Telegram Web Link
Suresh Raina ማለት በክሪኬት ስፖርት ክሬዚ ለሆኑት ህንዳውያን ፡ እንደ ድንቅ የሚታይ ፡ እጅግ ዝነኛና ፡ በኑሮውም ሚሊየነር የሆነ ታዋቂ ሰው ነው ።
በቅርቡም ከክሪኬቱ አለም አረፍ ብሎ በታዋቂው NDTV የስፖርት ተንታኝ በመሆን ለስሜቱ ይሰራል ።
....
እና ትናንት ወደ አንድ ቦታ እየሄደ እያለ በመሀል መኪናውን አቁሞ የሰፈር ጉሊት ውስጥ ብርቱካንና አትክልቶች ሲገዛ በአድናቂዎቹ ካሜራ ውስጥ ገብቷል ።
......
የማይደበዝዝ ዝና ያለው Suresh Raina ከፈለገ የሚፈልገውን አትክልትና ፍራፍሬ ፡ አደለም በመኪና ፡ በሄሊኮፕተር አስልኮ የመጠቀም ብቃት ያለው ሰው ነው ።
ሆኖም ከአንድ በሰፈር ውስጥ ካለች ጉልት ነጋዴ እቃ ሲገዛ አንድም ፀሀይ ላይ ተቀምጣ ፡ አላፊ አግዳሚው ይገዛኝ ይሆን በሚል ስሜት የምትቃኘውን ጉልት ነጋዴ ሴት ለማበረታታት ሲሆን. .. በሌላ በኩልም ፡ ታች ካለው ህብረተሰብ ጋር ትሁት ሆኖ ለመመሳሰል ነው ። down to earth ፐርሰናሊቲ ።
....


@Amazing_Fact_433
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ይሄን ፎቶ ተመልከት እና ፁህፉን አንብበው

በአማዞን ቤት ፡ እያንዳንዱ መፅሀፍ ሲሸጥ ደወል ይደወል ነበር ።
🔔

ጄፍ ቤዞስ ፡ እ.ኤ.አ. በ 1995 ላይ በትንሽ ጋራጅ ውስጥ አማዞንን የመሰረተ ጊዜ ፡ የሚጠቀሙበት ሰርቨር ብዙ የኤሌትሪክ ሀይል ስለሚፈልግ ፡ በስራ ሰአት ሚስቱ የፀጉር ማድረቂያ መጠቀም ፡ ወይም በቫኪዩም ክሊነር ቤት ማፅዳት አትችልም ነበር ።
....
ከዛም ይህን ድርጅት ከመሰረቱ ከቀናት በኋላ ቢዝነሱን ሰፋ አድርገው ሀያ የሚሆኑ ሰራተኖችን ቀጥረው ፡ በዌብሳይታቸው ገብቶ መፅሀፍ የሚገዛ ሰው መጠበቅ ጀመሩ ።
እና በዛን ወቅት ወደ አማዞን ዌብሳይት የሆነ ሰው ገብቶ አንድ መፅሀፍ ሲታዘዝ ፡ በአማዞን ቤት ደስታ ይሆናል ።

አስገራሚው ነገር አማዞን ሽያጭ በጀመረባቸው በነዚህ ሳምንታት ፡ አንድ መፅሀፍ ሲታዘዝ ፡ ደወል ይደወላል 🔔 ይሄኔ የአማዞን ሰራተኞች የሆነ ሰው በኦንላይን መፅሀፍ እንደገዛቸው ያውቃሉ ፡ እና ፡ ይህን ከአማዞን መፅሀፍ ያዘዘው ሰው ስም ለማየት ኮምፒውተሩን ይከባሉ ።
......
ማለትም በቀን ውስጥ አስር ጊዜ ሽያጭ ከፈፀሙ ፡ አስር ጊዜ ደወል ይደወል ነበር ማለት ነው ። ሆኖም አማዞን ብዙም ሳይቆይ ከሚጠበቀው በላይ ብዙ ትእዛዞች መቀበል በመጀመሩ አንድ መፅሀፍ ሲሸጥ ደወል መደወል ያቆመው በሳምንታት ውስጥ ነው ።
....
ዛሬስ. .....
ያ. .. አንድ መፅሀፍ ሲሸጥ ደወል ይደውል የነበረው አማዞን በአንድ ቀን ከስድስት ሚሊዮን በላይ የተለያዩ እቃዎችን ይሸጣል ። እንደድሮው ቢሆን በቀን ውስጥ ስድስት ሚሊየን ጊዜ ደወል ይደወል ነበር ማለት ነው ።
....
እያንዳንዱን ስኬቱን ደወል በመደወል ያበስር የነበረው አማዞን ፡ አንድ መፅሀፍ ሲሸጥ በደስታ ያጨበጭብ የነበረው አማዞን ፡ ዛሬ ላይ ከ1,525,000 በላይ ጊዜያዊና ቋሚ ሰራተኞችን ቀጥሮ ያሰራል ።

እንደምንም በቆጠባት አስር ሺህ ዶላር ቢዝነስ የጀመረው ጄፍ ቤዞፍ አሁን 197 ቢሊየን ዶላር ሀብት በስሙ አስመዝግቧል ።
......
ነገ በተሻለ ጉልበት ለመንቀሳቀስ ሀይል ይሆነን ዘንድ በያንዳንዱ ትናንሽ ስኬት ፡ እንደጄፍ ቤዞስ በደስታ ደወላችንን እናንሳ
🔔
........
ፎቶ ፡ የአሁኑ ቢሊየነር ጄፍ ቤዞፍ አማዞንን በመሰረተበት ወቅት
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ORANGUTAN

ይህ የጦጣን እጅ የሚስመስል እጅ ያለው ሰው ከመሰላችሁ ተሳስታችኋል፤ ይልቁንስ ለሰው ቀረብ ያለ እጅ ያለው የጦጣ እጅ ፎቶ ነው

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433group
ላብ በትክክል አይሸትም

ገላዎን ከታጠቡ በኋላ የሚያመርቱት ማንኛውም ላብ በጣም መጥፎ ጠረን እንደሌለው ልብ ይበሉ። ይህ የሆነበት ምክንያት በቆዳዎ ላይ ያለው ባክቴሪያ ላብ የሚሰብረው ጠረኑን የሚያመጣ ስለሆነ ነው።

@Amazing_Fact_433
@Amazing_Fact_433
የጥንት ሮማውያን /Public Toilet/ የህዝብ_ሽንት_ቤት ! 😁

@Amazing_Fact_433
@Amazing_Fact_433
ኤሌክትሪክ ወቶ እየጠገነ እንቅልፍ ወስዶት የተፈጠረው አስደንጋጭ የተስፈኛው ልጅ ሙሉ ታሪክ በቪድዮ https://www.tg-me.com/curiosity_chronicles/1139
#METHANE

በአየር ላይ በብዛት የሚገኘው greenhouse gas ካርቦንዳይኦክሳይድ ስለሆነ ነው እንጂ በአብዛኛው የሱ መጠን መቀነስ አለበት ሲባል የምንሰማው ሙቀት በማመቅ ደረጃ ሜቴን ከካርቦንዳይኦክሳይድ 25 እጥፍ የማመቅ አቅም ያለውና መጥፎው greenhouse gas ነው😲

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433group
Forwarded from 4-3-3 ስፖርት በ ኢትዮጵያ (🅰🅱uShe ️ ️)
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ለፈሰሰ ወተት አታልቅስ የሚባል አባባል አለ ፡ እኔ ግን በአንድ ወቅት በድጋሚ ገዝቼ ለልጆቼ የምሰጠው ወተት መግዣ ገንዘብ ስላልነበረኝ ፡ ለፈሰሰው ወተት አልቅሼ አውቃለሁ ።
....
ከሶስት ልጆቼ ጋር በአንዲት ክፍል ቤት እንኖር በነበረበት በዛን ወቅት ኑሮ እጅግ ከባድ ከመሆኑ የተነሳ ፡ አንዳንዴ ልጆቼን የምመግበው ሁሉ አጥቼ አውቃለሁ ።

አዲስ ልብስ መግዛትም ስለማይታሰብ ለልጆቼ የማለብሰው የቦንዳ ልብስ ነበር ።

ስጋና ሌሎች ጠቃሚ ምግቦችን በየጊዜው መግዛት ባለመቻሌም ፡ ባለኝ የምግብ መስራት ችሎታ ተጠቅሜ ፡ ከባቄላና ከለውዝ ቅቤ ጥሩ ምግቦችን እየሰራሁ ልጆቼ የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኙ ለማድረግ እሞክር ነበር ።
....
አምላክ ይመስገንና አሁን ይሄ ሁሉ ተረት ሆኗል ። እኔ ከወጣትነቴ ጀምሮ የሰራሁበትን የሞዴሊንግ ሙያ አሁን በ76 አመቴም አልተውኩትም ።

አሁንም የፋሽን መፅሄቶች ከቨር ላይ እወጣለሁ ፡ ለአመታት የሰራሁበት የስነምግብ ስፔሻሊስት ሙያዬም አለ ።
...........
እነዛ የቦንዳ ልብስ እያለበስኩ ፡ የለውዝ ቅቤና ባቄላ እየመገብኩ ያሳደኳቸውን ልጆቼ ደግሞ. ... የመጀመሪያ ሴቷ ልጄ Tosca እንደኔት ፍሌክስ አይነት የተለያዩ ፊልሞችን የሚያሳይ Passionflix የሚባል ካምፓኒ ከፍታ እየሰራች ነው ።
ሌላኛው ልጄ ኬምባል ደግሞ በተለያዩ የአሜሪካ ከተሞች ታዋቂ የሆነ የሬስቶራንትና ሌሎች ቢዝነሶች ላይ ተሰማርቶ ስኬታማ ሆኗል ።
ያው ሶስተኛው ልጄን ታውቁታላችሁ ኤለን መስክ ይባላል ።

የስፔስ ኤክስ እና የቴስላ መስራችና እንዲሁም የ X ( የትዊተር ) ባለቤት ነው ።
እና ያ ጥሩ ያልነበረ ጊዜ እንደሚያልፍ ማሰቤ ትክክል ነበር
( ማይ መስክ የኤለን መስክ ወላጅ እናት
)
Audio
በመኪና ሳይሆን በጋሪ... በኤልክትሪክ ሳይሆን በፋኖስ Amish family መቆያ - በእሸቴ አሰፋ
ለሪል ስቴት በሊዝ የገዛውን መሬት ፡ ለሌላ ጥቅም ያዋለው ናይጄሪያዊ ኳስ ተጫዋች ።
..........
ጄጄ ኦካቻ ፡ ከቀድሞ የናይጄሪያ ቡድን ተጫዋችነቱ በተጨማሪ ፡ ብዛት ባላቸው የአውሮፓ ክለቦች ያሳይ በነበረው ድንቅ ብቃት አለም ያወቀውና ተደናቂነትን ያተረፈ ዝነኛ ኳስ ተጫዋች ነበር ።
.....
ጄጄ ፡ ከእግር ኳስ አለም በይፋ ከተሰናበተ በኋላም በሀገሩ ናይጄሪያ ውስጥ በተለያዩ ቢዝነሶች ላይ ተሰማርቶ የቆየ ሲሆን ፡ በቅርቡ ባደረገው ነገር መነጋገሪያ ሆኗል ።
....
ኦካቻ በሚኖርበት ከተማ. .. ለራሱና ለቤተሰቡ የሚሆን እጅግ ዘመናዊ መኖሪያ ቤት ሰርቶ ካጠናቀቀ በኋላ ፡ ለዴልታ ስቴት ማዘጋጃ ቤት ብዛት ያላቸው ቤቶችን ለመስራት ጠይቆ ሰፊ መሬት በሊዝ ይገዛል ።

በዚህ በወሰደው መሬት ላይም ባጠቃላይ ብዛታቸው መቶ የሚሆኑ የተለያዩ ባለአንድና ሁለት መኝታ ቤት መኖሪያ ቤቶችንና ኮንደሚኒየሞችን ካሰራ በኋላ
............
.
.
.
በዴልታ ስቴት ለሚኖሩ በእድሜ ገፋ ላሉ .. ችግረኞችና የጎዳና ተዳዳሪዎች ሁሉንም ቤቶች ፡ በነጻ ሰጥቶ ሰውን አስገርሟል ።
.....
ጄጄ ሙሃመድ ያቪዝ ኦኮቻ ቤቶቹን ለነዚህ ሰወች ካስረከበ በኋላ እንደተናገረው. ..

እኔ ሚሊየን ዶላር የፈጀ ቪላ ውስጥ እየኖርኩ ፡ ለጎዳና ተዳዳሪዎችና ችግረኞች ምንም ማድረግ አለመፈለግ ሀጢያት ነው ብሏል ።
........
( ናይጄሪያ በአለም የታወቁ ሀብታሞች ያሉባት ሀገር ብትሆንም ፡ ለመስጠት በራሱ የሚሰጥ ልብ ይፈልጋልና. .. እነሱ ያላሰቡትን ኦካቻ አድርጎ አሳይቷቸዋል
Aphid የተባሉት ነፍሳት ልክ ሲወለዱ ሌላ አርግዘው ወይም እርጉዝ ሁነው ነው የሚወለዱት

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433group
በ ሩሲያ ለ ሳይንሳዊ ምርምር በላብራቶሪ ውስጥ ህይወታቸውን ላጡ አይጦች ክብር የቆመ ሀውልት አለ

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433group
በአንድ ወቅት Mozambique ላይ
መላጣ (ራሰ-በረሃ) ሰዎችን አሳደው መግደል ጀምረው ነበር!

እንደ ምክንያትነት የቀረበው ሃሳብ ደሞ "መላጣ የሆኑት አናታቸው ውስጡ ወርቅ ስለሆነ ነው!" የሚል አፈታሪክ ነው!

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433group
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2024/09/29 00:15:20
Back to Top
HTML Embed Code: