Telegram Web Link
አዲሱ ከሳር ቤት ሜክሲኮ መንገድ ተጠናቋል!
ከዘመድኩን በቀለ እና ከእስታሊን ገብረስላሴ ጋር ለምን ኦሮምያ ላይ ተሰራ ብላቹ ምታለቅሱ ኦሮሞዎች ትንሽ የጥሞና ጊዜ ቢኖራቹ መልካም ነው።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ፋኖ ትግራይ ገብቶ ህፃን አሮጊት ሳይል እንደደፈረ መዓዛ መሀመድ መስክራለች
ኢትዮጵያን እንዴት እንደ ኬንያ እናተራምሳት ብሎ twitter space ከፍቶ የፋኖን ያወያየው ሻቢያ ደጋፊ ነው ሀገሪቱን ለማፍረስ የህዝብ እልቂት እንዲደረግ ከጠላት ጋር መተባበር ምን ያህል የአይምሮ ዝቅጠት ላይ እንደተደረሰ ማሳያ ነው።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የመረርዝ ብልቃጡዋ እነ ኢሮብን፣ እንደርታን፣ ቤጃን፣ ኩናማን፣ ሳሆ ራያ ኦሮሞን… የደፈቀች ትግራይ ማንነታቸውን ያጠፋች ትግራይ ሸምጥጣ ክዳ ሰለ ኢትዮጵያ የመዘዘችዉ በጡጦ ተግታ ያደገች የት ህነግ እርዮት ስሙት።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሙዲናው ህዝብ ሞቶ እኔ ሥልጣን አልያሲያዘኝም በሚል ወጣቱን በዚን ያህል መዝለፍ ምን የሚሉት ነው ??
ለመጀመርያም ለመጨረሻም ጊዜ ከዲሲ ዋሽንግተን ዳላስ ኤርፖርት ቦሌ አለማቀፍ ኤርፖርት በሙብረር ሥልጣን የያዘው ብርሃኑ ነጋ ብቻ ነው ከዚህ በኃላ ሚደገም አይመስለኝም ህዝቡን አታባሉት
ይሄ የኦሮሞ ህዝብ ብቻ ሳይሆን የመላው የኢትዮጵያ ህዝብ አንገብጋቢ ጥያቄ ነው
ጦርነት ይቁም !!
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከሰላም የሚገኘው ትርፉ ብዙ ነው !!
#1NoWar
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
TPLF in intensive care unite ውስጥ ነው ያለው ባጭሩ #ኮማ ውስጥ ስለሆነ ☠️☠️☠️ ተባብረን #ከትግራይ ህዝብ ነቅለን መጣል አለብን እያሉ ነው
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የዶላር ቀበኞቹ ቡጡቡጥ ቀጥሏል
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በህውሃት መሬታቸው ተነጥቆ ከቀያቸው የተባረሩ የፊንፊኔ እና የፊንፊኔ ኦሮሞዎችን መልሶ ማደራጀት ቦታቸው ላይ መመለስ በኢኮኖሚ መገንባት የሽመልስ አብዲሳ እና የአዳነች አቤቤ ትልቁ የቤት ሥራ ነው።
የአገው ሕዝብን የክልልነት ጥያቄን አስመልክቶ ከአስተባባሪ ኮሚቴው የተሰጠ መግለጫ #ሼር ይደረግ

መግቢያ
የአገው ሕዝብ በጥቅሉ በምስራቅ አፍሪካ ረዥም ታሪክ ውስጥ በሃገረ መንግሥት ግንባታ፣ በግብርና ሥራ፣ በስነ ህንጻ፣ በዕድሜ ጠገብ በዓላት እና በጋለ የሃገር ፍቅር አርበኝነት የማይተካ ሚና የተጫወተ ሕዝብ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ይህ ሕዝብ በታሪክ ተመራማሪዎች “በስልጡንነትና በፈጠራ ችሎታ በአፍሪካ አቻ ያለተገኘለት ሕዝብ” ተብሎ ተጠቅሷል፡፡

ይሁን እንጂ የአገው ሕዝብ ላለፉት 750 ዓመታት በተጋረጡበት ተፈጥሯዊ እና ሰው ሠራሽ ችግሮች ምክንያት በቁጥር፣ በወሰን ግዛት እና በማንነት እየተመናመነ ሄዶ በአሁኑ ሰዓት በህልውና አደጋ ላይ ይገኛል፡፡ ከዛጉዌ ውድቀት ጀምሮ የአገው ሕዝብ ለአግላይ ትርክት፣ ለፖለቲካ መገለል እና ለማንነት ጥቃት እየተጋለጠ ሲመጣ ደግሞ ቀጠናው ለ ምዕተ-ዓመታት የጦር አውድማ ሆኖ እንዲቆይ አድርጎታል፡፡

ከእነዚህ ነባር ችግሮች በከፋ ሁኔታ ባለፉት 30 እና 40 ዓመታት የታዩት መዋቀራዊ በደሎች የአገውን ሕዝብ ከፍተኛ አደጋ ላይ ጥለዉታል፡፡ በደሎቹ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሱ የመጡበት ይህ ሕዝብ የደርግ ስርዓትን ለመገርሰስ ከፍተኛ ዋጋ የከፈለ ቢሆንም፣ በባሰ ሁኔታ ለህልውና አደጋ የተጋለጠው ከደርግ ቀጥሎ በመጣው የኢህአዴግ ዘመነ መንግሥት ነበር፡፡

በዚህ ዘመን የአገው ሕዝብ በሁሉም የልማት መለኪያዎች ወደ ኋላ እንዲቀር የተደረገ ከመሆኑም ባሻገር፣ ከ1980ዎቹ ጀምሮ ያነሳ የነበራቸው ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄዎችም እስከሞት ድረስ ሲያስቀጡት ቆይተዋል፡፡

በመሆኑም ህዝባችን እነዚህን ውስብውብና ዘርፈ-ብዙ ችግሮች መፍታት የሚቻለው በራስ አቅም ወይም ራስን በራስ በማስተዳደር ብቻ እንደሆነ በመገንዘብ ይህን ጥያቄ ከግብ ለማድረስ በይፋ በመታገል ላይ ይገኛል፡፡

በጥቅሉ፣ የአገው ዝህብ የክልልነት ጥያቄ የአገው ሕዝብን መሰረታዊ ችግሮች ለመፍታት ያለመ ሲሆን በዋናነት የሚከተሉትን ችግሮች ለመፍታት መሠረት በማበጀት ላይ ያጠነጥናል፡፡

ህልውናን ለማስቀጠል
የብሔረሰብ አስተዳደር ዞኖች የተመሠረቱት ህዝቦች ቋንቋቸውን፣ ባህላቸውን፣ ታሪካቸውን እና ማንነታቸውን እንዲጠብቁ፣ እንዲያሳደጉ እና በቋንቋቸው እንዲገለገሉ ለማስቻል እንደሆነ የሚታወቅ ቢሆንም፣ የአገው ሕዝብ ነባራዊ ሁኔታ ግን ይህን አያሳይም፡፡

በአሁኑ ሰዓት የአገው ባህል እየደበዘዘና እየተበረዘ፣ ታሪኩ እየተቀበረና እየተዘረፈ ቋንቋው ሽፋኑን እየቀነሰና እየጠፋ ባጠቃላይ ማንነቱ እየተዳከመ እንዲመጣ ተገዷል፡፡ አሁን ያለው ሁኔታ ሳይቀየር ከቀጠለ የአገው ሕዝብ ታሪክ ብቻ ሆኖ ሊቀር የሚችልበት እድል ሰፊ ነው፡፡ ታሪካዊው የአገው ሕዝብ ይህን የህልውና አደጋ መግታት እና በምትኩ ማንሰራራት የሚችለው ራሱን በራሱ ማስተዳደር ሲችል ብቻ መሆኑን መገንዘብ ከጀመረ ውሎ አድሯል።

በተለይም ጽንፈኛ ብሔርተኝነት እና አግላይ አስተሳሰቦች ባደጉ ቁጥር ችግሩ አንገብጋቢ እየሆነ መምጣቱን በሚገባ ይረዳል፡፡ ለዚህም ነው የራስ አስተዳደር ጥያቄ ማንሳት በጽነፈኛ ኃይሎች በኩል ከፍተኛ ዋጋ የሚያስከፍል ቢሆንም፣ ሊያመጣ የሚችለውን መፍትሄ ብቻ በማሰብ ህዝባችን በጽናት ለዛሬው ቀን የበቃው፡፡

ሕገ-መንግሥታዊ ሥልጣን ለመጋራት
የአገው ሕዝብ ያለበት ነባራዊ የአወቃቀር ችግር ከፈጠረው ጫና የተነሳ በሰሜኑ ቀጠናም ሆነ በጥቅሉ ብዙ ዋጋ በከፈለላት ኢትዮጵያ ጉዳዮች ላይ ያለው ፖለቲካዊ ተሳትፎ በጣም ዝቅተኛ ነው። ይህ የፖለቲካ ውክልና ማጣት ደግሞ ለዘመናት የተከሰቱት ችግሮች ስር እየሰደዱ እንዲሄዱ ብቻ ሳይሆን አዳዲስ ችግሮችም በየጊዜው እንዲወለዱ አድርጓል፡፡

በእነዚህ ችግሮች ዙሪያ የሚያነሳቸው ጥያቄዎችም ሰሚ እንዳያገኙ እያደረገ ይገኛል፡፡ ይህ ደግሞ መሬት ላይ የአገው ሕዝብ ልማትን ጨምሮ በሁሉም መለኪያዎች የተገለለ ማህበረሰብ እንዲሆን አስገዳጅ ሁኔታ ፈጥሯል፡፡

የአገው ሕዝብ የራሱን ክልል መመስረቱ በቀዳሚነት ከጥገኝነት ፖለቲካ እንዲወጣ በማድረግ በሁለንተናዊ መብቶቹና ፍላጎቶቹ ላይ የራሱን ውሳኔ እንዲተገብር ይረዳዋል። መልክዓ-ምድራዊ አቀማመጡ እና ችግሮቹ በአይነትም ሆነ በመጠን ከሌሎች የትግራይ እና የአማራ ክልል አከባቢዎች የተለዩ በመሆናቸው አካባቢውን የመሰለ መፍትሄ ለማበጀት የሚያስችል የፖለቲካ ምህዳርም ይፈጥርለታል፡፡

ለተጎሳቆለው ማህበረሰብም የተሳለጠ እና ውጤታማ አግልግሎት ለመስጠት እድል ይፈጥረለታል፡፡ ከዚህም አልፎ በሃገራዊ የፖለቲካ ተሳትፎው የሚገባውን ውክልና በማግኘ3ት የራሱን በጎ ብሔራዊ ሚና እንዲጫወት ያስችለዋል፡፡

የራስ አቅምን መሰረት ያደረገ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማት ለማምጣት በግልጽ እንደሚታወቀው፣ ህዝባችን የሚገኝበት የተከዜ ኮሪደር አካባቢ የሀገራችን የደህነትና የኋላ ቀርነት ምሳሌ ሆኖ መገለጽ ከጀመረ ውሎ አድሯል፡፡

በተጨባጨጭም ይህ አካባቢ በሃገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የትምህርት ሽፋንና ጥራት ጉድለት ያለበት፣ ለቁጥር የዳስ ክፍሎች የሚገኙበት፣ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለአመል እንኳን ያልደረሰበት፣ ዛሬም ድረስ ህጻናት በሚድኑ በሽታዎች በጅምላ የሚያልቁበት፣ እናቶች በወሊድ ምክንያት በብዛት የሚሞቱበት፣ አካባቢው በተፈጥሮ ሃብት የበለጸገ ሆኖ ሳለ ትኩረት በመነፈጉ ብቻ ዳቦ ላይ ቆሞ የሚራብበት አካባቢ ነው፡፡

እነዚህ ውስብስብ ችግሮች መፍትሄ የማይገኝላቸው መስለው ቢታዩም፣ መዋቅራዊ ችግር የፈጠራቸው ድክመቶች በመሆናቸው መፍትሄውም መዋቅራዊ መሆኑ እሙን ነው፡፡ እርሱም የአገው ሕዝብ መልክአምድሩን፣ መገለጫ ችግሮቹን እና ልዩ ሃብቱን መሠረት ያደረገ ፖሊሲ እና ስትራቴጂ ማበጀት ብቻ ነው፡፡

ይህ የመፍትሄ አቅጣጫ ሊሰምር የሚችለው ደግሞ ይህ ኩታ ገጠም በሆነ ቀጠና ውስጥ የሚኖር እና ልዩ የለውጥ ፍላጎት ያለው ሕዝብ በፌደሬሽን ደረጃ ራሱን በራሱ ማስተዳደር የቻለ እንደሆነ ብቻ ነው፡፡ ከዚህ አንጻር፣ የክልል ጥያቄው የማህበረሰባችን ችግሮች ሁሉ በመሠረታዊነት ሊቀረፉ የሚችሉበት ብቸኛ ድልድይ ነው ማለት ይቻላል፡፡

ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን
ከታሪክ መገንዘብ እንደሚቻለው፣ የሃገራችን ኢትዮጵያ አብዝሃኛዎቹ የግጭት ችግሮች የሚከሰቱት በሰሜኑ የሃገሪቱ ክፍል ነው፡፡ እነዚህ ችግሮች በቀድሞው ዘመን ከሥልጣን የበላይነት ጋር የተያያዙ የነበሩ ቢሆንም፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የማንነት፣ የወሰን እና የብሔር ግጮቶች ወደመሆን በማደግ ላይ ይገኛሉ፡፡

አነዚህ ግጭቶች ደግሞ የአገው ሕዝብን የዘለሉበት አጋጣሚ አይታወቅም፡፡ ነገር ግን ይህ ሕዝብ ራሱን በራሱ ማስተዳደር ቢችል የችግሩ አካል አለያም ተጠቂ በመሆን ፈንታ ለዘላቂ ቀጠናዊ ሰላም አይነተኛ ሊጫወት የሚችልበት እድል በጣም ሰፊ ነው፡፡

በመጀመሪያ ደረጃ፣ የአገው ሕዝብ በሁለቱም የሰሜን ኢትዮጵያ ሰፊ ህዝቦች መካከል የሚኖር እና በእርግጥም አገናኝ የሆነ ሕዝብ ነው፡፡ ከታሪካዊው ሃቅ አንጻርም ሁለቱን ወንድም ህዝቦች የአብራኩ ክፋይ አድርጎ የሚመለከት ወዳጅ ሕዝብ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ በቅርቡ የተከሰተውን የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ከመጀመሩ በፊት የአገው ሕዝብ የነበረውን የሰላም ጥረት መለስ ብሎ መቃኘት ብቻ በቂ ነው፡፡

ይህ አብነታዊ ጥረት የአገው ሕዝብ የፖለቲካ ውክልና እና የራስ አስተዳደር የሌለው በመሆኑ ከዳር ሳይደርስ የቀረ ቢሆንም፣ በሚና ደረጃ ግን ይህ ሕዝብ ለቀጠናው መረጋጋት አብይ ሚና ሊጫወት እንደሚችል ከወዱሁ መመልከት ይቻላል፡፡
2024/09/23 17:21:48
Back to Top
HTML Embed Code: