Telegram Web Link
ይህን ያውቃሉ?

በሀገረ ሆንዱራስ: ዮሮ በምትባል ከተማ ዣንጥላ የምትይዙት ለዝናብ ብቻ ሳይሆን እንደ በረዶ ከላይ ከሚወርዱት ከአሳዎች ምትም ለመዳን ነው

ይሄ ክስተት "lluvia de peces" የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን በየአመቱ እስከ አራት ጊዜ ድረስ ሊከሰት የሚችል የአሳ ዝናብ ነው
🙈የፈጣሪ ስራ ምንኛ ድንቅ ነው🥶😍

@Amazing_Fact_433
@Amazing_Fact_433
ቢያጨስ ይሻል ነበር ትላላችሁ ?

ይህ ሰው ለ 8 ዓመት ማጨስ ያቆምና ለማጨስ ያጠፋ የነበረውን ገንዘብ በመቆጠብ መኪና ገዛ ። ግን የሚያሳዝነው በመኪና አደጋ ሞተ !

@Amazing_Fact_433
@Amazing_Fact_433
☑️በበረራዎች ወቅት በአውሮፕላን ውስጥ የተከሰቱ ነገሮችን

እንዲሁም የመከስከስ አደጋ ሲያጋጥማቸው  መረጃዎችን ሰብስቦ የሚያስቀምጥልን "Black Box" እንደስሙ ጥቁር ሳይሆን በብርቱካናማ ቀለም ያሸበረቀ ነው
⚫️       🟠

☑️Black Box ዋነኛ ጥቅሙ አውሮፕላኑ የመከስከስ አደጋ ሲያጋጥመው በውስጡ የነበሩትን ክስተቶች

እንዲሁም የመከስከሱ መንስኤ ምን እንደሆነ ቀድቶ የሚያስቀምጥ እጅግ ጠንካራ ከሆኑ ብረቶች የተሰራ፤ የማይቃጠል የማይሰበር የማይፈነዳ የአውሮፕላን እቃ ነው

@Amazing_Fact_433
@Amazing_Fact_433
ቤተመንግሥት ስትጋበዙ ማድረግ ያለባቸው ነገሮች

⭐️ የሆነ ሀገር ሄዳችሁ ወይም እዚሁ ሀገር  ፡ ድንገት ቤተመንግስት ብትጋበዙ  ማድረግ ያለብባችሁ ነገሮች 

ለሀገር ፡ ከፍ ሲልም ፡ ለአለም የሚጠቅም ስራ የሰሩ ሰወች ያበረከቱት አስተዋፅኦ ታላቅ ሲሆን ፡  ፡ በቤተመንግስት ተጋብዘው በሀገር መሪ ወይም በንጉስ እጅ  ሊሸለሙ ይችላል ።

እና በዚህ የሽልማትና ምናልባትም የእራት ግብዣ ላይ የሚገኙ ሰወች ፡ በቤተመንግስት በሚያደርጉት ቆይታ ማሳየት የሚገባቸው ጸባይ ባህሪ ሁኔታ ፡ የፕሮቶኮል ኮድ ባብዛኛው ተመሳሳይ ነው ።

በዚህም መሰረት

ይህ ሽልማትና ፡ የራት ግብዣ ይገባቸዋል ለተባሉት ሰወች ቀደም ተብሎ መልእክት ይደርሳቸዋል ።
ይህ የጥሪ መልእክት የሚደረገው  በስልክ ወይ በሌላ ሳይሆን ፡ በደብዳቤ እንዲደርሰው ይደረጋል
.....
በቤተመንግስት ለሽልማት የተጠራው ሰው ቀኑ ከመድረሱ በፊት ፡ በንጉስ ወይም በሀገሪቱ ፕሬዝደንት  ፊት ሲቀርብ  ምን መልበስ ፡ ምን  ማድረግ እና ምን አለማድረግ እንዳለበት ይነገረዋል ።
......
.........ወደዚህ ቦታ ለመሄድ ፕሮግራም ከተያዘ በኋላ ዋናው ሊያሰብበት የሚገበው የአለባበስ ፕሮቶኮል ነው   ፡ በዚህ ፕሮግራም ላይ የሚገኙ ሰወች ሁሉ ወጥ የሆነ አለባበስ መልበስ አለባቸው ይኸውም ወንዶች ፡ በጣም ብልጭልጭ ያላለ ፡ ጥሩ  ሙሉ ልብስ  ከነክራቫት ሴቶች ደግሞ መደበኛ ቀሚስ ወይም ኮትና ጉርድ  ቀሚስ ከሸሚዝ ጋር እንዲለብሱ ይጠበቃል ።
........................

ማንኛውም ጥሪ የተደረገለት  ሰው በእለቱ ቤተመንግስት መድረስ ያለበት ፡ ከጥሪው ሰአት  ቀደም ብሎ መሆን ይኖርበታል ። ከዚያም. .ልክ ንጉሱ ወይም የሀገሪቱ መሪ  ጋር ሲገናኝ ፡ በአክብሮት አጠራር ንጉስ ሆይ ... ክቡር ፕሬዝደንት. ..  በሚል የማእረግ ስም ይጠራ ዘንድ ይጠበቅበታል ።  ይህ ሰው በሚያደርገው እያንዳንዷ ነገር የሚያሳየው ከበሬታ ፡  በቀጥታ ለሀገሩ ያለውን ክብር መግለጫ ነው ።
..........

ከንጉስ ወይም ከመሪ ጋር አካላዊ ንክኪ አይፈቀድም ። ማለትም በሚገናኙበት ጊዜ የሀገሪቱ መሪ ለሰላምታ ቀድመው እጅ ካልዘረጉ በስተቀር ለመጨበጥ መሞከር አይመከርም ።

...
ሽልማት ከሀገር መሪ በሚቀበሉበት ወቅትም  በአክብሮት ከአንገት ጎንበስ ተብሎ በሁለት እጅ መቀበል አለበት ። በዚህ ወቅትም የሀገሪቱ መሪ  ራሳቸው ንግግር ካልጀመሩ በቀር ፡ ቀድሞ ማናገር የጨዋ ወይም የሰለጠነ ሰው ባህሪ  አይደለም ።
..........
ከዚህ በኋላም መሪው ፡ ንጉሱ ፡ ወይም ፕሬዝደንቷ ቀድመው ሳይቀመጡ መቀመጥ ፡ ይህም  የጨዋ ስርአት አይደለም ። ገበታ በሚቀርብበት ወቅትም መሪው  መመገብ ሳይጀምሩ ። እጅን መዘርጋትም ስርአት  አይደለም ።
... ....
በዚህ በቤተመንግስት በሚደረግ ቆይታ ወቅት. .. በተለይ የቤተመንግስት ባለሟሎች የሚሰጡትን ትእዛዝ ማክበርና መታዘዝ ወሳኝ ነገር ነው ። ምክንያቱም የት ቦታ መቆም ፡ የት መቀመጥ ፡ ምን ማድረግ እንዳለብን የሚነግሩን እነሱ ናቸው ።
......
ይህን የፕሮቶኮል ህግ  ማክበር ለመሪው ማጎብደድ አይደለም  ። ይህን ህግ ማክበር ሀገሪቱን ማክበር ነው ።
በአለም አቀፍ ደረጃ የሚተገበር ጨዋና ፡ የሰለጠኑ ሰወች ሊተገብሩት የሚገባ የፕሮቶኮል ህግ ነው



@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ይህንን ያውቃሉ⁉️

በአመት ከ10ሺ በላይ ወፎች ከመስታወት መስኮቶች ጋር ምስላቸውን በመፋለም በሚደርስባቸው ግጭት ይሞታሉ።

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
#ፍትህ_ሳትኖር_ለተገደለችው_ህጻን_ሄቨን 😢😢😢😢😢

"... የ7 ዓመት ልጅ ነች እናቷ ነርስ ስለሆነች የተከራዩበት ቤት ትታት ትሄዳለች!

ነገር ግን ቤት ያክራያቸው ይህ በፎቶ የምትመለከቱት አከራይ ስሙ ጌታቸው የ7 ዓመት ህፃን ልጅን ጊቢ ውስጥ ወደ ሽንት ቤት ስትሄድ ጠብቆ አፎ ውስጥ አሽዋ በማድረግ አስገድዶ ደፍሯታል.

በዚህም

* መቀመጫዋ ና
* ማህፀኗ የተጎዱ ሲሆን

የጀርባ አጥንቷ በማህፀኗ በኩል እስከሚታይ ድረስ ደፍሯታል። ስደማበትም በውሀ አጥቧት፣ አንጏቷን አንቆ ገድሏታል፣  የወደቀች እንዲመስልም  ሰውነቷን በምላጭ በመተላተል ወደ ውጪ በማውጣት ጥሏታል።

ይህው እናትም የልጄን ፍትህ አሰጡኝ እያለች የኢትዮጵያ ህዝብ እየለመነች ይገኛል::

እናንተ ኢትዮጵያውያን ይህ ነገር በደንብ እንዲሸራሸር ፊስቡክ፣ ቴሌግራም፣ ቲክቶክ ላይ

* ሼር

እያደረጋችሁ ተባበሯት

ድምፅ ሁኑ

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
የስልሳ አመቷ እናት Nokubonga Qampi በትንሽ ስልካቸው ብርሀን እየታገዙ በእጃቸው ትልቅ ቢላ ይዘው ድቅድቅ ባለው ጨለማ ውስጥ እየሄዱ ነው ።
.....
እና ትንሽ እንደተጓዙ ልጃቸው አለችበት የተባለው ቤት ደረሱ ፡ የልጃቸው ጓደኛ ነበር የደወለችላቸው ፡ የልጃቸው ጓደኛ በተደናገጠ ድምፅ ፡ በሰፈሩ የሚታወቁ ሶስት ጉልበተኞች የእሳቸውን ልጅ አስገድደው ሊደፍሯት እየሞከሩ እንደሆነ ገልጻ እሷ ሸሽታ ማምለጧን ነገረቻቸው ።
....
አዛውንቷ Nokubonga ይህን እንደሰሙ ወደፖሊስ ስልክ ደወሉ ፡ ስልኩ አይነሳም ፡ ማድረግ ያለባቸው ፖሊስ ጣቢያ ሄዶ ማመልከት ነው ። ያ እስኪሆን ደግሞ ልጃቸው በደፋሪዎቿ ህይወቷ ሊያልፍ ይችላል ።
....
ስለዚህ ማድረግ ያለባቸው ከልጃቸው ጋር አብሮ መሞት ነበርና ፡ ከኪችን ትልቅ ቢላ ይዘው ነበር ልጃቸው አለችበት ወደተባለው ቦታ የደረሱት ።
....
ልክ እንደደረሱ የልጃቸው የድረሱልኝ ድምፅ ተሰማቸው ፡ እና ትንሽ ስልካቸውን እያበሩ ድምፅ ወደሰሙበት መኝታ ቤት ሲደርሱ ፡ ሶስት በሰፈሩ በረብሻና በጉልበተኝነት የሚታወቁ ጎረምሶች በክፍሉ ውስጥ ሆነው አንደኛው ልጃቸውን ሲደፍር ተመለከቱ ፡ እና ትልቅ ቢላቸውን አጥብቀው ይዘው ልጃቸውን እያስገደደ ወዳለው ወጣት ሮጡና በሀይል ወጉት ፡ ድርጊቱ ቅፅበታዊ የሆነባቸው ደፋሪዎች እመዛውንቷን እናት ለማጥቃት ተጠጉ ፡ ሴትዮዋ ከየት እንዳመጡት በማያውቁት ጉልበት ፡ ቢላቸውን ሰንዝረው ወደሳቸው የተጠጉትን ሁለት ወጣቶች ወጓቸው ።
.....
ያላሰቡት ጥቃት የገጠማቸው ሁለት ጎረምሶች በመስኮት ዘለሉ ፡ Nokubonga ቀድመው የወጉትን ደፋሪ አዩት ለመነሳት እየሞከረ ነው ። እዛው እንዳለ ደገሙት ።
.....
ወዲያውኑ ፀጥ አለ ።
.......
እና ቢላቸውን ጥለው ልጃቸውን ደግፈው ከክፍሉ ወጠው ሰወች እንዲደርሱላቸው መጣራት ጀመሩ ።
......
በአካባቢው ያሉ ሰወች ጥሪያቸውን ሰምተው የመጡት የአካባቢው ሰወች ፡ ልጃቸውን ወደሆስፒታል ይዘው ሄዱ ፡
....
ግርግሩን ሰምተው የመጡ የፖሊስ አባላት አዛውንቷን ወደ ጣቢያ ወሰዷቸው ፨
......
አዛውንቷ Nokubonga በአንድ ሰው ግድያ እና በሁለቱ ላይ ባደረሱት ከፍተኛ ጉዳት ክስ ተመሰረተባቸው ።
....
ልክ ይህ ዜና እንደተሰማ ፡ በደቡብ አፍሪካ ያሉ ሶሻል ሚዲያና እንዲሁም በተለያየ ቦታዎች ያሉ ሰወች የአዛውንቷን መከሰስ ተቃውመው ሰልፍ ወጡ ።
.......
ጉዳዩ ቫይራል ሆነ ፡ ሴትየዋ ያደረጉት ማንም እናት እና አባት ልጁ ስትደፈር ማድረግ የሚችለውን ነውና መከሰስ የለባቸውም ተባለ ።
....
ህዝብ በአንድ ድምፅ ከእናትና ልጅ ጎን ቆመ ።
......
ብዙም ሳይቆይ ፍርድቤቱ አዛውንቷ Nokubonga ን በነፃ ለቀቃቸው ። ልጃቸውም ሙሉ ጤና ሆና ከሆስፒታል ወጣች
......
ከዚህ ድርጊት መከሰት በኋላ የደቡብ አፍሪካ ህዝብ ለኚህ እናት አዲስ ስም አወጣላቸው ። Lion mama የሚል ።
....
አሁን አሁን ሰው የሚያውቃቸው በዚህ ስም ነው ።
....
የደቡብ አፍሪካ ህዝብ ከነዚህ እናትና ልጅ ጋር እንደቆመው ፡ እኛም ከዚህ የባሰ ወንጀል ለተፈፀመባት ለህጻን ሄቨን ፍትህ እንላለን ። እናም ከስር በተቀመጠው ሊንክ በመግባት እየተሰበሰበ ያለውን የፊርማ ካምፔን ይቀላቀሉ


https://chng.it/RNMNMvD4
የ7 አመት የተከራዩን ልጅ ደፍሮ ከዛም ባለፈ በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለው አውሬው ጌትነት የተባለው ወንጀለኛ ግለሰብ 25 አመት የተፈረደበት ሲሆን አሁን ጠበቆቹ ቅጣቱን ለማቅለል ደፋ ቀና እያሉ ነው።

እህቶቹ እንዲሁም ሌሎች ሰዎች የሟች ህፃን ሄቨን እናትን በየሄደችበት እያስፈራሯት ይገኛል የኢትዮጵያ ህዝብ ፍርድ ይስጠኝ ያለችው እናት ፍትህ ትፈልጋለች።

ቅጣቱ በቂ እንዳልሆነ ተጨማሪ ቅጣት ሊጣልበት እንደሚገባ ህዝብ ያንን እንደሚፈልግ ለማሳወቅ የፊርማ ማሰባሰብ እና ለእናቷ የገንዘብ ድጎማ ተጀምሯል።
https://www.change.org/p/justice-for-heaven-and-her-mother?recruited_by_id=94947080-5cca-11ef-af3a-c38f3884f55d&utm_source=share_petition&utm_campaign=psf_combo_share_initial&utm_term=signature_receipt&utm_medium=copylink

በዚህ ሊንክ በመግባት ፊርማችንን መስጠት የቻልን ደግሞ የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ እንችላለን።

4-3-3 ስፖርት በኢትዮጵያ በህጻኗ ላይ በተፈጠረው የግፍ ግድያ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልፃል።

ይህ ጉዳይ በጊዜ ካልተቋጨ ነገ እኔ እና እናንተም ቤት መግባቱ አይቀርም!

#ፍትህለሔቨን
#Justiceforheven

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
👉 || በአሜሪካ በኦኮሆማ ከተማ ቱልሳ በሚባል አካባቢ የዩኒቨርሱ መሃል የሚባል ገናና ቦታ ይገኛል ! በዚ ቦታ በክብ የተከበበት ቦታ ይገኛል ! በዚ በክብ ቦታው ውስጥ ማንኛውም ሰው ገብቶ እንደፈለገ ቢጮህ አጠገቡ የቆመው ሰው በፍፁም የሱን ድምፅ አይሰማም ! ከውጪ ያለውም ሰው የፈለገ ጮክ ብሎ ቢያወራ ወይም ሽጉጥ ቢተኩስ አልያም መድፍም ቢተኩስ ሰርክሉ ውስጥ ያለው ሰው በፍፁም አይሰማውም !

የኛን ሀገር ዘፋኞች ምናለ እዚህ ቢዘፍኑ 😭

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
የማሪያኔ ባችሜየር ልብ የሚነካ ታሪክ

ማሪያኔ ባችሜየር ሰኔ 3 ቀን 1950 በጀርመን ተወለደች! ለልጇ አና በጣም አፍቃሪ እና ታማኝ እናት ነበረች። አና የማሪያን ህይወት ብርሃን ነበረች ደስተኛ እና ብሩህ ትንሽ ልጅ በዙሪያዋ ላሉ ​​ሰዎች ሁሉ ታላቅ ደስታን የምታመጣ ህፃን ነበረች ማሪያ ቤታቸውን በፍቅር እና በደስታ በመሙላት ለአና ጥሩ ሕይወት እንዲኖራት ጠንክራ ትሰራ ነበር

የሚያሳዝነው ግን በ1981 ይሄ ሁሉ ነገር ተዘበራረቀ መጋቢት 5, 1981 አና የሰባት ዓመት ልጅ እያለች ክላውስ ግራቦቭስኪ በተባለ ሰው ተደፍራ ​​ተገደለች። ከዚያ በኋላ ያለው ህመም ለ ማሪያ በጣም ከባድ ነበር ማሪያን የምትወዳትን ሴት ልጅ በሞት ማጣቷን መቀበል አልቻለችም !

በ1981 በክላውስ ግራቦቭስኪ የፍርድ ሂደት ላይ ማሪያን ዓለምን ያስደነገጠ ነገር አደረገች የፍርድ ሂደቱ በተጀመረ በሶስተኛው ቀን ሽጉጡን በድብቅ ወደ ፍርድ ቤት ይዛ ገብታ ግራቦቭስኪን በጥይት 8 ጊዜ ተኩሳ ፍትህን በእጇ አስገባች !

ለድርጊቷ የእስር ቅጣት ቢፈረድባትም ነገር ግን ብዙ ሰዎች ለአና ብላ ያደረገችው ነገር ስለሆነ ብዙ ሰው ትክክለኛ ነገር እንዳደረገች አስበዋል !

ማሪያን በሴፕቴምበር 17፣ 1996 ከዚህ አለም በሞት የተለየች ሰሆን ነገር ግን የእናት ታሪክ የእናት ፍቅር ምን ያህል እንደሆነ በማርያን አይነተናል ልጇን በሞት በማጣቷ  የሚደርስባትን ጥልቅ ህመም የሚያሳይ ልብ የሚነካ ታሪክ ለ አለም አስተላልፋለች !

@Amazing_Fact_433
@Amazing_Fact_433
ትንኞች በዓለማችን ላይ እጅግ ገዳይ እንስሳት ናቸው፡በሚሸከሙት በሽታዎች ምክንያት ከማንኛውም ፍጡር የበለጠ ሰዎችን ይገድላሉ።

@Amazing_Fact_433
@Amazing_Fact_433
2024/09/30 07:29:40
Back to Top
HTML Embed Code: