Telegram Web Link
በቃ ወንድሟ መጥቶ እንዲህ ሲላት አልቻለችም ።
.....
ቀኑ ታናሽ እህቱ ከ Pre- KG የተመረቀችበት እለት ነው ። እና ከእናትና ከአባቱ ጋር በዚህ ዝግጅት ላይ የተገኘው የተመራቂዋ ወንድም እህቱ ፡ ከስንትና ስንት ድካም በኋላ ፡ ከእንቅልፏ ታግላ ፡ ከጨዋታዋ ጊዜ ቆጥባ ፡ ለዚህ ታላቅ የምረቃ ቀን በመድረሷ ፡ ተደስቶ እህቱ ወዳለችበት ቦታ በመሄድ pumpkin እህቴ l'm just so Proud of you አላት ።

ትንሿ pumpkin ይህን የአድናቆት ቃል ስትሰማ ........ በቃ አልቻለችም 😁 ስኬቷን አስባ. . በደስታ አለቀሰች ... እና አሁን ወንድሟ ራሱ እንባ እየተናነቀው እያባበላት ነው ።
.............
የስኬት ትንሽ የለውም ።
..................
🎴የእጅ ደም ስር ይሄንን ይመስላል

@Amazing_Fact_433
@Amazing_Fact_433
"ወንድ ልጅ አያለቅስም" ተብዬ ስላደግኩ ዲፕረሽን ከበደኝ
==========================

የሪስሊንግ ተፋላሚውና ተዋናዩ ድዌይን ጆንሰን በዲፕረሽን (ድብርት) ምክኒያት እያለቀሰ ይውል ነበር ቢባል ማን ያምናል?

✔️በአንድ ወቅት ዲፕሽን አጋጥሞት ነገር አለሙ አስጠልቶት ነበር። አንድ ቃለ መጠይቅ ላይ "ወንድ ልጅ አያለቅስም ተብዬ ስላደግሁ። ዲፕረሽን ሲያጋጥመኝ ማልቀስ ፈራሁ። ለሰዎች ስሜቴን መናገር አፈርኩ። ከዲፕረሽኑ(ከድብርቱ) በላይ ብቸኝነቱ ጎዳኝ" ብሏል።

✔️ድዌይን "ዲፕረሽን ማን ላይ እንደሚከሰት አይታወቅም። ህመሙ ሰው አይለይም። ሲከሰት እገዛ ለመጠየቅና ወደ ህክምና ለመሄድ ጥንካሬ ይጠይቃል። ወንዶች ደግሞ እገዛ መጠየቅ ደካማነት ይመስለናል።" ብሏል።

✔️ "ዲፕረሽን ውስጥ ስትሆን እንዳንተ አይነት ስሜት ሌላ ሰው ተከስቶ የሚያውቅ አይመስልህም። ነገር ግን አንተ የመጀመሪያው ሰው አይደለህም። የመጨረሻውም አትሆንም። የመከፋት ስሜት፣ ተስፋ መቁረጥ፣ በራስ መተማመን መውረድ ከ6 ሰዎች አንዱ ላይ የሚከሰት ነገር ነው። እኔ ለመጀመሪያ ጊዜ ዲፕረሽን ሲያጋጥመኝ ይህንን የሚነግረኝ ሰው ቢኖር ኖሮ ብዬ እመኛለሁ።" ብሏል።

የአእምሮ ህመም ፆታ፣ ብሄር፣ ሀይማኖት፣ የኢኮኖሚ ደረጃ፣ ተክለሰውነት አይለይም። ማን ላይ እንደሚከሰት አይታወቅም። ብዙ ወንዶች "ወንድ ልጅማ አያለቅስም" ብለው መከፋታቸውን ለመግለፅ ስለሚፈሩ በጭንቀትና በብቸኝነት ይሰቃያሉ። አንዳንዶች ከዲፕረሽን ለማምለጥ ሱስና ቁማር ውስጥ ይደበቃሉ።

ዲፕረሽን ውጤታማ ህክምና አለው። እገዛ መጠየቅና ወደ ህክምና መሄድ ደካማነት ሳይሆን ጠንካራነትን ነው የሚያሳየው



ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!
ዶ/ር ዮናስ ላቀው
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ሞትን_የሚያሸተው_ድመት!

እውነተኛ ታሪክ

በአሜሪካ ሮድ አይላንድ ውስጥ ባለ አንድ የአረጋውያን ማቆያ ውስጥ የሚኖር ድመት አለ።

ስሙም ኦስካር ይሰኛል።

ይህ ድመት በጽኑ የታመሙ እና መዳን የማይችሉ፣ ሞታቸውም የቀረበ ታማሚዎች አጠገብ ሄዶ ይተኛል።

ከጥቂት ሰዓታትም በኋላ ታማሚዎቹ ህይወታቸው ያልፋል።

ኦስካር ሞትን ማሽተት ይችላል።

ይህን የሚያደርገውም ከሞቱ ህዋሳት የሚወጣውን ኬሚካል በማነፍነፍ ነው።

እስካሁንም ድረስ ከመቶ በላይ ታማሚዎችን ሞት ቀድሞ ለይቷል። ነርሶች ኦስካርን ከታማሚ አጠገብ ከተመለከቱት የታማሚውን ቤተሰብ በአስቸኳይ ደውለው ይጠራሉ።

ከአእምሮ በላይ የሆኑ ተአምራት ዙሪያህን ከበውሃል። ነቅተህ መመልከትና ማስተዋል ስትጀምር ምን ሆኜ ነው ጨለማ ውስጥ የነበርኩት ትላለህ።

ልክ ድመቱ ኦስካር እንዳለው ኃይል አይነት ባንተ ውስጥም ብዙ የጥበብ ኃይላት አሉ።
ይህን የመንቃትና ነገሮችን የማወቅ ሂደት አንዳንዶች የሶስተኛው አይን መገለጥ ነው ይሉታል፡፡


ከድብቁ የአእምሮ መፅሐፍ የተወሰደ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🎴ቻይና የኢንተርኔት ሱሰኛ ለሆኑ ሰዎች የማከምያ ካምፕ አላት ! የመጀመሪያው በ2004 ቤጂንግ ውስጥ ተመሠረተው ነው ! ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ከ3,000 በላይ "ታካሚዎች" እዚያ ታክመዋል

@Amazing_Fact_433
@Amazing_Fact_433
🐜 አንዳንድ ጉንዳኖች የራሳቸው የሆነ አንቲባዮቲክስ ማምረት ይችላሉ

@Amazing_fact_433
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🎴በአንድ ወቅት ታዋቂ ዘራፊ እና ወንጀለኛ የነበረው ጄሴ ጀምስ ... የሆነ ወቅት ላይ አንዲት ባሏ የሞተባት ሴት መሽቶበት ማደሪያ በፈለገበት ሰአት ስላሳደረችው ያለባትን እዳዋን በሙሉ ለአበዳሪዎቿ እንድትከፍል ገንዘብ ሰጣት ሴትየዋም ገንዘቡን ተቀብላው ብድሯን ከፈለች ...... በነጋታው ግን ጀምስ ከአበዳሪዎቿ ላይ ገንዘቡን መልሶ ዘረፈው

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
የጥንታዊት ግብፁ ንጉስ ዳግማዊ ፔፒ ንግስናውን የተቀባው 16 ዓመቱ ሲሆን እስከ 94 ዓመቱ ድረስ ግብፅ ላይ በንግስና ቆይቷል።

ለረጅም ዘመን በቤተመንግስት ውስጥ በመሪነት የመቆየት ክብረ- ወሰን የሰበረው ንጉስ ፔፒ ነው፡፡


@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🎴ይህ በምስሉ ላይ የምታዩት የአእዋፍ ዝርያ " Himalayan Girffon Vulture " ይባላል ..... ሌሎች የአእዋፍ ዝርያዎችን ለማስፈራራት ሀሰተኛውን አይኑን ያሳያቸዋል ...... ትክክለኛው አይኑ ግን ያለው ከመንቁሩ ጥቂት ከፍ ብሎ ነው

እርግጠኛ ነኝ እናንተም ልክ እንደ እኔ መጀመሪያ ያያችሁት ሀሰተኛ አይኑን ነው

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
ከዓመታት በፊት ደቡብ አፍሪካ ውስጥ አንድ ሰው መሳይ ወጠምሻ ጭ*ራ*ቅ አንዲትን እንቦቀቅላ ህፃን አስገድዶ ይ*ደ*ፍ*ራ*ል !
በልጁ ላይ የተፈፀመውን ጭራቃዊ ተግባር የተመለከተው የህፃኗ ወላጅ አባት ቃጠሎውን ዋጥ አድርጎ ትንፋሹን ሰብሰብ አድርጎ ሲያስብ ጉዳዩን ወደ ህግ መውሰድ እና ፍትህ መጠበቅ የህዋነት መሆኑን ተገነዘበ።  ከዛም በራሱ መንገድ ጭራቁን አሳዶ ለመያዝ እና ለልጁ ለመበቀል ወሰነ።

ጀግናው አባት ኦፕሬሽኑን ጀመረ ! በራሱ መንገድ የጀመረው ኦፕሬሽን ፍሬ አፍርቶ የህፃኗ አባት የጭራቁን ማንቁርት ይዞ እራሱ ወዳዘጋጀው የፍርድ ቦታ እያዳፋ በመውሰድ ኦፕሬሽኑ በስኬት ተጠናቀቀ

ቀጣዩ ፍትህ የሚሰፍንበት የፍርድ ሂደት ተጀመረ የፍርድ ቦታው አንድ ዛፍ ነገር ያለበት ቦታ ነበር ። ዳኛውም እራሱ የህፃኗ አባት ነው። የህፃኗ አባት እንቦቀቅላነቷ እንኳን ሳያሳሳው በአሰቃቂ ሁኔታ ደ*ፍ*ሮ የ*ገ*ደ*ላ*ት*ን ሰው መሳይ ጭራቅ ከግንዱ ጋር ጠፍሮ አሰረው  ከዛም ከጭራቁ ፊት ለፊት እሳት አነደደ ። ቀጥሎም ስለት ነገር አወጣና ህፃኗ የተደፈረችበትን የጭራቁን መሽኒያ  ከመብቀያው ላይ ፈግፍጎ ጎመደው ! ኃይለኛ ስቃይ ውስጥ የገባው ጭራቁ የሲቃ ድምፅ እያሰማ ስቅስቅ ብሎ እያለቀሰ የህፃኗም አባት ከትትትት ብሎ ሳቀበት

ስቃዩን መቋቋም የተሳነው ጭራቁ እራሱን ሳተ ! የህፃኗም አባት ግላቭ ባጠለቀበት እጁ ጨብጦ የያዘውን የጭራቁን መሽኒያ እሳቱ ላይ ወረወረው ። እሳት ላይ የተጣለው የጭራቁ መሽኒያ እስኪበስል ጭራቁ እራሱን ከሳተበት ነቃ ! የህፃኗም አባት የበሰለውን የጭራቁን መሽኒያ በማጣበቂ ነገር አንስቶ ለጭራቁ በግዴታ በማጉረስ አላምጦ እንዲውጥ አስደረገው። ከዛም ትኩስ መሽኒያውን አላምጦ የዋጠው ጭራቅ ውስጡ በትኩሱ ተገሽልጦ የስቃይን ምንነት በሚገባ ቀምሷት ሞተ።

በቃ ለኔ ፍትህ ማለት እሄ ነው
በርካታ ዓለማችን ሀገራት የአስገድዶ መደፈር ወንጀልን ለመከላከል ወንጀለኛ መቅጫ ህጎችን ያዘጋጁ ቢሆንም የተወሰኑ ሀገራት ግን ጥፋተኞች ላይ ከባድ ቅጣትን በመጣል ይታወቃሉ !

ለአብነትም ቻይና ፣ ሳውዲ አረቢያ፣ ግብጽ፣ ደቡብ ኮሪያ እና ፓኪስታን የአስገድዶ መድፈር ወንጀል በፈጸሙ ጥፋተኞች ላይ የወንድ ብልትን ከማምከን ጀምሮ በስቅላት እና በእሳት በማቃጠል እንዲገድሉ የሚፈቅድ ህግ አላቸው፡፡

አሜሪካ ካሏት ጠቅላላ ግዛቶች መካከል ሰባቱ በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ የተባሉ ወንጀለኞችን ብልት ማምከን የሚያስችል ህግ ያላቸው ሲሆን በዚሁ ወንጀል እድሜ ልክ የተፈረደባቸው ወንጀለኞች ቶሎ ከእስር መለቀቅ ከፈለጉ ብልታቸው እንዲመክን መፍቀድ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ሰሜን ኮሪያ በዚሁ ወንጀል ጥፋተኛ የተባሉ ወንጀለኞችን በእሳት በማቃጠል ህይወታቸው እንዲያልፍ የምታደርግ ሲሆን ግብጽ አንቆ በመግደል እንዲሁም ሳውዲ አረቢያ ደግሞ አንገታቸውን በሰይፍ በመቅላት የሞት ፍርድ ትፈጽማለች፡፡

[ አል ዓይን ]

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
በጥንት ህንዳውያን አስተሳሰብ መሰረት መሬት በአራት ግዙፍ ዝሆኖች ላይ ያረፈች ስትሆን ዝሆኖቹ ደግሞ እጅግ በጣም ግዙፍ የሆነ ኤሊ ጀርባ ላይ እንደቆሙ ይታሰብ ነበር

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
Ufo(Aliens )እንዳሉ በየ ሀገሮች በ percente ሲጣራ
England 52%
Germen 56%
America 54%

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
ከአጠቃላይ የህዝብ ብዛት አንፃር ሲሰላ ከፍተኛ የተማረ ሰው ያላት አገር ፍልስጤም ናት!

  ግሪኮች ዳንስ አፍቃሪ ህዝቦች ናቸው፡፡

  በግሪክ ባህል ለአንዲት ሴት ልጅ አፕል (ቱፋህ) መወርወር ማለት ለጋብቻ እንደሚፈልጋት መግለፅ ነው፡፡

ሲጋራ በማጨስ ከፍተኛ ቁጥር ህዝብ ያላት ኩባ ስትሆን ሞንቴ ክሪስቶ፣ ሮምዬና ጁልየት የተባሉ የትምባሆ ዓይነቶች በሰፊው ይታወቃሉ፡፡

  ኩባ 4,000 ደሴቶች አሏት፡፡

  ከህዝብ ብዛት አንፃር ከፍተኛ የሀኪም ቁጥር ያላት አገር ኩባ ናት፡፡ ስርጭቱም አንድ ዶክተር ለ170 ሰዎች ነው፡፡

በጥንት ግብፃውያን ዘንድ የብር ማዕድን ከወርቅ የበለጠ ዋጋ ያወጣ ነበር፡፡

ጥንታዊ ግብፆች ከቀኝ ይልቅ ለግራ የሰውነት ክፍላቸው ልዩ ክብርና ጥንቃቄ ነበራቸው፡፡ ይህም የሆነው ልብ የ ሰው ልጅ የነፍስ ማዕከል ነው ብለው ስለሚያምኑና የሚገኘውም በስተግራ በኩል መሆኑን በማያያዝ ነው፡፡

አንዲት አገር እንዳለች ሙሉ ለሙሉ በዩኔስኮ በዓለም ቅርስነት ተመዝግባለች፡፡ ይህች ሉዓላዊት አገር እና ሙሉ ይዘቷ በዩኔስኮ ቅርስነት የተመዘገበው ቫቲካን ናት፡፡

የዓለማችን በቆዳ ስፋት ትንሽዋ አገር ቫቲካን የቆዳ ስፋት 44 ሔክታር ነው፡፡ በቆዳ ስፋት ትንሽ ብትመስልም በዓለማችን ላ ቁጥር አንድ ተፅዕኖ ፈጣሪ አገር ናት፡፡

የህዝብዋ ብዛት 932 ብቻ ሲሆን ያላት የባቡር ሃዲድ ርዝሙቱ 890 ሜትር ብቻ ነው፡


አንብብበው ከወደዱት 👍ይጫኑ

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ድንገት የአዞ መንጋጋ ውስጥ የገባ ሰው ካለ ለማምለጥ ቀላሉ መንገድ አይኑን ጫን አድርጎ በአንዲት ጣቱ ብቻ መውጋት ነው፡

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
ዩዴሞኒያ 23- መስምያ ጥጡ ማግሲ ቦግስ
==================
ቅርጫት ኳስ የረጃጅሞች ስፖርት ነው። የአለማችን ከፍተኛው የቅርጫት ኳስ ሊግ የአሜሪካው NBA ተጫዋቾችም አብዛኞቹ መለሎዎች ናቸው። መካከለኛ ቁመት ያላቸው ተጫዋቾች ከስንት አንድ ቢገኙ ነው።

ማግሲ ቁመቱ አንድ ሜትር ከስልሳ ብቻ ነው። ሆኖም ቅርጫት ኳስ ይወዳልም ይችላልም፤ NBA መጫወት ደግሞ ህልሙ ነው። ብዙ ሰዎች ህልሙን ሲነግራቸው ቁመቱን አይተው ይስቁ ነበር። እሱ ግን መስሚያው ጥጥ ነው። አብረውት የሚጫወቱት ልጆች በችሎታ እየበለጣቸውም በቁመቱ ምክኒያት ሙድ ይይዙበት ነበር። ማግሲ ግን መስያው ጥጥ ነበር።

ማግሲ "ብዙ ሰዎች የቁመቴን ማጠር ነው የሚያዩት እንጂ ልቤ ምን ያህል ትልቅ እንደሆነ፣ ህልሜ ምን ያህል ረጅም እንደተዘረጋ አያውቁም ነበር።" ይላል። በተጨማሪም "አንድም ቀን ረጅም ብሆን ኖሮ" ብሎ ተመኝቶ እንደማያውቅ ተናግሯል።

ማግሲ NBA ላይ ነገሰ። ወደታች የሚመለከቱት ተቀናቃኞቹን እንደምትሀት እያፈዘዘ ብዙ ነጥብ አስቆጠረባቸው። ከየት መጣ እንደመጣ ሳያውቁ በቅልጥፍና ብዙ ኳስ ነጠቃቸው። ብዙ ድል አስመዘገበ።

ማግሲ የሰባበረው ሪከርዶችን ብቻ ሳይሆን ብዙ "አይቻልም!" የሚሉ ድምፆችን ነው። የህልምህን ትልቅነት፣ የሀሳብህን ልክ፣ የብቃትን ደረጃ እና የትጋትህን መጠን የማያውቁ ሰዎች ለሚያወሩት ወሬ መስያህ ጥጥ ይሁን።

ዩዴሞኒያ ማግሲ፤ ዩዴሞኒያ ለሁላችንም
!
በቅርብ አመታት ውስጥ የተደረገው ጥናት እንደሚያመላክተው ከሆነ ከ 80% በላይ የሚሆነው የአለማችን ህዝብ አንድም ግዜ የአውሮፕላን በረራ አድርጎ አያውቅም 😮

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
እብዱ ታይሰን!

ቦክሰኛው ማይክ ታይሰን በአንድ ወቅት ከጉሬላ ጋር ለመደባደብ ሲል ለፓርኩ ጠባቂ 10,000 ዶላር ከፍሎ ነበር። 😂

ነገር ግን የፓርኩ ጠባቂ የታይሰንን ጥያቄ ውድቅ አድርጎበታል።

ብዙ ቀለል ቀለል ያሉ የመሞቻ መንገዶች ነበሩኮ ምን አለፋው!😁

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
ዘመን ማይሽራቸው ምርጥ ምርጥ መፅሃፍ መግዛት ከፈለጉ 👌

ቻናላችንን ይቀላቀሉ 👇
https://www.tg-me.com/Teramaj_Book_Store
አንድ አይጠ መጎጥ በጣም ሲርበው እና የሚበላ ነገር ካጣ የመጀመርያው እርምጃው የራሱን ጭራ መብላት ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ የሞተ አይጠ መጎጥ ፈልጎ መብላት ሲሆን ሶስተኛው ደግሞ ባጠገቡ ያለን ያልሞተ አይጠ መጎጥ ገድሎ መብላት ነው፡፡

  ለመጀመርያ ጊዜ የሰው ልጆች በራሳቸው ጥረት ከዱር . አምጥተው ወደ ቤት እንስሳነት የቀየሯት እንስሳ ፍየል ናት፡፡

  ለመጀመርያ ጊዜ የሰው ልጆች የጠጡት የእንስሳ ወተት የፍየል ወተት ነው፡፡

  ከእንስሳት ወተቶች ሁሉ ከፍተኛ የካልሽየም እና ቫይታሚን ኤ ንጠረ ነገር ክምችት ያለው የፍየል ወተት ነው፡፡

የፍየል ግልገል በእንግሊዘኛ ኪድ ትባላለች፡፡

  በምድር ላይ በሚኖር በእያንዳንዱ ሰው ቁጥር 1 000 000 ጉንዳኖች አሉ፡፡

  የቀይ ቀበሮ ሳይንሳዊ ስም ቫልፐስ ቫልፐስ ነው፡፡

  የአሞት ከረጢት የሌላት ብቸኛ አጥቢ እንስሳ አጋዘን ናት፡፡

አንብብበው ከወደዱት 👍ይጫኑ

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2024/09/29 19:29:30
Back to Top
HTML Embed Code: