Telegram Web Link
◉ ይህ▸ https://youtu.be/5YYX3k9Orho የኡስታዝ ኢልያህ ማሕሙድ ይፋዊ የዩቲዩብ ቻናል ነው። የተለያዩ ኢስላማዊ እና ንፅፅራዊ ትምህርቶች የሚለቀቁበት ብቸኛው ገጹ ስለሆነ Subscribe/Like/Share በማድረግ ዳዕዋውን ለወገኖቻችን በፍጥነት ያድርሱ።

® Ustaz Eliyah Mahmoud Telegram Channel.
የምስራች
...
ማዕከላችን ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል በአሏህ ﷻ እገዛ ከዚያም በታች በብርቱ ወንድሞችና እህቶች ጥረት ህጋዊ ሒደቱን አጠናቆ በይፋ ስራዎችን ጀምሯል። በሀገራችን እየተንሰራፋ የሚገኘውን የአክፍሮተ ሀይላት እንቅስቃሴ በዳዕዋ ለመመከትና እስልምና ያልደረሰባቸው አካባቢዎች ሪሳላውን ለማስፋት ትኩረት አድርጎ የሚሰራው ማዕከላችን ስራውን በተጠናከረ መልኩ ለመስራት ጉዞውን በአሏህ ﷻ ፍቃድ ጀምሯል።
...
በተጨማሪም የበጎ አድራጎት ስራዎች የሚያስፈልግባቸው አካባቢዎች ላይ ስራዎችን ለመስራት ራሱን የቻለ ህጋዊ የበጎ አድራጎት ፍቃድ ያለው ሲሆን በተለያዩ ቦታዎች በወገኖቻችን ላይ ለሚደርሱ እምነት ፈታኝ መከራዎች በተቻለው መጠን ለመስራት እንቅስቃሴውን ጀምሯል። የማዕከላችን አባል በመሆን በጉልበት እንዲሁም በገንዘብ የአቅማችሁን መደገፍ ለምትፈልጉ ከዚህ በታች ባለው የጎግል ፎርም አባል እንድትሆኑ እየጠየቅን በቀጥታ ለመደገፍ ከዚህ በታች ያለውን የማዕከሉ ኦፊሺያል አካውንት መጠቀም ትችላላችሁ።

አካውንት - 1000499318212
የአካውንት ስም - Hidaya Islamic Center
በአጭር ቁጥር - 8212 መጠቀም ይችላሉ።
____
በተሰማሩበት መስክ የሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል አባል በመኾን ዳዕዋውን ማገዝ ከፈለጉ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ የአባልነት ቅፅ በመሙላት ሊቀላቀሉን ይችላሉ፦

https://bit.ly/3r7DhoY
📌 የትብብር ጥያቄ

📌 270,000 ብር ብቻ

''እኛ መስማት የተሳናቸው ሙስሊሞች ዙርያ የምንሰራ ኢማን የኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ልማት ድርጅት እንባላለን። ከማህበራት ማደራጃ ፍቃድ ያለን ህጋዊ ተቋም ነን።

ህዳር 19 ላይ አለም አቀፍ የመስማት የተሳናቸው ሙስሊሞች ኮንፈረንስ ጋምቢያ ላይ እንድንሳተፍ የጥሪ ደብዳቤ ተልኮልናለን። ስብሰባው ለመላው ኢትዮጵያዊ ሙስሊም መስማት የተሳናው ይጠቅማል ብለንም እናምናለን። ግን አሁን እኛ የደርሶ መልስ የአየር ጉዞ ቲኬት ለመክፈል አቅሙ የለንም። የምንሄደው 3 ሰዎች ነን።

ለያንዳንዳችን ከ80 እስከ 90ሺህ ብር ወይም ለ3ታችን 270ሺህ ብር ገደማ ይጠበቅብናል። የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት የትብብር ደብዳቤ ፅፎልናል። እባካችሁ በኮንፈረንሱ ላይ እንድንሳተፍ ለአላህ ብላቹ ተባበሩን ይላሉ'' መልዕክታቸው።

ሁላችንም ብንተባበራቸው ቀላል ገንዘብ ናት። መስማት የተሳናቸውን፣ አይነ ስውራንን የመሳሰሉ ወገኖቻችንን በእምነታቸው እንዲጠነክሩ ማገዝ የሁላችንም ግዴታ ነው።

ከታች ባሉ አካውንቶች ድጋፍ በማድረግ እናግዛቸው።

📌 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት
📌 1000461347936
📌 IMAN ETHIO DEAF DEVT ORGA (IEDDO)

🔴 ሒጅራ ባንክ
🔴 1002450020001
🔴 IMAN ETHIO DEAF DEVT ORGA (IEDDO)

📌 ዘምዘም ባንክ
📌 0009389910301
📌 IMAN ETHIO DEAF DEVT ORGAN
አሰላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ

ውድና የተከበራችሁ ሙስሊም ወንድሞችና እሕቶች!

እንኳን 1,444ኛው የረመዷን ወር ፆም አላህ በሰላም አደረሳችሁ!!

አላህ ወሩን የዚክር፣ የዱዓእ፣ የቂያም፣ የድል ወር ያድርግልን
The owner of this channel has been inactive for the last 11 months. If they remain inactive for the next 28 days, they may lose their account and admin rights in this channel. The contents of the channel will remain accessible for all users.
ይህ የቁርኣን አፕ ቁርኣንን በምትቀሩበት ጊዜ ስህተቶችን እንድታርሙ ይረዳችኋል
እንኳን ለ 1,444ኛው የዒዱል አድሓ በዓል አላህ በሰላምና በጤና አደረሳችሁ!!

ጌታ አላህ ዒዱን የተባረከ፣ የመደሰቻ፣ ምስኪኖችንም የማስደሰቻ ቀን ያድርግላችሁ።

ዒዱኩም ሙባረክ፣ ተቀበለላሁ ሚንና ወሚንኩም
ዐሹራእ ደረሰ
በአቡ ሀይደር
አሰላሙ ዐለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን፡፡(አል-ፋቲሓ 2) ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡

#ዐሹራእ ምንድነው?

ዐሹራእ ማለት (የሙሐረም ወር) አስረኛው ቀን ማለት ነው፡፡ አሁን ያለንበት ወር ሙሐረም አንደኛው ወር ተብሎ ይጠራል፡፡

#ይህ ወር ክብር ያለው ወር ነው
አቢ ሁረይራህ(ረዲየላሁ ዐንሁ) ከነቢያችን(ዐለይሂ ሶላቱ-ወስ-ሰላም) እንዳስተላለፈልን የአላህ መልክተኛ እንዲህ ብለዋል፡- "ከረመዷን ቀጥሎ ከጾሞች ሁሉ በላጩ የአላህ ወር የሆነው ሙሐረም ነው" (ሙስሊም 2812)፡፡
ከሙሐረም ወር ውስጥ ደግሞ አስረኛው የዐሹራእ ቀን በላጭ ቀን ነው፡፡

#ለምን ይጾማል?
ዐብደላህ ኢብኑ-ዐባስ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንዲህ አሉ፡- "የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ወደ መዲና ሲገቡ አይሁዶችን በዐሹራእ ቀን ሲጾሙ አገኟቸው፡፡ ይህን ቀን የምትጾሙት ለምንድነው? ብለው ሲጠይቋቸው፡ እነሱም፡- ይህ ታላቅ ቀን ነው! አላህ ሙሳንና ተከታዮቹን ከፊርዐውንና ሰራዊቱ በማዳን እነሱን በባሕር ያሰጠመበት ቀን ስለሆነ ሙሳም ለአላህ ምስጋናን ለማድረስ ጾሞታል እኛም እንጾመዋለን ብለው መለሱ፡፡ የአላህ መልክተኛውም (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ፡- ለሙሳ (ወዳጅነት) ከናንተ ይልቅ እኛ የቀረብንና የተገባን ሰዎች ነን እኮ! በማለት እሳቸውም ጾሙት ሶሓባዎቻቸውንም እንዲጾሙ አዘዙ" (ሙስሊም 2714)፡፡
ከዛ በፊት ግን በመካ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ዐሹራእን ይጾሙ ነበር ነገር ግን ማንንም አላዘዙም፡፡

#ጥቅሙስ ምንድነው?
አቢ ቀታዳህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተናገረው የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "የዐረፋ ቀን ጾም አላህ ዘንድ ያለፈውንና የሚመጣውን (የሁለት) ዓመት (ትናንሽ) ኃጢአቶችን ያስምራል፣ የዐሹራእ ቀን ጾም ደግሞ ያለፈውን አንድ ዓመት (ትናንሽ) ኃጢአት ያስምራል" (ሙስሊም 1976)፡፡

ዐብደላህ ኢብኑ ዐባስ(ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንዲህ አለ፡- የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የዐሹራእን ቀን የጾሙና ሶሓቦቻቸውን ያዘዙ ጊዜ፡- "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ይህን ቀን እኮ አይሁዶችና ክርስቲያኖች ያከብሩታል ሲሏቸው፡ እሳቸውም፡- በቀጣዩ ዓመት አላህ ካደረሰን ዘጠነኛውን ቀን እንጾማለን አሉ፡፡" (ሙስሊም 2722)፡፡

በሌላ ዘገባ ላይ ደግሞ "ከ(ዐሹራእ) ቀን ከፊቱ ወይም ከኋላው አንድን ቀን ጹሙ" ብለዋል (አሕመድ የዘገቡት)፡፡

ያ ዓመት ሳይደርስ የአላህ መልክተኛ ከዚህ ዓለም ተለዩ፡፡ የኢስላም ሊቃውንትም ከዚህ ሐዲሥ በመነሳት የሁዳዎችን ላለመመሳሰል ዘጠነኛውንም ቀን ጨምሮ መጾም ነቢያዊ ሱንና መሆኑን ገለጹ፡፡

#መጾሙ ዋጂብ ነው ወይስ ሱንና?
የዐሹራእን ቀን መጾም ሑክሙ ሱንና ነው፡፡ በሒጅራ 2ኛው ዓመት የመጀመሪያው ወር ሙሐረም ላይ ስለነበር የተደነገገው የረመዷን ጾም እስኪደነገግ ድረስ ዋጂብ ነበር፡፡ ከ7 ወር በኋላ ግን በሒጅራ 2ኛው ዓመት 8ኛው ወር ሻዕባን ላይ የረመዷን ጾም ግዳጅነት ሲደነገግ፡ ዐሹራእ ግዳጅነቱ ተሰረዘ፡፡ ይህን በተመለከተ ቀጣዩ ሐዲሥ እንዲህ ይላል፡-
እናታችን ዓኢሻህ (ረዲየላሁ ዐንሃ) እንዲህ አለች፡- "የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ረመዷን ሳይደነገግ በፊት ዐሹራእን ይጾሙ ነበር፡፡ ካዕባም የሚሸፈንበት ቀን ነበር፡፡ አላህ ረመዷንን በደነገገበት ጊዜ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- የፈለገ ሰው (ዐሹራእን) ይጹመው ለመጾም ያልፈለገ ደግሞ ይተወው" (ቡኻሪይ 1489)፡፡

#መቼ እንጀምር?
የሙሐረም አስረኛው ቀን(ዐሹራእ) የፊታችን ጁምዓ ነው የሚውለው፡፡ ስለዚህ አላህ ወፍቆት ይህን ዐሹራእን መጾም የፈለገ ከአራቱ መንገዶች አንዱን መርጦ ይጹም፡-
ሀ. ጁምዓ ብቻ፡- 10ኛውን ቀን መጾም ማለት ነው፡፡ ዋናው ዐሹራእ ተብሎ የሚጠራውም ይህ ቀንነው፡፡

ለ. ሀሙስና ጁምዓ ፡- 9ኛውንና 10ኛውን ቀን መጾም ማለት ነው፡፡ ይህም በላጭ ነው፡፡

ሐ. ከ ሀሙስ-ቅዳሜ ፡- 9ኛ፣10ኛና 11ኛውን ቀን ማለት ነው፡፡ ይህ ከሁሉም በላጩ ነው፡፡

መ. ጁምዓና ቅዳሜ፡- 10ኛውና 11ኛውን ቀን መጾም ማለት ነው፡፡ ይህም ሱንና ነው
አላህ ይወፍቀን፡፡

#ስምንቱ የፆም ቀናት
አላህ ፆምን ያገራለትና የወፈቀው ሰው ደግሞ ከፈለገ በተከታታይ ለስምንት ቀናት መፆም ይችላል፡፡ እንዴት ካሉም፡-
ከሀሙስ-ቅዳሜ ፡- እነዚህ ሶስት ቀናት የሙሐመረም 9ኛ 10ኛና 11ኛ ቀናት ስለሆኑ፡ ከዐሹራእ ፆም ጋር በተያያዘ መልኩ ይፆማሉ ማለት ነው፡፡

ሰኞ፡- ይህ 13ኛው ቀን በራሱ የሱንና ፆም ቀን በመሆኑ ይፆማል ማለት ነው፡፡

ሰኞ -እሮብ ፡- እነዚህ ሶስት ቀናት የሙሐረም 13ኛ 14ኛና 15ኛ ቀናት ናቸው፡፡ አያሙል-ቢድ በመባልም ይጠራሉ፡፡ የወሩን ሶስት ቀናት በነዚህ ቀናት መፆም በላጭ ነው፡፡

ሀሙስ፡- ይህ 16ኛው ቀን በራሱ የሱንና ፆም ቀን በመሆኑ ይፆማል ማለት ነው፡፡
Click and Like ➤➤
http://fb.com/Ustaz.Abuhyder
2024/06/20 11:51:58
Back to Top
HTML Embed Code: