቶታል:: [ማቴ.፳፮፥፳፮] (26:26) ዮሐ.፲፫፥፩] (13:1)
ይሕ ሁሉ ለእኛ ድኅነት ተፈጽሟልና ምስጋናና ክብር ለፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይሁን::
🕊 † ኢዮጰራቅስያ ድንግል † 🕊
† ዳግመኛ በዚህ ዕለት እናታችን ቅድስት ኢዮጰራቅስያ ድንግል አርፋለች::
ቅድስቲቱ በ፭ [ 5 ] ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበረች እናት ስትሆን ገና በ9 ዓመቷ ምድራዊ ሐብትን ንቃ መንናለች:: ምክንያቱም ዘመዶቿ የሮም ነገሥታት እነ አኖሬዎስ ነበሩና:: ድንግል ኢዮጰራቅስያ በገዳም : በጾምና በጸሎት : በፍፁም ትሕትናና ታዛዥነት : እንዲሁም በፍቅር ኑራ በዚህች ቀን አርፋለች::
† ከቅድስት እናታችን በረከት አምላኩዋ ይክፈለን::
🕊
[ † መጋቢት ፳፮ [ 26 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱሳን ሐዋርያት
፪. ቅድስት ድንግል ኢዮጰራቅስያ
፫. ቅዱስ ፍርፍርዮስ ሰማዕት
[ † ወርሐዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
፪. አቡነ ሐብተ ማርያም ጻድቅ
፫. አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ
፬. ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን
፭. አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን
† " ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘለዓለም ሕይወት አለው:: እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሳዋለሁ:: ሥጋዬ እውነተኛ መብል : ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነውና:: ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል:: እኔም በርሱ እኖራለሁ::" † [ ዮሐ.፮፥፶፫ ] (6:53-56)
† " እግራቸውን አጥቦ : ልብሱንም አንስቶ ዳግመኛ ተቀመጠ :: እንዲሕም አላቸው :- 'ያደረግሁላችሁን ታስተውላላችሁን ? እናንተ መምሕርና ጌታ ትሉኛላችሁ:: እንዲሁ ነኝና መልካም ትላላችሁ:: እንግዲህ እኔ ጌታና መምሕር ስሆን እግራችሁን ካጠብሁ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ እግራችሁን ትተጣጠቡ ዘንድ ይገባል::' " † [ዮሐ.፲፫፥፲፪-፲፬] (13:12-14)
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖

†
[ መድኃኔ ዓለም ]
🕊
† እንኳን ለጌታችንና አምላካችን መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ዓመታዊ የስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †
[ አቤቱ ፥ ነፍሴን ከሲኦል አወጣሃት ! ]
🕊 💖 🕊
" ጌታዬና መድሃኒቴ ኢየሱስ ክርስቶስ የደረሰበትን ጉስቁልና ሊተካከል የሚችል ጉስቁልና እንደምን ያለ ነው? ቀላያት ፊቱን በተመለከቱ ጊዜ የሚንቀጠቀጡለት ፀሐይ ብርሃኗን የምትከለክልለት : ጨረቃ የምታለቅስለት : ከዋክብት የሚረግፉለት : ክፉዎች አይሁድ ተፉበት : እጃቸውን አክርረው መቱት : ከስድብ ሁሉ የከፋ ስድብ ሰደቡት::
ስድባቸው እንዲሁ የቃላት ብቻ አልነበረምና ምራቅና ቡጢም አለበት እንጂ : ይህ ብቻ አይደለም : - ክርስቶስ ሆይ በጥፊ የመታህ ማን ነው? ትንቢት ተናገርልን ¡ የሚል ስላቅም አለበትና:: ጌታዬና ንጉሴ መከራ ያልደረሰበት አካል አልነበረውም:: ጭንቅላቱ ላይ የእሾኽ አክሊል ደፉበት : ፊቱን በጥፊ መቱት ፡ ትከሻውን መስቀል አሸከሙት : እጁን በችንካር ቸነከሩት : እግሩን በምስማር ቸነከሩት : አፉን ኮምጣጤ አጠጡት : መላ አካልቱን በጅራፍ ገረፉት :: ወዮ ! እንዲህ ያለ መውደድ እንደምን ያለ ፍቅር ነው፡፡ "
[ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ]
🕊
[ መድኃኔ ዓለም ]
💖 ድንቅ ትምህርት 💖
[ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ]
" አቤቱ ፥ ነፍሴን ከሲኦል አወጣሃት ፥ ወደ ጕድጓድም እንዳልወርድ አዳንኸኝ።" [መዝ.፴፥፫]

[ † እንኳን ለታላቁ ክርስቲያናዊ ንጉሥ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †
🕊 † ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ † 🕊
† ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ለቤተ ክርስቲያን የፈፀመውን መልካም ተግባር ያሕል መሥራት የቻለ ንጉሥ በሐዲስ ኪዳን የለም:: ጻድቁ ንጉሥ ከቅድስት እናቱ እሌኒና ከአረማዊ አባቱ ቁንስጣ በበራንጥያ ተወለደ::
ዘመኑ ዘመነ ዐጸባ [የመከራ ጊዜ] ወይም የሰማዕታት ዘመን በመሆኑ ክርስቲያኖች በግፍ የሚጨፈጨፉበት ወቅት ነበር:: ክርስቲያኖችን ከምድረ ገፅ ለማጥፋት በተደረገው የ፵ [40] ዓመታት ዘመቻ አብያተ መቃድስና መጻሕፍት ተቃጠሉ:: ብዙዎቹ በየበርሃው ተሰደዱ:: ሚሊየኖች በግፍ አለቁ::
የዚሕን ዘመን መከራ በውል ያልተረዳ ሰው ቅዱስ ቆስጠንጢኖስን ሊያከብር አይችልም:: ምክንያቱም ይህን የመከራ ዘመን በፈቃደ እግዚአብሔር አስቁሞ : ቀርነ ሃይማኖት የቆመው : ብዙ ሥርዓት የተሠራው : ቤተ ክርስቲያንም ያበራችው በዘመኑ ነውና::
ቅዱሱ ንጉሥ ለሁሉም ነቢያት : ሐዋርያትና ሰማዕታት አብያተ ክርስቲያናትን ራሱ በመሠረታት በቁስጥንጥንያ አንጿል:: በዘመኑ ቤተ ክርስቲያን በሰላም ኖራለት : በኃይለ መስቀሉ ጠላት ጠፍቶለት ኑሮ በዚህች ቀን አርፏል:: "ቆስጠንጢኖስ" ማለት "ሐመልማል" ማለት ነው::
††† ዳግመኛ በዚሕ ቀን የዓለማት ፈጣሪ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ እኛ በሆነው ሞቱ በመቃብር ውስጥ አድሯል::
††† ጌትነት ያለው አምላካችን በይቅርታው ይጐብኘን:: መልካም መሪንም ይስጠን::
🕊
† መጋቢት ፳፰ [ 28 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩. ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ (ጻድቅ ንጉሥ)
፪. ቅድስት እሌኒ ንግስት
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. አማኑኤል ቸር አምላካችን
፪. ቅዱሳን አበው [አብርሃም: ይስሐቅና ያዕቆብ]
፫. ቅዱስ እንድራኒቆስና ሚስቱ ቅድስት አትናስያ
፬. ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ
፭. ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ [ሰማዕት]
† " እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ: ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር: ልመናና ጸሎት: ምልጃም: ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ: ስለ ነገሥታትና መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ:: ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው::" † [፩ጢሞ. ፪፥፩-፬

#አባ-ጳኲሚስ ዘወትር፣ #አማኑኤል ክርስቶስ፣ የሰው ልጆችን ለማዳን ሲል በዕለተ ዓርብ የተቀበለውን መከራ በማሰብ አብዝቶ ይሰግድ ነበር፤
አንድ ቀን እንዲህ እየሰገደ ከሰውነቱ በሚወጣው ላብ መሬቱን አረጠበው፤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ተገለጠለት፤
#አባ_ጳኲሚስም "ጌታዬ እንዲህ የምኾነው አንተን #አገኛለኊ ብዬ ነው" አለው፤
#ጌታችንም በዕለተ ዓርብ እንደ ተሰቀለ ሆኖ ታየውና "እኔም አንተን #ለማዳን ብዬ ነው፣ እንደዘህ የተሰቀልኩት" አለው።
[ ታላቁ ቅዱስ ጳኲሚስ - የተጋድሎ ሕይወቱ እና ሥርዐተ ገዳሙ ፤ በወ/ሮ ዘውዴ ገ/እግዚአብሔር ፤ ገጽ፦ ፸፬/74 ፤፳፻፫/
#ሰናይ___ቀን🙏
አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇
@Enatachn_mareyam