Telegram Web Link
ክሪፕቶ ከረንሲ ምንድነው

ዲጂታል ወይም ቨርቹዋል የሚባል ደህንነቱ የተጠበቀ ብሎክ ቼይን (Block chain) የባንክ ሲስተም ነው።

ዲ-ሴንትራላይዝድ በሆነ ኮምፒውተር ሲስተም የታገዘ ማለትም ይህን እንቅስቃሴ የሚቆጣጠረው ራሱ ሲስተሙ እንጂ ማንነቱ የተወሰነለት አካል አይደለም።

ይህም ከብሎክቼይን ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ለደህንነት ስጋት እንደማይፈጥር የዘርፉ ምሁራን ይገልፃሉ።

This decentralized structure allows cryptocurrencies to exist outside the control of governments and central authorities

የዚህም ግብይት  ሂደት online ብቻ የሚደረግ ይሆናል። እሱም እስካሁን ከኖርንበት የገንዘብ ዝውውር ጋር የራሱን ምንዛሬ በቀንና በሰዓት ያሳውቃል። በዚህም ሰዎች የራሳቸውን ኮይን ይሸጣሉ። ይገዛሉ።

ይህን ሲስተም በሙሉ እና በከፊል ህጋዊ አድርገው የተቀበሉ ሃገራት ብዙ ሲሆኑ እንደምሳሌም
- El Salvador
- European Union
- United States
- Canada
- Japan
- South Africa ጥቂቶቹ ናቸው።

በአንፃሩም በሃገራቸው ላይ በከፊልም ሙሉ በሙሉ እገዳ ከታሉ ሃገራት መካከል ጥቂቶቹ
Algeria
- Egypt
- Morocco
- Nigeria
- Bolivia
- Afghanistan
- Bangladesh
ይገኙበታል።

በሃገራችን ዲጂታል ከረንሲ መፈቀዱ ሙሉ በሙሉ ያልተረጋገጠ ሲሆን ነገር ግን የዚህ አካል የሆነው የካፒታል ማርኬት ስርዓት ህጋዊ ሆኖ እንዲቀጥል በቅርቡ ይፋ ተደርጓል።(በባንክ ስርዓት ውስጥ ባይገባም እግድ አልተጣለበትም።

ዝርዝር ነገር ከፈለጋችሁ በኮሜንት ስር አሳውቁኝ።

ይቀጥላል...

@DBU11
@DBU_ENTERTAIN
የቀጣይ አመት በጀት 1.03 ቢሊዮን ብር ለ ደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ ተመደበ።

ከ 1 ቢሊዮን ብር በላይ ከተመደበላቸው ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ  13 ደረጃ ይገኛል ።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 1.9 ቢሊዮን ብር በጀት የመጀመሪያው ደረጃ ላይ ይገኛል ። በሁለተኛ ደረጃ ባህርዳር :ጎንደር :ጂማ :ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በቅደም ተከተል ተቀምጠዋል።

ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ በ1.03ቢሊዮን ብር በጀት 13ተኛ ደረጃ ይገኛል ።

የተመደበው በጀት በዩኒቨርስቲዎች እቅድ መሠረት ነው ።

@DBU11
@DBU11
ማስታወቂያ

በ ሰላም ሚኒስትር እና በ ትምህርት ሚኒስተር  ትብብር  የ በጎ አድራጎት ስልጠና  ስትከታተሉ ቆይታችሁ ዛሬ ስልጠናውን የ ጨረሰችሁ ተማሪዎች ከላይ በምስሉ በተቀመጠው የስም ዝርዝር መሰረት  የመረጃ ጉድለት ያለባችሁ ነገ(አርብ) ጧት ከ 1:00_2:00 ድረስ ብቻ በማሰልጠኛ  ቦታችሁ በአካል መታችሁ እንድታስተካክሉ እናሳስባለን።

አስተባባሪዎች


@DBU11
በሀኪም ግዛው ሆስፒታል የተመላላሽ ህክምና ፋርማሲ በአዲስ መልኩ አገልግሎት መስጠት ጀመረ
----------------------------------------------------------------------
የደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ሀኪም ግዛው ሆስፒታል የተመላላሽ ህክምና ፋርማሲ በአዲስ መልኩ አገልግሎቱን በስፋትና በጥራት መስጠት ጀመረ፡፡

ማዕከሉ የተገልጋዮቹን ምቾት በጠበቀ መልኩ አገልግሎቱን መስጠት የሚያስችል ሰፊ ማረፊያ ቦታ ያለው፣ በልዩ ሁኔታ የምክር አገልግሎት አግኝተው የሚስተናገዱ ባለጉዳዮች የሚስተናገዱበት ክፍል ያለው፣ አላስፈላጊ እንግልቶችን የሚያስቀርና ሁሉንም አገልግሎቶች በአንድ ቦታ እንዲያገኙ ታስቦ በAPTS (Auditable Pharmacy Transactions and Services) ስታንዳርድ የተደራጀ ነው፡፡
በዘርፉ በቂ ባለሙያዎች ተመድበው ፈጣንና ግልፅነት ያለው አገልግሎት የሚሰጥበት፣ ተጠያቂነትን ያሰፈነ የአሰራር ስርዓት ተዘርግቷል፡፡ በተጨማሪም ከወረቀት ነፃ የዲጂታል አሰራርን በመዘረጋት የተቀላጠፈና የተገልጋዮቹን እንግልት በሚቀንስ መልኩ አገልግሎት እየሰጠ ነው፡፡

በሆስፒታሉ በተመላላሽና ተኝቶ ህክምና እንዲሁም በድንገተኛ ህክምና የሚታከሙ ታካሚዎች በሀኪሞቻቸው ከሚታዘዙላቸው መድሃኒቶች ከ95 በመቶ በላይ የሚሆነውን መድሃኒት በሆስፒታሉ ውስጥ ባሉ ፋርማሲዎች እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡ ለዚህም የደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ እና ሀኪም ግዛው ሆስፒታል አመራሮች በሆስፒታሉ ውስጥ የመድሃኒትና መሰል የግብዓት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛሉ፡፡

በቀጣይም የከተማውና አካባቢውን ማህበረሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ መድሃኒቶችን የሚያገኝበት የማህበረሰብ አገልግሎት መስጫ ፋርማሲ ለማደራጀት የህንፃ ግንባታው ተጠናቶ አገልግሎቱን የሚሰጡ ባለሙያዎችን ማሟላት፣ የመድሃኒት ግዢና አቅርቦት ቅድመ ዝግጅት ስራዎች በስፋት እየተከናወኑ ይገኛሉ

@DBU11
የሰው ልጅ ትዕዛዝ የተማረበት
ፈጣሪ በፍጡሮቹ እንደማይጨክን ያሳየበት
ታላቅ በዓል !
ለእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ  እንኳን ለኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

@DBU11
@DBU_ENTERTAINMENT
የፕሬዘደንሻል ሜንቶርሺፕ የምረቃ ስነ-ስርአት በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አዳራሽ ተካሂዷል።

ሰኔ 8-2016 ዓ.ም የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት የፕሬዘደንሻል ሜንቶርሺፕ የምረቃ ስነ-ስርአት በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አዳራሽ ተካሂዷል።

የፕሬዚደንሻል ሜንቶርሺፕ ፕሮግራም ሴቶች በራስ መተማመናቸውን የሚያሳድግና አቅማቸውን የሚያጎለብት መሆኑን የኢፌደሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገልፀዋል።

በመርሀ ግብሩ ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ኮራ ጡሸኔ፣ የአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ደረጄ እንግዳ ፣ እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።

በፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ሀሳብ አመንጪነት በቢል ኤንድ ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ድጋፍ የተዘጋጀው ይህ ስልጠና እስካሁን ለ1ሺህ 500 ሴት ተማሪዎች በአምስት የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እንዲማሩ መደረጉ ተመላክቷል።

የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ፣ ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ፣ የሀሮማያ ዩኒቨርሲቲና ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የመርሀ ግብሩ ተጠቃሚ እንደነበሩ ተገልጿል።

የፕሮግራሙ አላማ ሴት ተማሪዎች ትምህርት ጨርሰው ወደ ስራ ከመሰማራታቸው በፊት ለስራው አለም ክህሎት እንዲጨብጡ እንዲሁም ባሉበት መስክ ላይ ተመራጭ እንዲሆኑ ማስቻል መሆኑ ተገልጿል።

ተመራቂዎቹ በቆይታቸው 40 ችግር ፈቺ ፕሮጀክቶችን ቀርጸው ተግባራዊ እንዲሆኑ ማድረጋቸው ተገልጿል።

ፕሮግራሙ የዳበረ የህይወት ልምድ ያላቸው ሴቶች ለተማሪዎቸ ልምዳቸውን በማካፈል አቅማቸውን የሚያሳድጉበት መሆኑ ተመላክቷል።

በግቢያችን ደብረብርሃንም ከመቶ በላይ ሴት ተማሪዎች የመርሃ ግብሩ ተጠቃሚ ነበሩ።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት

@DBU_ENTERTAINMENT
@DBU11
DBU Daily News
ክሪፕቶ ከረንሲ ምንድነው ዲጂታል ወይም ቨርቹዋል የሚባል ደህንነቱ የተጠበቀ ብሎክ ቼይን (Block chain) የባንክ ሲስተም ነው። ዲ-ሴንትራላይዝድ በሆነ ኮምፒውተር ሲስተም የታገዘ ማለትም ይህን እንቅስቃሴ የሚቆጣጠረው ራሱ ሲስተሙ እንጂ ማንነቱ የተወሰነለት አካል አይደለም። ይህም ከብሎክቼይን ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ለደህንነት ስጋት እንደማይፈጥር የዘርፉ ምሁራን ይገልፃሉ። This decentralized…
#የቀጠለ

ወቅታዉ ጉዳይ ስላልነው የቶን ምንዛሬ ወይም Notcoin

ከወር በፊት አለቀ ስለተባለው በቴሌግራም ታፕ በማድረግ እና የተለያዩ እለታዊ ክንውኖችን በመፈፀም የተሰበሰበ አንድ ከረንሲ ኖት ኮይን ይባላል።

ይህንንም ተከትሎ ቴሌግራም የራሱን ሲስተም ወደ ቢዝነስ ሚዲያነት አሳድጎታል።

የቴሌግራም የግብይት ቢዝነስም The Open Network System ሲል የሰየመውን የTON Exchange  ይፋ አድርጓል።

ይህም በየዕለቱ እና በየሰአቱ የራሱ የሆነ የገንዘብ ምንዛሬ መጠንን ይይዛል።


በዚህን ሰዓትም ያንን የሚመስሉ ቦቶች እየተስፋፉ ይገኛሉ።

ታዲያ
ከዚህ በፊት ኖትኮይን ሰርታችሁ ወይም ወደቶን ቀይራችሁ ወደ ገንዘብ መቀየር የምትፈልጉ

በቴሌግራም አድራሻ @Cryptoguys22 ማናገር የምትችሉ ሲሆን

እንዴት መቀየር እንደምትችሉ የማታውቁም +251935441788 መረጃ ማግኘት ወይም ፍቃደኛ ሆኖ ከተገኘ በአካል መገናኘት ትችላላችሁ።

@DBU11
@DBU_ENTERTAIN
የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ስልጠና የወሰዳችሁ ተማሪዎች ዛሬ 7:30 በ PR አዳራሽ እንድትገኙ ስንል እናሳስባለን።

የተማሪዎች ህብረት

@dbu11
@dbu_entertain
EXIT EXAM Schedule FINAL 12.xls
280.5 KB
#መውጫ ፈተና (Exit Exam)


የፈተናው የዲፓርትመንት ድልድል እና የመፈተኛ ጊዜ ከላይ በፋይሉ ቀርቧል

@DBU11
@DBU_ENTERTAIN
DEBREBREHAN UNIVERSITY ENGINEERING COLLAGE TENTATIVE EXIT EXAM SCHEDULE

@DBU11
@DBU_ENTERTAIN
EXIT EXAM Schedule - Revised.xls
196.5 KB
#RevisedExitExamSchedule

ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ከአርብ ሰኔ 14/2016 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ ይታወቃል፡፡

የመውጫ ፈተና የተሻሻለ መርሐግብር ከላይ ተያይዟል።

@dbu11
የድረሱልኝ ጥሪ

ከዚህ በላይ በተያያዘው ደብዳቤ ላይ ስሙ የተለጠፈው ተማሪ የኛን እርዳታ ይፈልጋልና እባካችሁ እንድረስለት::

@DBU11
መልካም ዕድል

ከዛሬ ሰኔ 14 ጀምሮ እስከ ሰኔ 19 ድረስ ለ5 ቀናት የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና ለምትወስዱ የዩኒቨርሲቲያችን ተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ መልካም እድልን እንመኝላችኋለን።

DBU DAILY NEWS

@DBU11
@DBU_ENTERTAIN
ለማስታወስ ያህል

Pdf መፅሔት ማሰራት የምትፈልጉ ያለው ጊዜ አጭር ስለሆነ በ @Dbuprint ላይ የሚከተሉትን ማስረጃዎች አሟልታችሁ መላክ ይጠበቅባችኋል።

ሙሉ ስም
ስልክ ቁጥር
ላስትዎርድ
እና በመፅሔቱ የሚካተት 2ፎቶ
1 በጋዋን የተነሳ
2 በልዩ ልብስ(ሱፍ፣ጥበብ)

ያለው ጊዜ አጭር በመሆኑ እስከ ቀን 23 እሁድ ድረስ ብቻ ማስገባት ይጠበቅባችኋል።

በጋዋን ፎቶመነሳት የምትፈልጉ
ፎቶ ቤኪ
ከተማ ከሚኪ ካፌ ፊት ለፊት።
ፎቶቤቱን በተመለከተ 0926716804 መደወል ይችላሉ።


የአንድ ዲጂታል መፅሔት ዋጋ 150
በመፅሔት ውስጥ የሚካተተው ክፍያውን የከፈለ ብቻ ነው


ለአጠቃላይ መረጃ
0930324919
0940219376

@DBU11
ሁሌም ወደ ከፍታ

ሆሄ ተስፋ አዲስ አበባ 5ኛውን የኪነጥበብ ዝግጅት በዋች ህንፃ(መገናኛ) በጣዕም የምግብ አዳራሽ  በትላንትናው ዕለት እሁድ ሰኔ 16 በልዩ ድምቀት አሳልፎ ውሏል።

በዝግጅቱ ላይ በቅርቡ በሞት የተለየን የሎሬት ዶ/ር ተወልደብርሃን ገ/እግዚአብሄር ልጅ ደራሲ ሮማን ተወልደ፣
ዮሃንስ ሃ/ማርያም (ፍቅር ሰው ማህሌት፣ሰው ቀለም አምላክ እና ሌሎች የግጥምና የአጭር ልብ ወለድ ደራሲ)

መንበረ ማርያም ኃይሉ (የቃል ሰሌዳ እና የጊዜ ሰሌዳ የግጥም መድብሎች አዘጋጅ)

እንዲሁም
የተለያዩ ጋዜጠኞች፣የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች፣የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል፣መቅረዝ ኪነት፣ወደግጥም የኪነጥበብ መድረክ ሃላፊዎችና አባላት ተገኝተዋል።

ፕሮግራሙ  መገናኛ ዋች ህንፃ ላይ በሚገኘው ጣዕም ባህላዊ ምግን ቤት ወሩን ጠብቆ ወሩን ጠብቆ ይቀርባል።

አብረን በጥበብ አስተውሎት ከፍ እንበል

ሆሄ ተስፋ የኪነጥበብ ቡድን

@DBU11
2024/06/24 13:06:28
Back to Top
HTML Embed Code: