Telegram Web Link
ይሄንን ያውቃሉ ???

በማርስ ላይ ፀሐይዋ ስትለቅ ፀሀዩ ሰማያዊ ቀለም ይሆናል።

@Amazing_Fact_433 @Amazing_Fact_433
በሀገረ ኮሎምቢያ ከመንግስት የገዘፈ ተፅእኖ ያለው የአደንዘዥ እፁ ንጉስ ተብሎ የሚታወቀው ፓብሎ ኢስኮባር በአንድ ወቅት በአለም የቱጃሮች ሰንጠረዥ ላይ በ 30 ቢሊዮን ዶላር ከአለም ሰባተኛው ሀብታም ለመሆን ችሎ ነበር

✔️ኢስኮባር በአደንዛዥ እፅ ዝውውር የሚታወቅ አለም አቀፍ ወንበዴ ተብሎ ተሰይሟል በዚህ የእፅ ዝውውር ኢስኮባር የሚታወቅበት አንድ ጠንከር ያለ ህግ አለው plata o plomo ይባላል

✔️በእንግሊዘኛው silver or lead በአማርኛ ስጠው ካልተቀበለህ ተኩሰህ ግደለው በሚለው ህጉ ከታላላቅ የመንግስት ሹማምንቶ እስካ ታችኛው መደብ ሰራተኞች የስራው አካል ያደርጋቸው ነበር

✔️በአንድ ወቅት ሀገሩ ኮሎምቢያ የ 10 ቢሊየን ዶላር እዳዋን መክፈል ባልቻለችበት ሁኔታ..የሀገሪቱን ጠቅላላ እዳ እኔ እከፍላለሁ ብሎ ነበር የኮሎምቢያ መንግስት አልፈቀደለትም እንጅ።

✔️ከፖሊስ ሽሽት ቤተሰቦቹን ይዞ ጫካ በሚያቋርጥበት ጊዜ ሴት ልጁ ቅዝቃዜ ስለተሰማት ብቻ 2ሚሊየን ዶላር ገንዘብ እንድትሞቀው አቃጥሎላታል በኢስኮባር የእፅ ዝውውር ሂደት ውስጥ ከ 4ሺ የሚበልጡ ሰወች ተገድለዋል ኢስኮባር ለእግርኳስ ከፍተኛ ፍቅር የነበረው ሲሆን በሀገሩ የሚገኙትን የእግርኳስ ቡድን በገንዘብ በመደገፍ ይታወቃል ።

✔️ገንዘቡን ባንክ ከማስቀመጥ ይልቅ ጫካ ውስጥ መቅበር የሚወደው ኢስኮባር የገንዘቡን 10% በአይጦች ተበልቶበታል መኖሪያ ቤቱ ላይ 63 ሚሊየን ዶላር የሚያወጣ የዳይኖሰር ሀውልት አሰርቷል

✔️የኳስ መጫወቻ ሜዳ የግላድያተሮች አሬና የኮርማወች መጋጠሚያ የቴኒስ ሜዳን ጨምሮ በመኖሪያ ቤቱ ላይ በርካታ መዝናኛወችን ገንብቷል

በመጨረሻም ልጁን መልካም ልደት ለማለት ስልኩን አንስቶ ሲደውል ስልኩ በመጠለፉ በኮሎምቢያ ፓሊሶች ተደርሶበትጅንስ ሱሪና ነጠላ ጫማ እንዳለበሰ በጥይት ተመቶ ወድቋልፖሊስም ድሉን viva Colombia በማለት አጣጥሟል
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች
Photo
ካቢኔው

አንድ ተጓዥ ብቻውን በእግር ዘና ለማለት ወደ ጫካ ለመሄድ ወሰነ። ብዙም ያልለመደው ነገር ነበር... የቀኑ አየር እንደሌለው ጊዜ የተለደመ ነበር። የሄደበት ጫካ ዛፎችና ቁጥቋጦዎች አካባቢውን የወጡበት ነበር። በተራሮች ላይ ተሰቅሎ ጊዜውን በደስታ ሲያሰልፍ ነበር። ወደ መኪናው እስኪመለስ ድረስ  ለእሱ ምንም አይነት እንግዳ ነገር አልነበረም። የስምንት ሰአት የእግር ጉዞ በቂ እንደሆነ አስቦ ነበር። ነገር ግን ያሰበው ሳይሆኖለት ቀረ... ሰማዩ አስቀድሞ እየጨለመ ነበር እና... በፍጥነት መመለስ ነበረበት። የሚገርመው ነገር የመመለሻውን መንገድ አለማወቁ ነው። መደናገጥ ጀመረ።

ሌሊቱ ቀድሞ በጣም መሸ እና ያለው ሁሉ ባትሪ ብቻ ነበር እና... እንዴት እንደሚመለስ ምንም አያውቅም። በአደገኛው ጫካ ውስጥ ለማለፍ በጣም ዘግይቷል እና... በጣም አደገኛ እንደሆነ ያውቃል። ለሊት በመሆኑ... ምንም መጠለያ እንደሌለው ሲያውቅ... ይጨነቅ ጀመር ፣ እንደ እድል ሆኖ፤ ከተሰባበረ ካቢኔ ውስጥ ገባ። ጨለማ ነበር፣ እና ማንም ሰው ለዓመታት የጎበኘው አይመስልም። ነገር ግን... እስከ ቀን ብርሃን ድረስ የሚያርፍበት ብቸኛው ቦታ እንደሆነ ሲያውቅ... ለማደር ታገዷል። በተለይ ባትሪው ብርሃን እያለቀበት ነው። በሩን ደጋግሞ አንኳኳ ነገር ግን ማንም መልስ ሊሰጠው አልቻለም። ስለዚህ እራሱን በሚያስገርም ሁኔታ አስገባ። ቤቱ ውስጥ ገባ ከዛም ማኝታ ቤት ገባ አንድ ሰው አልጋ ላይ ተመለከተው ። አልጋው ላይ የተኘው ሰውዬ የቤቱ ባለቤቱ ሲሆን... ቤቱ ውስጥ የገባው ሰውዬ ባለቤቱ ምንም እንደማይሰማው እርግጠኛ ነበር ወይም ምናልባትም ሞቷል የሚል ስጋት አደረበት። እናም ወደ ፊት ሄዶ አልጋው ላይ ተመቻችቶ ከቤቱ ባለቤቱ ጋር ለመተኛት ሲሞክር በክፍሉ ዙሪያ ያሉትን የስዕሎች ስብስብ ችላ ማለት አልቻለም። እንግዳ የሚመስሉ ሰዎች ሁሉ ወደ እሱ አፍጥጠው ይመለከቱታል። አንዳንዱ ፈገግታ ለብሶ ይመለከቱታል። እሱም ይንቀጠቀጣል።  ብዙም ሳይቆይ በጉዞው ላይ የነበረው ድካም የተሻለ ሆኖለታል እንዲተኛ አድርገውታል። ፊቶችን ችላ ማለት ቻለ።

በማግስቱ ጠዋት በማለዳ ላይ ከእንቅልፉ ሲነቃ በክፍሉ ዙሪያ ምንም ሥዕሎች አለመኖራቸውን በማየቱ ደነገጠ፣ ግን መስኮቶች ...

ታሪኩን በዚው እንግታው... ታሪኩ በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ሲሆን... ከ The Cabin ከተባለው ፊልም የተወሰደ ነው። ፊልሙን እንድትመለከቱት ጋበዞኳችሁ።
ወደላይ በማየት ሰማዩን እንዲህ መሆኑን አረጋግጡ።

@Amazing_Fact_433 @Amazing_Fact_433
ይሄንን ያውቃሉ ???

ሊንደን ቢ ጆንሰን በአውሮፕላን ቃለ መሃላ የፈጸሙ የመጀመሪያው እና ብቸኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ነበሩ። እሱም እ.ኤ.አ በኖቬምበር 22, 1996 ነበር።

@Amazing_Fact_433 @Amazing_Fact_433
በአንድ ወቅት  የታላቁ ማፊያና እፅ አዘዋዋሪ የፓብሎ ኤስኮባር ሴት ልጅ የሆነችው ማኑኤላ ኤስኮባር ከሞግዚቷ ጋር ሆና ቤድታይም ስቶሪ እያዳመጠች ነው ።

ሞግዚቷ የታላቁን ማፊያ ልጅ በተረት አባብላ  ለማስተኛት በጥንት የግሪክ ተረቶች ውስጥ ስላለው አንድ ፈረስ እያወራቻት ነው ። ይህ የተረት አለም ፈረስ ቀለሙ እንደበረዶ የነጣ ፡ በግንባሩ መሃል ቀንድ ያለው ፡ እና በጎኑ ላይ ባሉት ነጫጭ ክንፎች በሰማይ ላይ የሚበር ነበር ።

እናም ህፃኗ ማኑኤላ ይህን የፈረስ ታሪክ እንደሰማች ፡ ወደ አባቷ መኝታ ክፍል አመራችና እንዲህ አለችው ..........
papá necesito un caballo con cuerno y alas , ( " አባቴ ክንፍና ቀንድ ያለው ነጭ  ፈረስ እንድትገዛልኝ እፈልጋለሁ  " ). ... ....... ከዛስ. ..

ፓብሎ ኢስኮባር አለም ሳይፈልግ ያነገሰው ኮሎምቢያን አንቀጥቅጦ የገዛ የምንጊዜም የአደንዛዥ እጽ ንጉስ ነበር

........... .. ማኑኤላ ኢስኮባር በግንባሩ መሃል ቀንድ ያለው ነጭ  ባለክንፍ  ፈረስ እንዲኖራት ፈለገች  ።

እናም ከምንም ነገር በላይ ለሚወዳት አባቷ ነገረችው ። ልጁ ካለች አለች ነውና ፡ የሱ ልጅ ሆና በምድር ላይ የምታጣው ነገር የለምና. ..  እንደበረዶ ነጭ ቀለም  ፡ በግንባሩ መሃል ቀንድና ክንፍ ያለው (  unicorn )  ፈረስ መፈለግ ጀመረ ።

ፓብሎ ኢስኮባር ተከታዮቹን ጠርቶ አጣሁ የሚል ምክንያት እንደማይቀበል
በማስጠንቀቅ ልጁ የፈለገችው አይነት  ፈረስ ከየትም ብለው  እንዲያመጡ  ጥብቅ ትእዛዝ ሰጣቸው ።

ከተወሰነ ጊዜ በኋላም ማኑኤላ ኢስኮባር በጥንት የግሪክ ተረት ውስጥ ሰምታ እንዲኖራት የፈለገችውን በግንባሩ መሃል ቀንድ ያለው ባለክንፍ ፈረስ አምጥቶ ልጁን ሰርፕራይዝ አደረጋት ።

ይህ ፈረስ ቀንድና ክንፍ እንዲኖረው ለማድረግ በተደረገለት የፕላስቲክ ሰርጀሪ ቀዶ ጥገና ምክንያት ባጋጠመው ኢንፌክሽን ብዙ በህይወት መቆየት ባይችልም በወቅቱ ግን ልጁ የምትፈልገውን አግኝታ ደስ እንዲላት አድርጓታል

...............................
የጃፓኖች የስራ ባህል !


ከሁሉም በላይ ዓለምን የሚያስገርመው እና የሚያስደንቀው የጃፓናዊያን የስራ ባህል ነው !

ጃፓኖች የእረፍት ትርጉሙ አይገባቸውም!
የዓለማችን ረጅም ሰዓታቸውን በስራ ላይ የሚያሳልፉ ዜጎች ጃፓናዊያን ናቸው። በስራ ብዛት የሰው ልጅ የሚሞተው ጃፓን ውስጥ ብቻ ነው ! ሞቱን "Karoshi" ብለው ይጠሩታል። በዓመት ካላቸው የ 20 ቀን እረፍት ውስጥ 10 የሚሆነውን እንኳን በአግባቡ አይወስዱም። 63% የሚሆኑ ጃፓናዊያን በእረፍት ሰዓታቸው በሚከፈላቸው ገንዘብ ደስተኛ አይደሉም ። መንግስት "...የአመት እረፍታችሁን እባካችሁ ውሰዱ! በስራ ብዛት እና ጭንቀት እየሞታችሁ ነው! እስቲ ትንሽ ዘና በሉ!..."ብሎ ሲለምን የምትሰማው የጃፓን መንግስትን ብቻ ነው።

@Amazing_Fact_433
@Amazing_Fact_433
በየአመቱ ሁለት ቢሊየን ዶላር በአይጥ የሚበላበት ሰው ።

✔️ከመምህርት እናት እና ከአንድ ምስኪን ገበሬ የተገኘው ፓብሎ ኢስኮባር ወደ አሜሪካን የሚገባውን  80% የሚሆነውን ኮኬይን በቀጥታ የሚልከው እርሱ ሲሆን በዚህ የኮኬይን ንግድ በሳምንት እስከ 420 ሚሊየን ዶላር ወደኪሱ ይገባ ነበር

✔️ይህን ኮኬይን ወደ አሜሪካን የሚያስገባውም  ከአውሮፕላኖቹ ፓይለቶች ጋር በመነጋገርና የአውሮፕላን ጎማዎች ውስጥ  በመደበቅ ሲሆን ለዚህም አገልግሎታቸው እያንዳንዱ ፓይለት ባደረሰ ቁጥር ግማሽ ሚሊየን ዶላር ይሰጥ ነበር ።

✔️ከዚህም በተጨማሪ ፓብሎ ኢስኮባር በኮሎምቢያ ጥቅጥቅ ደኖች ውስጥ ባሉት የኮኬይን ማምረቻ ካምፖች ውስጥ የሚመረተውን  ይህን ብዛት ያለውን አደንዛዥ እጽ ለማስተላለፍ የራሱ የሆነ አውሮፕላኖችና ግዙፍ ባህር ሰርጓጅ ጀልባዎች ነበሩት ።

✔️ አደንዛዥ እጽ ማምረቻ ካምፖቹ ትልቅ ይዞታ እና በሚገባ በታጠቁ ኮማንዶዎች የሚጠበቁ ሲሆን በውስጣቸውም የሰራተኞች ልጆች የሚማሩበት ትምህርት ቤት ፡ ሆስፒታል እና የመዝናኛ ቦታዎች ነበሯቸው ።

✔️በአንድ ወቅት በየቀኑ ከነዚህ ቦታዎች ተመርተው በፍሎሪዳ ወደብ ያለብዙ ችግር ይራገፍ የነበረው የኮኬይን መጠን ሁለት ትላልቅ የአፍሪካ ዝሆኖችን ያህል ክብደት ነበረው ።

✔️ቤተክርስቲያን ሆስፒታል ፡ ስታዲየሞችንና ለከተማው ህዝብ የሚያስፈልጉ መሰረተ ልማቶችን ያለ ማንገራገር ይሰራ የነበረው ፓብሎ ኢስኮባር አንዳንድ ጊዜ ተደብቆ ወጥቶ ሮቢን ሁድ በሚል ስም ለተቸገሩ ሰወች እጅግ ብዙ ብር መስጠትን እንደቋሚ ስራው አድርጎትም የነበረ ሲሆን በዚያች ከተማ ውስጥ የሚኖር  ማንም ይሁን ማን ለችግሩ ለህመሙ የሚደርስለት ፓብሎ ኢስኮባር ነበር ።

✔️በዚያው መጠን በስራው ጣልቃ የገባበትን ሰው ለማስወገድ ሁለቴ የማያስበው ዶን ፓብሎ በብዙ ፡ ዳኞች ፖሊሶችና ሌሎች  ሰወች ግድያ ተጠያቂ ነበር ።

✔️በአሜሪካን ውስጥ  ከምታሰር በሃገሬ ሞቼ ብቀበር ይሻለኛል የሚለው ዶን ፓብሎ ፡ ሃገሩ ኮሎምቢያ ከአሜሪካን ጋር ያላትን ወንጀለኞችን አሳልፎ የመስጠት ስምምነት ከሰረዘች ሃገሪቱ ያለባትን 20 ቢሊየን ዶላር እዳ እንደሚከፍል ጠይቆ ነበር ።

✔️ፓብሎ ኢስኮባር ወይም ዶን ፓብሎ አንድ በጣም ችግር የሆነበት ነገር ገንዘቡን የሚያስቀምጥበት ቦታ ማጣት ነው፡

✔️እናም ለዚህ እንደመፍትሄ ብሎ የወሰደው በጥቂት ሚስጥረኛ ሰወች ብቻች በሚታወቁ ቦታዎች ፡ በእርሻ ውስጥ እና ሰው የማይኖርባቸው አካባቢዎች ገንዘቡን መቅበር ነበር በዚህም በአይጦች ከሚያገኘው ገቢ ውስጥ በአመት 10% ያጣ ነበር ይህ ወደ ገንዘብ ሲለወጥ ወደ ሁለት ቢሊየን አንድ መቶ ሚሊየን አካባቢ ይሆናል
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ሌላው ጃፓኖንች እጅግ በጣም ሰው አክባሪ እና ትሁት ከመሆናቸው የተነሳ ማንኛውንም እቃ ምግብ ወይም መጠጥ በሁለት እጃቸው እንጂ በአንድ እጃቸው በፍፁም አይቀበሉህም! እሱንም ከወገባቸው ጎንበስ ብለው ነው። የሚገርመው ቤት ውስጥ ውጪ የዋልክበትን ጫማ አድርጎ መግባት ነውር ነው። አይደለም ቤትህ አንዳንድ ምግብ ቤቶች ሳይቀር ተስተናጋጆች ጫማቸውን አድርገው እንዲገቡ አይፈቀድም ! በር ላይ ሸበጥ/ሲሊፐር ስለሚቀመጥልህ ቀይረህ መግባት ግድ ነው። ከዓለማችን ብቁ ተማሪዎች ካሏት ሀገር ውስጥ ተርታ ይሰለፋሉ። 100% የሚሆነው የሃገሪቷ ወጣቷ በሚገባ ፊደል የቆጠረ እና ቀጥቅጦ የተማረ ነው !

@Amazing_Fact_433
@Amazing_Fact_433
ከ5 ሳምንታት በኃላ ሐምሌ3 ፣ guess what?...

#Entrance_Exam🥲

@Amazing_Fact_433
✔️ይህን ያውቃሉ

ኤርትራ ውስጥ ATM ማሽን የሚባል ነገር
የለም።

ከባንክ ገንዘብ ማውጣት የምትችሉት የባንክ ባለሙያው|ከፋዩ ሰው ፊት በጥሬ/in cash ሲሆን

ይህም ሆኖ ደግሞ በወር ከ5000 ናቅፋ በላይ ማውጣት አይቻልም!


@Amazing_Fact_433
@Amazing_Fact_433
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ይሄንን ያውቃሉ ???

የሴሌና ጎሜዝ እናት እሷን በወለደችበት ጊዜ ገና 16 ዓመቷ ነበር!

@Amazing_Fact_433 @Amazing_Fact_433
Forwarded from Quality Button
ብዙ ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ ማሸነፍ የቻለው ክለብ የትኛው ነው ???
ይሄንን ያውቃሉ ???

በ68 ዶላር ብቻ የሉዊስ ቫዩቶን ኮንዶም መግዛት ይችላሉ።

@Amazing_Fact_433 @Amazing_Fact_433
2024/09/27 23:15:16
Back to Top
HTML Embed Code: