Telegram Web Link
ኦሮምያ ውስጥ ለሚደረገው እርስ በእርስ ጦርነት ማንም ጀግና ማንም አሸናፊ ማንም ተሸናፊ የለም ።ነገር ግን ዋጋ እየከፈለ ያለው ንፁኃኑ ብቻ ነው ።

መሶቡን ይዞ ለትሪ መጣላት ሞኝነት በድርድር. በንግግር የማይፈታ ነገር የለም
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የግዜ ጉዳይ ካልሆነ ኣሰብ የኢትዮጵያ መሆኑን ኣይቀርም፣ ያ ካልተደረገ ግን መፈንዳቱ ኣይቀርም
” ጀነራል ፃድቃን!
ኦሮምያ ውስጥ የሁለት ወንድማማቾች ደም አፋሳሽ ጦርነት ቆሞ በድርድር መፍታት አለበት የምለው በመሀል ምስኪኑ ንፁሀን እያለቀ እየተፈናቀለ ስለሆነ ነው ከታች ያለውን የአዲስ ማለዳ ዜና አንብቡት !!


በኦሮሚያ ክልል ግጭት በተቀሰቀሰባቸው አካባቢዎች 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ተፈናቅለዋል ተባለ

በኦሮሚያ ክልል ግጭት በተቀሰቀሰባቸው አካባቢዎች 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች መፈናቀላቸውን ሴንተር ፎር ዴቭሎፕመንት ኤንድ ካፓሲቲ ቢዩልዲንግ (CDCB) አስታወቀ።

ድርጅቱ በክልሉ ስላለው ኹኔታ አስመልክቶ ባወጣው ሪፖርት፤ “በክልሉ እየተካሄደ ያለው ግጭት ካስተለው መፈናቀል በተጨማሪ፤ የሰው ሕይወት ጠፍቷል፣ ንብረት ወድሟል እንዲሁም የልማት እንቅስቃሴዎች ተቀዛቅዘዋል” ያለ ሲሆን፤ የሕዝቡም ማህበራዊ ትስስር መሸርሸሩን ጠቁሟል፡፡

ድርጅቱ አደረኩት ባለው ጥናት መሰረት በአሁኑ ወቅት በኦሮሚያ ክልል 1 ሚሊየን 292 ሺሕ 323 ሰዎች ተፈናቅለዋል ያለ ሲሆን፤ ከእነዚህ ውስጥ 374 ሺሕ 400 ወይንም 29 በመቶ የሚሆኑት ብቻ በመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ገልጿል፡፡

የተቀሩት 71 በመቶ የሚሆኑት ተፈናቃዮች ደግሞ በማህበረሰቡ ውስጥ ተበታትነው እንደሚገኙ አስታውቋል፡፡

ድርጅቱ በዩኤስኤይዲ ትብብር ባዘጋጀው በዚህ ሪፖርት፤ በተለይም በምስራቅ ወለጋ እና ምዕራብ ወለጋ ያለው ኹኔታ እጅግ አሳሳቢ መሆኑን የተገለጸ ሲሆን፤ ከአጠቃላይ ተፈናቃዮች ውስጥ  859 ሺሕ ወይንም 66 በመቶ የሚሆኑት ከኹለት ዞኖች ብቻ የተፈናቀሉ መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

በተጨማሪም በክልሉ ያለው ግጭት በትምህርት ላይ ያመጣውን ተፅዕኖ በዝርዝር ያስቀመጠው ሪፖርቱ፤ በክልሉ 739  ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸውን እንዲሁም ከ210 ሺሕ በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ውጪ መሆናቸውን ገልጿል።

1 ሺሕ 117 መምህራንና የትምህርት ባለሙያዎች ከሥራቸው ገበታቸው ውጪ መሆናቸውንም ጨምሮ አመላክቷል፡፡

በተጨማሪም ድርጅቱ ከክልሉ ጤና ቢሮ አገኘሁት ባለው መረጃ መሰረት፤ ግጭት በተቀሰተባቸው አካባቢዎች የሚገኙ 208 ጤና ተቋማት ሙሉ በሙሉ፣ እንዲሁም 788 የሚሆኑት ደግሞ በከፊል መውደማቸው መገለጹን አዲስ ማለዳ ከሪፖርቱ ተመልክታለች፡፡

በዚህም 10 አምቡላንሶች መዘረፋቸውን፣ 45 የሚሆኑት መቃጠላቸውን እንዲሁም 25 ደግሞ ከአገልግሎት ውጭ መሆናቸው የተነገረ ሲሆን፤ በተጨማሪም 2 ሞተር ሳይክሎች መዘረፋቸውን፣ 5 የሚሆኑት ከአገልግሎት ውጭ መሆናቸውን እንዲሁም፤ 80 የሚሆኑት ደግሞ መቃጠላቸውን ገልጿል፡፡

“በምዕራብ ኦሮሚያ ወረዳዎች እና መካከለኛው አካባቢዎች በመንግሥት እና በክልሉ በሚንቀሳቀሰው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ታጣቂዎች መካከል የሚስተዋለው ግጭት፤ እንዲሁም በተለይ በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን በፋኖ ታጣቂ ቡድን የሚደረሰው ጥቃት ውድመት አድርሷል” ሲልም ሪፖርቱ ገልጿል።

በተጨማሪም “ግጭት በተቀሰቀሰባቸው አካባቢዎች ማህበራዊ ደንቦች ተሽረዋል፣ ማህበራዊ ተቋማት ወድመዋል፤ ጭካኔ እና ሕገወጥነት የተለመደ ሆኗል።” ያለው ሪፖርቱ፤ "ለዚህም በጥቅምት ወር 2015 በምዕራብ ወለጋ ዞን ሳሲጋ ወረዳ በገሎ ቀበሌ በመካነ ኢየሱስ ቤተ ክርሰቲያን ውስጥ፤ፐለአምልኮ በተሰበሰቡ ሰዎች ላይ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት የ14 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ማረጋገጫ ነው።" ሲል ገልጿል።

ሴንተር ፎር ዴቭሎፕመንት ኤንድ ካፓሲቲ ቢዩልዲንግ (CDCB) በሪፖርቱ በክልሉ የሚስተዋሉት ግጭቶች በተለይ ሴቶች እና ሕጻናትን ለአደጋ የጣሉ መሆናቸውን የገለጸ ሲሆን፤ ቤተሰቦቻቸውን በድንገት የሚያጡ ሕጻናት ቁጥር እየጨመረ መሆኑን አስታውቋል። በተጨማሪም ባለቤቶቻቸው የሞቱባቸው ሴቶች ለዝርፊያ፣ ለአስገድዶ መድፈ እና ለተለያዩ አካላዊ ጥቃቶች እየተጋለጡ መሆኑን ጠቁሟል፡፡

ስለሆነም በክልሉ የወደሙ መሰረተ ልማቶቸ እንዲስሩ ለአርሶ አደሮች ድጋፍ ማድረግ ያስፈልጋል ያለው ድርጅቱ፤ በተዋጊዎች መካከል በአስቸኳይ ሰላም እንዲወርድም በሪፖርቱ ጠይቋል።

ለደረሰውም ውድመት ከክልሉ፣ ከፌደራል መንግሥቱና ከግብ-ሰናይ ተቋማት አስቸኳይ እርዳታ እንደሚያስፈልግ አሳስቧል።
እናንተ አንገት ቁረጡ ኦሮሞ ታሪክ መስራቱን ይቀጥላል !!

ኢትዮጵያዊው ተመራማሪ ፕሮፌሰር ጋቢሳ ኢጄታ …

ተመራማሪ ፕሮፌሰር ጋቢሳ ኢጄታ የአሜሪካን ብሄራዊ የሳይንስ ሜዳሊያ ሽልማትን ከፕሬዚደንት ጆ ባይደን ተቀብለዋል።

ፕሮፌሰር ጋቢሳ በፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ብሔራዊ የክብር ሽልማት ከተሸለሙ 21 አሜሪካውያን ተመራማሪዎች መካከል አንዱ ሆነዋል።

መምህርና ተመራማሪው ፕሮፌሰር ጋቢሳ ኤጄታ ለሽልማቱ ያበቃቸው በከፍተኛ የምርምር ስራቸው የእፅዋት ዘረመል ምህንድስና በመጠቀም በረሃማ የአየር ንብረት እና ነፍሳትን የሚቋቋሙ የአዝርዕት ዘሮችን በማግኘታቸው ነው።

ግኝታቸው በሚሊዮን ለሚቆጠሩ የምግብ ዋስትናን እንደሚያረጋግጥ ታምኖበታል።

ፕሮፌሰር ጋቢሳ ኤጄታ በምግብ ዘርፍ ላበረከቱት አስተዋፅዖ ከዚህ በፊት ከዓለም የምግብ ፕሮግራሙ ሽልማት የተበረከተላቸው መሆኑ የሚታወቅ ነው።

ፕሬዚደንት ባይደን በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ይፋ ባድረጉት የተሸላሚዎች ዝርዝር በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ፈጠራ ዘርፍ ለሽልማት የበቁትን ተመራማሪዎች እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል ሲል አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዘግቧል።

https://www.tg-me.com/danny4677
ይህንን የዶ/ር ዲማ ነጋዎ ኢንተርቪው አድምጡት ብዙ ትማራላቹ የአባቶች የትግል ጥበብ እና ትልቅ ተጋድሎ የኦሮሞ ህዝብ የሰሩት ትልቅ ሥራዎች ይዘከራል
https://youtu.be/AKBI7F00c50?feature=shared

https://youtu.be/maPBwSDRqSA?feature=shared

https://youtu.be/j-ykrg2UTzk?feature=shared
ኦሮምያ ላይ ሚደረገውን ጦርነት እደግፋለው የምትሉ ከሆነ የናንተ እይታ ነው ደግፉ

ጦርነቱንም ሰላሙን አያገባኝ እንደፍጥርጥራቸው እምትሉ ከሆነህ እና ዝምታን ከመረጣቹ እሱም መብታቹ ነው ዝም በሉ

የተጀመረው ድርድር ይቀጥል ሁሉም ባለድርሻ አካላት መንግሥም ፣ተቃዋሚ ድርጅቶችም እንዲሁም ሙሁሩ ተቀምጦ ተነጋግሮ የመጨረሻ መፍትሄ ይምጣ ብለን ምንጠይቀውም መብታችንን እና ፍላጎታችንን አክብሩልን እኛ የኦሮምያ ምድር ደም መጠጣት ሊቆም ይገባል ስንል መፍትሄ ይሆናል ብለን ስለምናስብ ድርድሩ እንዲቀጥል መጠየቃችንን አናቆምም እናንተም ሙፍትሄ ባላችሁት መንገድ ቀጥሉ ።
የአርሲ ምዕመን ለመጀመርያ ግዜ አባት አገኘ
ለማንኛውም ከቻላቹ ከተማችን ውስጥ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኢግዚብሽን አዘጋጁ እንጂ ወታደር አታንጋጉብን።
<< በካርታ ላይ ካርታ ደርቦ መስጠትን ጨምሮ ህገ ወጥ የመሬት ወረራ ተበራክቷል >> - - የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን

አሻም ዜና | ጥቅምት 16 ቀን 2016 ዓ.ም

በከተማ አስተዳደሩ ‹‹ በህገወጥ መንገድ በካርታ ላይ ካርታ ደርቦ መስጠትን ጨምሮ ህገ ወጥ የመሬት ወረራ መስፋፋቱን ›› በፌዴራል የስነ- ምግባር'ና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስነ- ምግባር ፀረ ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አሰግደው ኃ/ጊዮርጊስ ተናግረዋል።

ምክትል ኮሚሽነሩ ይሄን ያሉት ኮሚሽኑ ባዘጋቸው የውይይት መርሃ ግብር ላይ ነው፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ስነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር የፌዴራል ስነምግባር ፀረ ሙስና ኮሚሽን ያቀረበውን መረጃ አጠናክረው በመናገር'ና የመረጃውን ትክክለኛነት በማረጋገጥ ለመከላከል እና ለማስተካከል በቅንጅት እየሰሩ ስለመሆናቸው አመላክተዋል።

‹‹ በከተማ አስተዳደሩ ውስጥ የሚታየው ህገ ወጥ የመሬት ወረራ ብሎም በካርታ ላይ ካርታ ደርቦ መስጠትን ጨምሮ የሚታዩ ብልሹ አሰራሮች መነሻቸው የአዳዲስ መመሪያዎች መበራከት እና በመረጃ አያያዙ በኩል ዘመኑን የዋጀ የአሰራር ስርዓት መዘርጋት አለመቻሉ ›› ስለመሆኑም ገልፀዋል።

በሌላ በኩል ‹‹ ከከተማዋ መስፋፋት ጋር ተያይዞ የሚነሱ ገበሬዎች መኖራቸውን ›› በማስታወስ ‹‹ ለገበሬዎች ካሳ የመስጠት አሰራር ሂደት ላይ የባለይዞታው ቤተሰብ በመምሰል ስማቸውን በመቀየርና መታወቂያ በማሰራት እንዲሁም ከደላሎች ጋር በመመሳጠር በአንድ ይዞታ ላይ በካርታ ላይ ካርታ ደርቦ የመያዝና በይዞታ ላይ ይዞታ የማረጋገጥ ህገ ወጥ ተግባር እንደሚከናወንም ›› አክለው አመላክተዋል።

በተመሳሳይ በከተማ አስተዳደሩ ውስጥ ከመሬት ጋር በተገናኘ ለሚስተዋለው ብልሹ አሰራር ብሎም ‹ አይን ያወጣ › ሙስና እንደምክንያት የተነሳው የመረጃ አያያዝ እና ስራን በቴክኖሎጂ በታገዘ መንገድ አለመከወንና የመሬት አደረጃጀት ጉድለት መኖሩን ነው።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ህዝባችን የኢትዮጵያ ነቀረሳ ማን እንደሆነ እየተረዳ የመጣ ይመስላል ።
የተጀመረው ድርድር እንዲቀጥል ሁላችንም ጫና. መፍጠር አለብን የኦሮምያ ጉዳይ በድርድር ማለቅ እና ሰላም መምጣት አለበት
በተረፈ ሰለ ስላም አታውሩ ምትሉን ሰላም ጠሎች እና ሥም አጠልሺዎች ነገ የምታፍሩበትን ነገር እየሰራቹ እንደሆነ እወቁ

#ሰላም_ለኦሮምያ
ለወለጋ ወገኖቻችን እርዳታ እጃችሁን የዘረጋቹ እናመሰግናለን !!!
2024/11/15 17:47:35
Back to Top
HTML Embed Code: