Telegram Web Link
ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን ሮባ ቀዌሳ የሸዋ ኦሮሞ ለዘመናት ከነበረበት ቄዬውና ከማሳው ከነበረበት ተደላድሎ በ "ታቦት ወረደ" በ "ጸበል ፈለቀ" ስም ተሸንግሎ፣ ከቄዬው ተፈናቅሎ ሌላው በሱ መሬት ሲተከል የተሰማውን መራር ሀዘን እንዲህ በማለት በጽሁፍ ገልጿል:-
ዜና፡ #በትግራይ ክልል 32 ወረዳዎች ላይ የከፋ ድርቅና የምግብ እጥረት ማጋጠሙን ክልሉ አስታወቀ

በትግራይ ክልል ደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ መካከለኛውና ሰሜን ምዕራብ አካባቢዎች የከፋ የድርቅ አደጋ ያጋጠማቸው መሆኑን የክልሉ ኮሚሽን የቅድመ ማስጠንቀቂያ እና ግብረ መልስ አስተባባሪ አቶ ልጅዓለም ካሕሣይ መናገራቸውን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘግቧል።

በክልሉ የተከሰተው የድርቅ አደጋ በዋነኝነት በጦርነቱ እና ከተፈጥሮ ጋር ተያይዞ የድርቅ አደጋ በመከሰቱ ያጋጠመ መሆኑን አስተባባሪው ገልጸዋል ብሏል።

ክልሉ ያጋጠመው አደጋ ከአቅሙ በላይ እንደሆነ ባሳወቀው መሠረት ርዳታው ለሚያስፈልጋቸው የክልሉ ዜጎች ተደራሽ ለማድረግ ዝግጅቱ መጠናቀቁን #የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ገልጿል ብሏል፡፡

በመጪዎቹ ሦስት ቀናት ለሦስተኛ ዙር የሚሰራጭ ርዳታ መኖሩን ጠቁሟል።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=2919
"Nowar" ስንል እኛ ሰላማው ዜጎች ነን ጦርነት አንፈልግም በሰላም ወጥተን በሰላም መግባት እንፈልጋለንና የምትዋጉ አካላት ቁጭ ብላችሁ ተነጋገሩና ሰላም አውርዱ ማለታችን እንጂ አንደኛውን ደግፈን ሌላኛውን ነቅፈን አይደለም።
Forwarded from informtion 24
ከፍተኛ ሚስጥራዊ መረጃዎች የሚገኙበት ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎች እንደ ልብ የሆኑበትንን ይህንን ገፅ ይከተሉ።

https://www.tg-me.com/information1005
የፊንፊኔ ከተማ አስተዳደር በአንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ውስጥ ከሚኖሩ ዳይሬክተሮች እና ቡድን መሪዎች መካከል ተመሳሳይ የብሔር ማንነት ያላቸው አመራሮች ብዛት ከ40 በመቶ እንዳይበልጥ ሊያደርግ ነው።

የከተማ አስተዳደሩ በቅርቡ ለሚተገብረው የሠራተኞች ድልድል ሲባል ከ14 ሺህ በላይ የከተማ አስተደደሩ ሠራተኞች ነገ አርብ ታኅሣሥ 12/2016 ዓ.ም. ለፈተና እንደሚቀመጡ የአዲስ አበባ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ለቢቢሲ ገልጿል።
https://bbc.in/41vTW6S
በፊንፊኔ ከ1654 በላይ የሻዕቢያ/ህግደፍ ሰላዬች በቁጥጥር ስር ውለዋል መንግሥት ቢዘገይም መልካም ሥራ ጀምሯል

ኢሳያስ አፍ ወርቂን ግፍ ሸሽተው የመጡ ኤርትራዊያን በዚህ ዘመቻ ጥቃት እንዳይደርስባቸው መለየት እና ጥበቃ ሊደረግላቸው ይገባል
መረጃ ‼️

በመከላከያ ሰራዊት አደራዳሪነት በአዴንና በአማራ ክልል ይካሄድ የነበር የሰላም ስምምነት በሰላም ተጠናቀቀ።

በአገው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ(አዴን) እና በ አማራ ክልል መንግስት ሲካሄድ የሰነበተው የሰላም ስምምነት በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አደራዳሪነት አደራዳሪነት ሊጠናቀቅ የቻለው አዴን ያቀረባቸው ፍትሃዊ የአገው ህዝብ ጥያዌዎች ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት አግኝተው ውይይት ተካሂዶባቸው ምላሽ የሚሰጣቸው ህጋዊ አግባብ የተግባር ስራ ለመሥራት የተወሰነ በመሆኑ በዛሬው እለት ታህሳስ 13/20016ዓ.ም በሙሉ መተማመን ተፈራርመዋል።

ዋና ዋናዎቹ፦
1)የአገው ህዝብ የራስ አስተዳደር ጥያቄ እንዲመለስ
2)አዴን በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በህጋዊ መንገድ ተመዝግቦ በፓርቲነት በሰላማዊ መንገድ እንዲታገል
3)የአገው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ሰራዊት ተሃድሶ ተሰጦት ትጥቅ በመፍታት መንግስት በሚያስቀምጠው አቅጣጫ እንዲካተት

ተራ ቁጥር ሶስት ወይንም ትጥቅ መፍታት፣ተሃድሶና ውህደት የሚከናወነው በተራ ቁጥር አንድና ሁለት የተጠቀሱት ስምምነቶች ተፈፃሚ ከሆኑ በኋላ ነው።

የአገው ዴሞክራሲ ንቅናቄ (አዴን )የአገውን ህዝብ ጥያቄ በትጥቅ ትግል ለማስመለስ በማለም ወደ በረሃ የወረደ እና በርካታ ሰራዊት በስሩ ያሉት መሆኑንም ምንጮቻችን ገልፀውልናል።
አ ገ ው ብ ሔ ራ ዊ ክ ል ላ ዊ መ ን ግ ስ ት
© Melesse Engida
#Oduu_Gamachiisaa.

Ijaarsi siidaa Mootii #Kumsaa_Morodaa magaalaa Naqamteetti eegalame.

Ijaarsi siidaa mooticha Kumsaa Morodaa birrii miiliyoona 23 oliin magaalaa #Naqamtee ijaaramuu eegaluu bulchiinsi magaalichaa beeksise.
Akka odeeffannoo bulchiinsa magaalichaatti, siidaan kun magaalaa #Naqamtee iddoo marfata 1ffaa jedhamutti birrii miliyoona 23.78'n magaala Naqamteetti ijaarama. .
Siidaan kun kan ijaaramu gaaffii jiraattota magaalaa Naqamteefi uummata godinaalee Wallaggaa baroota dheeraaf gaafataa turan deebisuu yaadamee ta’uu himameera.

Sirna jalqabsiisuu ijaarsa siidaa kanaarratti Kantiibaan Bulchiinsa Magaalaa Naqamtee, Obbo Misgaanuu Tulluu, Bulchaa Itti aanaa Godina #Wallagga_Bahaa, Obbo Gammadaa Tafarraa, jaarsoliin biyyaafi abbootiin amantaa argamaniiru.
የአማርኛ ታይፕራይተር የፈጠረ ኢንጅነር አያና ብሩ በግንቦት 1939 ዓ/ም በጽሑፍ መኪና ለመጀመሪያ ጊዜ በስነ ጥበብ ሚኒስቴር ተፈቅዶ ጽፎ ታትሞ ያወጣው ይህ ጽሁፍ ነበር። ይህንን የመጀሪያ በጽሁፍ መኪና የታተመውን ጽሁፍ አንቡት። The father of modern Ethiopia Typography ኢንጅነር አያና ብሩ ይባላል ትውልድና እድገቱ በወለጋ ሆሮ ጉድሩ ነው:: በ1930ዎቹ (1932 G.C) የመጀመሪያውን የአማርኛ ታይፕራይተር የፈጠረ ምሁር ነበሩ። ኢንጅነር አያና ኦሊቬቲ ከተባለ የጣሊያን ካምፓኒ ጋር ለ 40 አመታት ያህል ሰርቶ ነው ይህንን የአማርኛ ታይፕራይተር ግኝትን እውን ማድረግ የቻለው።
የኢትዮጵያን ስክሪፕት ለአሁኑ ትውልድ ያስተዋወቀ በመሆኑ የዘመናዊ ታይፖግራፊ አባት (the father of modern Typography) የሚል ስም ተሰጥቶታል።ልጃቸው ኮለኔል አበራ አያና በደርግ ዘመን የአዲስ አበባ ፖሊሰ ዋና አዛዥ የነበሩና በኢትዮጵያ ውስጥ የማረሚያ ቤት ስርዓቶችንና የህግ ታራሚዎችን አያያዝ የቀየሩ ታላቅ ሰው ነበሩ ። ባሻዩ ታላቁ ኢንጅነር አያና ብሩ ተመራምረው የአማርኛ ፊደል ታይፕራይተር ባይፈጥሩ ኑሮ ዛሬ ላይ አዳሜ የአማርኛ ታይፕራይተር ኪቦርድ ላይ ባልፃፍሽ ነበር። የሚያሳዝነው ይህንን በፈጠሩ ታላቅ ሰው ላይ ስንት የዘረኝነት ቅርሻት የሚያቀረሹ አሉ።
ስም ከመቃብር በላይ ነው ክብር ለሚገባው ክብር እንስጥ!
ባላምባራስ ነጋሽ Negash Qemant
አንድም የሀገር ውስጥ ቋንቋ የማያስተምረው ትምህርት ቤት 17 ቅርጫፎች ሙሉ ታገዱ
**
*

በፊንፊኔና አካባቢዋ ከ17 ቅርንጫፎት ከፍቶ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ተማሪዎችን ሲያስተምር የቆየው ጊብሰን ትምህርት ቤት ፍቃዱ መነጠቁንና መታገዱን የአዲስ አበባ ትምህርት ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በፃፈው ደብዳቤ ለማወቅ ተችሏል።

ትምህርት ቤቱ በዋናነት ለዓለም አቀፍ ዜጎችና የዲፕሎማት ማህበረሰብ ትኩረት በማድረግ ሲያስተምር መቆየቱ የሚታወቅ ሲሆን ትናንት በተሰጠው ይፋዊ ደብዳቤ መታገዱን ታውቋል።

የታገደበት ምክንያት ደግሞ የኢትዯጵያ የትምህርት ስርዓት(Curriculum) እንዲከተል ተደጋጋሚ ማስጠንቀቅያ የተሰጠው ቢሆን አለመቀበሉን ባለስልጣኑ በሰጠው ደብዳቤ አስታውቋል።

ጊብሰን ትምህርት ቤት ከKG እስከ መሰናድኦ ያለው የትምህርት አሰጣጥ ሙሉ በሙሉ በእንግሊዘኛ የሚያስተምር ሲሆን ምንም ዓይነት የአገር ውስጥ ቋንቋ የማይሰጥ መሆኑን ለእግዱ መንስኤ ነው ተብሏል።ቀጣይ የተማሪዎቹ እጣ ፈንታ ምን ይሆናል የሚል ጉዳይ የተገለፀ ነገር የለም።
2024/09/27 21:28:39
Back to Top
HTML Embed Code: