Telegram Web Link
🕊

ሕማማተ እግዚእነ በልሳነ አበው [ የጌታችን መከራ በሊቃውንት አንደበት ]


የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ ቄርሎስ እንዲህ አለ ፦

" ታመመ ፤ ሞትን ከተቀበለበት ከሥጋ ተዋሕዶ በመስቀል ላይ በፈቃዱ ለሥጋውያን ሞተ ፣ ባሕርየ መለኮት ሥጋን ተዋሕዶ በማኅፀን ካደረ ጀምሮ ሥጋ ገንዘቡ እንደመሆኑ በሥጋ ይኸንን ሥርዓት ፈጸመ፡፡ ለማይመረመር ለመለኮቱ ባሕርይ እንደሚገባ ደግሞ እርሱ ኅብስት አበርክቶ ሁሉን ያጠግባል፡፡ አይራብም ፣ አይጠማም ፣ አይደክምም ፣ አያንቀላፋም ፣ አይታመምም፣ አይሞትም ሕይወትን ለሁሉ ይሰጣል፡፡ ዳግመኛ በዚያ በሲኦል ተገዝተው ያሉ ነፍሳትን ያድን ዘንድ በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ወረደ በመለኮቱም ሲኦልን በዘበዘ፡፡"

†                       †                        †

የአንጾኪያው ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ዲዮናስዮስ ከላከው ሲኖዶሳዊ መልእክት የተገኘ ፦

" እርሱ መቼም መች ከመለኮቱ ሳይለይ የሰውነትን ሥራ ሁሉ ገንዘቡ አደረገ፡፡ ይኸውም መራብ፣ መጠማት ፣ መንገድ በመሔድ መድከም፣ በመስቀል ላይ መሰቀል ፣ በብረት ችንካር መቸንከር ነው፡፡ በሰውነቱ መቸም መች ሰው ነው ፣ በአምላክነቱም ሰውን የፈጠረ ነው፡፡ ግን ከማይከፈል ተዋሕዶ በኋላ መከፈል የለበትም፡፡ ሰው እንደ መሆኑ ስለ እኛ የታመመው የሞተው እርሱ ነው፡፡ በመለኮቱ ግን መቸም መች አይታመምም አይሞትም ፣ ሕማምንና ሞትንም አይቀበልም፡፡ በሞቱ ሞትን ያጠፋው እርሱ ነው፡፡ ሲኦልንም የበዘበዘው እርሱ ነው፡፡"

🕊

†                       †                        †
💖                    🕊                     💖
                         †                         

🕊    †    ሰሙነ ሕማማት   †    🕊

▬▬▬▬▬▬  †  ▬▬▬▬▬▬

         [    ዘሐሙስ   ]

▬▬▬▬▬▬  †  ▬▬▬▬▬▬

[ †  ጸሎተ ሐሙስ ይባላል  † ]

ጌታችን ለአይሁድ ተላልፎ ከመሰጠቱ በፊት በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ ሲጸልይ በማደሩ [ ማቴ ፳፮፥፴፮ ] ጸሎተ ሐሙስ ይባላል።ጌታችን የደቀመዛሙርቱን እግር በፍጹም ትህትና ዝቅ ብሎ ያጠበበት ዕለት በመሆኑም [ ዮሐ ፲፫፥፫-፲፩ ] ሕጽበተ ሐሙስ ይባላል።

[ †  የምስጢር ቀን ይባላል   † ]

ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ የቅዱስ ቁርባን ምስጢር [ ማቴ፳፮፥፳፮-፳፱ ] በዚህ ዕለት ተፈጽሟልና የምስጢር ቀን ይባላል።

[ †  የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል  † ]

መሥዋዕተ ኦሪት /በእንስሳት ደም የሚቀርብ መሥዋዕት/ቀርቶ ለአለም ድኅነት ራሱን ያቀረበበት ቀን በመሆኑ [ ሉቃ ፳፪፥፳ ] የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል።

[ † የነጻነት ሐሙስ ይባላል  † ]

ለኃጢአትና ለዲያቢሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱን እንዲሁም የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነም [ ዮሐ ፲፭፥ ፲፭ ] የነጻነት ሐሙስ ይባላል።

▬▬▬▬▬▬  †  ▬▬▬▬▬▬

- [  ብፁዕ አቡነ እንድርያስ ስለ ሰሙነ ሕማማት ያስተማሩት ትምህርት [ ክፍል - ፪ - ]

- [  የሰሙነ ሕማማት ዘሐሙስ [ በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ]

†    ድንቅ ትምህርት    †

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
-------------------------------------------------
                        👇
                         †                         

🕊    †    ሰሙነ ሕማማት   †    🕊

▬▬▬▬▬▬  †  ▬▬▬▬▬▬               

[ " ሊ ይ ዙ ት ይ ፈ ል ጉ ነበረ " ]

🕊                    
   
" ስለዚህ ሊይዙት ይፈልጉ ነበር ፤ ነገር ግን ጊዜው ገና ስላልደረሰ ማንም እጁን አልጫነበትም።" [ ዮሐ.፯፥፴ ]


       💖   ድንቅ ትምህርት  💖

[ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ]


         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
                       👇
.............ዕለተ ሐሙስ..........

#ጸሎተ_ሐሙስ_ይባላል

ጌታችን ለአይሁድ ተላልፎ ከመሰጠቱ በፊት በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ ሲጸልይ በማደሩ ማቴ ፳፮፥፴፮ ጸሎተ ሐሙስ ይባላል።ጌታችን የደቀመዛሙርቱን እግር በፍጹም ትህትና ዝቅ ብሎ ያጠበበት ዕለት በመሆኑም ዮሐ ፲፫፥፫-፲፩ ሕጽበተ እግር ይባላል።

በዚህም ምሳሌ ካህናት አባቶቻችን በእለተ ሐሙስ በእውቀት፣ በእድሜ፣ በክብር፣ በስልጣል ትልቅ ነኝ ሳይሉ ከዲያቆናት እስከ ምዕመናን ድረስ ዝቅ ብለው እግር በማጠብ ክርስቶስን በተግባር ይሰብካሉ።

#የምስጢር_ቀን_ይባላል፡-

ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ የቅዱስ ቁርባን ምስጢር ማቴ፳፮፥፳፮-፳፱ በዚህ ዕለት ተፈጽሟልና የምስጢር ቀን ይባላል።

#የሐዲስ_ኪዳን_ሐሙስ_ይባላል፡-

መሥዋዕተ ኦሪት /በእንስሳት ደም የሚቀርብ መሥዋዕት/ቀርቶ ለአለም ድኅነት ራሱን ያቀረበበት ቀን በመሆኑ ሉቃ ፳፪፥፳ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል።

#የነጻነት_ሐሙስ_ይባላል፡-

ለኃጢአትና ለዲያቢሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱን እንዲሁም የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነም ዮሐ ፲፭፥ ፲፭ የነጻነት ሐሙስ ይባላል።


#ሰሞነ__ሕማማት🙏

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇

@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
🕊

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

[ እንኩዋን ለእናታችን ቅድስት ሣራ ዓመታዊ የሰማዕትነት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ]

🕊    ቅድስት ሣራ   🕊

እናታችን ቅድስት ሣራ በዘመነ ሰማዕታት ከነበሩ ክርስቲያኖች አንዷ ናት:: ተወልዳ ያደገችው በሃገረ አንጾኪያ [ሶርያ] ውስጥ ነው:: ለክርስቲያን እንደሚገባ አድጋ በመንፈሳዊ ሥርዓት አግብታለች::

የመከራው ዘመን እየገፋ ሲመጣ ባሏ ሃይማኖቱን በመካዱ ሕይወቷ ተመሰቃቀለ:: በመሐል ላይ ደግሞ ነፍሰ ጡር ነበረችና መንታ ልጆችን ወለደች:: ልጆቿን ክርስትና ለማስነሳት ምድረ ሶርያን ዞረች:: ግን አልቻለችም::

ምክንያቱም ከመከራ ብዛት አብያተ ክርስቲያናት የሚበዙቱ ተቃጥለውና ፈርሰው ነበር:: ቀሪዎቹ ደግሞ ካህናትና ምዕመናን በማለቃቸው ምክንያት ተዘግተው ነበር::

ቅድስት ሣራ ልጆቿ የሥላሴ ልጅነተነን ሳያገኙ እንቅልፍ ሊወስዳት አልቻለምና ሕይወቷን አደጋ ላይ የሚጥል ግን መንፈሳዊ ውሳኔን ወሰነች:: ከሶርያ ተነስታ: በመርከብ ተጭና ወደ ግብፅ ወረደች::

በውሃው መካከል ላይ ሲደርሱ ታላቅ ማዕበል ተነስቶ አናወጣቸው:: በዚህ ጊዜ ቅድስት ሣራ ደነገጠች:: ልጆቿ ጥምቀትን ሳያገኙ መሞታቸው ነውና በእምነት ወደ ፈጣሪዋ ጸለየች:: ሁለቱን ልጆቿን ወስዳ በባሕሩ ላይ በአብ: በወልድ: በመንፈስ ቅዱስ ስም አጥምቃ: ከጡቷ አካባቢ በጥታ በሜሮን አምሳል ቀባቻቸው::

ድንገት ግን በዚህ አፍታ ማዕበሉ ጸጥ አለ:: እርሷም እያደነቀች ወደ ግብጽ ደርሳ ሊቀ ዻዻሳቱን [ቅዱስ ዼጥሮስን] "አጥምቅልኝ" አለችው:: ቅዱስ ዼጥሮስም ሥርዓቱን አድርሶ ሊያጠምቃቸው ባልዲውን ሲዘቀዝቀው ውሃው ረጋበት:: ሁለተኛም: ሦስተኛም ሞከረ:: ግን አሁንም ለሌሎቹ ሕጻናት የሚፈሰው ለቅድስት ሣራ ልጆች እንቢ አለ::

ቅድስት ሣራም "ምናልባት በድፍረቴ ምክንያት ይሆናል" ብላ የሆነውን ሁሉ እያዘነች ነገረችው:: ቅዱስ ዼጥሮስ ግን እግዚአብሔርን አመሰገነ:: አላትም "ፈጣሪ ባንቺ እጅ ስላጠመቃቸው የእኔን እንቢ አለ:: ልጄ ሆይ! ሃይማኖትሽ ትልቅ ነው::"

ከዚህ በሁዋላም ሥጋውን ደሙን አቀብሎ ባርኮ አሰናብቷታል:: ወደ ሶርያ ስትመለስ ግን ሌላ የከፋ ነገር ጠበቃት:: በባሏ ከሳሽነት ወደ ከሃዲው ንጉሥ [ዲዮቅልጥያኖስ] ቀረበች:: ንጉሡ ክርስቶስን ካጂ: የት እንደ ነበርሺም ተናገሪ አላት:: እርሷ ግን ሃይማኖቷ የጸና ነበርና እንቢ አለች::

በዚህም ምክንያት በ፫፻፫ [303] ዓ/ም አካባቢ በዚሁ ቀን አንድ ልጇን በሆዷ: ሌላኛውን በጀርባዋ አድርገው በእሳት አቃጥለው ገድለዋታል:: እነሆ ቤተ ክርስቲያን ታስባታለች:: ታከብራታለችም::

አምላካችን ቅድስት ሣራን እንዳጸና እኛንም ያጽናን:: ከበረከቷም ያድለን::

🕊

[ † ሚያዝያ ፳፭ [ 25 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅድስት ሣራና ፪ [2] ልጆቿ [ሰማዕታት]
፪. አቡነ ገብረ ማርያም ጻድቅ-ዘልሆኝ [ኢትዮዽያዊ]
፫. አባ በብኑዳ ባሕታዊ
፬. ቅዱስ ቴዎድሮስ መስተጋድል
፭. ቅድስት ዶራ

[ †  ወርሐዊ በዓላት ]

፩. ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት
፪. ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት
፫. ቅዱስ አበከረዙን ሰማዕት
፬. ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ
፭. አቡነ አቢብ /አባ ቡላ/
፮. ቅዱስ አባ አቡፋና ጻድቅ

" ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ: ወይስ ጭንቀት: ወይስ ስደት: ወይስ ራብ: ወይስ ራቁትነት: ወይስ ፍርሃት: ወይስ ሰይፍ ነውን? 'ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን:: እንደሚታረዱ በጐች ተቈጠርን' ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው:: በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን:: " [ሮሜ.፰፥፴፭-፴፰] (8:35-38)


† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
#ስምህን_ሰምቶ_ሞት_ይደንግጥ፤ ቀልያት ይሰንጠቁ ፤ዲያቤሎስ ይረገጥ!!
አንተ ሳትደክም ሁሉን ትሸከማለክ፤ ዝም ሳትል ለሁሉ #ታስባለክ፤ ጠላት ግን አንተን መጥፎ አለክ!!" #የፍቅር ዓለት፤የሕይወት ራስ ፤ የጽድቅ መዝገብ ሆይ!! "አንተ በነፃ ሥጋህን ቆርሰህ ደምህን አፍሰክ የሁሉን #ኃጢአት ይቅር ትላለክ፤ ጠላት ግን አንተን ኀጥአ አለክ!!" የድሆች አባት፤የፍትህ ቱንቢ፤ የእውነት ማማ ሆይ!! "አንተ በዙፋንክ ለሁሉ በጽድቅ ትፈርዳለክ፤ ጠላት ግን አንተን ግፈኞች ፍርድ አቆመክ!! 6666 ግዜ በመንዶል አጥንትክ እስኪታይ እየተቀያየሩ ከበው፤#ግፍ_ግፍ_ገረፉክ፤ኀያላን ኩሪቤል ቀና ብለው እማያዩትን ውብ ፊትህን 120ግዜ በጭካኔ በድንጋይ
#መቱክ#ተፋብክ....#አፌዙብክ፤ የተመሳቀለ እንጨት አሸከሙክመው 136ግዜ ገፍትረው ከመሬት ጣሉክ፤እየጎተቱ ወደ ጎለጎታ ወስደው ከነፍሰ ገዳዮች መሐል ሰቀሉክ!! #በመንግስተ_ሰማይ የተመላለሱ እግሮች መስቀል ቀኖ ተቸነከሩ፤ "አዳምን የፈጠሩ ቸር እጆች በመስቀል ቀኖ ተቸነከሩ" "ለአዳም እፍ ብለው ሕይወት የሰጡ መለኮታዊ ከንፈሮች፤የዝሆን #ሐሞት ተጋቱ " ወደ ውኆች መሠረት ሊወርድ፤ኀይለኛውን ሊያስር፤ምርኮን ከጥልቁ ሊበዘብዝ፤ ፤ቤተክርስትያኑን በደሙ ሊዋጅ፤መሠዊያውንም ሊሰራ ፤እንደሚታረድ በግ በዝምታ #ጎኑን_በጦር ተወግቶ ሕይወቱን ሰጠ!!.....
ኦ ክርስቶስ #አማኑኤል_ሆይ!!ሙሽራክ ተዋህዶ ትገዛልሀለች ፤ሕዝብህም ይሰግዱልኻል
፤ሕይወትህን ቤዛ አርገህ ከሞት ዋጅተኻቸዋልና!!!
የአብ የወልድ እና የመንፈስ ቅዱስ ሥም ከፀሐይ መውጫ፤እስከ ፀሐይ መጥለቅያ፤ለዘላለም #የተመሰገነ ይሁን!!!

#ፈራጁን_ሊፈርዱበት_በአደባባይ__አቆሙት

ለመቀላቀል 👇👇👇👇
@Enatachn_mareyam  
@Enatachn_mareyam
                       †                         

" ተነሡ ፥ እንሂድ ፤ እነሆ ፥ አሳልፎ የሚሰጠኝ ቀርቦአል አላቸው።

ይህንም ገና ሲናገር ፥ እነሆ ፥ ከአሥራ ሁለቱ አንዱ ይሁዳ መጣ ፥ ከእርሱም ጋር ብዙ ሕዝብ ሰይፍና ጐመድ ይዘው ከካህናት አለቆችና ከሕዝቡ ሽማግሎች ዘንድ መጡ።

አሳልፎ የሚሰጠውም። የምስመው እርሱ ነው ፤ ያዙት ብሎ ምልክት ሰጥቶአቸው ነበር።

ወዲያውም ወደ ኢየሱስ ቀረበና። መምህር ሆይ ፥ ሰላም ለአንተ ይሁን ብሎ ሳመው።

ኢየሱስም። ወዳጄ ሆይ ፥ ለምን ነገር መጣህ ? አለው። በዚያን ጊዜ ቀረቡ እጃቸውንም በኢየሱስ ላይ ጭነው ያዙት።"

[ ማቴ.፳፮፥፵፮-፶ ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
                              †                            


"ጊዜ ተስዓቱ ሰዓት አጽነነ ርእሶ ኢየሱስ ወይቤ ተፈጸመ ኵሉ።" [ ዮሐ ፲፱፥፳፰-፴ ]


                       †       †       †

" ኢየሱስም እናቱን ይወደው የነበረውንም ደቀ መዝሙር በአጠገቡ ቆሞ ባየ ጊዜ እናቱን። አንቺ ሴት ፥ እነሆ ልጅሽ አላት። ከዚህ በኋላ ደቀ መዝሙሩን። እናትህ እነኋት አለው። ከዚህም ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ ወደ ቤቱ ወሰዳት።

ከዚህ በኋላ ኢየሱስ አሁን ሁሉ እንደተፈጸመ አውቆ የመጽሐፉ ቃል ይፈጸም ዘንድ። ተጠማሁ አለ። በዚያም ሆምጣጤ የሞላበት ዕቃ ተቀምጦ ነበር ፤ እነርሱም ሆምጣጤውን በሰፍነግ ሞልተው በሁሶፕም አድርገው ወደ አፉ አቀረቡለት።

ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ። ተፈጸመ አለ ፥ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ።" [ ፲፱፥፳፭-፴ ]



ከ፮ [6] ስዓት እስከ ፱ [9] ሰዓት በሰማይ ሦስት በምድር አራት በጠቅላላው ፯ [7] ታምራት ተፈሙ።

በሰማይ   †  ፀሐይ ጨለመች፤
               †  ጨረቃ ደም ሆነች፤
               †  ከዋክብት ረገፉ
በምድር   †  አለቶች ተሰነጠቁ ፤
               †  መቃብሮች ተከፈቱ ፤
               †  ሙታን ተነሱ ፤
               †  የቤተ መቅደስ መጋረጃም ከሁለት ተቀደደ ፤ ምድር ተናወጠች።

[ማቴ.፳፯፥፴፪-፵፯ ፤ ሉቃ.፳፪፥፶፬ ፤ ዮሐ.፲፱፥፲፮-፳፪ ፤ ማር.፲፬፥፶፫ ፥ ማር.፲፭፥፳፩-፴፪ ፤ ዮሐ.፲፰፥፳፪ ፤ ሉቃ.፳፫፥፵፮]

ክርስቶስ አምላክነ ዘመጽአ ወሐመ በእንቲያነ በሕማማቲሁ ቤዘወነ።

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
2024/09/29 19:32:59
Back to Top
HTML Embed Code: