Telegram Web Link
#Alert

ከትናትን ጀምሮ በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አበዶንጎሮ ወረዳ ጫአይ እና ቦቶሮ ቦራ በተበሉ ቀበሌ የአማራ ፋኖ ጦርነት የከፈቱ ሲሆን በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት አድርሰዋል ።

በከፈቱት ጦርነት ለጊዜው አቶ ተሾመ ጃሉ አቶ ግዛው ጋልዳሳ እና አቶ ሽብሩ ቶሎሳ የተባሉ 3 ሰዎች ሕይወታቸው ያለፈ ሲሆን ፤ 4 የቀበሌ ሚሊሻዎችም ሕይወታቸው አልፋል።
ኤጂታ ነገሪ ይባላል፡፡አስታወሳችሁት!
ትዝ ይላችሁ እንደሁ በኛ ዘመን ትምህርት በራዲዮ የሚባል ነገር ነበር፡፡እንግሊዝኛ፣ሳይንስ፣አማርኛን የመሰሉ ትምህርቶች ከመደበኛው አስተማሪ በተጨመረ ከኢትዮጵያ የትምህርት መገናኛዎች ኤጀንሲ -Ethiopian Educational media Agency የሚተላላፍ የራዲዮ ፕሮግራም ነበራቸው፡፡
መምህሮቻችን ራዲዮ ተሸክመው ክፍሎቻችን ድረስ በመምጣት የሚተላለፈውን ትምህርት ያስደምጡን ነበር፡፡ከአፍ የማይጠፉ ውብ መዝሙሮችን አብሮ መዘመር፣ደግ ድምጽ ያላቸው የራዲዮ መምህራን ጥያቄን ተሸቀዳድሞ መመለስ ፣ትምህርታዊ ጭውውቶችን አፍ ከፍቶ ማዳመጥ-ግብሮቻችን ትዝታዎቻችን ነበሩ-ግሩም ጊዜ አሳልፈናል፡፡
ከአብዛኞቹ የራዲዮ ፕሮግራሞች መጀመሪያ እና ማብቂያ ላይ የፕሮግራሙ አዘጋጆች ስም ይነገር ነበር፡፡እጄታ ነገሪ በተደጋጋሚ እሰማው የነበረ ስም ነው፡፡
The Ethiopian Educational Media agency presents
English for grade 4,
Lesson 10- Showing direction
Produced by: Ejeta Negeri
እጄታ ነገሪ በልጅነቴ የሰመኃቸውን አብዛኞቹን ውብ የራዲዮ ትምህርቶች በበላይነት ሲቆጣጠር የነበረ ባለሙያ ነው፡፡አድጌ ሁሉ ስለ ልጅነት የትምህርት ዘመኔ ሳስብ እኒያ ጣፋጭ የራዲዮ ጊዜያት ይታሰቡኛል አብሮ ደግሞ የእጄታ ስም፡፡እኔ ብቻ ሳይሆን በርካታ የዘመን ተጋሪ ኢትዮጵያዊያን ይሄ ስም የሚተወሳቸው ይመስለኛል፡፡
እጄታ ያኔ ፕሮግራሞቹን ማቀናበሩ እንጂ በስንቶቻችን ጭንቅላት ውስጥ ለውጥ እና አይረሴ ትዝታ እንደተወ አያውቅ ይሆናል፡፡እኛ ግን አደግን-የትናንት ጨቅሎች በሀገሪቱ በመላ እንደ በዓል ፈንድሻ ተበተንን-እሱእኒያን ፕሮግራሞች ስለመስራቱ እረስቶ ይሆናል፡፡እኛ ግን ውለታውን አንረሳም፡፡

እናም ይሄን ሰው በመልክ ለማወቅ ወስኜ በኢንተርኔት ላይ አሰስኩት፡፡አገኘሁት፡፡እጄታ ዛሬ በትምህርት ሚኒስትር ውስጥ እንደሚሰራ ከማህደሩ አየሁ፡፡የፌስቡክ ወዳጆቹ ሁለት ፍሬ ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡የእውኑ አለም ወዳጆቹ እና አመስጋኞቹ ግን ብዙ ሺዎች ነን፡፡

ለምናውቅህ ግን ለማታውቀን እጄታ ነገሪ ስለ አበርክቶትህ እናመሰግናለን ፡፡ራዲዮ በተሰኘው አስማት ስላዳረስከን ብርሃን እናመሰግናለን፡፡ልጅነታችንን ቀለማም ብላቴናነታችን እጹብ ስላደረከው እናመሰግናለን፡፡

©ሀብታሙ ስዩም
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በዛሬው ምክክር ላይ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን
ለትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን "መንበረ ሰላማ" ተቀራርበን የእንነጋገር ጥሪ በድጋሚ አቅርባለች።
ቤተክርስቲያኒቷ በታሪክ ገጥሟት የማይታወቅ አደጋ ገጥሟታልና ቤተክርስቲያኗን እናድን የሚል ተማፅኖ አዘል መልዕክት ልከዋል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ፈተናዎቹን ለመሻገር ከፈለገች.

1. የኦሮሞን መሬት ታቦት ወረደ በሚል መውረር መዝረፍ ማቆም

2 . ማህበረ ቅዱሳንን ማፍረስ

3. እነ ዘመድኩን በቀለ እነ አባይ ነህ ካሴ እነ ቀሲስ ኤፍሬም እነ ዳቆን ሃብታሙ አያሌው እነ ፍንታሁን ዋቄ እነ አቡነ ሉቃስ የመሳሱሉትን ከየትኛውም አውደ ምህረት እና ደብሮች ላይ በኦርቶዶክስ ሥም እንዳይሰብኩ ማገድ እስካሁን በኦርቶዶክስ ሥም ለሰሩት ወንጀል ተጠያቂ ማድረግ

4 ሁሉም ብሄሮች የራሳቸው ቤተ ክህነት እንዲመሰርቱ መፍቀድ

5 በሁሉም ቋንቋዎች ሃይማኖታዊ ተልኮዎችን መፈፀም
ልዩ መረጃ‼️

እስክንድር ነጋ ከመንግስት ሰዎች የሰላም ድርድር ሂደት መጀመሩ ታውቋል

  እስክንድር ነጋ የፋኖ ታጣቂዎችን ወክሎ ከመንግስት ድርድር መጀመሩ ተገልጿል። በ3ኛ ወገን አመቻችነት እስክንድር ነጋ ከመንግስት ሰዎች ጋር ቀጥተኛ ያልሆነ የድርድር ሂደት መጀመሩ ተጠቁሟል።
የአቡነ ሉቃስ እርግማንና ንግግር ቤ/ያንንና ሲኖዶስን አይወክልም አትግደል የሚለውን ሕግ ሽረዋልና አባ ሉቃስ መንግስትን ይቅርታ ይጠይቁ ሲል ቅ/ሲኖዶስ ዛሬ ወሰኔ አስተላልፋል።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ትምክትና ቀረርቶ ወንዝ አያሻግርም የአማራን ህዝብ መከራ ከማራዘም ውጪ ከገዳም እና ከቁጥቋጦ ወጥታቹ ወረዳ መቆጣጠር አትችሉም ተደራድረህ የተስጠህን ተቀብለህ ስላማዊ ኑሮህን ኑር
"የሁለት አንጋፋ ፖለቲከኞች ዕይታ በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጥረት ዙሪያ !!"
አቶ ሌንጮ ለታ እና ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና
=======================
.
በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ 50 ዓመታትን ያሳለፉት ጎምቱው የፖለቲካ ሰው አቶ ሌንጮ “ኢትዮጵያ አሁን የተጋፈጠቻቸው ችግሮች ካለፉት ሥርዓቶች ተገፍተው የመጡ ናቸው” ይላሉ።

“ከ50 ዓመት በፊት እኛ ትግል ስንጀምር ኢትዮጵያ የአንድ ብሔር፣ የአንድ ባሕል እና የአንድ ቋንቋ ናት ተብሎ ይሰበክ ነበር። እኛም በዚያ ሰዓት አይሆንም ኢትዮጵያ ኢምፓየር ናት። ከዚህ ውስጥ ወጥተን መብታችንን ማስከበር አለብን ብለን ወደ ትግል ገባን” በማለት አንዴት ወደ ትግል እንደገቡ ያስታውሳሉ።

ከ1983 ዓ.ም. በኋላ ግን አገሪቱ ብዙ ብሔሮች የሚኖሩባት አገር ስለሆነች፣ ሕዝቦች በአብሮነት መኖር የሚያስችል “ብዙ ብሔረሰቦችን መብት የሚያጎናጽፍ ፌዴሬሽን ተመሠረተ፤ ይህም አንድ እርምጃ ነበር” ይላሉ አቶ ሌንጮ።

አንጋፋው ፖለቲከኛ አቶ ሌንጮ ብዝኀነት ያለው ፌዴሬሽን መመሥረቱ አንድ እርምጃ ቢሆንም ፌዴሬሽኑ እንደተፈለገው ዲሞክራሲያዊ አለመሆኑ አሁን አገሪቱ ለገጠማት ችግር መነሻ ነው ብለው ያምናሉ።

አቶ ሌንጮ አሁን ለብሔራዊ ምክክር የተቋቋመው ኮሚሽን ውስጥ በአማካሪ ኮሚቴነት ከሚሰሩት ውስጥ መካከል አንዱ ናቸው።

“በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ አንድ ምርጫ ብቻ ነው ያላት። እርሱም ብዝኀነት ያለውን ፌዴሬሽን ዲሞክራሲያዊ ማድረግ ነው። ይህ ካልሆነ ግን የአገሪቱ ሥርዓት ይወድቃል የሚል ስጋት አለኝ።

“ሥርዓት ሲፈርስ ደግሞ ጎረቤታችን ሶማሊያን አይተናል። አንድ ቋንቋ፣ አንድ ባሕል፣ እምነት ያለው ሕዝብ ካለፉት 30 ዓመት በኋላ መልሶ አገሪቱን ለመገንባት አልቻለም” በማለት ያላቸውን ስጋት ያብራራሉ።

አክለውም ኢትዮጵያ የመፍረስ አደጋ ገጠማት ማለት ደግሞ ይህችን አገር መልሶ ለመገንባት እንደ ቀላል የሚታይ ጉዳይ ነው ብዬ አላስብም” ይላሉ።

አቶ ሌንጮ ለታ በሀገሪቱ ውስጥ የሚታዩ ችግሮችን ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ መፍትሔ ለመፈለግ ብሔራዊ ምክክሩ ወሳኝ አማራጭ እንደሆነና ይህንኑም እንደሚደግፉ ይናገራሉ።

ይህ ምክክር እንዲሳካ ደግሞ የኦሮሞ ሕዝብ ከሁሉ በላይ ኃላፊነቱን መወጣት አለበት ሲሉ ጥሪያቸውን ያቀርባሉ።

“ይህ የብሔራዊ ምክክር ስኬታማ ሆኖ በአገሪቱ እውነተኛ ዲሞክራሲ እንዲስፋፋ ኦሮሞ ኃላፊነት አለበት። የኃላፊነት ስሜትም ሊሰማው ይገባል። እንደከዚህ ቀደሙ ከሌሎች አካላት መጠበቅ የለበትም” ይላሉ።

ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና

የኦሮሞ ኮንግረስ ፌደራሊስት (ኦፌኮ) ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑት ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ደግሞ የብሔራዊ ምክክሩ ፓርቲያቸው ለብዙ ዓመታት ሲጠይቅ የነበረው ጉዳይ መሆኑን ያስታውሳሉ።

ቢሆንም እንኳ ኮሚሽኑ አሁን በተዋቀረበት አካሄድ አገሪቱ ያለችበትን ችግር ይፈታል የሚል እምነት እንደሌላቸው ይገልጻሉ።

“አሁን የብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን የሚባለው ምንም ነገር መሬት ሳያስይዝ የሞተ ነው። ይህ ኮሚሽንም ለአንድ ዓመት፣ ለሁለት ዓመት ቴአትር ተጫውቶ የሚያልፍ እንጂ ትልቅ ነገር የሚያመጣ አይደለም” የሚል እምነት አላቸው።

የተቋቋመው የብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን ከመንግሥት ወገን ብቻ የተቋቋመ በመሆኑ ችግሮችን ይፈታል የሚል እምነት እንደሌላቸው ሲገልጹ መቆየታቸውን ያወሳሉ።

“በእንዲህ ዓይነት ጉዳይ ላይ ሁሉም አካል ነበር መሳተፍ የነበረበት። ይህም ሲባል የመንግስት አካላትና ተቃዋሚዎች ጭምር ማለት ነው። ሽምግልና ከሁለቱም ወገን ነው አንጂ ከአንዱ ወገን ብቻ አይደለም የሚሆነው። መንግሥት ኮሚሸኑን ይህንን ጊዜ ለማለፍ ነው ያቋቋመው። አንድ ተጫዋች ነው የራሱን ፍላጎት ለማሳካት ያቋቋመው” ሲሉ ይከስሳሉ ፕሮፌሰር መረራ።

በማስከተልም ይህ ኮሚሽን ከተቋቋመ በኋላ ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ፣ አንድም ተጨባጭ ሥራ ያላሳካ “መንግሥት ጊዜ ሊገዛበት ብቻ ያቋቋመው ነው” በማለት ይተቹታል።

አቶ ሌንጮ ለታ ግን አሁን የታሰብው የብሔራዊ ምክክር ለዚህች አገር መፍትሔ ሊያመጣ እንደሚችል ተስፋ አላቸው።

ተስፋቸው እውን እንዲሆን ግን የሕዝቦች ተሳትፎ እና አንድነት በጣም አስፈላጊ ነው ባይ ናቸው።
--
BBC News Amharic
.
.
.
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ትክክል ነህ ከዚህ በኃላ ወጣቱ መታገል ያለበት ድህነት እና ኃላ ቀርነት ብቻ ነው
♦️"ኦነግና ኦፌኮ ተጋብዘዋል"
የኦሮሚያ ፖለቲካ ፓርቲዎች ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን ታፈሰ
----
አቶ ሰለሞን በጋራ ድህረገፅና ዋትስአፕ ከመለቀቁም በላይ እኔም በግሌ አነጋግሬያለሁ፣ለምኜያለሁ ብሏል!
#Tikvah #VoAን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው!
---
ተጋብዞ ከመቅረት ግን ሄዶ ያለውን ችግር ማንሳት ይሻል ነበር። ባይሆን ለሚዲያ ክፍት ይሁን ብሎ ጫና ፈጥሮ አካፋን አካፋ ብሎ ህዝብ እንዲሰማ ማድረግ ነው እንጂ የምን መሸሽ? በክልል ደረጃ የሚደረገውን ውይይት በየትኛውም መልኩ (at any cost) ተሳትፎ የህዝብን የመከራ ጊዜ ማሳጠር ያስፈልጋል። "ችግር አለ" የሚለውን ሁሉም ወገን ተቀብሎታል። የቀረው የችግሩን አይነት፣ ደረጃ፣ ምንጫ/መነሻ ለይቶ የመፍትሄ አቅጣጫ ማስቀመጥ ነው። ጣትን ወደሌላው ወገን መጠቆምና ራስን ነፃ አድርጎ ማየት ለህዝቡ አንዳች ፋይዳ የለውም። አንዴ ወደ ፖለቲካው ጨዋታ ከተገባ በኋላ ገለልተኛም፣ነፃም መሆንም አይቻልም!
ካልሆነ ደግሞ፣በቃ የፖለቲካ ምህዳሩ ለተቃውሞ አይመችም ብሎ ጠቅልሎ ከጨዋታው መውጣት ይሻላል።
-----
መነጋገር ደግሞ ፊትለፊት፣አይን ለአይን እየተያዩ ነው። ፖለቲከኞች ይተፋፈራሉ እንዴ? አይደለም፣ከአንድ ህዝብ የወጡ ፖለቲከኞች፣ ሀገር እንኳን የማይጋሩ፣እንደ ቋሚ ጠላት የሚተያዩ ራሱ እየተያዩ ይነጋገራሉ እኮ!
---
በተለይ እስከመቼ ነው የኦሮሚያ ፖለቲከኞች "በስማበለው/Third Person or Media" በኩል መልስ የሚሰጣጡት? ገዳን የሚሰብክ የፖለቲካ ማህበረሰብ እንደ ቤተሰብ ተሰባስቦ መወቃቀስ ካልቻለ ስለ ገዳ ባያነሳ ይመረጣል።
---
ኮከሱ(😉) መፍቀድ ካለበትም ኮከሱን አስፈቅዶ በክልል ደረጃ የሚደረገው ውይይት ላይ መሳተፍ አስፈላጊ ነው ብዬ አምናለሁ።
---
🙏(Worku Bedada waktola)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ልደቱ አያሌው ስሞኑን የሽግግር መንግሥት ይመስረት እያለ State Department ተንበርክኮ እየለመነ እንደሆነ ይታወቃል ከ DC በአውሮፕላን መጥቶ ለመጀመርያም ለመጨረሻም ሥልጣን ያገኘው ብርሃኑ ነጋ ብቻ ነው ልደቱ አሁን ሙድ መያዣ ሄኗል
2024/09/22 12:18:23
Back to Top
HTML Embed Code: