Telegram Web Link
ከትንሳኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ፡-

#ሰኞ- ማዕዶት ይባላል፡-
ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡

#ማክሰኞ- ቶማስ ይባላል፡-
በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29

#ረቡዕ- አልአዛር ይባላል
በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን

#ሐሙስ- አዳም ሐሙስ ይባላል
በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን

#አርብ- ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል
በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና

#ቅዳሜ- ቅዱሳት አንስት ይባላል፡-
በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል

#እሁድ- ዳግም ትንሳኤ ይባላል፡-
በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል

#እንኳን_ለብርሃነ_ትንሣኤው_አደረሳችሁ

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇

@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
🕊

✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞

†   ሚያዝያ ፳፰ [ 28 ]  †  

[ ሚያዝያ ፳፰ [ 28 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

🕊  †  ሜልዮስ ሰማዕት  †   🕊

ቅዱስ ሜልዮስ ልጅነቱን በመንፈሳዊ ትምሕርት ያሳለፈ : በጉብዝናው ወራት ፈጣሪውን ያሰበ ደግ ክርስቲያን ነው:: ይሕችን ዓለም ከነ ክፋቷ ንቆ ኮራሳት ወደሚባል በርሃ ሔዶ በተራራውና በደኑ ውስጥ በጾምና በጸሎት: በትሕርምትም ለበርካታ ዓመታት ተጋድሏል::

በነዚህ የብሕትውና ዘመናቱ ልብሱን ፀሐይና ብርድ ቆራርጦ ስለ ጨረሳቸው ፈጣሪው ጸጉርን አልብሳታል:: የአባ ሜልዮስ ጸጉሩ እስከ እግሩ : ጽሕሙ እስከ ጉልበቱ ነበር::

እድሜው ገፍቶ ሲያረጅ እንዲያገለግሉት እግዚአብሔር ሁለት ወጣት ምስጉን ክርስቲያኖችን ላከለት:: እነርሱም አባ ኢያሱና አባ ዮሴፍ ይባላሉ:: ፪ቱ ቅዱሳን አምላካቸውን እግዚአብሔርንና አባታቸው ቅዱስ ሜልዮስን በፍጹም ቅንነት አገልግለዋል::

ከቆይታ በኋላ ግን በአካባቢው የነበሩ ጣዖት አምላኪዎች አራዊት እናጠምዳለን ብለው በዘረጉት መረብ ቅዱስ ሜልዮስን ያዙት:: ክርስቲያን መሆኑን ሲያውቁ "ለፀሐይ ስገድ" ብለው ደበደቡት::

ደቀ መዛሙርቱ ተሯሩጠው መጥተው አባታቸውን በመከራ መሰሉት:: ክርስቶስን አንክድም ስላሉ ሁለቱንም በሰይፍ አንገታቸውን መቷቸው:: ቅዱስ ሜልዮስን ግን ለ፲፭ [15] ቀናት ካሰቃዩት በኋላ በዚህች ቀን በቀስት በተደጋጋሚ ወግተው ገድለውታል:: ጻድቅና ሰማዕት ቅዱስ ሜልዮስ ብዙ ተአምራትን አድርጓል::

ገዳዮች ግን ወደ ሃገራቸው ሲመለሱ የሜዳ አህያ ሊያድኑ የወረወሩትን ቀስት የእግዚአብሔር መልአክ ወደነርሱ መልሶባቸው ልብ ልባቸውን ተወግተው ሙተዋል::

ቸር አምላክ ከቅዱሱ ሜልዮስና ከደቀ መዛሙርቱ
በረከትን ያካፍለን::

[ † ሚያዝያ ፳፰ [ 28 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ ሜልዮስ ዘደብረ ኮራሳን [ጻድቅና ሰማዕት]
፪. አባ ኢያሱና አባ ዮሴፍ [ ደቀ መዛሙርቱ ]
፫. ቅዱስ ብስጣውሮስ ሰማዕት [ተንባላት የገደሉት]

[ †  ወርኃዊ በዓላት ]

፩ ፡ አምላካችን አማኑኤል
፪ ፡ ቅዱሳን አብርሃም ፡ ይስሐቅ ፡ ወያዕቆብ
፫ ፡ ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ
፬ ፡ ቅዱሳን እንድራኒቆስ ወአትናስያ
፭ ፡ ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ
፮ ፡ ቅዱሳን አባዲር ወኢራኢ
፯ ፡ ቅድስት ሶስና

" ልትቀበለው ያለህን መከራ አትፍራ:: እነሆ እንድትፈተኑ ዲያብሎስ ከእናንተ አንዳንዶቻችሁን በወኅኒ ሊያገባችሁ አለው:: አሥር ቀንም መከራን ትቀበላላችሁ:: እስከሞት ድረስ የታመንህ ሁን:: የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለሁ:: " [ራዕይ.፪፥፲] (2:10)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
                      †                       

"የይውሕና ልብስን የምትለብሺ የርኅራኄ መጎናጸፊያንም የምትጎናጸፊ እመቤቴ ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ እያልሁ ዘወትር እጅ እነሳሻለሁ፡፡ የአበሳንና የኃጢአትን ሥር ከሰውነቴ ንቀዪ፡፡

ከልጅሽ ጎን በፈሰሰው ደምም የሰውነቴን ጉስቁልና አንጪ፡፡ የቅድስናና የንጽሕና የነጭ ሐርንም በእኔ ላይ ዘርጊ፡፡ ጸሎቴን ለመቀበልም ዘወትር ክንፎችሽን ዘርጊ፡፡ በምጠራሽ ጊዜም እኔን ለመርዳት ፈጥነሽ ድረሺ ፤ ለዘላለሙ አሜን፡፡"

[ እንዚራ ስብሐት ]

🕊

[ ኦርቶዶክሳዊነት ክርስቶሳዊ የብርሃን ሕይወት ! ]

†                       †                        †
💖                    🕊                     💖
🕊

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡

❖ ሚያዝያ ፳፱ [ 29 ] ❖

✞ እንኩዋን ለጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወርሐዊ በዓለ ልደትና ለቅዱሳኑ ዓመታዊ በዓለ ዕረፍት በሰላም አደረሳችሁ ✞

🕊  †   ተዝካረ በዓሎሙ ለቅዱሳን ቅዱስ አርስጦስ ሐዋርያ ወአባ አካክዮስ ጻድቅ   †   🕊

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዚህ ዕለት ከምታስባቸው ቅዱሳን ሐዋርያው ቅዱስ አርስጦስና አባ አካክዮስ ቅድሚያውን ይይዛሉ::

🕊  †  አርስጦስ ሐዋርያ †   🕊

ቅዱስ አርስጦስ ከ፸፪ [72]ቱ አርድእት አንዱ ሲሆን ከጌታችን እግር ለ፫ [3] ዓመታት ቁጭ ብሎ የተማረ: ፈጣሪው ከዋለበት ውሎ: ካደረበት አድሮ: የእጁን ተአምራት ያየ: የቃሉንም ትምሕርት ያደመጠ ሐዋርያ ነው::

ከጌታችን ዕርገት በሁዋላም በጽርሐ ጽዮን መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ ለስብከተ ወንጌል ወደ ዓለም ወጥቷል:: መጀመሪያ ከዋኖቹ ሐዋርያት ጋር በረዳትነት አገልግሏል:: ከቆይታ በሁዋላ ግን ሃገረ ስብከት ተሰጥቶት ብዙ ነፍሳትን ማርኩዋል:: አሕዛብንም ካለማመን ወደ ማመን አምጥቷል::

በነዚህ ጊዜያት ጭንቅ ጭንቅ መከራዎች ደርሰውበታል:: ቅዱስ አርስጦስ ሐዋርያ በተሰጠው መክሊት አትርፎ ፈጣሪውንም ደስ አሰኝቶ በዚሕች ቀን አርፏል::


🕊  †   አባ አካክዮስ  †   🕊

ዳግመኛ በዚህ ቀን አባ አካክዮስ አርፏል:: ቅዱሱ ከሕጻንነቱ ጀምሮ ንጽሕናን ያዘወተረ: በገዳማዊ የቅድስና ሕይወቱ የተመሠከረለት ነው:: ምሑርነቱንና ቅድስናውን የተመለከቱ ሰዎች በኢየሩሳሌም ላይ ዽዽስናን ሹመውታል::

በመንበረ ዽዽስናውም ላይ እያለ ዕረፍት አልነበረውም:: ኢ-አማንያን ይገርፉት: ያስሩት: ያረሰቃዩትም ነበር:: ቤተ ክርስቲያን ስለ ተጋድሎው ጻድቅ: የዋሕና ንጹሕ ብላ ትጠራዋለች::

እግዚአብሔር ከቅዱሳኑ ረድኤት: ጸጋና በረከት ይክፈለን::

[ †  ሚያዝያ ፳፱ [ 29 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ አርስጦስ ሐዋርያ [ከ፸፪ቱ አርድእት]
፪. አባ አካክዮስ ዘኢየሩሳሌም [ጻድቅና ንጹሕ]
፫. አባ ገምሶ ሰማዕት

[ †  ወርኀዊ በዓላት ]

፩. የፈጣሪያችንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት
፪. ቅድስት አርሴማ ድንግል
፫. ቅዱስ ዼጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት
፬. ቅዱስ ማርቆስ ዘቶርማቅ
፭. ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ኢትዮዽያዊት
፮. ቅዱስ ዘርዐ ክርስቶስ [ጻድቅና ሰማዕት]

" ሰብዓውም በደስታ ተመልሰው ጌታ ሆይ ! አጋንንት ስንኩዋ በስምህ ተገዝተውልናል አሉት:: እንዲህም አላቸው :- 'ሰይጣንን እንደ መብረቅ ከሰማይ ሲወድቅ አየሁ:: እነሆ እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ በጠላትም ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችሁአለሁ:: የሚጐዳችሁም ምንም የለም:: ነገር ግን መናፍስት ስለ ተገዙላችሁ በዚህ ደስ አይበላችሁ:: ስማችሁ ግን በሰማያት ስለ ተጻፈ ደስ ይበላችሁ::" [ሉቃ.፲፥፲፯] (10:17-20)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
                        †                        

🕊  💖        ሰ ላ ም ታ        💖  🕊

'' ክርስቶስ ተንስአ እሙታን
▸ በዐቢይ ኃይል ወስልጣን ፤
አሰሮ ለሰይጣን
▸ አግአዞ ለአዳም ፤
ሰላም
▸ እምይእዜሰ ፤
ኮነ
▸ ፍስሐ ወሰላም ''

'' ክርስቶስ በታላቅ በኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሳ ፤ ሰይጣንን አሰረው አዳምንም ነጻ አወጣው ፤ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ ፍፁም ሰላም እና ደስታ ሆነ። ''


†                       †                        †
💖                    🕊                     💖
#ማክሰኞ

ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ከ፲፪ቱ ቅዱሳን ሐዋርያት አንዱ ሲኾን ለጊዜው ትንሣኤ ሙታንን ከማያምኑ ሰዱቃውያን ወገን በመኾኑ የክርስቶስን ትንሣኤ ተጠራጥሮ ነበር:: ምሥጢሩ ግን "ካላየኹ - ካልዳሰስኩ አላምንም" ያለው ከፍቅሩ የተነሣ እውነት አልመስልኽ ብሎት ነው::

አንድም ጌታ መለኮታዊ ጎኑን እንዲዳስሰው ቢፈቅድለት ነው:: ይኽች የቅዱስ ቶማስ እጅ ዛሬም ድረስ ሕያው ናት:: ተአምራትንም ታደርጋለች::

በረከቱ ይደርብን 🙏 አምላካችን በምሕረት ዓይኑ ይመልከተን - ከሚተርፉትም ይደምረን 🙏 አሜን በእውነት!

#እንኳን_ለብርሃነ_ትንሣኤው_አደረሳችሁ

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
      •➢ 👇  ለማግኘት // 👇

@Enatachn_mareyam  
@Enatachn_mareyam
                        †                        

🕊  💖   ዕለተ ማክሰኞ   💖  🕊

[ " ቶማስ ወአብርሃም " ]

▬▬▬▬▬▬  †  ▬▬▬▬▬▬
------------------------------------------------

እንኩዋን ለበዓለ ዕለተ " ቶማስ ወአብርሃም " ዓመታዊ የመታሠቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

ልክ የሰሙነ ሕማማቱ ዕለታት ስምና ምሥጢር እንዳላቸው ሁሉ ከትንሳኤ በሁዋላ የሚገኙ ዕለታትም ስምና ምሥጢር አላቸው::

ሰኞን ቤተ ክርስቲያን "ማዕዶት" ብላ እንደምታከብር ትናንት የተመለከትን ሲሆን ማክሰኞን ደግሞ ቤተ ክርስቲያን "ቶማስ" : አንድም "አብርሃም" ብላ ታከብረዋለች::

፩. 🕊     †    ቶማስ    †    🕊

ከ12ቱ ቅዱሳን ሐዋርያት አንዱ ሲሆን ለጊዜው ትንሳኤ ሙታንን ከማያምኑ ሰዱቃውያን ወገን በመሆኑ የክርስቶስን ትንሳኤ ተጠራጥሮ ነበር::
ምሥጢሩ "ግን ካላየሁ : ካልዳሰስኩ አላምንም" ያለው ከፍቅሩ የተነሳ እውነት አልመስልህ ብሎት ነው::

አንድም ጌታ መለኮታዊ ጎኑን እንዲዳስሰው ቢፈቅድለት ነው:: ይህች የቅዱስ ቶማስ እጅ ዛሬ ድረስ ሕያው ናት:: ተአምራትንም ታደርጋለች::

፪.   🕊  †    አብርሃም    †   🕊

ከጻድቃነ ብሊት [ብሉይ] አንዱ የሆነው አባታችን አብርሃም ከጽድቁ የተነሳ ርዕሰ አበው [የአባቶች አለቃ] ተብሏል:: ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የአብርሃም ፈጣሪ ሲሆን የአብርሃም ልጅ መባልን ወዷልና::

በተለይ በከበረ ትንሳኤ የምናገኛትን መንግስተ ሰማያት በስሙ [የአብርሃም ርስት ተብላ] ተጠርታለችና አባታችን በዚህ ቀን ይታሰባል::

እግዚአብሔር ከ፪ቱ ታላላቅ ቅዱሳን ጸጋ በረከትን ያድለን::

"✞" እግዚአብሔርም ለአብርሃም ተስፋ በሰጠው ጊዜ። በእውነት እየባረክሁ እባርክሃለሁ እያበዛሁም አበዛሃለሁ ብሎ ፥ ከእርሱ በሚበልጥ በማንም ሊምል ስላልቻለ ፥ በራሱ ማለ ፤ እንዲሁም እርሱ ከታገሰ በኋላ ተስፋውን
አገኘ።
ሰዎች ከእነርሱ በሚበልጠው ይምላሉና፥ ለማስረዳትም የሆነው መሐላ የሙግት ሁሉ ፍጻሜ ይሆናል ፤ ስለዚህም እግዚአብሔር ፥ የተስፋውን ቃል ለሚወርሱ ፈቃዱ እንደ ማይለወጥ አብልጦ ሊያሳያቸው ስለ ፈቀደ ፥ እግዚአብሔር ሊዋሽ በማይቻል በሁለት በማይለወጥ ነገር ፥ በፊታችን ያለውን ተስፋ ለመያዝ ለሸሸን ለእኛ ብርቱ መጽናናት ይሆንልን ዘንድ ፥ በመሓላ በመካከል ገባ፡፡ "✞" [ዕብ. ፮:፲፫]

ወስብሐት ለእግዚአብሔር !

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]


†                       †                        †
💖                    🕊                     💖
                       †                       

🕊  💖  እንኳን  አደረሳችሁ  💖  🕊


🕊 " ታስበው ዘንድ ሰው ምንድን ነው ? ! " 🕊

▬▬▬▬▬▬  †  ▬▬▬▬▬▬

" ታስበው ዘንድ ሰው ምንድር ነው ? ትጐበኘውም ዘንድ የሰው ልጅ ምንድር ነው ? "

[ መዝ . ፰ ፥ ፬ ]

▬▬▬▬▬▬  †  ▬▬▬▬▬▬

💖        ድንቅ ትምህርት        💖

[      በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ      ]


†                       †                        †
💖                    🕊                     💖
🕊

✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞

❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖

❖ ሚያዝያ ፴ [ 30 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

እንዲህ ኃጢአታችን ጽዋዑን ሞልቶ በተረፈበት በዚህ ዘመን አንዲት ሰዓትም ውድ የሆነች የንስሃ ዕድሜ ናት:: እግዚአብሔር ግን ደግ ነውና ይሔው ሚያዝያን አስፈጸመን::

ባይገባን ነው እንጂ በዚሕች ወር ውስጥ :-

- ሚሊየኖች በደዌ የአልጋ ቁራኛ ሁነዋል::
- ሚሊየኖችም ለንስሃ ሳይበቁ እንዲሁ አንቀላፍተዋል [ሙተዋል]::

እስኪ እርሱ አምላካችን ቀሪዋን ዘመን ደግሞ ለንስሃና ለመልካም ሥራ ባርኮ ይስጠን::

🕊  †  ቅዱስ ማርቆስ ወንጌላዊ  †   🕊

በዚሕች ዕለት ከ፸፪ [72] ቱ አርድእት አንዱ የሆነ: ወንጌላዊ: ሐዋርያ: ሰማዕት: ዘአንበሳና ርዕሰ ሊቃነ ዻዻሳት የተባለ ቅዱስ ማርቆስ በሰማዕትነት ግብፅ ውስጥ ዐርፏል::

ቅዱስ ማርቆስ እናቱ ማርያም: አባቱ አርስጥቦሎስ ይባላሉ:: በልጅነቱ ኦሪትንና የዘመኑን ጥበብ ሥጋዊ በሚገባ ተምሮ ክርስቶስን ከቤተሰቦቹ ጋር ተከትሏል::

የመጀመሪያ ስሙ ዮሐንስ ሲሆን ከ፻፳ [120ው] ቤተሰብ በእድሜ በጣም ትንሹ ፳ [20 ዓመት] እርሱ ነበር:: ለ፫ [3] ዓመታት ከጌታ እግር ሥር ተምሮ: በበዓለ ሃምሳ ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ ለሐዋርያዊ አገልግሎት ብዙ ደክሟል::

በተለይ የግብፅና የኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን አባት ነው:: ክህነትን ያገኘን ከርሱ ነውና:: ቅዱስ ማርቆስ ፲፮ [16] ምዕራፍ ያለውን ወንጌሉን ሲጽፍ ኪሩብ ገጸ አንበሳ በቀኙ: ሊቀ ሐዋርያት በግራው ሆነው ይራዱት ነበር::

ቅዱሱ ክቅዱስ ዻውሎስ: ከበርናባስና ዼጥሮስ ጋር ተጉዟል:: ከብዙ ስቃይና መከራ በኋላ ሰሜን አፍሪካ አካባቢ በዚህ ቀን [በ ፷ [60] ዓ/ም አካባቢ] አረማውያን ገድለውታል::

ዳግመኛ በዚህ ቀን የቅዱስ ማርቆስን ወላጆችን እናስባቸው ዘንድ ይገባል::

❖ ቅዱስ አርስጥቦሎስ [ አባቱ ] የጌታ ቅን አገልጋይ የነበረ፡፡

❖ ቅድስት ማርያም [ እናቱ ]

- ከ፴፮ [36]ቱ ቅዱሳት አንስት አንዷ:
- ጌታችንን ያገለገለች:
- ቤቷን ለሐዋርያትና ለጌታ በስጦታ ያበረከተች ቅድስት ናት::

ቤቷም [ጽርሐ ጽዮን] የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን ስትሆን ይህች ቤት መንፈስ ቅዱስ ወርዶባታል:: የእመቤታችን ግንዘትም ተከናውኖባታል::

❖ እግዚአብሔር ከሐዋርያዊው ቅዱስ ቤተሰብ በረከትን ያድለን::

[ †  ሚያዝያ ፴ [ 30 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ ማርቆስ ሐዋርያ
፪. ቅዱስ አርስጥቦሎስ [አባቱ]
፫. ቅድስት ማርያም [እናቱ]

[ †  ወርኀዊ በዓላት ]

፩. ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
፪. አባ ሣሉሲ ክቡር
፫. ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት
፬. ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት

" . . . እጅግ ሰዎች ተከማችተው ይጸልዩበት ወደ ነበረው ማርቆስ ወደ ተባለው ወደ ዮሐንስ እናት ወደ ማርያም ቤት መጣ:: ዼጥሮስም የደጁን መዝጊያ ባንኩዋኩዋ ጊዜ ሮዴ የሚሏት አንዲት አገልጋይ ትሰማ ዘንድ ቀረበች:: የዼጥሮስ ድምጽ መሆኑንም ባወቀች ጊዜ ከደስታዋ የተነሳ ደጁን አልከፈተችም:: ነገር ግን ወደ ውስጥ ሮጣ ዼጥሮስ በደጅ ፊት ቆሞ እንዳለ አወራች::" [ሐዋ.፲፪፥፲፪] (12:12-15)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
2024/09/29 13:20:28
Back to Top
HTML Embed Code: