Audio
አዲስ ተከታታይ ደርስ ስለ ረመዷን ምንነት
🎙 አዘጋጅ⇊
በኡስታዝ አቡ ሀይደር
Join ➤➤ www.tg-me.com/abuhyder
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder

የኡስታዝ አቡ ሀይደር ትምህርቶች ስብስብ
አዲስ ተከታታይ ደርስ ስለ ረመዷን ምንነት 🎙 አዘጋጅ⇊ በኡስታዝ አቡ ሀይደር Join ➤➤ www.tg-me.com/abuhyder Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
Audio
አዲስ ተከታታይ ደርስ
ስለ ረመዷም ፆም ምንነት
ክፍል 2
🎙 አዘጋጅ⇊
በኡስታዝ አቡ ሀይደር
Join ➤➤ www.tg-me.com/abuhyder
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
ስለ ረመዷም ፆም ምንነት
ክፍል 2
🎙 አዘጋጅ⇊
በኡስታዝ አቡ ሀይደር
Join ➤➤ www.tg-me.com/abuhyder
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
የኡስታዝ አቡ ሀይደር ትምህርቶች ስብስብ
አዲስ ተከታታይ ደርስ ስለ ረመዷም ፆም ምንነት ክፍል 2 🎙 አዘጋጅ⇊ በኡስታዝ አቡ ሀይደር Join ➤➤ www.tg-me.com/abuhyder Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
Audio
አዲስ ተከታታይ ደርስ
ስለ ረመዷም ፆም ምንነት
ክፍል 3
🎙 አዘጋጅ⇊
በኡስታዝ አቡ ሀይደር
Join ➤➤ www.tg-me.com/abuhyder
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
ስለ ረመዷም ፆም ምንነት
ክፍል 3
🎙 አዘጋጅ⇊
በኡስታዝ አቡ ሀይደር
Join ➤➤ www.tg-me.com/abuhyder
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
የኡስታዝ አቡ ሀይደር ትምህርቶች ስብስብ
አዲስ ተከታታይ ደርስ ስለ ረመዷም ፆም ምንነት ክፍል 3 🎙 አዘጋጅ⇊ በኡስታዝ አቡ ሀይደር Join ➤➤ www.tg-me.com/abuhyder Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
Audio
አዲስ ተከታታይ ደርስ
ስለ ረመዷም ፆም ምንነት
ክፍል 4
🎙 አዘጋጅ⇊
በኡስታዝ አቡ ሀይደር
Join ➤➤ www.tg-me.com/abuhyder
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
ስለ ረመዷም ፆም ምንነት
ክፍል 4
🎙 አዘጋጅ⇊
በኡስታዝ አቡ ሀይደር
Join ➤➤ www.tg-me.com/abuhyder
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
የኡስታዝ አቡ ሀይደር ትምህርቶች ስብስብ
አዲስ ተከታታይ ደርስ ስለ ረመዷም ፆም ምንነት ክፍል 4 🎙 አዘጋጅ⇊ በኡስታዝ አቡ ሀይደር Join ➤➤ www.tg-me.com/abuhyder Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
Audio
አዲስ ተከታታይ ደርስ
ስለ ረመዷም ፆም ምንነት
ክፍል 5
🎙 አዘጋጅ⇊
በኡስታዝ አቡ ሀይደር
Join ➤➤ www.tg-me.com/abuhyder
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
ስለ ረመዷም ፆም ምንነት
ክፍል 5
🎙 አዘጋጅ⇊
በኡስታዝ አቡ ሀይደር
Join ➤➤ www.tg-me.com/abuhyder
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
Audio
አዲስ ተከታታይ ደርስ
በፃም ወቅት የተፈቀዱ ነገሮች
ክፍል 6

አዲስ ተከታታይ ደርስ በፃም ወቅት የተፈቀዱ ነገሮች ክፍል 6 🎙 አዘጋጅ⇊ በኡስታዝ አቡ ሀይደር Join ➤➤ www.tg-me.com/abuhyder Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
Audio
አዲስ ተከታታይ ደርስ
ፃምን የሚያፈርሱ ነገራቶች
ክፍል 7
🎙 አዘጋጅ⇊
በኡስታዝ አቡ ሀይደር
Join ➤➤ www.tg-me.com/abuhyder
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
ፃምን የሚያፈርሱ ነገራቶች
ክፍል 7
🎙 አዘጋጅ⇊
በኡስታዝ አቡ ሀይደር
Join ➤➤ www.tg-me.com/abuhyder
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
እንኳን ለተከበረው 1,443ኛው የረመዷን ወር ፆም አላህ በሰላም አደረሳችሁ!
አላህ ወሩን የዒባዳ፣ የድል፣ የአንድነት ያድርግልን
አላህ ወሩን የዒባዳ፣ የድል፣ የአንድነት ያድርግልን
ሸዋልን አደራ!
በአቡ ሀይደር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ምስጋና የዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ የተገባ ነው፡፡ የአላህ ውዳሴና ሰላም፡ የሰላም አለቃና መምህር ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ ይሁን፡፡ ድልና የበላይነት ሐቅን ለማንገስና ሀሰትን ለማርከስ፡ በደልን አጥፎቶ ፍትህን ለማስፈን ዕውቀታቸውን፣ ንብረታቸውን፣ ጉልበታቸውን፣ ጊዜያቸውንና ህይወታቸውን መስዋእት በማድረግ ለሚታገሉት የአላህ ባሮች ይሁን፡፡
® የሸዋል ወር በእስልምናው አቆጣጠር ከረመዷን ቀጥሎ የሚመጣ 10ኛ ወር ነው፡፡ ሸዋል የወሩ ስም እንጂ በወሩ ውስጥ የሚፆመውን 6ቀናት የሚመለከት ስም አይደለም፡፡ ይህ ወር እንደተቀሩት 11 ወራቶች እሱም 29/30 ቀናት አሉት፡፡ በዚህ ወር ውስጥ ደግሞ 6ቀናትን በማከታተልም ይሁን በማፈራረቅ መፆም እጅግ ተወዳጅ ነው፡፡ ዋጋውም (አጅሩም) በአሥር በመባዛት የስልሳ ቀን (ሁለት ወር) ፆምን አጅር ያስገኛል፡፡ ከረመዷን አንድ ወር ፆም (አሥር ወር አጅር) ጋርም በመደመር የአንድ ሙሉ ዓመት ፆም ምንዳ(ክፍያ) ይኖረዋል ማለት ነው፡፡ አላህ ይቀበለን፡፡ ይህንን በተመለከተም አሽረፈል ኸልቅ (የፍጥረቱ ሁሉ የበላይ) የሆኑት ነቢዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ በማለት አስተምረዋል፡፡ ኡመታቸውንም አነሳስተዋል፡-
"የረመዷንን ወር ጹሞ ከሸዋል ወር ስድስት ቀናትን ያስከተለ አመቱን ሙሉ እንደፆመ ነው" (ሙስሊም 1164)፡፡
® ስለዚህም የሸዋል ወር ፆም ረመዷንን የፆመ ሙስሊምን ሁሉ ይመለከታል ማለት ነው፡፡ የአዋቂዎችና የአባቶች ፆም ነው በማለት ሌላው አካል መዘናጋት የለበትም፡፡ ወይንም፡- ባልፆመው የማስጠይቀኝ፡ ግዴታ ያልሆነ ተግባር ነው ብለን አንሳነፍ፡፡ በመፆማችን ደግሞ የምናገኘውን አጅር እናስላ፡፡ አንድ ወር ሙሉ በተከታታይ በአላህ ተውፊቅና እገዛ መፆም ከቻልን ስድስት ቀናትን መፆም ደግሞ እንደምን ይጠናብናል?
አንዳንዱ ደግሞ ፆሙ ይከብዳል እንደ ረመዷን አይቀልም ይላል፡፡ እውነት ነው የሸዋል ወር ፆም ይከብዳል፡፡ ምክንያቱም፡- አንድ፡ በረመዷን የታሰረው ቀንደኛው ጠላታችን ሸይጧን ከዒድ ሶላት መጠናቀቅ በኋላ ተፈትቷልና ወደ ስራው ይመለሳል፡፡ ደግሞም ይህንን የሸዋልን ፆም ልክ እንደ ረመዷኑ ቤተሰብ፣ ጓደኞችና የመስጂድ ጀመዓዎች ሁሉም ስለማይፆሙት በሚፆሙት ላይ (አላህ ያገራለት ሲቀር) ሊከብድ ይችላል፡፡ ቢሆንም አላህ ዘንድ የሚገኘውን ሽልማት ያሰበና ያመነ ባሪያ ሊከብደው አይገባም፡፡
® እንዴት እንጹመው?
ከላይ ለመግለጽ እንደተሞከረው ሸዋል ሙሉ ወር በመሆኑ 29/30 ቀናት አሉት፡፡ የመጀመሪያው ቀን የዒዱ ቀን ነበር፡፡ ከዛ በኋላ የሚቀረው 28 ቀናት ይሆናል ማለት ነው (ወሩ 30 ለመሙላቱ እርግጠኛ መሆን ስለማንችል)፡፡ በነዚህ 28 ቀናት ውስጥ የሸዋልን ስድስት ቀናት በተከታታይ በማከታተልም ይሁን ቀናቱን ለያይቶ በማፈራረቅ መፆም ይቻላል፡፡ ከፈለገ ሰኞና ሀሙስ እደረገ፡ በአንድ ኒያ የሰኞና የሀሙስን እንዲሁም የሸዋልን ፆም በመነየት ሁለት አጅር መሰብሰብ ይቻላል፡፡
® ቀዷ ያለበትስ?
የረመዷን ቀዷ (በህመም፣ በሐይድ እና በመሳሰሉት) ያለበት ሰው፡ ቀዷው እያለበት የሸዋልን ፆም በመፆም ከዛ ቀዷውን ወዲያው ወይም በሌላ ጊዜ ማስከተል ይችላል ወይስ ቅድሚያ ቀዷውን ከዛም የሸዋልን ፆም? የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል፡፡
እዚህ ላይ ሁለት ነጥቦችን ማንሳት ይኖርብናል፡፡ እነሱም፡-
1. ከሑክም አንጻር
2. ከሚገኘው አጅር አንጻር
1ኛ. ከሑክም (ከሸሪዓዊ ፍርድ) አንጻር፡ ጉዳዩ በዑለማዎች (የኢስላም ሊቃውንት) መሐል ኺላፍ ቢኖርበትም፡ በላጩ ሐሳብ፡- ማንም ሙስሊም የረመዷን ቀዷ ቢኖርበት፡ ያንን ቀዷ ከመክፈሉ በፊት ሌሎች የሱንና ፆሞችን መጾም አይችልም የሚል መረጃ የለም የሚለው ነው፡፡ ይልቁኑ ቅዱስ ቁርኣን በግልጽ የሚናገረው፡ በበሽታም ይሁን በሙሳፊርነት እንዲሁም በሌላ ምክንያት የረመዷን ቀዷ ያለበት ሰው ‹በሌሎች ቀናት ቀዷውን ያውጣ› በማለት ተናገረው እንጂ፡ በሸዋል ወር ውስጥ ቀዷውን ይክፈል የሚል አይደለም፡፡ ጌታ አላህ እንዲህ ይላል፡-
"...فَمَنْ كَانَ مِنْكُمْ مَرِيضًا أَوْ عَلَى سَفَرٍ فَعِدَّةٌ مِنْ أَيَّامٍ أُخَرَ... " سورة البقرة 184-185
"…ከእናንተም ውሰጥ በሽተኛ ወይም በጉዞ ላይ የኾነ ሰው ከሌሎች ቀኖች ቁጥሮችን መጾም አለበት…" (ሱረቱል በቀራህ 184-185)፡፡
ስለዚህም የረመዷንን ቀዷ የመክፈያ ጊዜው እስኪመጣ በዚያ መሐል የሸዋልን 6ቀናት፣ ሰኞና ሀሙስ፣ የዙል-ሒጅጃህ ቀናት (በተለይ የዐረፋ ቀን) እና መሰል ፆሞችን መጾም አይቻልም አይባልም፡፡ ወላሁ አዕለም፡፡
2ኛ. ከሚገኘው ምንዳ አንጻር፡- ዋናው ቁልፉ ያለው እዚህ ጋር ነው፡፡ ሙሉ አመቱን እንደፆመ እንዲቆጠርለትና አጅሩም ተቀማጭ እንዲሆንለት የፈለገ ሰው ግን ግዴታ ቀዷውን ቀድሞ ማጠናቀቅ አለበት፡፡ ምክንያቱም ከላይ በሐዲሡ ላይ እንደተገለጸው የሸዋልን ወር ፆም ያስከተለ የተባለው ‹ረመዷንን ለፆመ› ሰው ብቻ ነው፡፡ አንድ ሰው ረመዷንን ጹሟል የሚባለው ሙሉውን ሲያጠናቅቅ ነው፡፡ የተወሰነ ቀሪ ዕዳ ካለበት፡ ረመዷንን የፆመ የሚለው ሐዲሥ ውስጥ አይካተትም፡፡ ስለዚህም የአጅሩ ተካፋይ እንድንሆን ቅድሚያ ቀዷችንን በማጠናቀቅ ከዚያም ወደ ሸዋሉ ፆም መግባት ይቻላል፡፡ ደግሞም ቅድሚያ ዕዳን ከፍሎ ማጠናቀቁ ተገቢ ተግባር ነውና፡፡ የተሟላውን የአመት አጅር ለማግኘት ከሸዋል ወር ስድስት ቀን ጾም በፊት ቅድሚያ የረመዷን ቀዷ መከፈሉ ግድ መሆኑን ከሚገልጹ የዑለማዎች ፈትዋ መሐከል፡-
1. ኢብኑ ባዝ (ረሒመሁላህ) ፡- ፈታዋ ኑሩን ዐለ-ደርብ ካሴት ቁ 918
2. ሙሐመድ ቢን ሷሊሕ አል-ዑሠይሚን (ረሒመሁላህ) ፡- ፈታዋ አል-ሐረሙል መኪይ ካሴት ቁ 7
አቋራጭ መንገድ ካለ?
መቼም ይሄ (shortcut) አቋራጭ መንገድ የሚባለው ነገር ተላምዶናል፡፡ በሰላምታ ወቅት (as wr wb) በሰላዋት ጊዜ (s.a.w) በምስጋና ተግባር ላይ (jzk)… ታዲያ አሁንም በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ እንዲሉ፡ የረመዷንን ቀዷና የሸዋልን ስድስት ቀናት ፆም በአንድ በመነየት አጣምሮ መፆም ይቻላል ወይ? የሚል ጥያቄ ተነሳ፡፡
ይህን ጥያቄ ፈዲለቱ-ሸይኽ ሙሐመድ ቢን-ሷሊሕ አል-ዑሠይሚን እንዲህ ይመልሱታል፡- ‹‹የረመዷን ቀዷ እያለበት የዐረፋን ቀን ወይም የዐሹራእን (የሙሐረምን 10ኛ ቀን) የፆመ ሰው ፆሙ ትክክል ነው፡፡ ደግሞም እነዚህን ቀናት የረመዷንን ቀዷእ በመክፈል ኒያ በአንድ ላይ ቢፆማቸው ሁለት አጅርን ያገኛል፡፡ የዐረፋ ቀን ፆምና የዐሹራእ ፆምን አጅር ከረመዷን ቀዷእ አጅር ጋር ማለት ነው፡፡ እሱም እነዚህ የሱና ፆሞች ቀጥታ ከረመዷን ጋር ቀጥታ ግንኙነት የሌላቸው በመሆናቸው ነው፡፡ የሸዋል ወር ስድስት ቀናት ፆም ግን ከረመዷኑ ጋር የሚያያዝ በመሆኑ ምክንያት በአንድ ኒያ ሰብስቦ መፆሙ አይሆንም፡፡ ቅድሚያ ቀዷውን ከፍሎ ከዛም የሸዋልን ስድስት ቀናት ፆም ያስከትል›› (ፈታዋ-ሲያም 438)፡፡
ወላሁ አዕለም

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
#የሸዋል ፆም ፍች (ትንሹ ዒድ)
በአቡ ሀይደር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ምስጋና የዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ የተገባ ነው፡፡ የአላህ ውዳሴና ሰላም፡ የሰላም አለቃና መምህር ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ ይሁን፡፡ ድልና የበላይነት ሐቅን ለማንገስና ሀሰትን ለማርከስ፡ በደልን አጥፎቶ ፍትህን ለማስፈን ዕውቀታቸውን፣ ንብረታቸውን፣ ጉልበታቸውን፣ ጊዜያቸውንና ህይወታቸውን መስዋእት በማድረግ ለሚታገሉት የአላህ ባሮች ይሁን፡፡
በተወሰኑ (ሁለት ወይም ሶስት) ብሔሮች ዘንድ ከረመዷን ዒድ (ዒዱል-ፊጥር) ማግስት ጀምሮ ለተከታታይ ስድስት ቀናት የሸዋልን ጾም ይጾሙና ሰባተኛውን ቀን እንደ ዒድ ያከብሩታል፡፡ ምክንያቱን ጠይቄ ለማወቅ እንደሞከርኩት ይህን ይመስላል፡-
የዒዱል-ፊጥር ቀን ደብዘዝ ብሎ በደንብ ሳይሞቅ የምናሳልፈው ቀኑ አንድ ቀን ስለሆነና በነጋታው ተመልሰን ወደ ሸዋል ጾም ስለምንገባ ነው፡፡ ስለዚህ ባሉት ተከታታይ ስድስት ቀናት የሸዋልን ጾም በመጾም ሁለቱንም (ረመዷንንም ሸዋልንም) እንጨርስና ከሰባተኛው ቀን ጀምሮ በደንብ ዒዱን እናከብራለን፡፡ እንበላለን እንጠጣለን፡፡ ጎረቤት፣ ጓደኛ፣ ዘመድ እንጠይቃለን፡፡ ብዙ ቀናቶች አሉንና፡፡
ከዚህ ምክንያት መረዳት እንደሚቻለው ሰዎቹ የዒዱል-ፊጥር ቀን አንድ ቀን ብቻ በመሆኑ በሰፊው ለመብላትና ለመጠጣት፣ ከዘመድ አዝማድ ጋር ለመዘያየር የማይበቃ መሆኑ ነው እንጂ የሸዋል ዒድ አለ ብለን አይደለም የሚል ነው፡፡
ማስተካከያ፡-
1ኛ/ የኢስላም ሃይማኖት እንዳስተማረን ከሁለቱ ዒዶች (ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓ) ውጪ፡ ሙስሊሞች ሌላ ዒድ የላቸውም፡፡ የአላህ መልክተኛ ከደነገጉት ውጪ አዲስ ስርአትን መደንገግ በሃይማኖቱ ላይ መጨመር ነው፡፡ ይህ ደግሞ ቢድዐ ይባላል፡፡ የሸዋል ወር 8ኛው ቀን የሸዋል ፆም መፍቻ ዒድ ቢሆን ኖሮ፡ በዒድ ቀን መፆም ሐራም ነውና በዚህ ቀን አትፁሙ የሚል ትእዛዝ በሐዲሥ በሰፈረ ነበር፡፡ ግን የለም፡፡
2ኛ/ የሸዋል መጀመሪያ ቀን ዒዱል ፊጥር መሆኑ የታወቀ ነው፡፡ ዒድ ደግሞ የመደሰቻ፣ የመብያና የማብያ፣ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት መለዋወጫ ቀን ነው፡፡ ግን በመጀመሪያው ቀን ብቻ ነው መብላትና ማብላት፣ መዘየርና መደሰት የሚቻለው ያለው ማነው? የሸዋልን ሁለተኛና ሶስተኛ ቀናትስ መብላትና ማብላት፣ መዘያየር አይቻልም? ይቻላል፡፡ ስለዚህ ከላይ የቀረበው ምክንያት አጥጋቢ አይደለም፡፡
3ኛ/ የሸዋል ስድስት ቀናት ጾም በመጀመሪያዎቹ የሸዋል ቀናቶች ላይ ብቻ የተገደበ አይደለም፡፡ ሸዋል ሙሉ አንድ ወር 29/30 ነው፡፡ ስለዚህ ከወሩ ውስጥ የሚመቸውን ቀን መርጦ በማከታተልም ሆነ በማፈራረቅ ሸዋልን መጾም ይቻላል፡፡ እናም የደስታውን ቀን ማርዘም የሚፈልግ ከዒዱል-ፊጥር በኋላ ያለውንም ቀን መጠቀም ይቻላል፡፡ በቀሩት ቀናት ደግሞ ሸዋልን መጀመር ይቻላል፡፡
4ኛ/ ከዒዱል-ፊጥር ማግስት ጀምሮ ያሉትን ተከታታይ ስድስት ቀናት የጾመ ቤተሰብ በቀጣዩ ቀን በመብላትና ቀኑን እንደ ዒድ ቆጥሮ ሲያሳልፈው፡ ከመሐከላቸው አንድ ሰው ጾሙን ባለመጨረሱ (ቀዷእ ቢኖርበት ወይም ዘግይቶ ቢጀምር) እነሱ የሚበሉበትን ቀን ቢጾመው የቤተሰቡ አካላት ይቃወሙታልን? በዒድ ቀን እንዴት ትበላለህ ይሉታልን? አዎ! ከሆነ ምላሹ፡ ሰዎቹ ቀኑን ዒድ አድርገው ይዘውታል ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ በዲነል-ኢስላም ላይ የተጨመረ ፈጠራ ‹‹ቢድዓህ›› ይባላል፡፡ አላህና መልክተኛው ከዒዱል-ፊጥር እና ከዒዱል አድሓ ውጪ የበዓል ቀን አልደነገጉልንም፡፡ የሸዋል ዒድ የሚባለው መሰረት የለውም እና እንደ-ዒድ አድርገው የሚይዙ ሰዎችን ቢድዓ መሆኑን ማስተማርና ማስገንዘብ ይጠበቅብናል፡፡
4. ሌላው ሊታወቅ የሚገባው ነገር ቢኖር፡- ከዒዱል ፊጥር ማግስት ጀምሮ በተከታታይ የሸዋልን ስድስት ቀናት የጾመ ሰው በቀጣዩ ቀን መብላት መጠጣት አይችልም ማለት አይደለም፡፡ ሰውየው ጾሙን እስካጠናቀቀ ድረስ መብላት መጠጣት ይችላል፡፡ ዋናው ነገር በቀኑ ላይ ሲበላም ሆነ ሲጠጣ ቀኑን ዒድ ነው ብሎ እንዳይመለከተውና እንደ-ዒድ አድርጎ እንዳይዘው ነው፡፡ የዒዱል-ፊጥር ቀንንም በአግባቡ ሊያከብረው ይገባል፡፡ ወላሁ አዕለም፡፡

https://www.tg-me.com/mahircomp123 ወደዚህ ግረፕ ግቡና በኢስላም ላይ የሚነሱ የጠላት ክሶችንና ምላሾቹን በማንበብ: እራሶትን በዕውቀት ያንጹ።
Telegram
Sαlαh ❲Fαith Defender❳ ⚒
ይህ ቻናል ሙስሊም ባልሆኑ አካለት እሥልምና ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች ንፅፅራዊ ምላሾችን የሚሰጥ ነው።