Telegram Web Link
አስተውላችሁ ከሆነ ብዙ የአውቶማቲክ መክፈያ ማሽኖች (ATM) ካርዱን ከመለሱልን በዃላ ነው ገንዘቡን የሚሰጡን።

ይኽም የሆነበት ምክንያት ብዙውን ጊዜ ተጠቃሚዎች ገንዘቡን ቀድመው ከወሰዱ ካርዱን ሊረሱት ይችላሉ ከሚል የስነልቦና ግምት ነው።


@Amazing_Fact_433
@Amazing_Fact_433
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ከ 1300 በላይ ተከታታይ ፊልሞች በ 433 Films አሉ

ተከታታይ English 👉 @Seriesbayx

ተከታታይ በትርጉም 👉 @Series_Amhh
ፍትሃዊው ዳኛ Frank Caprio

አሜሪካ ውስጥ የ15 አመት ታዳጊ ከአንድ ሱቅ ሲሰርቅ ተያዘና ከዛም ሊያመልጥ ሲል ከሱቁ ይእቃ መደድርደሪያ አንዱን ሰበረው ከዚያም ወደ ፍርድ ቤት ተወሰደና ፍርድ ቤት ቆመ

ይህ ፍትሃዊ ዳኛ የሰጠው ፍርድ!!
ዳኛው የክስተቱን ዝርዝር ሁኔታ ከሰማ በኋላ ልጁን እንዲህ ሲል ጠየቀው።

ዳቦና አይብ ሰርቀህ የሱቁን መደርደሪያ ሰብረሀል ይህ እውነት ነው ?

ልጁም አንገቱን ደፍቶ በሀፍረት አዎ ሲል መለሰ፡-

ዳኛ፡ "ለምን ሰረቅክ?"

ታዲጊው ልጅ: በጣም ፈልጌው ነው

ዳኛ፡ ከመስረቅ ይልቅ መግዛት አልቻልክም ነበር?

ልጅ፡አዎ የሰረቅኩትን እቃ ለመግዛት ገንዘብ አልነበረኝም።

ዳኛ፡ ወላጆችህን ገንዘብ ልትጠይቅ አትችልም ?።

ልጅ፡ እኔ ያለኝ፣ አልጋ ላይ የተኛች እና ስራ የሌላት የታመመች እናቴን ብቻ ነው... ለሷ ስል ዳቦና አይብ ሰርቄያለሁ።

ዳኛ፡ እና አንተ... ምን እየሰራህ ነው? ሥራ የለህም?

ልጅ፡- የመኪና ማጠቢያ ሆኜ እሰራ ነበር። እናቴን ለመርዳት አንድ ቀን ዕረፍት ወሰድኩ፣ በዚህም ከስራዬ ተባረርኩኝ ሲል በሀዘን መለሰ ።

ከልጁ ጋር የነበረው ውይይት ካለቀ በኋላ ዳኛው ፍርዱን አስታወቁ፡-“ሌብነት በተለይም ዳቦ መስረቅ በጣም አሳፋሪ ወንጀል ነው።

ለዚህ የስርቆት ወንጀል ሁላችንም ተጠያቂ ነን። ለዚህ የስርቆት ወንጀል ዛሬ እኔ ራሴን ጨምሮ እዚህ ክፍል ውስጥ የተገኘ ሁሉ ተጠያቂ ነው” አለ።

በመቀጠልም ሁሉም ተሰብሳቢዎች አሥር ዶላር ይቀጣሉ እና ማንም ሰው 10 ዶላር ሳይከፍል ከአዳራሹ አይወጣም.
ዳኛው ከኪሱ የ10 ዶላር ቢል አንሥቶ እስክሪብቶ አወጣና እንዲህ ብሎ መጻፍ ጀመረ።

"በተጨማሪም የተራበውን ልጅ ለፖሊስ ያደረሰው ሱቅ ባለቤት 1,000 ዶላር እንዲቀጣ አዝዣለሁ እና ቅጣቱ በአንድ ሰዓት ውስጥ ካልተከፈለ ሱቁ ተዘግቶ ይቆያል."
በአዳራሹ ውስጥ የነበሩት ሁሉ ለልጁ ይቅርታ ጠይቀው ሙሉ ገንዘቡን ሰጡት። ዳኛው እንባውን ለመደበቅ እየሞከረ ከችሎቱ ወጣ።

ተሰብሳቢዎቹ የዳኛውን ውሳኔ ከሰሙ በኋላ ዓይናቸው በእንባ ተሞላ።
ዳኛው አክለውም “አንድ ሰው ዳቦ ሲሰርቅ ከተያዘ መላው የዚች ሀገር ህዝብና ህብረተሰብ ሊያፍር ይገባል” ብለው ተናገሩ

ዳኛ ፍራንቸስኮ "ፍራንክ" ካፕሪዮ የፕሮቪደንስ ሮድ አይላንድ ዋና የማዘጋጃ ቤት ዳኛ ነው። እሱ የሚመራባቸውን የዕለት ተዕለት የፍርድ ቤት ጉዳዮች ውስጥ በጣም ከሚታወቅባቸው ተግባራቱ እጅግ ፍትሀዊ ፍርዶቹ እና በገደብ የለሽ ደግነቱነው።

የእያንዳንዱ ተከሳሽ ታሪክ መጨረሻቸው አስደሳች ባይሆንም ዳኛ ካፕሪዮ ግን በሰዎች ውስጥ ምርጡን ለማድረግ እና ሰዎች ምርጡን ማየት ይገባቸዋል ብሎ ያመነባቸውን ተከሳሾች ለመርዳት እውነተኛ ፍላጎት ያለው። ምርጥ ዳኛ ነው

☞Who is the nicest judge in the world ብለው Google ላይ Search ቢያረጉ የዳኛ Frank Caprio ምስል እና ታሪክ ይመጣል
#Mami Kedir
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
➠ ከአባቱ ጋር በጥቅም በመጣላታቸው ምክኒያት

- #አባቱን
- #እናቱን አና
- #አጎቱን ገድሎ የ9አመቱ ወንድሙ ለይ በመተኮስ አደጋ ያደረሰው ተከሳሽ 'ከፍታ ካፋላ' በሞት ፍርድ እንዲቀጣ ተወስኗል።

➠ ተከሳሹ በጋርዱላ ዞን የሃይበና ቀበሌ ነዋሪ ነው።

©️ Tikvah

@Amazing_Fact_433
ይሄንን ያውቃሉ ???

85% የሚሆነው የአለም ህዝብ የሚጠቀመው እጅ ቀኝ እጅ ነው።

@Amazing_Fact_433
@Amazing_Fact_433
ይሄንን ያውቃሉ ???

እ.ኤ.አ. በ 2019 በህንድ ጉጃራት የሚኖር አንድ ሰው እባቡ ነክሶት ከቆየ በኋላ እባብ ነክሶ ነበር። እሱና እባቡ ሞቱ።

@Amazing_Fact_433
@Amazing_Fact_433
Forwarded from Quality Button
የአንድ ሰው የአይን ክብደት ስንት ነው ???
በነገራችን ላይ Facebook ላይ ስለ Lgbt መጥፎ ነገር የፃፉ አካውንት እና ፔጅ በዚ ወር በሙሉ Ban ተደርገዋል።

ሚዲያው ይህን ሰይጣናዊ ነገር በግድ ኦንዲደግፍም ተደርጉዋል እያንዳዱ ትላልቅ የውጭ ሚዲያ በዚ ወር ስለነሱ ዘገባ በግድ ማረግ አለበት መቃወም አይቻልም።

ሀገራችን እና አፍሪካን ከዚ ሰይጣናዊ ተግባር ፈጣሪ ይጠብቃት

@Amazing_Fact_433
@Amazing_Fact_433
➠ እውነተኛ ታሪክ ነው በተባለው ፊልም መሰረት:-

◉ ተፎካካሪውን እጩ ፕሬዝዳንቱን ለመግደል ሲል አይሮፕላን ውስጥ ቦምብ አፈንድቶ 107 ሰው ገድሏል ...

◉ አንዴ እንደውም ሊይዙት በመሞከራቸው ብቻ ከ1000 በላይ የሚሆኑ ፓሊስ ኦፊሰሮችን 'ለማስጠንቀቂያ ያህል' ብሎ አስገድሏል...

◉ ከ2000 በላይ ኑፁሃንን እንዳስገደለ ይነገርለታል...

◉ ከሀገሬው ፕሬዝዳንት ጋር ተደራድሮ ቤተመንግሥት የሆነ ጠባቂ የሌለው 'እስርቤት' አሰርቶ ኖሮበታል ...

◉ አንዴ ጀርመን እንደ ጀብደኛ ሲያደርጋት ሚስቱን፣እናቱን እና ልጆቹን 'የወንጀለኛ ቤተሰብ ናቸው ፣ ሀገሬ አትገቡም' በማለት በቅንጡ ሆቴል በማቆየቷ ምክንያት ሰውየው የጀርመን ኤምባሲ በመደወል አስፈራርቷቿል...

◉ 200 ቶን የሚያህለውን F16 (ከጀት የሚለቀቅ ቦምብ) ጋር እኩል የሆነ ቦምብ ለቤተ መንግስቱ በቅርብ ርቀት በማፈንዳት ህዝብ ጨርሷል...

➠ ይሄን ያህል ካልናቹ የቀረውን ታሪክ ከፊልሙ ተመልከቱ።

◉ ተከታታይ ፊልሙ 'Narcos' ይባላል በኮሎምቢያዊው አደንዛዥ እፅ አዘዋዋሪ ፓብሎ ኤስኮባር ለይ ተመስርቶ የተሰራ የ30 episodes ተከታታይ ፊልም ነው፤ እናንተ 20ኛው ድረስ እዩት።

◉ በHD ለማግኘት 👉 Narcos
◉ በትርጉም ለማግኘት👉 ናርኮስ
የአለማችን ውዱ ፒዛ 40 ቢሊየን 226 ሚሊየን 600 ሺ ብር ነው የተሸጠው !

በ2010 እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር። የቢት ኮይን (የዲጅታል መገበያያ ገንዘብ) መስራቹ ሳቶሺ ናኮሞቶ በማህበራዊ ሚዲያ አንድ ፒዛ ለሚያመጣልኝ ሰው 10,000 ቢት ኮይን እሰጠዋለሁ አለ።

ብዙዎች ምንድነው የሚቀባጥረው ሚሊየንስ ቢሆን ምን ሊፈይደን ብለው ችላ አሉት።

አንድ ወጣት ግን ኮይኑ ባይፈይድም አንድ ፒዛ ብጋብዘውስ ምንችግር አለው በሎ ወሰደለትና እንደ ቀልድ 10 000 ኮይኑን ወሰደ።

አሁን ላይ አንድ ቢት ኮይን 4 ሚሊየን 22 ሺ 660.88 ብር ሲሆን በ10 ሺ ስንመታው 40 ቢሊየን 226 ሚሊየን 600 ሺ ብር ይሆናል ! 😳

@Amazing_Fact_433
@Amazing_Fact_433
ክርስቲያኖ ሮናልዶ የሚፈልጋት እውነተኛዋ ሴት እስካሁን አልተገኘችም ።
....
ፖርቹጋላዊው ዝነኛው የእግር ኳስ ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ፡ ከጥቂት አመታት በፊት ፡ ከፒርስ ሞርጋን ጋር አድርጎት በነበረው ኢንተርቪው ፡ በልጅነት እድሜው ፡ ከልምምድ መልስ ከስታዲየም ሲወጡ ስለሚርባቸው ፡ ስታዲየሙ አካባቢ ወደሚገኝ የማክዶናልድ መደብር እየሄዱ ፡ የተራረፈ እና ሳይሸጥ የዋለ በርገር እየጠየቁ ይመገቡ እንደነበርና

በዚህ አዘውትረው እየሄዱ በርገር ከሚጠይቁበት የማክዶናልድ መደብር ሶስት ሴቶች እንደነበሩ ፡ ከነሱም መሀከል አንዷ ኤድና እንደምትባል ተናግሮ ፡ ቢያገኛት ፡ በዛ በድህነት ወቅት ላደረገችለት መልካም ነገር ዛሬ በተራው አግኝቶ ሊያመሰግናትና ፡ ውለታዋን ሊከፍል እንደሚፈልግ ፡ ይህ ኢንተርቪውም ያችን መልካም ሴት ለማግኘት እንደሚረዳው ተናገረ ።
.......
ይህ ኢንተርቪው ከተላለፈ በኋላም በፖርቹጋል በሚገኘው ማክዶናልድ ውስጥ ትሰራ የነበረች Paula luca የምትባል ሴት ፡ ሮናልዶ የሚፈልጋት ሴት እሷ እንደሆነች ። ተናገረች ።

ፖርቹጋል ውስጥ የሚገኝ አንድ ራዲዮ ይህችን ሴት አግኝቶ አናገራት ። ይህ ወሬ ብዙም ሳይቆይ ከሴትየዋ ምስል ጋር በሶሻል ሚዲያ ተሰራጨ ፡
ሮናልዶ ይህን እንደሰማ ግን ያቺ እሱ የሚፈልጋት ሴት ይህች እንዳልሆነች ትክክለኛዋን ሴት አግኝቶ ለማመስገን አሁንም እንደሚፈልግ ተናገረ ።
.....
ይህ ከሆነ አመታት ተቆጥረዋል ።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ ፡ በልጅነት ዘመኑ ላደረገችለት መልካም ነገር ሁሉ አግኝቶ አመሰግናለሁ ሊላት ፡ ውለታዋንም በብዙ እጥፍ ሊከፍላት የሚፈልገው ያቺ ሴት ግን አሁንም አልተገኘችም ።
.......
ፍለጋው አልቆመም ፡ ሮናልዶ ውለታውን ሳይረሳ ሊያመሰግናት የሚፈልጋት ሴት አሁንም ትፈለጋለች ።
....
ይህ የሮናልዶ ተግባር ለሌላውም ትልቅ ትምህርት ሆንዋል ። ከአመታት በፊት መልካም ያደረጉልንን ሰወች ፈልጎ ለማመስገን መለመድ ያለበት ተግባር ነው

አስመስክሯል ......

በዋሲሁን ተስፋዬ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from Quality Button
#ጥያቄ...

በኢትዮጵያ እግርኳስ ታሪክ አንበል ሆኖ የአፍሪካን ዋንጫ ማሳካት የቻለው ተጫዋች ማነው ???
ይሄንን ያውቃሉ ???

ሰጎኖች 75 ዓመት ገደማ ይኖራሉ እና... ለ50 ዓመታት ሊራቡ ይችላሉ.።

@Amazing_Fact_433
@Amazing_Fact_433
የጀርመናውያኑ ናዚዎች በሁለተኛው የዓለም ጦርነት እ.ኤ.አ በ 1939 ዓ.ም ፖላንድን ከወረሩ በኋላ የመሰረቷቸው ኦሽዊትዝና ሴቢቦር የተባሉት የአይሁዳውያን ማጎሪያ ካምፖቻቸው ዋንኞቹ ናቸው....ከኦሽዊትዝ የተረፈና ከጦርነቱ በኋላም የኦሽዊትዝን ሚስጥር ለአለም ያጋለጠው ብቸኛው አይሁድ ዶክተር ሚክሎስ ኒዥሊ (Doctor Miclos Nyiszly) ይባላል...ይህ ሰው ከውድ ባለቤቱና ሴት ልጁ ጋር ከሃንጋሪ ተይዞ ኦሽዊትዝ ቢገባም ሚስቱ፣ልጁና ሌሎች በሚልዮን የሚቆጠሩ አይሁዳውያን በኦሽዊትዝ ማጎሪያ ካምፕ አይናቸው እያየ በእሳት ተቃጥለዋል አልያም በናዚ ትእዛዝ በአስከፊ ሁኔታ ተገለዋል። በወቅቱ ጀርመናውያኑ ዶክተር ሚክሎስን ለምርምር ስራቸው ሲሉ በህይወት ስላቆዩት 1945 ዓ.ም ጀርመን ስትሸነፍ እሱም በተአምር በህይወት በመትረፉ ያየውን የኦሽዊትዝን ግፍ በመፅሃፍ አሳትሞ ለአለም አበረከተ... ምናልባት እሱ በህይወት ተርፎ ታሪኩን ባይፅፈው ኖሮ የኦሽዊትዝ ግፍ ለአለም እንቆቅልሽ ሆኖ ተዳፍኖ ይቀር ነበር...


መፅሃፉም በአማርኛ በደራሲና ተርጓሚ ማሞ ውድነህ ተተርጉሞ "የኦሽዊትዝ ሚስጥር" ተብሎ ለኛ ለኢትዮጵያውያን አንባብያንም ተደራሽ ተደርጓል !! ከሴቢቦር ማጎሪያ ካምፕ ግን ታሳሪ አይሁዶች ተቀናጅተው በፈጠሩት ከእስር የማምለጥ ዘመቻ አብዛኛዎቹ የግፈኞቹ የናዚ ወታደሮች ጥይት እራት ቢሆኑም የተወሰኑቱ ግን ለማምለጥ ችለዋል...ይህም እውነተኛ ታሪክ "Escape from Sobibor" ተብሎ በፊልም ተሰርቷል...በነገራችን ላይ የጀርመን ናዚዎች በሁለተኛው የአለም ጦርነት ጅማሬ ከ 1939 ዓ.ም እስከ 1945 ዓ.ም የጦርነቱ ፍፃሜ ድረስ ከወረሯቸው የአውሮፓ አገራት በፊታውራሪያቸው ቻንስለር በጨካኙ አዶልፍ ሂትለር ትእዛዝ ከያሉበት እየታደኑ ከ 6 ሚልዮን በላይ አይሁዳውያን በማጎሪያ ካምፖቹ ውስጥ በጅምላ በግፍ ተገድለዋል!!
ውድ አንባብያን ስለ ናዚዎቹ አረመኔነትና ጭካኔ ይበልጥ ለመገንዘብ "የኦሽዊትዝም ሚስጥር" የሚለው እውነተኛ ታሪክ ያጨቀውን መፅሀፍ እንድታነቡና በእውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የተሰራው Escape from sobibor የሚለውን ፊልም እንድታዩ ጋበዝናቹ !

@Amazing_Fact_433
@Amazing_Fact_433
ይደንቃል ይገርማል

እነዚህን Abby Hensel እና Brittany Hensel የተሰኙ ተጣብቀው የተፈጠሩ መንትዮች (Conjoined twins) አስታወስካቸው ኣ?

-

Joshua Bowling የተባለ የWar Veteran ነርስ፣ ከአንደኛዋ ጋራ፣ ማለትም ከAbby Hensel ጋራ ባለፈው ጋብቻ ፈጽሟል። ሁለተኛዋ ግን አሁንም Single ናት።

-

አካላቸው አንድ ቢሆንም፣ ሁለቱም እህትማማቾች የተለያየ ጭንቅላት ስላላቸው፣ የተለያየ ቴስት፣ ባህሪ፣ አመለካከት፣ አቋም፣ ፍላጎት፣ እና ሙድ አላቸው። ግን ተግባብተው እና ተናብበው ተዋድደው ይኖራሉ። ሁለቱም ተምረው፣ ተመርቀው፣ መምህር ሆነው ያገለግላሉ። አንድ ደሞዝ ለሁለት ይበላሉ።

-

ይኸው አንዷ ደግሞ ከአንዱ ወንድ ጋራ ተዋውቃ፣ ተላምዳ፣ ተጀናጅና፣ ተዋድዳ፣ ተፋቅራ አገባችው። እንደፐፈጣሪ ፈቃድ በቅርቡ ልጅ ትወልዳለች።

ጌታዬ።

እነዚህ ሴቶች ተጋፍጠው ካሸነፉት ችግር እና Wierdoነት አንፃር። እነዚህ ተጣባቂዎች ጭራቅ መስለው፣ የሰዉን አፍ ችለው ከተቋቋሙት Challenge አንፃር ካየኸው - አንተን የሚያጋጥምህ መከራ፣ ዲፕረሽን ውስጥ የሚከትህ ጉዳይ፣ ሙድህን አጥፍቶ Down የሚያደርግህ ነገር Insignificant ነው። ምንም ማለት ነው።

◦ የሠው ልጅ ጠንካራ ነው።
◦ የሠው ልጅ የሚገርም ፍጥረት ነው።
◦ የሠው ልጅ የማይወጣው Challenge የለም።

©Eyob mihereteab

@Amazing_Fact_433
@Amazing_Fact_433
ይህን ያውቃሉ ?

የመጀመሪያው ኮንዶም የተሰራው  በፈረንጆቹ 1640 ሲሆን

የተሠራበት ግብዓትም ከዓሣና ከተለያዩ  እንስሳት አንጀት ነው !

@Amazing_Fact_433
@Amazing_Fact_433
" ከአሁን በኋላ አደለም የወንዝ ውሀ ልትጠጡ ልብሳችሁ እንኳን በወንዝ ውሀ አይታጠብም " ( ሚስተር ቢስት )

ዝነኛው አሜሪካዊ ዩቲዩበር ሚስተር ቢስት በአለም ላይ በዩቲዩብ ሰብስክራይበር ብዛት የሚወዳደረው የለም ። ሚስተር ቢስት ፡ 275 ሚሊየን ሰብስክራይበር በመያዝ በአንደኝነት ይመራል ።
...........

ይህ የ26 አመት ወጣት ከዚህ ባለፈ የሚታወቀው በበጎ አድራጎት ስራው ነው ።
እና ከስድስት ወራት በፊት በኬንያ በሚገኝ አንድ የገጠር መንደር ተገኝቶ ሰወችን አናገረ ፡ ኑሮ እንዴት ነው ?
አሪፍ ነው
ምንድነው የሚቸግራችሁ ?
ውሀ አሉት
በከፍተኛ ሁኔታ የውሀ ችግር አለብን ፡ የወንዝ ውሀ ነው የምንጠጣው ።
ጥሩ እኛም የመጣነው ይህንን ችግራችሁን ተረድተን ነው ፡ አለና ቦታ ተመርጦ ለዚሁ ጉዳይ አዘጋጅቶ በመጣው ግዙፍ የውሀ ማውጫ ተሽከርካሪ አማካኝነት ወደታች መቶ ሜትር እየተቆፈረ ውሀ የማውጣት ስራ ተጀመረ ።
..............
ከጥቂት ቀናት በኋላም ለዛች መንደር የመጀመሪያ የሆነው የውሀ ጉድጓድ ተቆፍሮ ልክ ውሀው ሲወጣ ሚስተር ቢስት መቁጠር ጀመረ .......

አንድ !
.....

ጉዞ ወደ ቀጣይ መንደር ....
እዛም ሌላ የውሀ ጉድጓድ ተቆፈረ ።

ሁለት አለ .

በዚህ ሁኔታ በተለያዩ የኬንያ ከተሞች እየተዘዋወረ የውሀ ጉድጓድ መቆፈሩን ቀጠለና የመጨረሻዋ ከተማ ውሀ ሲወጣ ሚስተር ቢስት አርባ አምስት ብሎ ቆጠረ ።

በኬንያ ብቻ አርባ አምስት የሚሆኑ ፡ ፈሰው ፈሰው የማያልቁ ዘመናዊ የውሀ ጉድጓዶችን ሰርቶ ፡ የተወሰኑ ትምህርት ቤቶችን አድሶ ዘመናዊ ኮምፒውተር ገዝቶ ጉዞውን ወደ ዚምባብዌ አደረገና ኬንያ ላይ ካቆመው ጀምሮ የውሀ ጉድጓዶችን መቁጠር ጀመረ ።

አርባ ስድስተኛው የውሀ ጉድጓድ በዙምባብዌ ተቆፈረ ።

አርባ ሰባተኛው ተከተለ ።
.......
በዚህ ሁኔታ በተለያዩ የዚምባብዌ ከተሞች ውሀ ላጡ ነዋሪዎች የውሀ ጉድጓድ መቆፈሩን ቀጥሎበት ሀምሳኛው ላይ ደረሰ ።
ስልሳን አለፈ .

እንዲህ እንዲህ እያለ አምስት ለሚሆኑ የአፍሪካ የገጠር መንደሮች ፡ ለሰላሳ አመታት ያለሀሳብ ሊጠቀሙበት የሚችሉና ለአራት መቶ ሺህ ህዝብ የሚያገለግሉ አንድ መቶ የውሀ ጉድጓዶችን አስቆፍሮ አስረክቧል ።
......
ሚስተር ቢስት ይህንን የውሀ ቁፋሮ ባከናወነበት ከተሞች በአንዷ የገጠር መንደር ተገኝቶ ውሀ አስቆፍሮ ፡ ሁለት ከተሞችን የሚያገኛኝ የኮንክሪት ድልድይ ሰርቶ . ... ብቸኛ የሆነውን የአንደኛ ደረጃ ት/ት ቤት በዘመናዊ መልኩ እንደገና ካስገነባ በኋላ ፡ ለሁሉም ተማሪዎች ወደትምህርት ቤት የሚመላለሱበት ብስክሌት ገዝቶ ሰጥቷል ።
.....
2024/09/28 09:28:04
Back to Top
HTML Embed Code: