Telegram Web Link
የወላይታ ሕዝብ ሆይ፦
ነገ ሰኔ 12 2015 ዓ/ም ላንተ ታሪካዊ ቀን ነዉና በነቂስ ወጥተህ ምረጥ። አስተዉል፦ይህ ሪፈረንደም የፖለቲካ ፓርቲዎች ፉክክር አይደለም።
በካርድህ የወላይታን ሕዝብ መጻኢ ዕድል የምትወስንበት ነዉ። የዘራኸውን ብቻ ታጭዳለህ።
መልካም ዘር ዝራ

መልካም ሪፈረንደም!
በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ ጎንጎ ቀበሌ ነዋሪ ኦሮሞዎች ላይ በመከላከያ እና በፌዴራል ፖሊስ አባላት የተፈፀመ ዝርፊያ ፤---

1ኛ አቶ ሚካኤል በቀለ 1 ሌዘር ጃኬት ሁለት ሱር ባለ ሦስት ሊትር ጀሪካን ዘይት 9 ፍሬ ፤ የታሸጉ የማንጎ ጁስ 9 ካርቶን ሙሉ ።

2ኛ ታዬ ኢሬና 10 ሺህ ብር ፤ 1 ሶላር የሁለት ልጆቹ ጨምሮ 3 ሞባይሎች።

3ኛ አቶ አብዲሳ ሞርካ 5 ሺህ ብር ያውም (አስራት ለመክፈል የተቀመጠ ገንዘብ ) ።

4ኛ ጅራ ባይሳ 10 ሺህ ብር ፥ 1 ጀሪካን ዘይት ።

5ኛ አቶ ዋጋሪ ያዳ 8 ሺህ ብር ፥ 2 ጦር እና 3 ካራ (ቢላዋ )።
6ኛ አቶ ግርማ ቴሶ 20 ሺህ ብር ።

7ኛ አቶ ሂካ ፈይሳ 84 ሺህ ብር ፤ 12 ሽቦ ወርቅ
40 ኪ ግ ማር (እዚያው ተሰብስበው የበሉት )።

8ኛ ወ/ሮ ጀማነ ኦልጅራ 1 ሞባይል አንድ ጫማ

9ኛ አቶ ገነቲ ኩሳ 1500 ብር ።

ይህ ሁሉ በሚፈፅሙበት ጊዜ ተጎጂዎችን ቁጭ ብላችሁ የምናደርገውን እዩን ብለው ከመዛት ውጭ ሌላ የወሰዱባቸው እርምጃ አልነበረም።
( Temesgen Gemechu )
በኦሮምያ እንደዚህ ከየትኛውም ባንድራ በነፃ መልኩ ሃይማኖታዊ ክብረ በዓል እንዲከበር ነው ምን ፈልገው ይሄ በጣም ደስ ይላል
#Ethiopia: Eight killed, 13 injured in fresh attack in #Kiremu, East #Wollega, local admin accuses “extremist group” from #Amhara region

Eight civilians have been killed, 13 injured and 15 went missing following a fresh attack on 16 June, carried out by the irregular Fano militia in the village of Wasti, in Kiremu district of East Wollega zone, in Western Oromia, residents told Addis Standard.

A resident of #Kiremu who asked not to be named for safety reasons shared the names of the deceased and those who were injured with Addis Standard, noting that the perpetrators crossed the border from neighboring #Amhara region.

Beyene Bekare, Oljira Tolera, Amanu Hirko, Hailu Eticha, Asaye Beyene, Tolera Hirpha, Tamasgu Yaya and Bikila Bakalu are those who were killed during the attack, the resident said adding that their age ranges between 20 and 58.

Jiregna Hirpha, Kiremu district communication officer corroborating the residents account told #Addis_Standard that the militants have opened permanent military bases and are operating in four of the ten villages of the district namely Bagil, Caffee Gudina, Haro and Marga Jireenya.

https://addisstandard.com/news-eight-killed-13-injured-in-fresh-attack-in-kiremu-east-wollega-local-admin-accuses-extremist-group-from-amhara-region/
#Alert


አንገት ቆራጩ #ፋኖ ትናት ሌሊት 9:00 ጀምሮ ከጃዊ ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ መተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ ጃቫ ልዩ ቦታው ኮርድኝ እና ሰሜነ የተባሉ መንደር ነዋሪ በሆኑ የአገው ተወላጆች ላይ ጦርነት ከፍተው እስካሁን ባለው መረጃ ሴት እና ህፃናት ጨምሮ 12 ንፁሃን መግደላቸውና ጦርነት ከፍተው መንደራቸውን ማቃጠላቸው የታወቀ ሲሆን ዛሬም ጦርነቱን አባብስው ህፃናት እና አሮጊቶችን አንገት በማረድ ላይ ናቸው
የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መንበረ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ሐምሌ 9 ቀን በርዕሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ፅዮን ማርያም የተለያዩ የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ያከናውናል

Bini Berhe
በአማራ ክልል፤ ማዕከላዊ ጎንደር ዞን የቆላድባ ከተማ ነዋሪ የሆነው ደጀን አረጋ የ3 ዓመት ልጅ ሕፃን አማኑኤል ወንድማገኝን ከደብረ ማርቆስ ከተማ 06 ቀበሌ በማገት ወደ ጠገዴ ወረዳ እርጎየ ቀበሌ ጫካ በመውሰድ ቤተሰቦቹ 500 ሺሕ ብር እንዲያመጡ ሲጠይቅ የነበረ ሲሆን፤ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የጠገዴ ወረዳ ኮምኒኬሽን ገልጿል።

ሕጻኑን በጫካው ውስጥ ለ7 ቀን ያክል ይዞ ቤተሰቦቹን 500 ሺሕ ብር እንዲከፍሉ ሲጠይቅ ከቆየ በኃላ ፖሊስ ባደረገው ኦፕሬሽን ሕጻኑን ከአጓቾች እጅ ማስለቀቅ መቻሉ ተገልጿል።
የኦሮሞ ህዝብ ከዚህ ስርአት ተጠቃሚ እንደሆነ በማስመሰል በአክራሪ ቡድኖች የሚነዛው የጥላቻ ቅስቀሳ በአፋጣኝ መቆም እንዳለበት ረዳት ፕሮፌሰር አሰፋ ወዳጆ አሳሰቡ።
==============================================

ረዳት ፕሮፌሰሩ እንዳሉት፣ በኦሮሞ ህዝብ ላይ ከፍተኛ የጥላቻ ቅስቀሳ እየተደረገበት ይገኛል።

የጥላቻ ቅስቀሳ እያደረገ የሚገኘው ቡድን የኦሮሞን ህዝብ ከዚህ ስርአት ተጠቃሚ አድርጎ ለመሳል ሰፊ ዘመቻ እያደረገ ይገኛል ብለዋል።

ይህ ቡድን ትናንት በተመሳሳይ መልኩ በትግራይ ህዝብ ላይ የጥላቻ ቅስቀሳ ሲያደርግ እንደቆየ ረዳት ፕሮፌሰሩ አስታውሰው፣ በዚህም በትግራይ ህዝብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንዲደርስ ማድረጉን ጠቅሰዋል።

ይህ ቡድን የጥላቻ ዘመቻን በማድረግ የተካነ መሆኑን ገልፀው፣ የዚህ አይነቱ የጥላቻ ዘመቻ ለሀገሪቷና ለህዝቦቿ አደጋ መሆኑን ተናግረዋል።

እንደዚህ አይነቱን ዘመቻ በአንክሮ መከታተል እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።
በቦረና ድርቅ ምክንያት ከሕዝብ የተሰበሰበው ገንዘብ ለተጎጂዎች አልደረሰም ተባለ

ቅዳሜ ሰኔ 17 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን በድርቅ የተጎዱ ነዋሪዎችን ለመደገፍ እና መልሶ ለቋቋም በአገር ውስጥ እና በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የተሰበሰበው ገንዘብ አልደረሰንም ሲሉ በድርቁ የተጎዱ ሰዎች ለቪኦኤ ኦሮምኛ ተናግረዋል፡፡

"ድርቁ በተከሰተበት ወቅት ሲደረግ የነበረው ሰብአዊ ድጋፍ ጥሩ የነበረ ቢሆንም፤ ተሰበሰበ የተባለው ገንዘብ ወዴት እንደገባ አናውቅም።" ሲሉ ነው የድርቁ ተጎጂዎች ያስረዱት።

በወቅቱ በርካታ ሰዎች በማህበራዊ ሚዲያ በዘመቻ መልክ ብር ከተሰበሰቡ በኋላ ገንዘቡ ወዴት እንደገባ የሚታወቅ ነገር የለም ያሉት ተጎጂዎቹ፤ ለእነርሱ በእርዳታ የመጣ እህል ገበያ ላይ ሲሸጥ እንደነበርም ጠቁመዋል።

የቦረና ዞን የቡሳ ጎኖፋ መምሪያ ተጎጂዎችን መልሶ ለማቋቋም የክልሉ መንግሥት በሕዝቡ ሥም የሰበሰበውን ገንዘብ እንዲሰጥ በተደጋጋሚ መጠየቁን እና መልስ እየጠበቀ መሆኑም ተመላክቷል።

የኦሮሚያ ክልል ቡሳ ጎኖፋ ቢሮ የተሰበሰበው ገንዘብ በክልሉ መንግሥት አቅጣጫ ሰጪነት በቡሳ ጎኖፋ ቢሮው አካውንት በተለያዩ ባንኮች 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር እንደሚገኝ አመላክቷል።

ቢሮው አክሎም፤ የተሰበሰበው ገንዘብ በትክክል ሥራ ላይ እንዲውል እና በድርቁ የተጎዱ ሰዎችን በሚገባ መልሶ ለማቋቋም የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተቀርጸው ወደ ሥራ እንደሚገባ በመገለጽ፤ ያንን ለማድረግ ግን ጊዜ ያስፈልጋል ብሏል።

በሕዝብ ሥም ገንዘብ ሲሰበስቡ የነበሩ እና ለግል ጥቅማቸው ሲያውሉ የነበሩ ሰዎችም በሕግ አግባብ ተጠያቂ እንዲሆኑ ተደርጓል ነው የተባለው።

በእርዳታ አሰጣጥ ሂደቱ ከታዩ ክፍተቶች መካከል በትክክል መረዳት ያለባቸው ሰዎች ሳይረዱ በማታለልና በብልጠት መረዳት የሌለባቸው ሰዎች እርዳታ ሲወስዱ እንደነበር ጠቅሶ፤ ይህን የማጥራት ሥራም ጎን ለጎን እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጿል።  

የክልሉ መንግሥት በተጎጂዎቹ ሥም የሚሰበሰበው ማንኛውም የእርዳታ ገንዘብ በቡሳ ጎኖፋ ቢሮ እውቅና ብቻ እንዲሰበሰብ እና ግለሰቦች በራሳቸው ሥም የሚሰበስቡት ገንዘብ እንዳይኖር መመሪያ ሰጥቶ እንደነበር ይታወሳል።
____
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n
ካሜሪካን የመጡ chick-fil-A Fast food ሰራተኞች ኢትዮጵያ በመሄድ ለፌዴራል ፍርድ ቤት ዳኞች እና የስራ ሀላፊዎች የአመራር ክህሎት ሥልጠና ሰጥተዋል።
አትሌት ድርቤ ወልተጂ በቼክ ሪፐብሊክ በተደረገው የ1,500 ሜትር የሴቶች ውድድር ላይ በ3:57.38 በመግባት አዲስ የአለም ሪከርድ አስመዝግባለች ::

Congratulations 🎊

#ContinentalTourGold
#WorldAthletics
2024/09/27 15:35:28
Back to Top
HTML Embed Code: