Telegram Web Link
ዛሬ የቤት እመቤት ቀንን እናከብራለን!

በህይወትዎ ውስጥ ያሉትን ልዩ ሴቶች(እናቶቻችን) ለማክበር ጥሩ አጋጣሚ ነው።

አለም አቀፈዊ የቤት እመቤት ቀን በየአመቱ ህዳር 3 ላይ ይከበራል በቤቶቻችንን ውሰጥ የሚሰሩትን እናቶችን እና የቤት ሰራተኞችን ለማክበር እና ለማድነቅ የተዘጋጀ በዓል ነው።

በቻናላችን ውስጥ ያለቹ የቤት እመቤቶች ወይም ደግሞ የቤት እመቤት ልጆች የሆናችሁ ቀሪው ዘመናችሁ ያምር ዘንድ እንመኛለን።

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
ዳይመንድ ላይ ተኝታ ፡ ሰላማዊ እንቅልፍ የራቃት ኮንጎ ።

በአለም በድህነት ከሚታወቁ ሃገራት ሶስተኛዋ ዲሞክራቲክ ኮንጎ ስትሆን ፡ በጣም የሚገርመው በአለም በከፍተኛ ደረጃ አልማዝ ከሚያመርቱ ሃገራትም ሶስተኛዋ ዲሞክራቲክ ኮንጎ ናት 🤔
...........
ዛሬ ፡ በዱባይ የጌጣጌጥ መደብሮች. . በኒውዮርክ ፡ ፓሪስ ፡ ለንደን እና ቶኪዮ በሚገኙ ትላልቅ የዳይመንድ መሸጫ ሱቆች ላይ ሚሊየን ዶላሮች የሚጠራባቸው የአልማዝ ጌጣጌጦችና ወርቆች .. ተዝቀው የሚወሰዱት. . ከዚች ካልታደለች ደሃ ሃገር ነው ። እንደውም በአለም ላይ በአልማዝ ክምችታቸው ዲሞክራቲክ ኮንጎን የሚበልጡት ሩሲያና ቦትስዋና ብቻ ናቸው ።

ይሄ ብቻ አይደለም ፡ ከነዳጅ ሀብቷ በተጨማሪ ፡ በአለም ደረጃ ለሚመረቱ ለአውሮፕላን ፡ ለመኪና ለሴራሚክስና ለኤሌትሪክ እቃዎች መስሪያ የሚያገለግለው 60% የኮባልት ምርት የሚሄደው ከዚችው ሃገር ነው ።
ከላይ ያወራነው በመመረት ላይ ያለ ማእድኗን ነው ፡ ግን ይህ ብቻ አይደለም. ......
ዲሞክራቲክ ኮንጎ. . ገና ያልተነካ ከ 23 ትሪሊዮን ዶላር በላይ የሚሆን ማእድን ያላትም ሃገር ነች ። በሌላ በኩል ደግሞ በዚህ አመት ብቻ 26 ሚሊዮን ህዝቦቿ ለምግብ ዋስትና ችግር ተጋልጠዋል ። 3.4 ሚሊዮን ህጻናት ደግሞ ለከፋ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት በመዳረጋቸው የምእራባውያንን እርዳታ ይሻሉ ።
..........
ፈጣሪ በአልማዝና በወርቅ ቀላቅሎ በሰራው በዚች ሃገር ፡ ከሚኖሩ ዜጎቿ መሃል ንፁህ የመጠጥ ውሃ የሚያገኙት ግማሽ ያህሉ ብቻ ናቸው ።
ምድሯ በጣም በማእድን ከመበልፀጉ የተነሳ አንድ ሰው በባዶ እጁ ቆፍሮ ማእድን ማውጣት ይችላል የሚባልባት ኮንጎ ፡ ወደ መዋእለ ህጻናት ሄደው የሚማሩት ህጻናት አንድ ፐርሰንቱ ብቻ ናቸው ፡ ለአለም የሚበቃ ሃብት ይዛ መቶ ሚሊየን የማይሞሉ ህዝቦቿን ማኖር ባቃታት ዲሞክራቲክ ኮንጎ ፡ ውስጥ የሚንቀሳቀሱት ከአንድ መቶ ሃያ በላይ የሚሆኑ ፡ ታጣቂ ቡድኖች ግን በችግር ምክንያት አንድም ቀን የሚተኩሱት ጥይት አጥተው አያውቁም ።
.............
በአለም በወባ በሽታ በሚሞቱ ዜጎች ቁጥር ዲሞክራቲክ ኮንጎ ሁለተኛውን ደረጃ ይዛለች ፡ በዚህም ከአምስት አመት በታች የሆኑ 19 በመቶ ህጻናት በየአመቱ ለሞት ይዳረጋሉ ፡ የኮንጎ ህዝብ የሚበላና የሚጠጣ ብቻ አይደለም ችግሩ ፡ የጤና ጉዳይም ብቻ አይደለም ፡ በነጻ የሚገኝ ሰላሙን እንኳን አጥቷል ።
.............
ማእድኖቿን ወስደው መሳሪያ የሚያስታጥቋቸው ምእራባውያንም በበኩላቸው ፡ እሳቱ እንዲቀጣጠል ሰርጎገብ እስከመላክ በሚደርስ ጣልቃ ገብነት ይሳተፋሉ ። ከአመት አመት ለውጥ የለም ፡ አልማዙ ይወጣል ፡ ወርቁ ይሸጣል ፡ ማእድናቶቿ እንደጉድ ይጋዛሉ ፡ በምትኩ መሳሪያ ይጫንላቸዋል ። ስንዴ በርዳታ ይላካል ። ...............

ይህች በምስሉ ላይ የምናያትም የዲሞክራቲክ ኯንጎ ቦክሰኛ ናት ። ማርሴላት ሳኮቢ ፡ በፓሪሱ ኦሎምፒክ ላይ በተካፈለችበት ወቅት ፡ በዚህ ሁኔታ ፡ የቦክስ መድረክ ላይ ሆና ፡ አለም የኮንጎ ሁኔታ ላይ ዝምታን መምረጡ እንዳሳዘናት በምልክት በመግለፅ በሀገሯ ሰላም እንዲሰፍን በቻሉት ሁሉ እንዲያግዟቸው ጠይቃ ነበር


Wassihun tesfaye
የሃገሬ ሰው "ጮማ ራስ” የሚለው የምሩን ነው ለካ! 60% የሰው ልጅ አዕምሮ ስብ ነው!

ቀሪው 40% ውሃ፣ ጨው፣ ፕሮቲን፣ ካርቦሃይድሬት ነው! በተረፈ በደም ስሮች ና በነረቮች የተሞላ
ነው!
ግንዱ ላይ ቀጥታ ፍሬ የሚወጣበት Jabuticaba የተባለ በብራዚል የሚገኝ የእፅዋት ዝርያ

@Amazing_fact_433
" ለምንድነው እናትህ አሁንም ከአንተ ጋር የምትኖረው?"

ክሪስቲያኖ ሮናልዶን ጋዜጠኛው ክሪስቲያኖ ሮናልዶን እንዲህ ሲል
ጠየቀው:- ለምንድነው እናትህ አሁንም ከአንተ ጋር የምትኖረው? ለምን የራሷን ቤት አትገዛላትም?’

ክሪስቲያኖ መለሰ:- እናቴ የራሷን ህይወት መስዋዕት አድርጋ ነው እኔን ያሳደገችኝ፡፡ እራቴን በልቼ እንድተኛ ፆሟን ታድር ነበር፡፡

ገንዘብ የሚባል ነገር ጭራሽ አልነበረንም፡፡ የመጀመሪያውን የእግር ኳስ ትጥቄን አሟልቼ እንድጫወት በሳምንት ሰባት ቀን፤ እና ምሽቱን ጽዳት ሠራተኛ ሆና አሳልፋለች፡፡

የኔ ጠቅላላ ስኬት ለእሷ የተሰጠ ማስታወሻ ነው። እኔ በህይወት እስካለሁ ሁልጊዜም ከጎኔ ትኖራለች፡፡ ከእኔ ማግኘት ያለባትን ሁሉ እሰጣታለሁ:: መሸሸጊያዬና የህይወቴ ታላቋ በረከት ናት።

ክብር ለእናቶች

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
በአሜሪካ ሰሜን ካሮሊና ውስጥ Whynot የምትባል ከተማ አለች። ስያሜዋን ያገኘችውም የከተማይቱ ሰማዎች ለከተማዋ ስም ለማውጣት ክርክር ላይ እያሉ አንዱ ይህ ስም ለምን አይሆነም ሌላው ያ ስም ለምን አይሆንም እየተባባሉ ከስምምነት ባልደረሱ ጊዜ አንድ ሰው ለምን "ለምን አይሆንም" የሚለው ስም ራሱ ስም አይሆንም የሚል ሀሳብ በማንሳቱና ነዋሪዎቹ በመስማማታቸው ምክንያት ከዚያን ወዲያ ጀምሮ Whynot እየተባለች መጠራት ጀምራለች

@Amazing_fact_433
በ1950ዎቹ በሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ በተደረገ ጥናት ዶር ከርት ሪቸተር ሶስት አይጦችን ወስዶ ውሃ በሞላበት እቃ ውስጥ አስቀመጣቸው::

አይጦቹ ምን ያክል ከውሃው ለመውጣት ወደ ላይ ይዋኛሉ የሚለውን መፈተን ነበር የዚህ ጥናት ዓላማ::

በአማካይ ከ15 ደቂቃ በሗላ አይጦቹ ተስፋ በመቁረጥ ውሃው ውስጥ ይሰጥሙ ነበር::

ተመራምሪዎች ሌሎች አይጦች አምጥተው አይጦቹ ተስፋ ቆርጠው ከመስጠማቸው በፊት በእጃቸው ጠልቀው ያወጧቸውና አድርቀው ለጥቂት ደቂቃዎች እንዲያፉ ያደርጏቸዋል::

ከዛም በሗላ ለሁለተኛ ዙር ወደ ውሃው ውስጥ ይጨምሯቸዋል::

በሁለተኛው የሙከራ ጊዜ አይጦቹ ውሃ ውስጥ ለመውጣት ለምን ያክል ጊዜ የሞከሩ ይመስላችህሗል? አስታውሱ: ተስፋ እስከመቁረጥ የዋኙት ከትንሽ ደቂቃዎች በፊት ነው...

ምን ያክል ጊዜ የዋኙ ይመስላችሗል?

ሌላ 15 ደቂቃ? 10 ደቂቃ? 5 ደቂቃ? አይደለም! 60 ሰአት!

ይሄ በስህተት የተከሰተ አይደለም። እውነት ነው ለ60 ሰአት ከውሃ ውስጥ ለመውጣት ዋኝተዋል.

ከዚህ የተወሰደው መደምደሚያ ምንድነው; አይጦቹ ሊያድናቸው የሚመጣ እንዳለ ሲያምኑ ሰውነታቸውን በመጀምሪያው ዙር አይቻልም ብለውት ከነበረው ገደብ በብዙ አልፈው መግፋት ችለዋል::

ከዚህ ሃሳብ ጋር እተዋችሃለሁ:

ተስፋ የደከሙ አይጦችን 60 ረጅም ሰአት እንዲዋኙ ካስቻላቸው, እኛ ፈጣሪ አንድ ቀን እንደሚደርስልን ብናምን, ምን ያክል ልንጏዝ እንችላለን?

የፈጠራችሁ አምላክ አንድ ቀን እንደሚደርስላችሁና እንደማይረሳችሁ አስታውሱና በርትታችሁ ተስፋ ባለመቁረጥ የህይወትን የውጣ ውረድ ዋና ዋኙ! በርቱ!
Winnie-the-Pooh የተባለው የካርቶን ፊልም በሀገረ ቻይና እንዳይታይ ታግዷል ፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት ሜመሮች ከቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂፒንግ ጋር ስላመሳሰሉት ነው ፡፡ እናም በቻይና ማንም ሰው የዚህን ካርቶን ፊልም ስም በሶሻል ሚዲያ መጥራትም ስለሱ መፃፍም የተከለከለ ሆኗል ! !

@Amazing_Fact_433
@Amazing_Fact_433
በ 4-3-3 Films የሌለ ፊልም የለም ...

አማርኛ ፊልም 👉 @Amharic_Films

እንግሊዘኛ ፊልም 👉 @Films_433

እንግሊዘኛ ፊልም በትርጉም 👉 @Eng_Amhh

ህንድ በትርጉም 👉 @Hindi_Amharic

ተከታታይ ፊልም በትርጉም 👉 @Series_Amhh

ተከታታይ ፊልም English 👉 @SeriesBayX

ቱርክ ፊልም👉 @ertugrulkuruls

Animation ፊልም 👉 JOin Here

ሆረር ፊልም 👉 JOin Here

የፍቅር ፊልም 👉 JOin Here

Action ፊልም 👉 JOin Here

Comedy ፊልም 👉 JOin Here
አይማን አሊ ይባላል የጆርዳን ተወላጅ ሲሆን የ 22 ዓመት ወጣት ነው በቲክ ቶክ ገፁ ከ 1. በላይ ተከታይ አለው Instagram ምም እደዛው ይሄ አይግረማቹ በሀገሩ ጆርዳን አሉ ከተባሉ ቆንጆ እና ውብ ወንዶች አንዱ እሱ ነው

እናም በ 2023 የካንሰር ታማሚ እደሆነ አወቀ ለአንድ አመት ያህል በ ኬሞቴራፒ ቆየ

በዚህ አንድ ዓመት ውስጥ ግን ይሄ የምታዩት ውበት ቁንጅና የሰውነት ቅርፅ የፊቱ ፂም ፀጉሩ እርግፍ ብሎ ጠፋ በሽታው ክፉ አደል እግዚአብሔር ሁላችንንም ከዚህ በሽታ ይጠብቀን 🙏

እና ወደ ታሪኩ ስመልሳቹ እሱ ሆስፒታል ሆኖ በዙ ጠላቶች ስላሉት ሞቷል ብለው የቲክቶክ ሚዲያውን ሞሉት

ይሄን የሰሙ በሚዲያ ታዋቂ የሆኑ ድህረ ገፆች ሆስፒታል ድረስ በመሄድ ኢንተርቪ አደረጉለት አለመሞቱንም በዛው አረጋገጡ ነገር ግን እሱ ለዓመት ከሚዲያ ቢርቅም አጋጣሚውን ተጠቅሞ ምን አስተላለፈ መሰላቹ

እኔ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆኜ ሰውነቴ አልቆ ውበቴ እረግፎ የመዳን ተስፋ አለኝ ፈጣሪ ይመረኛል ጥሎ አይጥለኝም

በህመሜ ውስጥም ፈጣሪዬን አመሰግነዋለሁ

እናንተም ተስፋ የሜያስቆርጥ ነገር ቢገጥማቹ
ይሄንን መቋቋም እና ማለፍ አልችልም ብላቹ በፍፁም ተስፋ አትቁረጡ

በመከራ ውስጥም በደስታ ውስጥም ፈጣሪ አለ የማያልፍ ቀን የለም ሁሌም አልሃምዱሊላህ በሉ
ከህመሜ እዳገግም በፀሎታቹ/በዱዓቹ አስቡኝ አለ

አያቹ እሱ በዚህ ነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ በሆነበት ሁኔታ ውስጥ ፈጣሪን አረሳም በፈጣሪ ሙሉ ተስፋ አልቆረጠም
ማመስገን አላቆመም በጠፋው ውበቱም አላማረረም እደውም ባሳለፍኩት ቀፋፊ ሂወት ትምህርት ሆኖኛል ሁሉም ነገር አላፊ ጠፊ ነው አለ

እኛ ግን ምንም ሳንሆን የሆነች ነገር አልሳካ ካለን በትንሹም በትልቁም ፈጣሪ እረስቶኛል ፈጣሪ ዘገየብኝ ፈጣሪ ያዳላል እያልን እናማርራለን

በምንም ይሁን በምን ባለን ነገር ተመስገን ማለት ይልመድብን

አይማን እግዚአብሔር ጨርሶ ይማረው እኛም ከኛ
የባሰውን እያየን እናመስግን🙏
ይህች ልጅ sahar tabar የምትባል ሞዴል ኢራናዊት ናት። ምን ዋጋ አለው እንዲሉ ፈጣሪ ውብ አድርጎ ቢፈጥራትም በጣም ውብ መሆን ፈለገችና በጣም የምታደንቃትን Angelina Jolie መምሰል ፈለገች። ወደ አንድ ፕላስቲክ ሰርጀሪ ወደሚሰራ ክሊኒክ ሄደችና ክፍያዋን ከፍላ አንጀሊና ጆሊን አስመስላችሁ ስሩኝ አለች። ፕላስቲክ ሰርጀሪው ረጅም ጊዜ ወስዶ ተሰራላት።

ለውጡ የሚከተለውን መስሏል !!

ፈጣሪ ሁላችንንም የፈጠረን ራሳችንን እንድንሆን አድርጎ ነው! ውበታችን ጎልቶ የሚወጣውም ሌላን ሰው ስንመስል ሳይሆን ራሳችንን ስንሆን ብቻ ነው!
አንዲት የክፍላቸው ተማሪ ካንሰር ትታመማለች
እናም በሚደረግላት ህክምና ምክንያት እንደተለመደው ፀጉሯ ቀስበቀስ ይመለጣል።
ታድያ የክፍል ጓደኞቿ ልዩነት እንዳይሰማት ብለው አድርገው የጠበቋት ነገር ድንቅ ነበር።
@Amazing_Fact_433
@Amazing_Fact_433
❤️respect 🙌
በቀለኛው እንስሳ ነብር ነው። ነብር በቀለኛ በመሆኑ በእጅጉ ይነገራል። ጉዳት ያደረሰበትን አለያም ደግሞ የተተናኮለውን ተከታትሎ የበቀል ምላሽ በመስጠት ይታወቃል። ለምሳሌ በህንድ ሀገር ውስጥ አንድ ገበሬ የሆነ ነብር ላይ ጉዳት አድርሶበት ነበር ከቀናት በውሀላ ነብሩ ገበሬው ቤት ድረስ ሄዶ ገበሬውን ገድሎታል።

@Amazing_Fact_433
⚡️

በቅርብ የተዋወኳት ልጅ አለች። ናርዶስ ትባላለች። እድሜዋ ከ14 ብዙም የሚያልፍ አይደለም።

እንዴት ተዋወኳት?

ከትምህርት ቤት ስመለስ የማልፈው በነሱ በር ነው። ሁሌ በራቸው ላይ አያታታለሁ። ስታየኝ ፈገግ ትላለች። ላለማስከፋት ፈገግታዋን በስስ ፈገግታ እመልስላታለሁ። ትስቃለች።

አንድ ቀን በደጃቸው ሳልፍ በዚሁ ፈገግታ እየሮጠች ወደ እኔ መጣችና እጇን ለሰላምታ ዘረጋችልኝ። ጨበጥኳት። አመሰግናለሁ አለችኝ። ድምጿን ስሰማ ደነገጥኩ። ድምጿ እና መልኳ አይገናኝም። ጎርነን ያለ ድምጽ ነው ያላት። ያልጠበኩት ድምጽ ስለሆነ ትኩር ብዬ አየኋት። ፈገግ አለች። ፈገግ አልኩላት። ደስ አላት። እየሮጠች ወደ ቤቷ ገባች።

ሌላ ቀን ከትምህርት ቤት ስመለስ ጠብቃ በተለመደው ፈገግታዋ ካስቆመቺኝ በኋላ ሂሳብ ብዙም ስለማይገባኝ እንድታስጠናኛ ፈልጋለሁ አለቺኝ። ድፍረቷ ገረመኝ ደስ አለኝም። ምክንያቱም ከዚህ በፊት እንዲህ አይነት ነገር አልገጠመኝም።

ጊዜ ስለሌለኝ ሰፋ ላለ ጊዜ ማስጠናት እንደማልችል እና ጥያቄዎች ካሏት ጥያቄዎቹን ልሰራላት እንደምችል ነገርኳት። ለተወሰነ ጊዜ በዚህ መንገድ በራቸው ላይ ሳስጠናት ቆየሁ።

የሆነ ቀን በደጃቸው ሳልፍ የነናርዶስ በር ላይ ግርግር አለ። ጠጋ ብዬ አየሁ። ናርዶስ ለያዥ ለገናዥ  አስቸግራለች።

"ሴት አይደለሁም ወንድ ነኝ። ሴት ብላችሁ አትጥሩኝ ናርዶስ አይደለሁም።"

"አጭበርባሪ ነው ይሄ መንፈስ እያታለለ ነው...

"ፀበል የለሞ እንዴት...

"አንድ ሰው ጋር ደውሉ እንጂ...

እኔ ባለሁበት ደርቄ ቀረሁ። ናርዶስ...

ግቢያቸው ውስጥ አጥር ተደግፋ ወደ ቆመች ሴት ተጠጋሁና ናርዶስ ምን ሆና እንደሆን ጠየኳት።

"ያማታል! ጉብዝናዋ ላይ አሰሩባት። ቁንጅናዋ ላይ እንደዚህ አረጉባት ። ይኸው ትምህርቷን ካቆመች 3አመት ሆነ። እሷን ለማዳን ያልዞርንበት ሃኪም ቤት ያልተንከራተትንበት ፀበል የለም። ግን ምንም ለውጥ የለም።" እንባዋን በስሱ አፈሰሰችው። እንባዋን በመዳፏ ጠረገችና...

"ሁልጊዜም ከጠዋት እስከ 6 ሰዓት ደህና ትሆናለች።  እንጫወታለን እናወራለን ብዙዙ እናወራለን። ድምጿ እንዴት እንደሚያምር። ምን ያደርጋል ደህንነቷ ከ7 ሰዓት አይዘልም። ውስጧ ያለው መንፈስ ይቀሰቀሳል። ድምጿ ይጎረንናል መንፈሱ ማጥመድ ከሚፈልገው ሰው ውጪ ማንንም አትቀርብም አታወራም።" ብላ ትክዝ አለች።

ባለሁበት ደርቄ ቀረሁ።

እና እስካሁን ሳስጠና የነበረው እሷን ነው ወይስ እሱን ነው
?

ቀጣዩ ክፍል 200 Like በኋላ ይቀጥላል

Inbox የተላከ እውነተኛ ታሪክ ነው
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
💘

"ሁልጊዜም ከጠዋት እስከ 6 ሰዓት ደህና ትሆናለች።  እንጫወታለን እናወራለን ብዙዙ እናወራለን። ድምጿ እንዴት እንደሚያምር። ምን ያደርጋል ደህንነቷ ከ7 ሰዓት አይዘልም። ውስጧ ያለው መንፈስ ይቀሰቀሳል። ድምጿ ይጎረንናል መንፈሱ ማጥመድ ከሚፈልገው ሰው ውጪ ማንንም አትቀርብም አታወራም።" ብላ ትክዝ አለች።

ባለሁበት ደርቄ ቀረሁ።

እና እስካሁን ሳስጠና የነበረው እሷን ነው ወይስ እሱን ነው?

ውስጤን ደነዘዘኝ። ያልሞቀ አካሌን ላብ ላብ አለኝ። ብዬ ብዬ ደደብ መንፈስ ላስጠና¡ (ይሄን ቃል ውስጤ እንጂ አንደበቴ አላለውም። ምክንያቱም የሚተነፍስ በድን ሆኛለሁ።)

መሸሽ ፈለኩ። ወዴት እንደምሸሽ ግን አላውቅም። እየተከተለኝ ቢሆንስ? ምናልባት ውስጤ ቢሆንስ? ወረረኝ። መላ አካሌን ወረረኝ።

ልጅቷን አይዞሽ ብዬ ዞር ስል ከናርዶስ ጋር አይን ለአይን ተፋጠጥን። ስታየኝ(ሲያየኝ) ፈገግ አለች። አለ። ማማተብ ፈለኩ።

ጣቴን መስቀልኛ ላጣምራት ስል እጄን አሰረኝ። እንዳላማትብ ቆለፈኝ። አሁን በቁጥር የማላስታውሰውን መጠን ያህል አማተብኩ ።

አሁንም የናርዶስ አይን አይኔ ላይ እንደተተከለ ነው። ማማተብ አቃተኝ። እጄ እግሬ ላይ የተሰፋ መሰለኝ። እኔን ስታየኝ ሊይዟት አቅም አነሳቸው መሰለኝ ለቀቋት። ፈገግታዋ እየጨመረ ተጠጋችኝ። 

"እየጠበኩህ ስትቆይብኝ እኮ ...

ሰው ሁሉ ተኣምር የሚያይ ይመስል አፉን ከፍቶ ዙርያችንን ከቦ ይመለከተናል።

"ለምን ቆየህ?"

እ...
"መልስልኝ እንጂ! ለምን ዘገየህ? አንተን አይደል ስጠብቅ የነበረው።"

"ት ን ሽ  ስ ራ  በ ዝ ቶ ብ ኝ  ነ ው!" አፌ ተንተባተበ። ፈቅጄ አልነበረም ቃል ከአፌ የወጣው። ማን አስገደደኝ? ማን አፌን ከፈተው? ማን በዚህ መንገድ እንድመላለስ እግሬን አስለመደው?

"ስለምን ትጎዳኛለህ? ላንተ ስል ስንቱን ትቻለሁ። የምረጋጋው ሳይህ ነው። አቅም የማገኘው ሳይህ ነው።"

ጆሮዬ ይጮኻል። ገላዬ ይጮኻል። የሰው አይን ይጮኻል። መንገዱ ይጮኻል። መኪናው ይጮኻል። ህንፃው ይጮካል።

በዚህ ሰዓት ለኔ ጊዜ የሚቆጥር አይመስለኝም። ለምን? ልቤ ቆሟላ። ስለምን ላስብ? ህይወትን ለማሸነፍ ደፋ ቀና ማለቴን? መኖር የጭቃ ዳገት ሆኖብኝ ወደ ፈኋላ መፈጥፈጤን? መንገድ ልቤን ሲሰብረው ልቤ እስኪድን ላለመቆም በእግር መሄድ መጀመሬን? በሰይጣን መታጨቴን? ለመንፈስ መገበሬን? ስለምን ላስብ?

ህልም ቢሆን የሚባልላቸው ብዙ ሁነቶች አሉ። ይህም ህልም በሆነ...!

በፍጥነት ገፍትሬያት አልፌያት ሄድኩ። አዳሬን እንቅልፍ በአይኔ ሳይዞር ነጋ። እንዳፈጠጥኩ ዶሮ ጮኸ። እንዳፈጠጥኩ ወፎች ዘመሩ። እንዳፈጠጥኩ...

በተኛሁበት ልብሴ ፊቴን ሳልታጠብ ስራ ገባሁ። ማስተማር አይበለው! ሁኔታዬ ለራሴ ግራ እስኪገባኝ ድረስ ተለወጠ። እያስተማርኩ መንቀጥቀጥ ጀመርኩ። የተማሪው ፊት ሁሉ የናርዶስ ፊት መሰለኝ። ድምፃቸው ሁሉ ጎረነነብኝ።

"ሰርዬ እንዴ ሰር ምን ሆነህ ነው?"

"አረ ቢሮ ሰው ጥሩ ሰርዬ...

መሸሽ ፈለኩ። ወዴት እንደምሸሽ ግን አላውቅም። እየተከተለኝ ቢሆንስ? ምናልባት ውስጤ ቢሆንስ?

የመጨረሻው ክፍል ነገ ማታ 2 ሰአት ይጠብቁን እስከዛ
👍👍
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2024/11/15 06:17:05
Back to Top
HTML Embed Code: