Telegram Web Link
ው ጀርሲ ውስጥ አንድ JBJ Soul Kitchen የሚባል ሬስቶራንት አለ ። በዚህ ሬስቶራንት የቻለ ሰው ከፍሎ እንደውም ከተመገበው ምግብ በላይ ትርፍ ገንዘብ ሰጥቶ ይወጣል ።
የሌለው ደግሞ በነጻ ብቻ ሳይሆን በክብር ጭምር ተመግቦ ፡ አመስግኖ ይሄዳል ። ( የዚህ ቤት ደንበኞች ባብዛኛው መክፈል የማይችሉ ሰወች ናቸው )
.....
እና እዚህ ሬስቶራንት ለመጀመሪያ ጊዜ የሄደ ሰው ፡ ብዙ ብር ከፍሎ መድረክ ላይ ሲዘፍን ያየውን አንድ ታላቅ ዘፋኝ ሰው እዚህ ምግብ ቤት ሰሀን ሲያጥብ ሲያየው ሊደነግጥ ይችላል ።
....
ምክንያቱም ይህ ሰሀን ሲያጥብ ፡ ወይ ድስት ሲያማስል የሚታየው ሰው ቀላል ሰው አይደለም ።
.....
ምናልባት የሀርድ ሮክ ሙዚቃ ሰሚ ወይም አድናቂ የሆነ ሰው ቦን ጆቪን አሳምሮ ያውቀዋል ።
ቦን ጆቪ በሙዚቃው አለም ለአራት አስርት አመታት ቆይቷል ፡ ሆኖም ዛሬም በተለያዩ ቦታዎች ዝግጅቱን ሲያቀርብ ፡ አሁንም ስታዲየም ወይም አዳራሽ ሙሉ ህዝብ እየተጋፋ የሚያየው የሮክ አቀንቃኝ ነው ።
....
እና ይህ ዝነኛ እና ባለቤቱ ከአመታት በፊት ....ለምን ሀይለኛ ሬስቶራንት አንከፍትም ? ማለት ዝም ብሎ አይነት ሳይሆን. . በቃ ከምግብ በፊት አፕታይዘር ፡ ከዛ ዋና ምግብ ፡ ከዛ ዲዘርት የሚቀርብበት አሪፍ ምግብ ቤት ከፍተን ከፍለው መመገብ ለማይችሉ ወገኖችን አንመግብም ብለው አሰቡና የመጀመሪያውን ዘመናዊ ሬስቶራንት ኒውጀርሲ ውስጥ ከፈቱ ።
.......
ይህ በ2011 የተከፈተ የቦንጆቪ ሬስቶራንት መክፈል ያልቻሉ ሰወችን በነጻና በክብር እየመገበ አሁን ላይ ቅርንጫፉን ወደ አራት አድርሷል ።
.........

ቦን ጆቪ ይህንን አስመልክቶ ሲጠየቅ በትላልቅ መድረኮች ላይ ያዩኝ ሰወች ፡ በሌላኛው ቀን የተመጋቢዎችን ሳህን ሳጥብ ሲያዩ ይገረማሉ ። ሆኖም ይህ ለእኔ የሚያስደስተኝና ፡ ለማህበረሰቡ ላደርገው የሚገባ ትንሽ ነገር ነው ፡ ሀብታምነትም ሆነ ዝነኝነት ይህን መሰል መልካም ነገሮችን ከማድረግ ሊገድበን አይገባም ሲል ይናገራል ።
.....
ቦን ጆቪ ላለፉት አርባ አመታት በትዳር አብሯት ከቆየው ዶሮቲ አራት ልጆች ያለው ሲሆን ከ124 ሚሊየን ዶላር በላይ ሀብት አፍርቷል ።
ይህ የ16 አመት የልጅ ሀብታም ፡ ከባርሳ ጋር ለሶስት አመታት ተፈራርሞ ከሚያገኘው 5,010,000 ዩሮ ሌላ በየሳምንቱ ቅዳሜ 32,115 ዩሮ ለኪሱ ይከፈለዋል ።
......
ላሚኒ ያማል ይባላል ከሞሮኳዊ አባትና ከኢኳቶሪያል ጊኒ ከምትገኝ እናት በስፔን የተወለደው ይህ የመጭው ዘመን ኮከብ ፡ በ16 አመቱ ለብሄራዊ ቡድን ተሰልፎ በአውሮፓ ዋንጫ ላይ የተጫወተ በእድሜ ትንሹ ተጫዋች በሚል ሪከርድ ተመዝግቦለታል ።
....
ላሚኒ ከእግር ኳስ ተጫዋችነቱ ሌላ ተማሪም ነው ። በአንድ ጎን ኳሱን እየተጫወተ ፡ ወደማረፊያው ሲሄድ ደግሞ ደብተሩን ገልጦ ያነባል ።
.........
ይህ ትናንት እና ዛሬ በሶሻል ሚዲያ ቫይራል ሆኖ የዋለ ምስል ሀገሩ ስፔንን ወክሎ ለመሳተፍ በሄደበት በጀርመን ፡ ባረፈበት ሆቴል ሩም ውስጥ ሰሞኑን ለሚወስደው ፈተና ለመዘጋጀት በማጥናት ላይ ላይ እያለ በጓደኞቹ ተነስቶ የተለቀቀ ምስል ነው ።
.....
አደለም ራሱ ሀብታም እየሆነ ያለ ልጅ ይቅርና ፡ የሀብታም ልጅ ስለሆነ ብቻ ማጥናት እንደሌለበት የሚያስብ ብዙ ሰው ባለበት ጊዜ የዚህ ልጅ ለትምህርቱ በዚህ ደረጃ ትኩረት መስጠቱ ብዙዎችን አስገርሟል
proboscis monkey 🐵

በፕሮቦሲስ ዝንጀሮዎች ዓለም ዉስጥ ረዘም ያለና ትልቅ ቀዳዳ ያለዉ አፍንጫ መኖር ወሳኝ ጉዳይ ነዉ

አንድ ወንድ ዝንጀሮ የአፍንጫዉ መጠን በጨመረ ቁጥር ሴቶች ዝንጀሮዎች በቀላሉ እንዲሳቡ እና ሌሎች ወንዶች ዝንጀሮዎችን እንዲርቁ ያደርጋቸዋል።

@Amazing_Fact_433 @Amazing_Fact_433
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እስኪ ፈታ በሉበት😂😂😂 ሰዎች ሌብነት ክፉ ነው።

የአመቱ አስቂኝ ሌባ ብለነዋል።😂

@Amazing_Fact_433
@Amazing_Fact_433
በእግር ኳስ ታሪክ ፈጣኑ ቀይ ካርድ 'LEE TODD' የተባለ ተጫዋች ላይ የተመዘገበ ሲሆን ዳኛው የመጀመሪያ ጨዋታ ለማስጀመር ፊሽካ ሲነፋ በጣም ስለጮኸ "F*CK ME THAT WAS LOUD"ብሎ ሲናገር ዳኛው ጨዋታ በተጀመረ በ 2 ሴኮንድ ውስጥ በቀይ ካርድ ሊያስወጣው ችሏል።

Via [ foot ball world fact ]

@Amazing_Fact_433
@Amazing_Fact_433
ይህን ያውቁ ኖሯል?

የጥንት ግሪኮች እርቃናቸውን ወደ ጂምናዚየም ይሄዱ ነበር።“ጂምናዚየም” የሚለው ቃል “የራቁት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ትምህርት ቤት” ማለት ነው።

@Amazing_Fact_433
@Amazing_Fact_433
ከሶስት ቀናት በፊት ሰኞ እለት ፡ በዱባይ አንድ አዲስ የቅንጦት ሬስቶራንት ተከፍቷል ። ይህ TATEL የሚል ስያሜ የተሰጠው ዘመናዊ ሬስቶራንት ካሁን በፊት ፡ በማድሪድ ፡ በሳውዲ አረቢያ ሪያድ በሜክሲኮ ሲቲና ፡ ለመኖር እጅግ ውድ በሆነው የዝነኞችና ሀብታሞቹ መንደር በቨርሊ ሂልስ ውስጥ ቅርንጫፎችን ከፍቶ ላለፉት ሁለት አመታት ሲሰራ የቆየ ሬስቶራንት ሲሆን ሰኞ እለት በዱባይ የተከፈተው አምስተኛ ቅርንጫፉን ነው ።
......
ይሄ በተከፈተ በሶስት ቀን ዝናን እያተረፈ ያለው ሬስቶራንት የማነው ?
...
በአለም የሜዳ ቴኒስ ስፖርት ውስጥ ራፋኤል ናዳል ያለው ስም ታላቅ ነው ፡ የቴኒሱ አለም ሮናልዶ የሆነው ስፔናዊው ራፋኤል ናዳል ከአመታት ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በቴኒሱን አለም የታወቀ ዝነኛ እና ሚሊየነር ሰው ነው ።
እና የዚህ የታቴል ሬስቶራንት አንደኛው ባለቤት እሱ ሲሆን ፡ ሌላኛው የዚህ ሬስቶራንት ባለቤት ደግሞ ፡ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ነው ።
....
እንግዲህ እነዚህ ሁለት ዝነኞች ናቸው ፡ በቀደም በዱባይ ቅርንጫፍ የከፈተውን ካምፓኒ በጋራ ያቋቋሙት ።
...
ወደ ኋላ መለስ ብለን ስናይ ፡ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከልጅነቱ ጀምሮ በእግር ኳስ አለም የቆየ ነው ። በተመሳሳይ ራፋኤል ናዳልም ፡ ከልጅነቱ ጀምሮ የሚታወቀው በስፖርቱ አለም ብቻ ነበር ።
...
ሆኖም በኖሩበት በስፖርቱ አለም ያፈሩትን ስም እና ዝና ወደ ቢዝነስ ለመለወጥ አሰቡ ፡ እናም ስለሆቴል ቢዝነስ የሚያውቁ ፕሮፌሽናሎችን በስራቸው አድርገው ወደ ሬስቶራንት ቢዝነስ ገብተው እየሰሩ ነው ።
.....
ሁለቱም የዘመናችን ታላላቅ ዝነኞች ቢሆኑም በተለይ ሮናልዶ ፡ በአለም ላይ ከጥግ እስከጥግ የሆነ ዝና ያለው ፡ በማስታወቂያ በየቀኑ ብዙ ገንዘብ የሚያገኝ ፡ ሀብታም ስለሆነ ፡ ገንዘብ አለኝ ፡ ስም አለኝ ብሎ ረክቶ ያለመቀመጡና ፡ በእግር ኳሱም ሆነ በቢዝነሱ አለም አሁንም ብዙ የመስራት ፍላጎቱና ኢነርጂው የሚገርምና ሌላውም ሊማርበት የሚገባ ነው ።
ኮንዶሞች ለመጀመሪያ ጊዜ የተዋወቁት በ17ኛው ክፍለ ዘመን ሲሆን የተሰሩትም ከ አሳና እንሰሳት አንጀት ነበር

@Amazing_fact_433
Bangladesh is more populated than Russia 😯

@Amazing_fact_433
ስንበላሽ ጊዜ Restart & Reset በዚህ መልኩ ይከናወን ነበር።

  [አንዱ በManual ሲስተካከል ሁለቱ በብሉቱዝ ይደርሳቸዋል]

@Philosphyloves
@Philosphyloves
በታሪክ ውስጥ ካሉት ትላልቅ እና ከፍተኛ የታሪኮ ባለቤቶች የሮማውያን ግዛት አንደኛው ነው ሮማውያን በአውሮፓ፣ በኤስያና በከፍሪካ ግዛቶች ነበሯቸው እነዚህንም ግዛቶች ለ1000 ዓመታት እንደገዙ ይነገራል። በግዛቶቻቸው ውስጥም ብዙ አይረሴ ቅርሶችን ትተዋል። ከነዚህም ውስጥ፣ ሐውልቶች፣ አምፊ ትያትሮቾ፣ ህንጻዎች፣ መንገዶች፣ ድልድዮችና ቅርጻ ቅርጾች ይገኙበታል። ከነዚህም ውስጥ ዋንኛው ፑላ አሬና ፑላ ክሮኤሺያ ነው

ፑላ አሬና በክሮኤሺያ ኢስትሪያን ባሕረ ገብ መሬት ጫፍ ላይ ይገኛል እና ምናልባትም ከሮም ውጭ የሚገኘው ትልቁ አምፊቲያትር ነው። አወቃቀሩ የተገነባው በንጉሠ ነገሥት አውግስጦስ ዘመን (ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ27 እስከ 14 ዓ.ል. ሲሆን ከእርሱ ቀጥሎ ዘውድ የደፉ ነገሥታት ብዙ ጊዜ አስፋፍተውታል። ከግዙፉ የኢስትሪያን የኖራ ድንጋይ የተገነባው መድረክ ዛሬም ውበቱን ጨርሶ አልተወም።

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
2024/11/16 12:52:35
Back to Top
HTML Embed Code: