Telegram Web Link
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በህውሃት መሬታቸው ተነጥቆ ከቀያቸው የተባረሩ የፊንፊኔ እና የፊንፊኔ ኦሮሞዎችን መልሶ ማደራጀት ቦታቸው ላይ መመለስ በኢኮኖሚ መገንባት የሽመልስ አብዲሳ እና የአዳነች አቤቤ ትልቁ የቤት ሥራ ነው።
የአገው ሕዝብን የክልልነት ጥያቄን አስመልክቶ ከአስተባባሪ ኮሚቴው የተሰጠ መግለጫ #ሼር ይደረግ

መግቢያ
የአገው ሕዝብ በጥቅሉ በምስራቅ አፍሪካ ረዥም ታሪክ ውስጥ በሃገረ መንግሥት ግንባታ፣ በግብርና ሥራ፣ በስነ ህንጻ፣ በዕድሜ ጠገብ በዓላት እና በጋለ የሃገር ፍቅር አርበኝነት የማይተካ ሚና የተጫወተ ሕዝብ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ይህ ሕዝብ በታሪክ ተመራማሪዎች “በስልጡንነትና በፈጠራ ችሎታ በአፍሪካ አቻ ያለተገኘለት ሕዝብ” ተብሎ ተጠቅሷል፡፡

ይሁን እንጂ የአገው ሕዝብ ላለፉት 750 ዓመታት በተጋረጡበት ተፈጥሯዊ እና ሰው ሠራሽ ችግሮች ምክንያት በቁጥር፣ በወሰን ግዛት እና በማንነት እየተመናመነ ሄዶ በአሁኑ ሰዓት በህልውና አደጋ ላይ ይገኛል፡፡ ከዛጉዌ ውድቀት ጀምሮ የአገው ሕዝብ ለአግላይ ትርክት፣ ለፖለቲካ መገለል እና ለማንነት ጥቃት እየተጋለጠ ሲመጣ ደግሞ ቀጠናው ለ ምዕተ-ዓመታት የጦር አውድማ ሆኖ እንዲቆይ አድርጎታል፡፡

ከእነዚህ ነባር ችግሮች በከፋ ሁኔታ ባለፉት 30 እና 40 ዓመታት የታዩት መዋቀራዊ በደሎች የአገውን ሕዝብ ከፍተኛ አደጋ ላይ ጥለዉታል፡፡ በደሎቹ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሱ የመጡበት ይህ ሕዝብ የደርግ ስርዓትን ለመገርሰስ ከፍተኛ ዋጋ የከፈለ ቢሆንም፣ በባሰ ሁኔታ ለህልውና አደጋ የተጋለጠው ከደርግ ቀጥሎ በመጣው የኢህአዴግ ዘመነ መንግሥት ነበር፡፡

በዚህ ዘመን የአገው ሕዝብ በሁሉም የልማት መለኪያዎች ወደ ኋላ እንዲቀር የተደረገ ከመሆኑም ባሻገር፣ ከ1980ዎቹ ጀምሮ ያነሳ የነበራቸው ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄዎችም እስከሞት ድረስ ሲያስቀጡት ቆይተዋል፡፡

በመሆኑም ህዝባችን እነዚህን ውስብውብና ዘርፈ-ብዙ ችግሮች መፍታት የሚቻለው በራስ አቅም ወይም ራስን በራስ በማስተዳደር ብቻ እንደሆነ በመገንዘብ ይህን ጥያቄ ከግብ ለማድረስ በይፋ በመታገል ላይ ይገኛል፡፡

በጥቅሉ፣ የአገው ዝህብ የክልልነት ጥያቄ የአገው ሕዝብን መሰረታዊ ችግሮች ለመፍታት ያለመ ሲሆን በዋናነት የሚከተሉትን ችግሮች ለመፍታት መሠረት በማበጀት ላይ ያጠነጥናል፡፡

ህልውናን ለማስቀጠል
የብሔረሰብ አስተዳደር ዞኖች የተመሠረቱት ህዝቦች ቋንቋቸውን፣ ባህላቸውን፣ ታሪካቸውን እና ማንነታቸውን እንዲጠብቁ፣ እንዲያሳደጉ እና በቋንቋቸው እንዲገለገሉ ለማስቻል እንደሆነ የሚታወቅ ቢሆንም፣ የአገው ሕዝብ ነባራዊ ሁኔታ ግን ይህን አያሳይም፡፡

በአሁኑ ሰዓት የአገው ባህል እየደበዘዘና እየተበረዘ፣ ታሪኩ እየተቀበረና እየተዘረፈ ቋንቋው ሽፋኑን እየቀነሰና እየጠፋ ባጠቃላይ ማንነቱ እየተዳከመ እንዲመጣ ተገዷል፡፡ አሁን ያለው ሁኔታ ሳይቀየር ከቀጠለ የአገው ሕዝብ ታሪክ ብቻ ሆኖ ሊቀር የሚችልበት እድል ሰፊ ነው፡፡ ታሪካዊው የአገው ሕዝብ ይህን የህልውና አደጋ መግታት እና በምትኩ ማንሰራራት የሚችለው ራሱን በራሱ ማስተዳደር ሲችል ብቻ መሆኑን መገንዘብ ከጀመረ ውሎ አድሯል።

በተለይም ጽንፈኛ ብሔርተኝነት እና አግላይ አስተሳሰቦች ባደጉ ቁጥር ችግሩ አንገብጋቢ እየሆነ መምጣቱን በሚገባ ይረዳል፡፡ ለዚህም ነው የራስ አስተዳደር ጥያቄ ማንሳት በጽነፈኛ ኃይሎች በኩል ከፍተኛ ዋጋ የሚያስከፍል ቢሆንም፣ ሊያመጣ የሚችለውን መፍትሄ ብቻ በማሰብ ህዝባችን በጽናት ለዛሬው ቀን የበቃው፡፡

ሕገ-መንግሥታዊ ሥልጣን ለመጋራት
የአገው ሕዝብ ያለበት ነባራዊ የአወቃቀር ችግር ከፈጠረው ጫና የተነሳ በሰሜኑ ቀጠናም ሆነ በጥቅሉ ብዙ ዋጋ በከፈለላት ኢትዮጵያ ጉዳዮች ላይ ያለው ፖለቲካዊ ተሳትፎ በጣም ዝቅተኛ ነው። ይህ የፖለቲካ ውክልና ማጣት ደግሞ ለዘመናት የተከሰቱት ችግሮች ስር እየሰደዱ እንዲሄዱ ብቻ ሳይሆን አዳዲስ ችግሮችም በየጊዜው እንዲወለዱ አድርጓል፡፡

በእነዚህ ችግሮች ዙሪያ የሚያነሳቸው ጥያቄዎችም ሰሚ እንዳያገኙ እያደረገ ይገኛል፡፡ ይህ ደግሞ መሬት ላይ የአገው ሕዝብ ልማትን ጨምሮ በሁሉም መለኪያዎች የተገለለ ማህበረሰብ እንዲሆን አስገዳጅ ሁኔታ ፈጥሯል፡፡

የአገው ሕዝብ የራሱን ክልል መመስረቱ በቀዳሚነት ከጥገኝነት ፖለቲካ እንዲወጣ በማድረግ በሁለንተናዊ መብቶቹና ፍላጎቶቹ ላይ የራሱን ውሳኔ እንዲተገብር ይረዳዋል። መልክዓ-ምድራዊ አቀማመጡ እና ችግሮቹ በአይነትም ሆነ በመጠን ከሌሎች የትግራይ እና የአማራ ክልል አከባቢዎች የተለዩ በመሆናቸው አካባቢውን የመሰለ መፍትሄ ለማበጀት የሚያስችል የፖለቲካ ምህዳርም ይፈጥርለታል፡፡

ለተጎሳቆለው ማህበረሰብም የተሳለጠ እና ውጤታማ አግልግሎት ለመስጠት እድል ይፈጥረለታል፡፡ ከዚህም አልፎ በሃገራዊ የፖለቲካ ተሳትፎው የሚገባውን ውክልና በማግኘ3ት የራሱን በጎ ብሔራዊ ሚና እንዲጫወት ያስችለዋል፡፡

የራስ አቅምን መሰረት ያደረገ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማት ለማምጣት በግልጽ እንደሚታወቀው፣ ህዝባችን የሚገኝበት የተከዜ ኮሪደር አካባቢ የሀገራችን የደህነትና የኋላ ቀርነት ምሳሌ ሆኖ መገለጽ ከጀመረ ውሎ አድሯል፡፡

በተጨባጨጭም ይህ አካባቢ በሃገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የትምህርት ሽፋንና ጥራት ጉድለት ያለበት፣ ለቁጥር የዳስ ክፍሎች የሚገኙበት፣ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለአመል እንኳን ያልደረሰበት፣ ዛሬም ድረስ ህጻናት በሚድኑ በሽታዎች በጅምላ የሚያልቁበት፣ እናቶች በወሊድ ምክንያት በብዛት የሚሞቱበት፣ አካባቢው በተፈጥሮ ሃብት የበለጸገ ሆኖ ሳለ ትኩረት በመነፈጉ ብቻ ዳቦ ላይ ቆሞ የሚራብበት አካባቢ ነው፡፡

እነዚህ ውስብስብ ችግሮች መፍትሄ የማይገኝላቸው መስለው ቢታዩም፣ መዋቅራዊ ችግር የፈጠራቸው ድክመቶች በመሆናቸው መፍትሄውም መዋቅራዊ መሆኑ እሙን ነው፡፡ እርሱም የአገው ሕዝብ መልክአምድሩን፣ መገለጫ ችግሮቹን እና ልዩ ሃብቱን መሠረት ያደረገ ፖሊሲ እና ስትራቴጂ ማበጀት ብቻ ነው፡፡

ይህ የመፍትሄ አቅጣጫ ሊሰምር የሚችለው ደግሞ ይህ ኩታ ገጠም በሆነ ቀጠና ውስጥ የሚኖር እና ልዩ የለውጥ ፍላጎት ያለው ሕዝብ በፌደሬሽን ደረጃ ራሱን በራሱ ማስተዳደር የቻለ እንደሆነ ብቻ ነው፡፡ ከዚህ አንጻር፣ የክልል ጥያቄው የማህበረሰባችን ችግሮች ሁሉ በመሠረታዊነት ሊቀረፉ የሚችሉበት ብቸኛ ድልድይ ነው ማለት ይቻላል፡፡

ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን
ከታሪክ መገንዘብ እንደሚቻለው፣ የሃገራችን ኢትዮጵያ አብዝሃኛዎቹ የግጭት ችግሮች የሚከሰቱት በሰሜኑ የሃገሪቱ ክፍል ነው፡፡ እነዚህ ችግሮች በቀድሞው ዘመን ከሥልጣን የበላይነት ጋር የተያያዙ የነበሩ ቢሆንም፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የማንነት፣ የወሰን እና የብሔር ግጮቶች ወደመሆን በማደግ ላይ ይገኛሉ፡፡

አነዚህ ግጭቶች ደግሞ የአገው ሕዝብን የዘለሉበት አጋጣሚ አይታወቅም፡፡ ነገር ግን ይህ ሕዝብ ራሱን በራሱ ማስተዳደር ቢችል የችግሩ አካል አለያም ተጠቂ በመሆን ፈንታ ለዘላቂ ቀጠናዊ ሰላም አይነተኛ ሊጫወት የሚችልበት እድል በጣም ሰፊ ነው፡፡

በመጀመሪያ ደረጃ፣ የአገው ሕዝብ በሁለቱም የሰሜን ኢትዮጵያ ሰፊ ህዝቦች መካከል የሚኖር እና በእርግጥም አገናኝ የሆነ ሕዝብ ነው፡፡ ከታሪካዊው ሃቅ አንጻርም ሁለቱን ወንድም ህዝቦች የአብራኩ ክፋይ አድርጎ የሚመለከት ወዳጅ ሕዝብ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ በቅርቡ የተከሰተውን የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ከመጀመሩ በፊት የአገው ሕዝብ የነበረውን የሰላም ጥረት መለስ ብሎ መቃኘት ብቻ በቂ ነው፡፡

ይህ አብነታዊ ጥረት የአገው ሕዝብ የፖለቲካ ውክልና እና የራስ አስተዳደር የሌለው በመሆኑ ከዳር ሳይደርስ የቀረ ቢሆንም፣ በሚና ደረጃ ግን ይህ ሕዝብ ለቀጠናው መረጋጋት አብይ ሚና ሊጫወት እንደሚችል ከወዱሁ መመልከት ይቻላል፡፡
በሁለተኛ ደረጃ፣ የአገው ሕዝብ ወደፊት የሚመሰርተው ብሔራዊ አስተዳደር በተፈጥሮው አቃፊ እና መድብለ-ባህላዊ የመሆን እድሉ ሰፊ መሆኑ ለቀጠናው ሰላም የራሱ አስተዋጽኦ ያበረክታል ብለን እናምናለን፡፡ እንደሚታወቀው የአገው ሕዝብ በቀጠናው የነበረውን የበላይነት በታሪክ ሂደት አጥቶ የሁለቱ ክልሎች ማሟያ ቢሆንም፣ ዛሬም ድረስ ማንነቱን እንደያዘ አገውኛ፣ ትግርኛ እና አማርኛ ቋንቋዎችን የሚናገር ሕዝብ ነው፡፡

ይህ ነባራዊ እውነታም የአገው ሕዝብ የትኛውንም ሕዝብ በቋንቋው የማግለል ስነልቦናዊ ውቅር የሌለው አቃፊ ሕዝብ መሆኑን አይነተኛ ማሳያ ነው፡፡ በተጨባጭም በዛጉዌ ዘመን የመራው ስርአት ለመላው ዓለም አብነታዊነት ያለው መድብለ-ባህላዊ ስርአት ነበር፡፡ ይህ እሳቤ ደግሞ በወደፊቱ ክልል የሚኖሩ ህዝቦች ማንነታቸው ተከብሮ እንዲቀጥሉ ከማስቻሉም በላይ፣ ለሰሜኑ ቀጠናም ሆነ ለመላው ኢትዮጵያ በጎ ናሙና እንደሚያደርገው ከወዲሁ መመልከት ይቻላል፡፡

ማጠቃለያ
የአገው ሕዝብ እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ችግሮች አሁን ባለው መዋቅር የሚፈቱ ሳይሆኑ መዋቅራዊ ለውጥ የሚሹ መሆናቸውን በመገንዘብ በክልል ደረጃ እንዲዋቀር ከ85 ሺ በላይ የድጋፍ ፊርማ በማሰባሰብ ለብሄረሰብ ምክር ቤቱ፣ ለፉደሬሽን ምክር ቤትና ለሚመለከታቸው አካላት በትላንትናው እለት አስገብቷል፡፡

በመሆኑም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መንግስት የአገው ሕዝብ ያቀረበው ህገመንግሥታዊ የክልል ጥያቄ የህልውና፣ የልማት፣ የተገቢ ፖለቲካዊ ውክልና እና የዘላቂ ሰላም ጉዳይ ከመሆኑም ባሻገር ሃገራዊ ፋይዳ ያለው መሆኑን በመገንዘብ የሃገሪቱ ህግ በሚፈቅደው አሰራር መሠረት አፈጣኝ ምላሽ ይሰጠን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

በአገው ሕዝብ ዙሪያ የምትሰሩ ሁሉም የፖለቲካ ድርጅቶች እና ሲቪክ ማህበራት የህዝባችን ጥያቄ ምላሽ እስኪያገኝ ድረስ እርስ በእርስ በመናበብ እና ህገመንግሥታዊ አካሄድን ብቻ በመከተል ትግላቸሁን በጽናት ትቀጥሉ ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

መላው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች የአብራካችሁ ክፋይ የሆነው የአገው ሕዝብ እየታገለለት ያለውን ፍትሃዊ ትግል በአንክሮ በመከታተል የበኩላችሁን አስተዋጽኦ ታበረክቱ ዘንድ በወንድማዊ አክብሮት እንጠይቃለን፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ የምትገኙ ሃገር አቀፍ የሕዝብ ተቋማት ሁሉ የክልል ጥያቄው ህዝባችን ለዘመናት ሲጋፈጣቸው ከኖሩት ችግሮች ለመላቀቅ መሠረት የሚያበጅበት አይነተኛ መንገድ መሆኑን በመገንዘብ የበኩላችሁን በጎ ሚና ትጫወቱ ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።

በግንዛቤ እጥረት እና ነባራዊ ሁኔታዎችን ባለመገንዘብ የአገው ሕዝብን የራስ አስተዳደር ጥያቄ በጥርጣሬ ወይም በአሉታዊ መንገድ የምትመለከቱ ወገኖቻችን ሁሉ ይህ ሕዝብ ሌሎች ህዝቦችን ከመወደድ እና እኩል ተጠቃሚ ከመሆን ውጭ ሌላ ምንም አይነት እሳቤ እንደሌለው ትገነዘቡ ዘንድ እንወዳለን፡፡ በዚህ አጋጣሚ ለበለጠ ማብራሪያም ኮሚቴው ምንጊዜም ዝግጁ መሆኑን ማስታወስ እንወዳለን፡፡

በመጨረሻም ኮሚቴው የክልልነት ጥያቄው እየገፋ መምጣቱን ተከትሎ ከተመሠረተ አንድ ዓመት ሊሞላው ጥቂት ወራት ቀርተዉታል፡፡ በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ከሁሉም አቅጣጫ የሚመጣበትን ፈተና በመቋቋም ህዝባዊ ጥያቄውን በሰነድ እና በህዝባዊ ፊርማ አስደግፎ ለማቅረብ ችሏል፡፡

ይህን ከግብ ለማድረስ ደግሞ በርካታ ባለድርሻ አካላት የየበኩላቸውን አወንታዊ ሚና ተጫውተዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ የጥያቄው ባለቤት የሆነው የዋግ ኽምራ እና አጎራባች አካባቢ ሕዝብ ትልቁን ድርሻ ይወስዳል፡፡ ቀጥሎም ከዞኑ ውጭ በመላው ሃገሪቱና ከአገርም ውጭ የሚኖረው የአገው ተወላጆች የራሳቸውን የማይተካ ሚና ተጫውተዋል፡፡

በጥቅሉ ጥያቄው የአገው ሕዝብ አስደናቂ ሊባል በሚችል ሁኔታ በየዘርፉ የተሳተፈበት ነው ማለት ይቻላል፡፡ በዚህ አጋጣሚ ኮሚቴው መላው የአገው ሕዝብ ጥያቄው ከዳር እስኪደርስ ድረስ ትግሉን በዴሞክራሲያዊ መንገድ እና በጽናት እንደሚቀጥል ለሰፊው የኢትዮጵያ ዴሞክራት ሕዝብ ማስታወስ ይወዳል፡፡

የአገው ክልላዊ መንገስት ምሥታ አስተባባሪ ኮሚቴ
ሰኔ 22/2016 ዓ/ም
አዲስ አበባ/ፊንፊኔ
.
.
.
.
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ህዝቡን ስላም ከመንሳት ውጪ ሚመጣ ለውጥ የለም የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ ጠይቃቹ ግቡ
በመጨረሻም ህዝቡን ዘርፈው ሲጨርሱ እርስ በእርስ መጋደል ጀምረዋል
ተዋጋልኝ ያለ ህዝብ ሳይኖር ለህዝብ ነው ምዋጋው በማለት ሥልጣን ማማ ላይ ለመውጣት የሚደረግ ሀገር ማተራመስ መጨረሻው እርስ በእርስ ተባልቶ ማለቅ ነው።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የጎሮቤት ሱማሌ ላንድ እህታችን በአፋን ኦሮሞ የዘፈነችው ዘፈን ነው
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በመጨረሻም እርስ በእርስ ተጫረሱ
ኢትዮጵያ፣ የባህር በርን አስመልክቶ፣ ከሶማሊላንድ ጋር የተፈራረመችውን የመግባቢያ ሰነድ ውድቅ ካላደረገች፣ ንግግር የሚባል ነገር የለም ስትል የነበረችው ሞቃዲሾ፣ ያለምንም ቅድሚያ ሁኔታ ከኢትዮጵያ ጋር በጉዳዩ ላይ ለመነጋገር መወሰኗን አንዳንድ የዜና ምንጮች እየገለጹ ነው። ንግግሩ፣ በቱርክ እንደሚካሄድ ተገለጸዋል
በውጪ የሚኖሩ ሹምባሻ ባንዳ የባንዳ ዘሮች ሱማሊያዎች ከታች ፋኖ ከላይ ሆነን ኦሮሞን እናጥፋ ሲሉ የኑበሩ ጃዊሳዎች መጥፎ ዜና ነው

በነገራችን ላይ ከኦሮሞ ካምፕ አንዳንዶች ከአንገት ቆራጭ ፋኖ Progressive የሆኑ ዲሞክራቲክ የሆኑ አንገት ቆራጭ ፋኖዎች ጋር አብረን እንሰራለን ማለት የጀመሩ እያየን ነው. ሞክሩት እና የዘላለም ግብአተ መሬታቹ ህዝቡ እንደሚፈፅም ከወዲሁ ልንነግራቹ እንወዳለን
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ይሄንን ውርጋጥ ሻቢያ ልክ ማስገባት ተገቢ ነው ከዚህ በኃላ ማንም አፉን ሲከፍት ዝም ማለት ተገቢ አይደለም።
ትግራይ በፀበል አጋንንት ሲወጣ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አርቲስት ተብዬዎች እያደረጉ ያሉትን ህዝብ በህዝብ ላይ ማነሳሳት አንዱን ብቻ ነጥሎ ከፍ በማድረግ ሌሎቹን ማኮስስ በቃ ሊባሉ ይገባል።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ብፁዕ አቡነ አብረሀም ስለ አቡነ ሉቃስ!
Forwarded from Gumaa Saaqqataa (Gumaa Saaqataa)
በዱባይ '"ልሙጡ ነው ባንዲራችን "'ሲል ያመሸውን የቴዲ አፋሮ የፕላቲኒየም ስፖንሰር ከቦሌ ቡልቡላ እሰከ ኮዬ ፈጨ ያለውን መሬት ያለ ጨረታ የተሰጠው' ኦቪድ ሪል እስቴት' ነው።
ያለውጤት ተጠናቋል
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በቱርክ አንካራ ዛሬ ሰኔ 24/2016 ያደረጉት ውይይት ያለምንም ውጤት ተጠናቋል፣እ/ኤ/አ መስከረም 2/2024 እንደገና ለመገናኘት በቀጠሮ መለያየታቸውን የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳን ( Hakan Fidan) ገልጸዋል።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከተማው ፅዱ መሆኑ ብቻ በቂ አይደለም ማህበረሰቡ መሰልጠን ቆሻሻን ማፅዳት የራስን እና የአካባቢን ፅዳት መጠበቅን ይጨምራል።
2025/07/07 12:13:05
Back to Top
HTML Embed Code: