Telegram Web Link
😳ስለ ጥፍራችን አንዳንድ አስገራሚ ነገሮችን ልንገራቹ-የጥፍር ቀለም ቅርፅና ስፋት ለተለያዩ የጤና ችግሮች መጋለጣቸውን እንደሚያሳይ ተገለፀ!!!ከታች የተዘረዘሩት ነጥቦች ጥፍሮቻችን ለአደገኛ ለአደገኛ በሽታ መጋለጣቸውን ሊያሳዩን ይችላሉ
1 የጥፍር ቀለም መቀያየር
2 የጥፍር መወፈር
3የጥፍር መሰንጠቅ
4የጥፍር ወደ ውጪ መታጠፍ እና 5የጥፍር መቦርቦር ናቸው
እነዚህ ምልክቶች ሰውነታችን እክል እንዳጋጠመው የሚያሳዩ ማስጠንቀቂያዎች ሊሆኑ ይችላሉ!!!🙈
የስምንት አመቷ ታዳጊ እና ማራዶና ( እንደልቡ )
....

የቀድሞው የኪውባ ፕሬዝደንት ፊደል ካስትሮ እጅግ አድርገው የሚያቀርቡትና እንደጓደኛቸው የሚያዩት ዲያጎ ማራዶና ፡ ከእፅ ሱሰኝነት ተላቆ ሰላማዊ ህይወት እንዲመራ ይፈልጉ ነበር ።

✔️እና አንድ ጊዜ ወደ እሳቸው ጋር መጥቶ ከዚህ ሱስ እንዲታቀብ ለማድረግ ወደ ኪውባ ጠርተውት ነበር ።
....
በነገራችን ካይ ኪውባ ለማራዶና ሁለተኛ ሀገሩ ናት ፡ በፈለገበት ጊዜ ወጥቶ የሚገባባት ፡ ከህዝቡ ጋር ቤተሰብ ሆኖ የሚኖርበት ቦታው ነው ።
....
እና ከሱስ እንዲያገግም ጠርተውት በነበረበት ወቅት ፡ የተከበረውን የኪውባ የነጻነት በአል አስመልክቶ በተዘጋጀው የእራትና የሙዚቃ ምሽት ላይ ተገኝቶ እየተዝናና ነው ።

በዚህ ትልቅ ፕሮግራም ላይም ፡ ትላልቅ የፖለቲካ ሰወች ፡ ታዋቂ አርቲስቶችና የእግር ኳስና የኪነጥበብ ሰወች ተገኝተዋል ።
....
የምግብ ግብዣው ከተጠናቀቀ በኋላ ፡ Havana Fiala የሚለው ተወዳጅ የኪውባ ሙዚቃ ተከፍቶ እየተጨፈረ እያለ. .. አንዲት ልብሶቿ በመኪና ዘይትና ግሪስ የቆሸሹ ፡ ፊቷ የተጎሳቆለ. .. ከእድሜዋ በላይ ብዙ ችግር ያየች የምትመስል የስምንት አመት ታዳጊ ፡ ድንገት የአዳራሹን በር ከፍታ ገባች ።
.........
ይደንሱ የነበሩት ሰወች ሁሉ ድንገት ወደ አዳራሹ የገባችውን ታዳጊ. .. ይህች ደግሞ ምን ልትሆን መጣች በሚል መንፈስ እየተመለከቷት እያለ አስተናጋጆች ፡ ሳትጋበዝ በድንገት ወደ አዳራሹ የገባችውን ልጅ እያቻኮሉ አስወጧት ።
....
በስፍራው የነበሩት ተጋባዦች አንዲት ጎስቋላ ልጅ ፡ በድንገት ወደ አዳራሹ ገብታ ፡ በአስተናጋጆች ስትባረር ቢያዩም ፡ ከአንድ ሰው በስተቀር ፡ ሁሉም ተጋባዦች ምንም እንዳልተፈጠረ ቆጥረው ወደቀድሞው ሙዳቸው ተመለሱ ።
ያ የልጅቱን መግባትና ፡ ወዲያውኑ በአስተናጋጆች መባረር ከልብ ያሳዘነው ሰው ማራዶና ነበር ።
...
እና ማራዶና ይህንን አይቶ ዝም ማለት አልቻለም ፡ ዳንሱን አቋርጦ ታዳጊዋን ሊፈልግ ወጣ ።
....
ልጅቱ የመንገዱ ዳር ቁጭ ብላ ታለቅሳለች ።
....
በቤተሰቧ የኑሮ አቅም ማነስ ምክንያት መማር ስላልቻለች በዚህ እድሜዋ በአካባቢው በሚገኝ አንድ ጋራዥ የምትላላክ ናት ፡ እና ባጋጣሚ በዛ ስታልፍ የሙዚቃው ድምፅ ስቧት ለመጫወት ለመጨፈር ነበር የገባችው ።
...
ማራዶና ልጅቱን ካባበለ በኋላ እጇን ይዞ ወደ አዳራሹ ይዟት ገባ ።
......
በስፍራው የነበሩ ሁሉ በግርምት አዩት ። ምግብ አስቀረበላት ፡ ስትጨርስም ፡ ልክ እንደልጁ እጇን ይዞ አብረው ጨፈሩ ፡ ብዙዎች ከእሱ ጋር አብረው ለመደነስና ፎቶ ለመነሳት ፈልገው እየጠበቁት እንደሆነ ቢያውቅም ሙሉ ትኩረቱን ለልጅቱ ሰጥቶ የናፈቃትን ጭፈራ አብሯት ደነሰ ።
.........
እና ሙዚቃው ሲያልቅ እጇን ይዞ ከአዳራሹ ጀርባ ወዳለው ትልቅ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይዟት ሄደ ።
....
በዚህ አዳራሽ ውስጥ እንደጓደኛ የሚያያቸው የኪውባው ፕሬዝደንት ፊደል ካስትሮ ፡ ከኮሎምቢያው መሪ እና ከሌሎች ትላልቅ ፖለቲከኞች ጋር ውይይት ላይ ነበሩ ።
.......
የጦፈ ውይይት ላይ የነበሩት ሰወች ማራዶና ታዳጊዋን ይዞ ወደ አዳራሹ ሲገባ በማየታቸው በግርምት ያዩት ጀመር ።
.....
ማራዶና መናገር ጀመረ ።
ጓደኞቼ ስላቋረጥኳችሁ ይቅርታ ፡ ግን ይህን መናገር ስላለብኝ ነው ከዚህች ታዳጊ ጋር የመጣሁት ።
ወዳጆቼ ፡ በርግጥ እኛ ምንም አልጎደለብንም ፡ እንበላለን እንጠጣለን ፡ ዛሬ ደግሞ የአብዮቱን በአል ለማክበር እየጠጣን እየጨፈርን ነው ።
ቪዳል ታያለህ ( ቪዳል ካስትሮን የሚጠራበት ስም ነው ) ቪዳል ታያለህ ? ይህችን መሳይ ምስኪኖች ግን በኑሮ ደረጃቸው ምክንያት በዚህ እድሜያቸው ተጎሳቁለዋል ።
ጓደኛዬ ፊደል ይህን በተመለከተ የሆነ ነገር ማድረግ ያለብህ ይመስለኛል ብሎ ወጣ ።
.....
ልጅቱን ከስጦታ ጋር ወደቤተሰቦቿ ላካት ።
....
ይህ ከሆነ ከቀናት በኋላ ፡ የኪውባ ፕሬዝደንት ፡ በጓደኛቸው በዲያጎ ማራዶና አሳሳቢነት. .. ለታዳጊ ወንዶችና ሴቶች የጉልበት ብዝበዛን የሚከለክልና ፡ ጥበቃ የሚያደርግ ፡ በኑሯቸው ምክንያት የተጎሳቆሉትን የሚንከባከብ " White Decree " የተባለውን ህግ በአዋጅ እንዲፀድቅ አደረጉ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የአውሮፓዋ ሀያሏ ሀገር ጀርመን በጣም ብዙ የኤሌክትሪክ ሀይል ያላት ሲሆን በጣም የኤሌትሪክ ሀይል ከመብዛቱ የተነሳ ለህዝቦቿ ኤሌክትሪክን ሲጠቀሙ በየ ወሩ አበል ወይም ተቆራጭ ገንዘብ ትከፍላቸዋለች!

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
በምስሉ ላይ ከሚያማምሩ ልጆቿ ጋር የምናያት አሜሪካዊቷ አክትረስ ጄኔፈር ጋርነርን ነው ።
.....
እና እነዚህ የጄኔፈር ጋርነር ልጆች ቤት ውስጥ ማክበር የሚጠበቅባቸው የቤት ውስጥ መተዳደሪያ ህግ አለ ። ይህ ህግ ስማርት ስልክን የሚከለክል ነው ። በዚህ ህግ መሰረትም የጄኔፈር ልጆች ከትምህርት ሲመጡ ፡ ስልክ ይዞ ቁጭ ማለት አይችሉም ። ስልክ የሚፈቀደው በሳምንት አንድ ቀን እሁድ ለዛውም ፡ ሳምንቱን በመልካም ስነምግባር ሳይረብሹ ካሳለፉ ብቻ ነው ።
........
🥅 ከዛ ውጭ የጄሎ ልጆች ከጥናት ውጭ ያለ ጊዜያቸውን የሚያሳልፉት ፡ በቤት ውስጥና ፡ በጊቢዋ ውስጥ በተዘጋጀላቸው ፡ ቦታ ፡ ኳስ ፡ ሆኪ ። ጆተኒ ፡ ባስኬት ቦል እና የመሳሰሉ ጨዋታዎችን በመጫወት ነው ።

🛴 በነገራችን ላይ ጄኔፈር ብቻ ሳትሆን , እስከቅርብ ጊዜ ድረስ ዩቲዩብን በዋናነት ታስተዳድር የነበረችው Susan Wojcicki እንዲሁም ማርክ ዙከርበርግ ... ታዋቂዋ የቴኒስ ሻምፒዮና ሴሪና ዊሊያምስ ልጆቻቸውን ስልክን በዘፈቀደ እንዳይጠቀሙ ህግ ያወጡ ዝነኞች መሀል ይገኙበታል ።
.......
ዝነኛው የእግር ኳስ ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶም ለልጆቹ ስልክ ከመስጠት ይልቅ የተለያዩ ጨዋታዎች እንዲጫወቱ በማድረግ ይታወቃል ።
.....
ከዚህም ሌላ አሁን አሁን በተለያዩ ሀገራት ታዳጊ ልጆች በቤት ውስጥ የተለያዩ ጨዋታዎችን እንዲጫወቱ የሚያበረታቱ ነገሮች በማድረግ ላይ ይገኛሉ ።
....
በኛስ ሀገር?
ታዳጊ ልጆች ጣፋጭ የሆነውን የልጅነት ጊዜ ስልክ ላይ ተጠምደው ማሳለፍ በኛ ሀገርም እጅግ የተለመደ ነገር እየሆነ ነው ። ነገር ግን ይህ ለልጆች ከጎጂነቱ ውጭ ብዙም ጥቅም እንደሌለው በመረጋገጡ ነው እነዚህ ትላልቅ ዝነኞች ልጆቻቸውን ከዚህ ያገዱት

....
ከ1ሺ በላይ መጽሐፎች(በPdf) የሚገኙበት ግዙፍ ዲጂታል ላይብረሪ!

👇👇
@Bemnet_Library
@Bemnet_Library
በወጣትነቱ Stallone በጣም ደሀ የነበረ ሲሆን ውሻውን በ 40$ ይሸጠዋል  በኃላ የሀብት ማማ ላይ ሲወጣ ውሻውን ደግሞ በ15,000$ መግዛት ቻለ። ሰሞኑን የውሻ ቀን ነው በዚህ አጋጣሚ ውሻ ያላችሁ ሰዎች እንኳን አደረሰላችሁ።😁

August 26 dogs birthday 🐕

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
የእስስት ምላስ የሰውነቷን ሁለት እጥፍ ይረዝማል፡፡

እስስት ሁለቱን አይኖቿን በአንድ ጊዜ በተለያየ አቅጣጫ ላይ ማሳረፍ ትችላለች። ለምሣሌ አንዱን ግራ አንዱን ቀኝ፣ አንዱን ላይ አንዱን ታች፤ አንዱን ግራ ጥግ አንዱን ቀኝ ጥግ ላይ ማሳረፍ ትችላለች፡፡

እስስት ሙሉ ለሙሉ አይኗ ቢጠፋም የቆዳዋ ቀለም የአካባቢውን የቀለም አይነት ተመስሎ መቀያየር ይችላል፡፡ ስለዚህ እስስቶች የአካባቢያቸውን ቀለም የሚያነቡት በአይናቸው ብቻ ሳይሆን በቆዳቸውም ጭምር ነው
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በየቀኑ ለ 40 ደቂቃ ያህል ሙሉ በሙሉ ዓይነ ስውር እንደሚሆኑ ያውቃሉ ?

ይህ የሚሆነው እይታዎን ከአንድ ነገር ወደ ሌላ ሲቀይሩ ነው። ሚገርመው ነገር ደግሞ የደበዘዘ ምስል ላለማሳየት ሲል አንጎላችን ሆን ብሎ እይታችንን ይከለክለናል።

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
የሎተሪ ቲኬቶችን  ከማሸነፋ በመንገድ ላይ የመሞት እድል ሎተሪ ከማሸነፍ እድል  ከፍ ያለ ነው😁

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
ባለፈው ሳምንት ጃፓን አየር መንገድ ውስጥ ሁለት መቀስ ጠፍቶ ከ44 በላይ በረራዎች እንዲቋረጥና የመንገደኞች ተርሚናል እንዲዘጋ ተደርጎ ነበር።

ይህ የሆነበት ምክንያት ምንአልባት መንገደኞቹ መቀሱን አውሮፕላን ውስጥ ይዘው ገብተው በድምፅ አልባ መሳሪያነት ተጠቅመው አውሮፕላኑን ሊጠልፉ ይችላሉ ተብሎ ተሰግቶ ነው !
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በሰዓት አቅጣጫ የምትሽከረከር ብቸኛዋ ፕላኔት ቬነስ ናት። በ225 የምድር ቀናት አንድ ጊዜ በፀሐይ ዙሪያ ይጓዛል ነገር ግን በ243 ቀናት አንዴ በሰዓት አቅጣጫ ይሽከረከራል።

@Amazing_Fact_433
@Amazing_Fact_433
ይሄንን ያውቃሉ⁉️

ክርስትያኖ ሮናልዶ በካናዳ ዩኒቨርስቲ እንደተማረስ ያውቃሉ?

በሌላ በኩል... በብሪቲሽ በኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ የአራተኛ ዓመት የሶሺዮሎጂ ተማሪዎች የክርስቲያኖ ሮናልዶን ሕይወትና ሥራ እንደምያጠኑስ ያውቃሉ?

@Amazing_Fact_433
@Amazing_Fact_433
ይህ የምትመለከቱት ጎረቤት ሱዳን መገኛውን ያደረገ _የአለማችን ብቸኛው እንስሳ ነው ምክንያት ካላቹ ደሞ ከዝርያው የመጨረሻው እሱ ነው እሱ ከሞተ በኋላ አለም ላይ Northerner White Rhino የሚባል እንስሳ አይኖርም ለዛም ነው በወታደሮች የሚጠበቀው

@Amazing_Fact_433
@Amazing_Fact_433
ይህ ሰው በተለያዩ 20 ሬስቶራንቶች ከተመገበ በኋላ ገንዘብ ላለመክፈል ሲል የልብ ህመሙ እንደተነሳበት በማስመሰል ወንጀል በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል ። ቅጣትም ተላልፎበታል።

@Amazing_Fact_433
@Amazing_Fact_433
Vijay Sethupathi ምርጥ ከሚባሉት የቦሊውድ አክተሮች መሀከል አንዱ ነው ።
Krithi Shetty ም በቅርብ ጊዜ ቦሊውድን ተቀላልቅለው ጥሩ ስም ካፈሩ አክትረሶች መሀል ትመደባለች ።
እና እነዚህ ሁለቱ Uppena የሚል ርእስ ያለው አንድ ተወዳጅ ፊልም አብረው ተውነዋል ።
በዚህ ፊልም ላይ ፡ ቪጄ የክሪቲ አባት ሆኖ ነበር የሰራው ።
......
ይህ ፊልም ከተሰራ ከተወሰኑ ጊዜያት በኋላ አንድ ፕሮዲውሰር ፡ ሌላ ፊልም ፅፎ ቪጄ ዋና ተዋናይ ሆኖ ከክሪቲ ጋር እንዲሰራ ጥያቄ አቀረበለት ።
.........

ምን አይነት ፊልም ነው ሲል ቪጄ ጠየቀ
" የፍቅር ፊልም ነው ፡ ካንተ ጋር የምትሰራውም የምትግባባት የምታውቃት ሴት ናት "
ማናት ?
" Krithi Shetty ናት "

ቪጄ ይህንን እንደሰማ ፡ ለፕሮዲውሰሩ ከሷ ጋር መስራት እንደማይፈልግ ነገረው ።
..........

ምክንያቱ ደግሞ ፡ ከጥቂት አመታት በፊት ከክሪቲ ጋር አባትና ልጅ ሆነን ተውነናል ። እኔ በእድሜ ከሷ በጥቂት እድሜ የምታንስ ልጅ አለችኝ ። እና ከክሪቲ ጋር እንደ አባትና ልጅ ሆነን ስንሰራ ፡ የእውነት አባቷ የሆንኩ ያህል ደስ ብሎኝ ነው የሰራሁት ።
...
እና አሁን ደግሞ. .. ከዚህች የልጄ የእድሜ እኩያ ከሆነችና ፡ እንደ አባቷ ሆኜ አብሬ ከሰራሁ ልጅ ጋር ፡ እንደ አፍቃሪ ሆኜ መስራት አልፈልግም ። እሷን በፍቅር እያሰብኩ ፡ በዚህ ቅልጥ ያለ የፍቅር ታሪክ ያለው ፊልም ላይ መስራት አልችልም ። የፊልም አፍቃሪያንስ ፡ ከጥቂት ጊዜያት በፊት እንደ አባትና ልጅ ስንተውን ተመልክቶን ፡ አሁን የፍቅር ፊልም ስንሰራ ሲያይ ምን ያህል ይዋጥለታል ? የሚል ምላሽ ነበር የሰጠው
በሰሜን እና በደቡብ ዋልታዎች ላይ ጉንፋን ለመያዝ የማይቻል ነው።

እና ጉንፋን ሊያዙ አይችሉም  ምክንያቱ ግልጽ ነው ምሰሶው ላይ በጣም ቀዝቃዛ ስለሆነ ተራ ቫይረሶች በቀላሉ እዚያ አይተርፉም።

#Health

@Amazing_Fact_433
@Amazing_Fact_433
ዘመን ማይሽራቸው ምርጥ ምርጥ መፅሃፍ መግዛት ከፈለጉ ቻናላችንን ይቀላቀሉ 👇
https://www.tg-me.com/Teramaj_Book_Store
https://www.tg-me.com/Teramaj_Book_Store
2024/09/30 11:26:48
Back to Top
HTML Embed Code: