Telegram Web Link
ለመላው የኦሮሞ ኦርቶዶክስ ሲኖዶስ መንበረ ጴጥሮስ ተከታዮች እና የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በዓል አደረሳቹ ።
Forwarded from Gumaa Saaqqataa (Gumaa Saaqataa)
ምን የሚሉት ነውር ነው ይህንን ልጅ ማሰር??

ከሀረርጌ በድርቅ ተፈናቅለው
ወደ ፊንፍኔ የመጡ ወገኖቻችንን እያናገረ እያለ ፖሊስ መጥቶ ማሰሩ ሳያንሰ
"የኦነግ ሸኔ አባል" .. የሚል ክስ መስርተው ዛሬ ፍርድ ቤት አቅርበውታል። ለተጨማሪ ምርመራ የቀን ቀጠሮ ፍርድ ቤቱ ሰጥቷቸዋል።

ስለእነዚያ ምስኪኖች ግዴታ የነበረበት ህዝብን አስተዳድራለሁ የሚለው መንግስት ነበር ። ሚበሉትን አጠተው ሜዳ ላይ የረገፉ ወገኖቹን መርዳት "ኦነግ ሸኔ" ያስብላል?
ነውረኞች‼️
Forwarded from Hanan Federalist (Han Fed)
ከውጭ ሆኖ የሚንጠን ማነው
~~~~~
በአንድ እቃ ውስጥ 100 ጥቁር ጉንዳኖች እና 100 ቀይ ጉንዳኖችን አስገብተን ብናስቀምጣቸው አይነካኩም:: ነገር ግን እቃውን አጥብቀን ብናወዛውዘው ወይም ብንንጠው ጉንዳኖቹ የቀለማቸው እየለዩ መገዳደል ይጀምራሉ። ቀይ ጉንዳኖች ጥቁር ጉንዳኖችን እንደ ጠላቶች ቆጥረው መግደል ይጀምራሉ::

በተመሳሳይም ጥቁር ጉንዳኖች ቀይ ጉንዳኖችን እንደ ጠላቶቻቸው ቆጥረው ይገድላሉ:: ነገር ግን የሁለቱም እውነተኛ ጠላት ያሉበትን እቃ (ጠርሙስ/ፕላስቲክ) የሚንጠው (ውጫዊ) ሦስተኛ ወገን ነው።

ኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ በሌሎች አገራት ያለው የግጭት/የመገዳደል እውነታም ከዚህ የተለየ አይደለም:: ከግጭቱ ውጭ ሆኖ የሚንጥ ሦስተኛ ወገን አለ:: ስለሆነም ብሄር እና ቀለም እየለየን ከመጠቃቃታችን/ከመገዳደላችን በፊት ከውጭ ሆኖ የሚያናውጠን/የሚበጠብጠን/የሚንጠን . . . ማነው ብለን ራሳችንን መጠየቅና መለሽ መፈለግ ይጠበቅብናል:: ማን እንደሆነ ማሰብ አለብን!
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ከልካይ የላቹ የገበሬውን መሬት ስበብ እያፈለጋቹ ዝረፉት
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ታቦቱን አቁመው ሬጌውን አቅልጠውታል
በችግሮቹ ዙሪያ ጥናት አስገብቼ ነበር!

-አማርኛ አወላገድክ ተብሎ ከቅጥር ውጭ ይደረጋል!
-በበረራ ወቅት ገዢው ፓርቲ ያፀደቃቸው 5ቱ ቋንቋዎች እንኳን ስራ ላይ አልዋሉም!
-ሀገረህይወትን ህገመንግስቱ አያውቀውም!
♦️
የኔ ጥያቄ ፖለቲካዊ አይደለም፥ፍትሃዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት እንጂ! ይሄ ብሔር ይጠቀም፣ያ ብሔር ይጠቀም የሚልም አይደለም። ጭብጡ ሁሉም ኢትዮጵያዊ እኩል የሚጠቀምበት ተቋም ይሁን ነው።
ለዚህም በማከተሉት ርዕሶች ላይ ጥናት አድርጌ አስገብቼያለሁ!
1) ቅጥር ላይ ያለው ችግር ነው። የአየር መንገዱ የስራ ቋንቋ እንግሊዝኛ ነው። ስራ ፈላጊ ከሁሉም አቅጣጫ ተሰልፎ ይመዘገባል፣ ግን ችሎታ ያለው ሁሉ በፍትሃዊነት ከብሔር-ብሔረሰብ አይቀጠርም። ረብ-የለሽ ሰበብ ተፈልጎ እንዳይቀጠር ይደረጋል። ለምሳሌ ቃለ-መጠይቅ ላይ አማርኛ አወላገድክ-አኮላተፍክ ተብሎ ብቻ ከስራ ውጭ ይደረጋል! አማርኛ ግን የቅጥር መስፈርቱ ውስጥ የለም።
2) የሆቴሎች፥የኤርፖርቶችና የአውርፕላኖች ስያሜ ነው። ይሄም ሁሉንም ክልልና ብሔር ብሔረሰብ እኩል የሚያስተናግድ መሆን አለበት። አሁን ግን እንደዚያ አይደለም! ለምሳሌ ኦሮሚያን ይወክላሉ ተብለው የወጡ ሶስት ስሞች ነበሩ-ባሌ ተራራ- ኒያላ-አበበ ቢቂላ ናቸው። እኔ ሁሉንም ክልሎች የሚወክሉትን አስገብቼ ነበር።
3)የማፕ ችግር ነው። ናዝሬት፣ግዮን፣ደብረዘይት፣ሀገረህይወት የሚባል ኦፊሴላዊ ቦታ የለም። አስገራሚው ነገር ጊዮንና ሀገረህይወት የት እንደሆኑ በእውነት አላውቅም። ጠያይቄ ለወሊሶና አምቦ ድሮ የተሰጡ ስሞች እንደነበሩ መሆኑን ሰማሁ! ይሄንን ለማስተካከል ፍላጎት የለም!
4) በበረራ ወቅት የደህንነት መረጃዎች የሚሰጡበት ቋንቋዎች ናቸው። አማርኛና እንግሊዝኛ አሉ። እነርሱ ላይ እንደ ተሳፋሪው የቋንቋ ችሎታ ተጨማሪ ቋንቋ ቢጨመርበት ችግር የለውም። ለምሳሌ ወደ ፈረንሳይ በረራ ሲደረግ ሶስተኛው ቋንቋ ፈረንሳይኛ ይሆናል። ለሀገር ውስጥ በረራ...ወደ ትግራይ ትግርኛ፣ወደ ጅጅጋ ሶማሊኛ፣ወደ ሌሎችም እንዲሁ ቢደረግ ምናለበት። በአንድ ወቅት ወደ ድሬዳዋ ስንበር አጠገቤ የተቀመጡ ሽማግሌ አፋን ኦሮሞና ሶማሊኛ ብቻ ይሰሙ ነበር። የደህንነት መረጃውን አልሰሙም ማለት ነው! ሌላው ቀርቶ መንግስት የገዢው ፓርቲ የስራ ቋንቋ ብሎ ያወጣቸውን አምስቱን ቋንቋዎች እንኳን ስራ ላይ በማዋል ብንጀምርስ የሚል ጥያቄ አለኝ!
5)እንደ ደምቡ በበረራ ወቅት የምትፈልገውን ሙዚቃና ፊልም መርጠህ ታዳምጣለህ፣ ታያለህ። ለምሳሌ የአፋን ኦሮሞ ሙዚቃ ከአሊ ቢራና በጣት ከሚቆጠሩ ውጭ የለም። ፊልም ከነ አካቴው የለም። የሌሎች ብሔር ብሔረሰቦችም እንደዚያው! ለምን?
6) የአስተናጋጆች (ሆስቴሶች) የአለባበስ ስርዓት ነው። በቢዝነስ ክላስ በቋሚነት የሚለበሰው በተለምዶ የሐበሻ ልብስ የሚባለው ነው። ይሄ ልብስ ሁሉንም ብሔር ብሔረሰብ የሚወክል አይደለም። የሌሎች ለምን አይለበስም? ይህ value ይጨምራል፣ቱሪዝምን ያበረታታል እንጂ አይቀንስም!
---
ከላይም እንደጠቀስኩት የኔ ጥያቄ የፍትሃዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ነው። የትኛውም ብሔር የበላይ ወይንም የበታች ይሁን የሚል አቋም የለኝም። በእኩልነት ይጠቀሙ ነው። ተቋሙም ኢትዮጵያን ይምሰል ነው! ጥናቱንም ለሁሉም ኃላፊዎች አስገብቼያለሁ
የመንግስት አቅጣጫም ይሄ እንደሆነ አውቃለሁ።አፈፃፀም ላይ ግን ክፍተት አለ። ችግሩ ገና አልተነካም። ቅጥርን እንኳን ብናነሳ ከድሮው የተለወጠ ነገር የለም!
------
ኢንጅነር ተሊላ ዴሬሳ ጉተማ
🙏
Forwarded from Addis Standard Amharic
ዜና: #የወልቃይት አካባቢዎችን መከላከያ ሠራዊት እንደተቆጣጠረ ነዋሪዎች ገለጹ

በወልቃይት ፀገዴ ሰቲት #ሁመራ ዞን የተወሰኑ አካባቢዎች ባለፈው ዓርብ ሚያዝያ 25 ቀን 2016 ዓ.ም በመከላከያ ሠራዊትና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ግጭት ተከስቶ እንደነበር፣ ይህንንም ተከትሎ መከላከያ ሠራዊት አካባቢዎቹን በአሁኑ ወቅት ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን ነዋሪዎች ገለጹ።

በአካባቢው የመከላከያ ሠራዊት እንዳልነበርና የአካባቢው ሚሊሻና ፖሊስ ፀጥታውን ሲቆጣጠሩ እንደነበር ነዋሪዎች መግለጻቸውን ሪፖርተር ዘግቧል።

ከእሑድ ሚያዝያ 20 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ የሰላም መደፍረሶች እንደነበሩ አንድ የአካባቢው የአገር ሽማግሌ እንደገለጹለት ያስነበበው ዘገባው “ሚያዝያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም. ምሽት የፋኖ ታጣቂዎች ‘በጠገዴ ወረዳ’ የምትገኘው ማክሰኞ ገበያ ከተማ ገቡ፤ ሚያዝያ 25 ቀን 2016 ዓ.ም. ንጋት ላይ ከከተማው የወጡ ሲሆን፣ ከከተማው ብዙም በማይርቅ ቦታ ላይ በመከላከያ ሠራዊትና በታጣቂዎቹ መካከል ግጭት መፈጠሩን ሰማን” ማለታቸውን አስታውቋል።

በነዋሪዎች ሕይወትም ሆነ ንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን የአገር ሽማግሌው እንደገለጹለት ያስነበበው ሪፖርተር አሁን ላይ ግጭቱ መብረዱንና አካባቢዎቹንም መከላከያ ሠራዊት መቆጣጠሩን ገልጸዋል ብሏል።

የፋኖ ታጣቂዎች ወደ ከተማው ሲገቡ ከተማውን የመቆጣጠር እንቅስቃሴ የሚመስል ድርጊት አለመመልከታቸውን የአገር ሽማግሌው ገልጸዋል ያለው ዘገባው በነዋሪዎቹም ሆነ በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን ተናግረዋል ብሏል።

ሆኖም ከከተማ ወጣ ብሎ በሚገኝ ሥፍራ በመከላከያ ሠራዊትና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ሚያዝያ 25 ቀን ግጭት ተከስቶ እንደነበር መግለጻቸውን አመላክቷል።

በአሁኑ ጊዜ አካባቢዎቹን የመከላከያ ሠራዊት መቆጣጠሩንና ግጭቱም መብረዱን አስረድተዋል ብሏል
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ይሄ ዛሬ በወለጋ ነቀምቴ ነው ተብሏል እንግዴ ይሄንን ሁሉ ህዝብ አበል ተከፍሎት ነው ማለት አንችልም የኦሮሞ ህዝብ ፍላጎት በኦሮሞ ፖለቲካ ሃይሎች እርቅ ፣አንድነት ፣ ሰላም እንዲመጣ ያለውን ፅኑ ፍላጎት የሚያሳይ ይመስለኛል

ከጦርነት አትራፊዎች ሌላ ሥራ በጊዜ መፈለግ ሳይሻል አይቀርም።
ህውሃትን አለማድነቅ አይቻልም !!

ህውሀት በአንድ በኩል ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉትን ታጣቂዎች በሱዳን በኩል ታስታጥቃለሽ በሌላ በኩል በፕሪቶርያ ስምምነት ፌዴራል መንግሥቱን እጅ ጠምዝዛ የፈለገችውን ታስፈፅማለች በዚህ ስምምነት አንዱ ህወሃት ባለፉት 27 ዓመታት ከኦሮሞ ህዝብ እና ከደቡብ ህዝብ ስብስባ ያፈራችው ሀብት ንብረት እንዲመለስ ነበረ እሱም እንዲመለስ አድርገዋል

ፊንፊኔ እና ፊንፊኔ ዙርያ በሳይለት ጆኖሳይድ እንዲጠፋ የተደረገው ኦሮሞ ፍትህ ሳያገኝ መሬቱም በሌሎች ተወሮ ቀርቷል የወለጋ እና ጉጂ ወርቅ እና ቡናቸው የሃረርጌ ጫት የቦረና እጣን የኢሉ የጅማ ሀብት ያለ ፍትህ ተበልቶ ቀርቧል ማለት ነው
ህውሃት መቀሌ ቁጭ ብላ ከሁሉም ጋር እየሰራች ጥቅሟን እያስከበረች ነው የኦሮሞ የፖለቲካ ሃይሎች ለስልጣን እየተገዳደሉ ነው. የኦሮሞ አክቲቪስቶች አማራን ለማናደድ ወልቃይታ ለትግራይ ሊመለስ ነው ብለው እንደ አርጋው በዳሶ በጭንቅላታቸው እየጨፈሩ ነው
አማራው በኦሮሞ ጥላቻ ናውዞ በየሶሻል ሚዲያው የኦሮሞን ህዝብ ሲሳደብ ይውላል
የአማራ አክቲቪስቶች በትግል ሥም ከህዝብ በስበስቡት ገንዘብ ሀብት ንብረት በውጪ እየገዙ ነው
ለማንኛውም ስላም ለሀገራችን !!
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ፖለቲከኞቻችን ትግል ላይ ናቸው !!
በሰሜን ጎንደር 6 ወረዳዎችና 83 ቀበሌዎች ለተከታታይ አመትታ ዝናብ ባለመዝነቡ ድርቁ በካድሬው ተደብቆ ወደ ረሃብ አድጎ አዛውንትና ሕፃናት ወላድ እመጫቶች አቅመ-ደካሞች፣ አዛውንትና ሕፃናት በረሃብ አለንጋ እየተገረፉ ይገኛሉ።

በአሁኑ ወቅትም በተከሰተው ድርቅና ረሃብ 452 ሺህ ሰዎች ለእለት እርዳታ የተዳረጉ ሲሆን 104 ሺህ የሚሆኑት ህፃናት፣ 14 ሺህ እናቶችና ነብሰጡሮች በጥቅሉ በጃን አሞራ፣ በየዳ እና ጠለምት ወረዳዎች፣ ድርቁ ባስከተለው ጉዳት፣ 56 ሰዎች በረሃብ ህይወታቸዉ ማለፉን ከ72ሺሕ በላይ እንስሳትም ሙተዋል።
ኢትዮጵያ ውስጥ መጥፎ ባህል እንዲፈጠር እና ወንጀል እንዲስፋፋ ሲሰሩ የነበሩ ጋጠወጦች ፖሊስ በቁጥጥር ሥር አውሏል እናመስግናለን 🙏🙏🙏
.
.
.
.
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ይሄ የምታዩት ህዝብ ኤርትራ ውስጥ ከመሰላቹ ተሳስታቹሀል ይሄ ዩጋንዳ ካምፖላ ከኢሳያስ አፍወርቂ ሸሽተው ጥገኝነት ሚጠይቁ ናቸው ኢትዮጵያ ውስጥ የሚደረጉት ጦርነቶች በድርድር ተቋጭቶ ወደ ሰላም ካልመጣን የኢትዮጵያ ህዝብ እጣ ፈንታ ይሄ ነው የሚሆነው
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ወያኔ አዝሎ አራት ኪሎ ያደርሰኛል ከምትለው ጋር ሁሉ ትዳራለች
እናንተ ባትኖሩ በምን እንስቅ ነበረ ?
Forwarded from Gumaa Saaqqataa (Gumaa Saaqataa)
ከማህበረሰቡ ወግና ባህል ፍፁም ተቃራኒ የሆነ ሐሰተኛ እና አፀያፊ የፈጠራ ታሪክ እያሰራጩ ህዝብን የሚያደናግሩ ዩቲዩበሮችን በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ሃሰተኛ መረጃ እና ከማህበረሰቡ መልካም ባህልና ወግ የተቃረኑ አፀያፊ የፈጠራ ታሪኮችን በማህበራዊ ሚዲያ እያሰራጩ በህዝብ ላይ ውዥንብር እና መደናገርን የሚፈጥሩ ግለሰቦች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል፡፡

ማህበራዊ ሚዲያን ገንዘብ ለማግኘት ሲሉ ብቻ ከእውነት የራቁ መሰረተ ቢስ የፈጠራ አፀያፊ ወሬዎችን እየፈበረኩ በማሰራጨት የህዝብን ደህንነት ስጋት ላይ ሲጥሉ ከነበሩ ዩትዩበሮች መካከል በፊንፍኔ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 አማረ እና ቤተሰቦቹ በተባለ ህንፃ ላይ ቢሮ ተከራይተው የተለያዩ የዩቲዩብ ገፆችን በመክፈት የማህበረሰቡን ሥነ ልቦና የሚጎዱ የፈጠራ ታሪክ በማሰራጨት የተጠረጠሩ ስድስት ግለሰቦች በህዝብ ጥቆማ እና ፖሊስ ባደረገው ክትትል ተይዘው በየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ምርመራ እየተጣራ ይገኛል፡፡
በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል መቅደስ መብራት መኮንን የተባለችው ግለሰብ ሮሄ፣ ልዩነት፣ ጣዕም፣ አዲስ አለም፣ ዘይቤ፣ ህይወት፣ እይታ፣ እና ዩኒት ህይወት የተባሉ የዩቲዩብ ገፆችን በመክፈት በስራ አስኪያጅነት ስትመራ የነበረች ናት ተብሏል፡፡

ብሩክ ወርቅነህ ጌታሰው የተባለ ግለሰብ ደግሞ ገፆቹን በምክትል ስራ አስኪያጅነት እና በአስተባባሪነት ሲመራ የነበረ ሲሆን ናትናኤል አበራ በቀለ፣ እየሩሳሌም አስማረ ምህረት እና ምህረት ያሲን ቲጋ የተባሉት ግለሰቦች ደግሞ በፕሮግራም አቅራቢነት እንዲሁም ናትናኤል ዮሃንስ አሸነፍ በካሜራ ባለሙያነት ሲሰሩ የነበሩ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
2024/09/25 07:24:15
Back to Top
HTML Embed Code: