Telegram Web Link
#ሆሄ_ተስፋ

አዲስ አበባ - መገናኛ በጣዕም የባህል ምግብ አዳራሽ ተዘጋጅቶ የነበረው የሆሄ ተስፋ የኪነጥበብ ቡድን ልዩ ኪነጥበባዊ ዝግጅት በሙዚቃ እና በስነፅሁፍ ጥበባዊ ዝግጅት ታጅቦ በድምቀት ተጠናቋል።

በዝግጅቱ ላይ የተለዩ እንግዶች የተገኙ ሲሆን
👉የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል ተጠሪዎች
👉የመቅረዝ ስነኪን ተጠሪዎች
እንዲሁም በዝግጅቱ ላይ የምንወደዳቸው እና የምናደንቃቸው ገጣሚያን

ገጣሚ ጥላሁን ስማው (የማስተዋል እያዩ "ከፋኝ" ሙዚቃ ግጥም ደራሲ)

ገጣሚት መንበረማርያም ኃይሉ(የቃል ሰሌዳ እና የጊዜ ሰሌዳ የግጥም መድብሎች አዘጋጅ)

የወደ ግጥም ኪነት ተጠሪዎች

እንዲሁም ሌሎች በዝግጅቱ ላይ ተገኝተዋል።

የባህላዊ ምግብ አዳራሽ ባለቤት የሆኑት አቶ ዮሃንስም እንደገለፁት ይህን ዝግጅት በቋሚነት በድርጅታችን በኩል እንዲካሄድ ስንፈቅድ ከልዩ ደስታ ጋር ሲሆን በወር አንድ ጊዜ ለሚደረገው ቋሚ የሆሄ ተስፋ መድረክ ሁሌም በራችን ክፍት ነው ሲሉ ገልፀዋል።

መገኛውን ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ያደረገው ክበብ በአዲስ አበባ መመስረቱ የተመረቁትን፣በዩኒቨርሲቲ ካሉት ጋር እንዲያገናኝ እንዲሁም አቅምና ክህሎትን በማጎልበት ትልቁን ህልም የሚያሳካ መንገድ እንደሆነ ተገልፁአል።

@DBU11
@DBU_entertain
የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ በ Doctor of Medicine መምህራን አወዳድሮ ለመቅጠር ባለፈው ወር ባወጣው የቅጥር ማስታወቂያ መሠረት ዝቅተኛ ተፈላጊ ችሎታውን አሟልታችሁ የተመዘገባችሁ ብቻ ግንቦት 22/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት በአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ግቢ ለፈተና መጠራችሁን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

ተፈታኞች ለፈተና ስትሔዱ መታወቂያ መያዝ እና በሰዓቱ መገኘት ይኖርባችኋል፡፡ ማንኛውም ተፈታኝ የሞባይል ስልክ ይዞ ወደ ፈተና መግባት አይችልም፡፡

@dbu11
ለተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ

የምርቃት ጊዜ እንደመቃረቡ እና ጊዜውም አጭር እንደመሆኑ መጠን ለባይንደር እና ህትመት ስራዎች ብዛቱ መታወቅ ስላለበት እንዲሁም የማሰሪያ ገንዘቡ ገቢ መሆን ስላለበት የባይንደር እና የህትመት ፎርም ከዛሬ ሃሙስ ግንቦት 22/2016 ጀምሮ በክፍል ተወካዮች በኩል ለእያንዳንዱ ክፍል ስለሚሰራጭ እስከ ቅዳሜ ድረስ ክፍያውን እንድታጠናቅቁ ስንል እናሳስባለን።

የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ የተመራቂ ተማሪዎች(GC) ኮሚቴ
@DBU11
@DBU_ENTERTAIN
ለሴት ተማሪዎች

"ከዚህ ቀደም ባዘጋጀነው የውይይት መድረክ ብዙ ሴት ተማሪዎች ደስተኛ እንደነበሩና በድጋሜ እንዲዘጋጅ በቀረበ ጥያቄ መሠረት አርብ በ23-09-2016 ሴቶቻችንን ያቀራርባል ያልነውን ውይይት አዘገጅተናል"
ዝግጅቱንም ብሎክ 07 ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ መታችሁ ተሳተፉ ሲል የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ዳይሮክትሬት ጥሪ አቅርቧል።

@dbu11
@dbu_entertainment
🌟 Calling for Engineering Students! 

(CoTM , Mechanical ,Civil,Software and Electrical engineering students and staff)🌟

📅 Save the date: June 4th, 2:30 AM!

🏗️ Join us at Debre Berhan University  "BIM ( Building information modeling ) Workshop: The Future of Digital Construction" 🚀

👷‍♀️ Unlock New Career Horizons in Engineering! 🌐

👨‍🔧 Gain valuable insights from industry leaders and experts 💡


👉 Join our Telegram group for updates and discussions: https://www.tg-me.com/+IxJzPHyA8khiODE0
# አትሌቲክስ ክለብ
=============
የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አትሌቲክስ ክለብ ባሳለፍነው ሳምንት በተለያዩ የአለም አትሌቲክስ ውድድሮች ላይ በመሳተፍ አስደሳች ውጤት አስመዝግቧል፡፡

በዚህም መሰረት፡-
1. በቻይና ኮርላንድ ከተማ በ21 ኪ.ሜ ሩጫ ውድድር የተሳተፈችው አትሌት ነጻነት ታፈረ የቦታውን ሪከርድ ጭምር በማሻሻል ያሸነፈች ሲሆን የዋንጫ፣የሜዳለያና የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላታል፡፡

2. በዛው በቻይና በተከታታይ በሶስት ከተሞች ማለትም በዞንግሽን፣በፋዞን እና በወይዞን ከተሞች በየሳምንቱ በተደረጉ የ21 ከ.ሜ /ግማሽ ማራቶን/ ሩጫ ውድድር ላይ የተሳተፈችው አትሌት እንይሽ መንጌ የሶስት ዋንጫ፣የሶስት የወርቅ ሜዳለያና የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላታል፡፡

3. በጃፓን ኮቤ ከተማ በተደረገ የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር ላይ ክለባችን ያፈራው አትሌት ይታያል ስለሽ በ1500 ሜትር ኢትዮጵያን ወክሎ በአለም አደባባይ የብር ሜዳለያ በማስመዝገብ አመርቂ ውጤት አስመዝግቧል፡፡አትሌቱ ነሐሴ 2016 ዓ.ም ለሚካሄደው የፓሪስ ኦሎምፒክ በ1500ሜ ኢትዮጵያን ወክሎ እንደሚሳተፍ ተረጋግጧል፡፡

ለአትሌቱ መልካም እድል እንመኛለን፡፡

@DBU11
@DBU_ENTERTAIN
ለተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ

የባይንደር ስራና ህትመት ውል ሰኞ ስለሚጠናቀቅ በክፍል ተወካዮች በኩል የማሰሪያ ብር እንድትልኩ እና የመጨረሻ ቀን እሁድ ስለሆነ የአንድ ባይንደር ዋጋ 250 ብር እንድታስገቡ እናሳስባለን።

ጂሲ ኮሚቴ

@DBU11
@DBU_ENTERTAIN
#Notice

ሆሄ ተስፋ ተወዳጅ የኪነጥበብ ስራዎቹን ለማቅረብ ዝግጅቱን አጠናቆ ጥሪ የቀረበ ቢሆንም በአንዳንድ ምክንያቶች ዝግጅቱን ማቅረብ አልቻለም።
ለዚህም ሆሄ ተስፋ ይቅርታ ጠይቋል። ዝግጅቱን የሚያቀርብበትን ቀንም በቅርቡ የሚያሳውቅ ይሆናል።

@dbu11
@dbu_entertainment
ተመራቂ ተማሪዎች

የባይንደር 250 ብር ዛሬ የመጨረሻ ቀን በክፍል ተወካዮቻችሁ በኩል አድርሱን።

GC committee

@DBU11
@DBU111
መጽሄት ለምታሰሩ

የመጽሄት ዲዛይን ይዘት ምን ምን ያካትታል

በመጀመሪያዎቹ ገጾች ላይ
የተማሪው ሙሉ ፎቶ እና መልዕክት በሙሉ ገጽ
የዲፓርትምርንቱ ተማሪዎች ሙሉ ገጽ ላይ
የአሶሴሽን ማስታወሻ ፎቶ በሙሉ ገጽ ላይ

በጠቅላላ ገጾች ላይ
የተማሪ ሙሉ ስም
የተማሪ ሁለት ፎቶ በምርቃት ጋዋን እና በልዩ ልብስ
የተማሪ አጭር መልዕክት
ስልክ ቁጥር

እንዲሁም አጭር የአስተዳደር አካላት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክቶችና ፎቶ ይሰፍርበታል።

ፎቶ ማስነሻን ጨምሮ
የአንድ መጽሄት ዋጋ 750 ብር

Nati B
@DBU11
@DBU_ENTERTAIN
ለ ተመራቂ ተማሪዎች

የባይንደር 250 ብር ዛሬ የመጨረሻ ቀን በክፍል ተወካዮቻችሁ በኩል አድርሱን።

GC committee

@DBU11
@DBU111
ይህ የዛሬ ገፃችን ነው።

ዛሬን እንደምናለፍ ነገ እንደዛሬ አይደለንም

ዛሬን እንደኖርን ነገም በአንድ ቦታ አንገኝም

መልካችን፣አብሮነታችን፣መድረሻችን፣ ዳግም መገናኛችንም እንደየራሳችን ይለያያል።

ይህ ጥሩ ትዝታ ማስፈሪያ ነው።
ተበታትነን እንኳን እንድንገናኝ በአዲሱ የመፅሄት ገፅ ላይ ላይ ስልክ ቁጥር እንዲካተት አድርገናል።

የአንድ መፅሔት ዋጋ ፎቶን ጨምሮ 750 ብር
ፎቶ ፋይል ለሚያመጣ 700 ብር


Nati.B
@dbu11
@dbu_entertain
2024/06/28 10:53:00
Back to Top
HTML Embed Code: