Telegram Web Link
🕊

[ ✞ እንኩዋን ለቅዱስ "ስምዖን ዘአርማንያ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞ ]


🕊   ቅዱስ ስምዖን ሰማዕት    🕊

ቅዱስ ስምዖን የአርማንያ ሰው ቢሆንም ሰማዕትነትን የተቀበለው በሃገረ ፋርስ [በአሁኗ ኢራን አካባቢ] ነው:: ፋርስ ከ1ኛው መቶ ክ/ዘ እስከ ተንባላት [መሐመዳውያን] መነሳት [ ፯ኛው መቶ ክ/ዘ ] ድረስ ባለው ጊዜ ብዙ ሰማዕታት ለክብር በቅተውባታል::

ብዙዎቹ የዚያው [ የፋርስ ] ዜጐች ሲሆኑ ጥቂቶቹ ደግሞ የተሰዉት ከሌላ ሃገር መጥተው ነው:: ፋርሳውያን አብዝተው ፀሐይን ያመልኩ ነበርና ክርስቲያኖቹን የሚያሰቃዩት ይህቺውን ፍጡር እያመለኩ እንዲንበረከኩ ነበር::

ቅዱስ ስምዖንም ከፋርስ ግዛቶች በአንዱ ኤዺስ ቆዾስነትን [እረኝነትን] ተሹሞ ነበርና የመከራው ተሳታፊ ሆኗል:: በጊዜው ክርስትና እንደ ዛሬው "ሠርግና ምላሽ" አልነበረምና ቅዱስ ስምዖን [እረኛው] እና ፻፶ የሚያህሉ ልጆቹ [መንጋው] ስለ ክርስቶስ ፍቅር ብዙ ሆነዋል::

በእምነታቸው ጸንተው በመገኘታቸውም እንዲገደሉ ተወስኖባቸው ፻፶፩ዱም ተሰውተዋል::

አምላከ ሰማዕታት በጽናታቸው አጽንቶ ከበረከታቸው ይክፈለን::

🕊

[ †  ሚያዝያ ፲፱ [ 19 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ ስምዖን ሰማዕት [ አርማንያዊ ]
፪. "፻፶" ቅዱሳን ሰማዕታት [ የስምዖን ማሕበር ]

[ †  ወርሐዊ በዓላት ]

፩. ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት
፪. ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት
፫. አቡነ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ
፬. አቡነ ስነ ኢየሱስ
፭. አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም

" እግዚአብሔር ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ: እስከ አሁንም ስለምታገለግሏቸው ያደረጋችሁትን ሥራ: ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመጸኛ አይደለምና:: በእምነትና በትእግስትም የተስፋውን ቃል የሚወርሱትን እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞች እንዳትሆኑ ተስፋ እስኪሞላ ድረስ እያንዳንዳችሁ ያን ትጋት እስከ መጨረሻ እንድታሳዩ እንመኛለን:: "  [ዕብ.፮፥፲-፲፫]


† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
እንኩዋን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓመታዊ በዓለ ዑደተ ሆሳዕና በሰላም አደረሳችሁ


🕊         በዓለ ሆሳዕና            🕊

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከሆሳዕና ጀምሮ እስከ ዸራቅሊጦስ ድረስ ያሉ ዐበይት በዓላትን ሁለት ጊዜ ታከብራለች:: በዚህም መሠረት :-

፩ኛው = "ጥንተ በዓል" ሲሆን {"ጥንተ በዓል" ማለት በዓሉ : ተአምሩ [የማዳን ሥራው] የተፈፀመበት የመጀመሪያው ቀን ማለት ነው::}

፪ኛው = ደግሞ "የቀመር በዓል" ይሠኛል::
መሠረቱ የቅዱሳን ሐዋርያት ቀኖና እና የአባታችን የድሜጥሮስ መንፈሳዊ ቀመር ነው::

ስለሆነም ዓለም ከተፈጠረ በ ፭ሺህ ፭፻፴፬ [5,534] ዓመት : የዛሬ ፩ ሺህ ፱፻፸፰ [1,978] ዓመት : በዛሬዋ ዕለት [ዕለተ እሑድ] ስም አጠራሩ ከፍ ከፍ ይበልና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፍጹም ትሕትና በአህያዋና በውርንጫዋ ጀርባ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም [ቤተ መቅደስ] ገብቷል::

ታላቅ የምስጋና መስዋዕትም ከመላዕክት : ከሐዋርያት : ከሕጻናት : ከአረጋውያን : ከፀሐይ : ከጨረቃ : ከከዋክብት : ከቢታንያ ድንጋዮች . . . በአጠቃላይ ከፈጠረው ፍጥረት ሁሉ ቀርቦለታል:: ጌትነቱንም በገሃድ ገልጧል::

ከበዓሉ በረከት ይክፈለን:: እኛንም ለጣዕመ ምስጋናው የተዘጋጀን ያድርገን::

" አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ እጅግ ደስ ይበልሽ:: አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ እልል በዪ:: እነሆ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው:: ትሑትም ሆኖ በአህያም: በአህያይቱ ግልገል በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል::" [ዘካ.፱፥፱]

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
ሆሳዕናችን ሆይ
በአህያዋ ጀርባ የተመለከቱህ
አዳኝ መድሐኒት እንደሆንክ ያወቁህ
ክብር በአርያም ብለው ሆሳዕና
ህጻናት አዛውንት በጥዑም በምስጋና፣
ልብስ እና ዘንባባ እያነጠፉልህ
ብሩክ ነህ ዘለዓለም ብለው ተከተሉህ፤
እንዳይዘምሩልህ ቢያደርጉም ከልካዩች
አንተን ለማመስገን ዘለሉ ደንጋዮች።
ግባ ወደ ልቤ ግባ ኢየሩሳሌም
ታስፈልገኛለህ መድኃኒቴ ለእኔም
ሆሳዕና እንዳልል ክብር በአርያም
ስምህን መስክሬ እንዳላገኝ ሰላም
አስሮኛል ኃጥያት በደል ክህደቱ
ተፈትቼ ልምጣ እንደ አህያይቱ
ይሸከምህ ጌታ የልቤ ትከሻ
አንተን ብቻ ያንግስ እስከመጨረሻ
ቆመህ ስታንኳኳ ልክፈተው ደጃፉን
የክብር ንጉስ ሆይ ኑርበት እልፍኙን
ይሁንልህ ዙፋን እረፍበት ግባ
እንዲመችህ ላንጥፍ የእምነት ዘንባባ
ሆሳዕናችን ሆይ ትብዛ አሜናችን
ክብር እና ምስጋና ይድረስህ ጌታችን።

@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
Henok:
🙏🙏🙏🙏🙏ሰኞ..🙏🙏🙏🙏🙏🙏....
   በሆሳህና ማግስት ሰኞ በድጋሜ ከቢታኒያ ወደ እየሩሳሌም ገብቷል።
እሁድ የሆሳህና ዕለት ጊዜዉ መሽቶ ስለነበር በማግስቱ ሰኞ ከቢታኒያ
ወደ እየሩሳሌም ሲገባ ሁለት ነገሮችን አድርጓል ።
እነሱም:-
1.ቅጠል ብቻ ሆና ፍሬ ያላገኘባት ዕፀ በለስ ረግሟታል ።
2. ወደ መቅደስ ገብቶ የሚሸጡትንና የሚለዉጡትን አስወጥቷል ።
ማቴ 21፥19 ማር 11፥12-19 ለቃ 19 ፥ 45-46

በዚህ ዕለት በቤተክርስቲያን የሚሰበከዉ ምስባክ :-
  1.በአንድ ሰዓት መዝ.72 ፥ 18-19
  2 . በሶስት ሰዓት መዝ. 122 ፥ 1-2
  3. በስድስት ሰዓት መዝ. 122 ፥ 4-5
  4 . በዘጠኝ ሰዓት መዝ. 65 ፥ 5-6
  5. በአስራ አንድ ሰዓት መዝ. 13 ፥2-3
ክርስቲያን ሆይ ?
  በቤተክርስቲያናችን ይህ ሰኞ የዚህ ታሪክ መታሰቢያ ነዉ ። ዛሬ ቢሆን
ጌታችን ወደ  እኛ ሕይወት ቢመጣ የሚገኘዉ ምንድን ነዉ ? ፍሬ
ወይስ ቅጠል? የእግዚአብሔር ቃል ግን ለንስሐ ሚገባ ፍሬ አድርጉ
ይለናል  ። (ማቴ 3፥8) ስለዚህ እግዚአብሔር ከእኛ የሚፈልገዉን
የመንፈስ ፍሬ ይዘን  ልንገኝ  ይገባናል ።(ገላ. 5፥ 22) እንዲህ ከሆነ
ይባርከናል እንጅ አይረግመንም ።
     
ክርስትናዊ ሕይወት
  ፈተና ፈርተዉ የሚሸሹበት ሳይሆን በፈተና ዉስጥ አልፈዉ
ለክብር የሚበቁበት ሕይወት ነዉ፤ ዕያ 1፥ 12
   ክርስቲያን ማለት ምንም ተስፋ በሌለበት ተስፋ የሚያደርግ ነዉ፤
ክርስቲያን ማለት ሰዉ በጠፋበት ዘመን ሰዉ ሆኖ  የሚገኝ ነዉ
       ኢሳ 6 ፥8

ፈጣሪ ሆይ የእናታችን  የድንግል ማርያም ልጅ ሆይ ፍሬ የሚገኝብንና
የፍሬ ሰወች አድርገን አሜን አሜን አሜን
👏👏👏👏👏 የሚጸለይ ጸሎት👏👏👏👏
ጻም ከቻልሽ ከምሽቱ 1 ሰዓት ምግብ ሳትበይ መቆየት ካልቻል 12 ካልቻልሽ 9 ይሆናል ካልቻልሽ ማለት የጤና እክል ማለቴ ነው
      መዝሙረ ዳዊት መዝሙር 1እስከ 30 ያለውን ምዕራፍ ይጸለያል
                 ኪሪያላይሶን 44
                      እግዚኦማሀረነ ክርስቶስ 44
                በእንተ ማርያም ማሀረነ ክርስቶስ 44
የህመም ችግር ካለ በመቀነስ መስገድ ትችያለሽ
      የመጽሀፍ ቅዱስ ጥቅስ ከላይ ያሉትን  አንብቢ
     በተቻለሽ  መጠን በቤተክርስቲያን ያለውን ሙሉቀን ለመካፈል ብትችይ ስራ አስፈቅደሽ ካልተቻለ ከላይ የተዘረዘሩትን ማድረግ ነው
          👏👏👏👏 የሀዘን ጊዜ ስለሆነ👏👏
# ከሰዋች ጋር ግንኙነት ባይኖርሽ ሀሳብሽ ጸሎት ላይ ቢሆን
# ደስታን ከሚሰጡ ነገሮች መራቅ
# ውስጥሽ የፈጣሪሽን መከራ ማሰብ
# ከዘፈን ከፊልም ከፊስቡክ ወዘተ መራቅ
# ስለማንም ግለሰብ ማውራት ማማት መራቅ
# ከፍቅረኛ ጋር አለመገናኘት
   #ባለትዳር ከሆንሽ ለይታችሁ መተኛት
# መሬት አንጥፈሽ መተኛት ከሌሊቱ 6 እና 9 እና12 ከእንቅልፍ ተነስተሽ መስገድ የቻልሽውን  ያህል
# ከጻምሽ ባኃላ እስትጠግቢ አለመብላት
# እህቴ ሆይ ፦ብዙ አለማውራት
# በጠዋት ቤተክርስቲያ ሄደሽ ስርአቱን ተካፈለሽ ወደስራሽ መጓዝ እነዚህና የመሳሰሉትን መፈጸም የግድ ነው
    🌕🌕🌕ማሳሰቢ🌖🌖🌖🌖🌖
ከላይ ከተጻፈው የጸሎት መርሀ ግብር ይበልጥ ጊዜ ሰተሽ  በቤተክርስቲያን ያለው የጸሎት ልመና ይበልጣል ሙሉቀን ቤተክርስቲያን ስርዓት አላት የዛ ተካፈይ ብትሆኝ ካልተቻለ ከላይ ያለውን መተግበር
አምላክ ልመናሽን ይስማ ጸጸትሽን ይቀበል

#ሆሳዕና
በዕለተ ሆሳዕና እስራኤላውያን ለምን የዘንባባ ዝንጣፊ፤ የቴምር ዛፍ ዝንጣፊ እና የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው  ዘመሩ? (ማቴ. 21÷1-17፣ ማር. 11÷ 1-10፣ ሉቃ. 19÷29-38፣ ዮሐ. 12÷12-15)

#የዘንባባ_ዝንጣፊ፡-
☞ይስሃቅ በተወለደ ጊዜ አብርሃም ደስ ብሎት ዘንባባ ይዞ እግዚአብሄርን አመስግኖበታል የደስታ መግለጫ በመሆኑ አነተ ደሰታ የምታስገኝ ሃዘናችንንም የምታርቅ አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡
☞ ዘንባባ ደርቆ እንደገና ህይወት ይዘራል የደረቀ ሕይወታችንን የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ የሰላም ምልክት ነው የሰላም አምልክ ነህ ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ እሾሃማ ነው አንተ ህያው አሸናፊ አምላክ ነህ ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል እንጅ ጌታም አንተ ባህርይህ የማይመረመር ነው ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ የነፃነት ምልክት ነው ከባርነት ነፃ የምታወጣን አንተነህ ሲሉ ነው አኛም ይህን በማሰብ ዘንባባ ይዘን ሆሳእና በአርያም እያልን እለቱን እናስባለን፡፡

#የቴምር_ዛፍ_ዝንጣፊ፡-
☞ የቴምር ዛፍ ፍሬ ጣፋጭ ነው፦ በሃጥያት የመረረውን ሂወታችን የምታጣፍጥልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ የቴምር ፍሬ የሚገኘው ከዛፉ ከፍታ ላይ ነው አንተ አምላካችን ልዑለ ባህሪ ነህ ከፍ ከፍ ያልክ አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ የቴምር ዛፍ ፍሬ በውስጡ ያለው ፍሬ አንድ ነው አንድ አካል አንድ ባህሪ ነህ ሲሉ ነው።
☞ የቴምር ፍሬ በእሾህ የተከበበ ነው ይህም የአንት ባህሪ የማይመረመር በእሳት የተከበበ ነው ሲሉ ነው።

#የወይራ_ዛፍ_ዝንጣፊ፡-
☞ የወይራ ቅጠል የሰላም ማብሰሪያ ነው ሰላማችንን የምታበስርልን የምታስገኝልን አንተ ነህ ሲሉ ነው፡፡
☞ የወይራ ቅጠል ከእንጨት ሁሉ ጽኑ ነው አንተም ጽኑ ሃያል አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ ወይራ ለመብራት ያገለግላል ፍሬው ዘይት ያወጣል ከወይራ የሚገኝ ዘይት ጨለማን አሸንፎ ብርሃን እንደሚሰጥ ሁሉ አንተም ጨለማ ህይወታችንን የምታስወግድልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ በኦሪት ግዜ የወይራ ዘይት ለመስዋአትነት ይቀርብ ነበር አንተም እንደ ዘይቱ ለመተላለፋችን መስዋዕት ሆነህ የምትቀርብ አምላክ ነህ ሲሉ ነው። በመስቀል ላይ መስዋዕት ሆኗልና።

በዓሉን በዓለ ክብር በዓለ ፍስሐ ያድርግልን፡፡
🕊

[ † እንኳን ለሐዋርያው ቅዱስ ብሩታዎስ ዓመታዊ
የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]


† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †

🕊   † ቅዱስ ብሩታዎስ  †   🕊

† ሐዋርያው ቅዱስ ብሩታዎስ በሐዲስ ኪዳን የመጀመሪያው የውዳሴ ማርያም ደራሲ ነው:: ይህስ እንደምን ነው ቢሉ :-ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፈቃዱ ሙቶ ከተነሳ ከ፰ ዓመታት በኋላ ቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያ ያምናል:: ባመነ በ፮ ዓመቱ [ማለትም ከክርስቶስ ዕርገት ፲፬ ዓመታት በኋላ] እየሰበከ ግሪክ አቴና /ATHENS/ ደርሶ ብዙ ፈላስፎችን ወደ ክርስትና ሲያመጣ አንዱ ይህ ቅዱስ ብሩታዎስ ነበር::

ቅዱስ ብሩታዎስ በክርስቶስ አምኖ: ተጠምቆ: ሐዋርያትን ተከትሏቸው: እነሱም ቅስና ሹመውታል:: ጵጵስና እንሹምህ ቢሉት በፊታቸው ተንበርክኮ አልቅሷል:: አይገባኝም ማለቱ ነበር::

ታዲያ ቅዱስ ብሩታዎስ ሐዋርያት ስለ ድንግል እመቤታችን ሲጨዋወቱ እየሰማ "መቼ አይቻት" እያለ በፍቅሯ ይቃጠል ነበር:: አንዴ ግን ወሰነ:: "እመቤቴን ሳላያት እንቅልፍ አላይም" ብሎ በሽማግሌ እግሮቹ ከግሪክ ወደ ኢየሩሳሌም ተጓዘ::

የሚገርመው እርሱ እሥራኤል [ጽርሐ ጽዮን] የደረሰው በ፵፱ ዓ/ም ጥር ፳፩ ቀን እመቤታችን ልታርፍ ሰዓታት ሲቀራት ነበር:: ቅዱሱ ሽማግሌ እመቤታችንን በአካለ ሥጋ ስላያት በፊቷ እንደ እንቦሳ ዘለለ:: እየሰገደም አመሰገናት:: እመ ብርሃንም በንጹሐት እጆቿ ባረከችውና ዐረፈች::

ይሕን ጊዜ ምሥጢር ተገልጦለት ዜማና ቅኔ ያለውን የመጀመሪያውን ውዳሴ ማርያም ዕለቱኑ ደርሶ ለሐዋርያት ሰጣቸው:: እነርሱም ከምስጋናው ጣዕም የተነሳ ተደነቁ:: ከሐዘናቸውም ተጽናኑ::

ይሕ ድርሰት በዘመነ ሰማዕታት በመጥፋቱ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ አምልቶና አጉልቶ ደርሶታል::

ቅዱስ ብሩታዎስ ግን ብዙ ሃገራትን በሐዋርያነት አዳርሶ በመልካም ሽምግልና አርፏል::

† ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ብሩታዎስ ላይ ያሳደረውን የድንግል እናቱን ፍቅር በእኛም ላይ ያሳድርብን::

🕊

[ † ሚያዝያ ፳፩ [ 21 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ ብሩታዎስ ሐዋርያዊ
፪. አባ ዕንባቆም ጻድቅ ሰባኬ ሃይማኖት ዘደብረ ሊባኖስ [በትውልድ የመናዊ በጸጋና አገልግሎት ግን ኢትዮጵያዊ አባት ናቸው:: ደራሲ : ሰማዕት : ባሕታዊና ሊቀ ምኔትም ነበሩ::]
፫. ቅዱስ አካክሪስ
፬. ቅዱስ ይወራስ

[ †  ወርኀዊ በዓላት ]

፩፡ እግዝእትነ ማርያም
፪፡ አበው ጎርጎርዮሳት
፫፡ አባ ምዕመነ ድንግል
፬፡ አባ ዓምደ ሥላሴ
፭፡ አባ አሮን ሶሪያዊ
፮፡ አባ መርትያኖስ
፯፡ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል

" ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን መግለጥ ለእያንዳንዱ ለጥቅም ይሠጠዋል:: ለአንዱ ጥበብን መናገር በመንፈስ ይሰጠዋልና:: ለአንዱም በዚያው መንፈስ እውቀትን መናገር ይሰጠዋል . . . ለአንዱም በልሳኖች የተነገረውን መተርጐም ይሰጠዋል:: ይህን ሁሉ ግን ያ አንዱ መንፈስ እንደሚፈቅድለት እያንዳንዱ ለብቻው እያካፈለ ያደርጋል:: " † [፩ቆሮ. ፲፪፥፯-፲፩]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
†                †                †

[   † ሰሙነ ሕማማት  †   ]

                      †                       

‹ ሰሙን › – " ሰመነ ስምንት [ ሳምንት ] አደረገ " ማለት ነው፡፡ ይኸውም ከዕለተ ሆሣዕና ሠርክ እስከ ትንሣኤ ሌሊት ያለውን ጊዜ ወይም ቀናት የሚያመለክት ነው፡፡ ‹ ሕማም [ ሕማማት ] › – ‹ ሐመ ታመመ › ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲኾን ይህም የሰውን ዘር ዂሉ ከዲያብሎስ ባርነት ነጻ ለማውጣት ጌታችን አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፈቃዱ የተቀበላቸውን ጸዋትወ መከራዎች የሚያሳስብ ነው፡፡ ዕለታቱ የዓመተ ኵነኔ ወይም የዓመተ ፍዳ ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ክርስቲያኖች የክርስቶስን ውለታ እያሰቡ እጅግ የሚያዝኑበት ፣ የሚያለቅሱበት ፣ የሚሰግዱበት ቤት ንብረታቸውን ትተው ከሌላው ቀናትና ጊዜያት በተለየ መልኩ ቤተ ክርስቲያናቸውን የሚማጸኑበት ፤ ጧት ማታ ደጅ የሚጠኑበት ፤ ኀጢአታቸውን በቤተ ክርስቲያን አደባባይ ለካህኑ የሚናዘዙበት በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ የሚገኝ ሳምንት ነው፡፡

                      †                       

በዚህ ሳምንት ብዙ አዝማደ መባልዕት አይበሉም ፤ ይልቁን በመራብ በመጠማት በመውጣት በመውረድ በመስገድ በመጸለይ በመጾም በየሰዓቱ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ጸዋትወ መከራዎች በማሰብ አብዝቶ ይሰገዳል፡፡ መከራውን ፣ ሕማሙን ፣ ድካሙን የሚያስታውሱ ከቅዱሳት መጻሕፍት ኢሳይያስ ፣ ኤርምያስ መዝሙረ ዳዊት ፣ ግብረ ሕማማት ወዘተ በየሰዓቱ ይነበባል፡፡ መስቀል መሳለም የለም፡፡ ካህናትም " እግዚአብሔር ይፍታህ " አይሉም፡፡ ሥርዓተ ፍትሐት አይፈጸምም፡፡ ይኸውም ይህ ሳምንት ከሞት ወደ ሕይወት የተሸጋገርንበት ከጨለማ ወደ ብርሃን የተጓዝንበት የመሸጋገሪያ ወቅት ምሳሌ በመኾኑ ነው፡፡ በዕለተ ምጽአት መላእክት የመለከት ድምፅ በማሰማት የዳግም ምጽአትን ዕለት ለማሳሰብ ምእመናን ጥሪውን ሰምተው ለዚህም አስቀድመው ተዘጋጅተው የበዓሉ ታዳሚዎች መኾናቸውን በማጠየቅ በዚህ ሳምንት ዲያቆኑ ቃጭል እየመታ በየሰዓቱ ምእመናኑን ያሳስባል፡፡

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
"#ታመመ! ሞትን ከተቀበለበት ከሥጋ ጋር ተዋሕዶ በመስቀል ላይ በፈቃዱ ለሥጋውያን ሞተ፤

ባሕርየ መለኮት ሥጋን ተዋሕዶ በማኅፀን ካደረ ጀምሮ ሥጋ ገንዘቡ እንደመኾኑ በሥጋ ይኽንን ሥርዓት ፈጸመ፡፡

ለማይመረመር ለመለኮቱ ባሕርይ እንደሚገባ ደግሞ እርሱ ኅብስት አበርክቶ ኹሉን ያጠግባል፤ አይራብም፤ አይጠማም፤ አይደክምም፤ አያንቀላፋም፤ አይታመምም፤ አይሞትም! ሕይወትን ለኹሉ ይሰጣል፡፡

ዳግመኛ በዛ በሲዖል ተገዝተው ያሉ ነፍሳትን ያድን ዘንድ በአካለ ነፍስ ወደ ሲዖል ወረደ 🙏 በመለኮቱም ሲዖልን በዘበዘ"

ቅዱስ ቄርሎስ ዓምደ ሃይማኖት (ዘእስክንድርያ)

አቤቱ አምላካችን እየሱስ ክርስቶስ ሆይ ማረን ይቅር በለን🙏🙏🙏

ለመቀላቀል 👇👇👇👇
@Enatachn_mareyam  
@Enatachn_mareyam
                       †                       

  [   🕊  ሕ ማ ማ ት   🕊  ]  

🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒               

[  ሕማማት + ለምን + እንዴት  ]

🕊             

[  የሕማማት ሳምንት ሥርዓቶች ! ]

- የሕማማት ትርጉምና ምሥጢር
- ጸሎትና የጸሎት መጻሕፍት
- የጾም ሰዓትና ሥግደት
- ሌሎችም ሥርዓቶች

    💖   ድንቅ ትምህርት  💖

[ ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ]


         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
                       👇
2024/09/29 23:24:48
Back to Top
HTML Embed Code: