Telegram Web Link
.....

✅️በምስሉ ላይ የሚታየው ወጣት ልጅ ስራ ሊቀጠር ለቃለ-መጠይቅ ቀጠሮ ወደ ድርጅቱ ቢሮ መጥቶ ለመግባት ተራውን እየጠበቀ ነው። ያው እንደሚታወቀው ከቃለ-መጠይቅ ጋር ልዩ ትኩረት የሚደረግበት ጉዳይ ፕሮቶኮል ነው።

✔️እናም ወጣቱ ከረባቱን ማስተካከል ተስኖት ሲቸገር ቀይ ኮት የለበሱት ሴትዮ አዩትና ከጎናቸው የነበሩትን ባላቸውን በክርናቸው ጎሸም አድርገው ወደ ልጁ ጠቆሙና ሌሎች እንዳያዩ ጋርደው ቆሙ። ባልተቤታቸውም የወጣቱን ከረባት በተገቢው መልኩ አስተካከሉለት.....ይህ ፎቶ የሚያስተላልፈው መልዕክት የዋዛ እንዳይመስልህ....

✔️ሁሌም መልካም ለማድረግ አጋጣሚውን ስታገኝ መልካም ተግባርን አድርግ....መልካም ስራ የዓለም ጌጥ፣ የዓለም ውበት ነው🙏🙏

አንድ ስንሆን ጠንካሮች ብቻም አይደለም የምንሆነው.....ቆንጆዎችም ጭምር እንጅ
🤞🤞
_//___
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በጥቂት ጊዜ ተከፍቶ ተወዳጅነት ያፈራውን የክሪፕቶ ቻናላችንን ይቀላቀሉ🔥🔥

በ4-3-3 ክሪፕቶ ቻናል ከ ዜሮ ተነስተን እንዴት ክሪፕቶ እና ኤር ድሮፖችን መስራት እንዳለብን የምናሳያቹ ይሆናል:: ከ4-3-3 ክሪፕቶ ጋር መልካም ቆይታ !❤️

Join us 👇

https://www.tg-me.com/+7kjTJpKolnVjMDU0
https://www.tg-me.com/+7kjTJpKolnVjMDU0
አይዞህ
Abdu Kiar
የአብዱ ኪያር አዲስ ያበደ አልበም በዘፈን ቻናላችን ያገኙታል ።
ቻይና ለመጀመሪያ ጊዜ የአማርኛ ቋንቋ ድግሪ ተማሪዎችን አስተምራ አስመረቀች።

Viva #FastMerej

@Amazing_Fact_433
@Amazing_Fact_433
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በምስሉ ላይ ያሉት ሁለቱም ታዋቂ የፊልም ተዋናዮች ናቸው። በስተግራ ያለው ስቲቭ ቡስኬሚ ነው። የእሳት አደጋ ሰራተኛ ነበር። አሁን የተዋጣለት አክተር ነው። በስተቀኝ ደግሞ አንጀሊና ጆሊ አለች። ታዲያ አንጀሊና በጣም ውብ ተብላ ስትሞካሽ ስቲቭ ደግሞ አስቀያሚ (ለቃሉ ይቅርታ እጠይቃለሁ) ተደርጎ ይቆጠራል። በጣም አስገራሚው ጉዳይ በፎቶው ላይ እንደምትመለከቱት መልካቸው በጣም ይመሳሰላሉ። ወንድምና እህት ናቸው ቢባል ማንም ያምናል።

አንድ ትልቅ ቁምነገር የገባኝ ይኼኔ ነው፦

በውበትና አስቀያሚነት
በሰላምና ጦርነት
በፍቅርና ጥላቻ መካከል ያለው መስመር ቀጭን ነው!!!
ኬቨን በርቲሃ ኑሮ ታከተው: አለም አስከፋቺው :የገዛ ህይወቱን ማጥፋት ብቸኛ አማራጭ አድርጎ ወሰነ

ይህንን ውሳኔውን ለማሳካት ደግሞ በአሜሪካ ሳንፍራንሲስኮ ግዛት ወደ ሚገኘው እና በከፍታው እውቁ ድልድይ ወደሆነው ጎልደን ጌት ድልድይ አመራ

ሆኖም ግን ከድልድዩ ጫፍ ቆሞ ራሱን ለማጥፋት ሲዘጋጅ የፖሊስ መኮንኑ ኬቨን ብሪግስ በቦታው ደረሰ:: ህይወቱን እንዳያጥፋ እየተማፀነው ለአንድ ሰአት ከሰላሳ ሁለት ደቂቃዎች አብሮት ቆየ

ኬቨን በርቲሃ ሀሳቡን ቀየረ : ህይወቱም ተረፈች

ከ10 አመታት በኃላ ኬቨን በርቲሃ እና ኬቨን ብሪግስ እዚያው ድልድይ ላይ ተገናኝተው አወጉ: እዚያው ድልድይ ላይ እየተሳሳቁ ተጨዋወቱ

ዋናው ነገር ዛሬን ማለፍ ነው : ማን ያውቃል ነገ ውስጥ ምን አይነት ሳቅ እንዳለ

ሰው መሆኛ መንገድ ብዙ ነው !!
- በ2022 ለይ የህንድ ባለስልጣን የነበረው Bhagwant Punjab የአንድ ወንዝ ውሀ በብርጭቆ ይቀዳና "ቅዱስ ውሀ ነው" ብሎ እንደማይጎዳ ለማሳየት ይጠጣዋል...

- ከሁለት ቀን በኋላ ግን በሆድ ህመም ምክንያት ሆስፒታል ይገባል።

@Amazing_Fact_433
🔵#ትምህርትና_ዓለም

በዓለማችን ላይ ምርጥ የትምህርት ስርዐት ካላቸው ሀገራት መካከል ፊንላንድ ቀዳሚ ነች፡፡


ፊንላንድ ውስጥ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት 9 ዓመት ብቻ ነው የሚማሩት፡፡ በእነዚህ 9 ዓመታት ውስጥ ፈተና የሚፈተኑት 1ጊዜ ብቻ ነው፤ እሱም ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነው፡፡

የቤት ስራ የሚባል ነገር የለም ሁሉም ክፍል ውስጥ ነው የሚያልቀው፡፡ 1ኛ ፣2ኛ... የሚባል የደረጃ አሰጣጥ የለም፡፡

ትምህርት ነጻ ነው፤ የሀብታም የደሃ ትምህርት ቤት ብሎ ነገር የለም ሁሉም ቦታ እኩል የትምህርት ስርዓት ነው ያለው፡፡

አንድ መምህር ከ4 ሰዓት በላይ አያስተምርም
፡፡
_//___
(
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔵ክፍሉን በላዩ ላይ ቆልፎ የተጫዋቾችን ባህሪ የሚያጠናው ዳኛ ።

✔️ በእግር ኳስ አለም ስለነበሩ ምርጥና ፡ ጎበዝ ዳኞች ሲነሳ ቀድሞ የሚታወሰው ጣልያናዊው Pierluigi Collina ነው ።
......
እንደዛሬው ቫር ሳይታወቅ ፡ ጎል ላይን ቴክኖሎጂ ሳይታሰብ ፡ ኦፍሳይድን የሚለይ ዲቫይስ ሳይሰራ ፡ ኮሊና ሁሉንም አሟልቶ ፡ በፍትሀዊነት ሲዳኝ ኖሯል ።
......
✔️በ2002 የአለም ዋንጫ ወቅት ነው ። ኮሊና ብራዚልና ጀርመን የሚያደርጉትን የፍጻሜ ጨዋታ ፡ በመሀል ዳኝነት እንዲመራ መመረጡን ከሰማ በኋላ ለፊፋ ሰወች አንድ ጥያቄ አቀረበ ።
.....
ኮሊና የፈለገው ነገር የብራዚልንና የጀርመንን ቀደም ያሉ ጨዋታዎች የተቀረፁበትን ቪዲዮ ( VHS ) እንዲሰጡት ነበር ።
.....
✔️እና ብዛት ያለው ቪዲዮ መጣለት ፡ ከዛም ለአንድ ቀን ተኩል ፡ ምግቡን እዛው እያስመጣ ክፍሉን ቆልፎ የሁለቱን ቡድኖች የተቀረፁ ጨዋታዎች ሲያይ ቆየ ።
.....
ኮሊና እንዲህ ነው ። አንድን ቡድን ከማጫወቱ በፊት ስለዛ ቡድን ተጫዋቾች ሁኔታ ፀባያቸው ምን እንደሚመስል ፡ ምን አይነት ተንኮሎችን እንደሚሰሩ በደንብ አጥንቶ ስለሚገባ ፡ እኔ ነኝ ያለ ተጫዋች አይሸውደውም ። አይኑን አፍጥጦ ይመጣብሀል
.....
እሱ ቫር ነው ። ጎል ላይን ቴክኖሎጂ ነው ። ሁሉም ነገር ነው ። እንደውም ፡ በእድሜ ምክንያት በ2005 ከዳኝነት በይፋ እስከተሰናበተ ድረስ ባብዛኛው ኮሊና ሲያጫውት ተበደልኩ የሚል ቡድንም ሆነ ደጋፊ በብዛት አያጋጥምም ነበር ።
.....
ምክንያቱም ስራውን ይወዳል ፡ ፍትሀዊ ለመሆን ቡድንን እንደመፅሀፍ አውቆ ጠንቅቆ ይገባል ፡ ለማንም ሳያዳላ ይፈርዳል ።
..............
በየትኛውም የስራ መስክ እንዲህ አይነት , ስራቸውን የሚወዱ ለስራቸው የሚጨነቁ ሰወች ሲኖሩ ፡ ከአገልግሎት ተሰናብተው እንኳን ፡ ስለብርታት ጉብዝናቸው እንዲህ ይወራላቸዋል
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በ 4-3-3 Films የሌለ ፊልም የለም ..

አማርኛ ፊልም 👉 @Amharic_Films

እንግሊዘኛ ፊልም👉 @Films_433

እንግሊዘኛ ፊልም በትርጉም 👉 @Eng_Amhh

ህንድ በትርጉም 👉 @Hindi_Amharic

ተከታታይ ፊልም በትርጉም 👉 @Series_Amhh

ተከታታይ ፊልም ያለ ትርጉም👉 @SeriesBayX

ቱርክ ፊልሞች 👉 @ertugrulkuruls

Animation ፊልም 👉 @Animation_FilmsHd

4-3-3 Films የነፃ ፊልሞች መገኛ 🔥
የሆነ ጊዜ ለይ በብራዚል አንድ ሌባ የ27 አመት UFC ተደባዳቢ የሆነችን ሴት ሊዘርፍ ሲሞክር በምስሉ ለይ በምትመለከቱት መልኩ ተለማምዳበታለች።

@Amazing_Fact_433
ኡጋንዳዊው የ11 አመት ታዳጊ ፡ Saad Ssozi በሰፈርም ሆነ በት/ት ቤት ፡ በትላልቅ አይኖቹ ምክንያት ሰው እያሾፈበት አምፖል አይን እያሉ የሚያበሽቁት ልጅ ነው ።
...

✅️ሆኖም Saad Ssozi ወይም በቲክቶክ ስሙ Tenge Tenge ተፈጥሮ በሰጠው ትላልቅ አይን ምክንያት ሊያፌዙበት ሲሞክሩ ማንንም አይሰማም ። እንደውም በዚህ ስድብ ከመሸማቀቅ እና ከማዘን ይልቅ በተፈጥሮ ትላልቅ የሆነው አይኑን ይበልጥ እያፈጠጠ ቀልድ ይሰራበት ጀመር ።
.......
በዚህ መልኩ ተቀባይነት ያገኘው Tenge Tenge አሁን ላይ በቲክቶክ 7.1 million እንዲሁም በኢንስታግራም 2 ሚሊየን ፎሎወሮች ያሉት ሲሆን ፡ በማስታወቂያ የሚያገኘው ብርም ቀላል አይደለም ።
እንደውም ሰሞኑን Zamelect Properties የሚባል ሪልስቴት ጋብዞት ዱባይ የተጓዘ ሲሆን ከኤርፖርት ሲገባ በሮልስ ሮይስ ፋንተም በአንደኛ ደረጃ የክብር እንግዳነት ተቀብለው ቀላል በማይባል ገንዘብ የ Zamelect Properties አምባሳደር ሆኗል ።
......
ያለ ትላልቅ አይን አንዳች ነገር ያልነበረው እና አምፖል አይን የሚል ስድብ ሲሰማ ያደገው ታዳጊ ስድቡን ወደ ገንዘብ ፡ ፌዙን ወደቢዝነስ ቀይሮ ፡ በሚወረወርበት ድንጋይ ቤት እየሰራ ፡ በዚህ መልኩ ህይወቱን እየለወጠ ነው
.....
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2024/09/28 09:30:43
Back to Top
HTML Embed Code: