Telegram Web Link
🟢የ "ኪታቡ ተውሒድ" ና የ" ኪታብ አሱሉል ኢማን" የተላለፉት ደርሶች በቴሎግራም ሊንክ ተሰብስቦ በmp3 ያገኙት ዘንድ በሊንክ ተዘጋጅተው እነሆ ጀባ ተብላችኋል
⇊ኪታቡ_ ተውሒድ⇊
Pdf ➭https://www.tg-me.com/abuhyder/1955
P32➭https://www.tg-me.com/abuhyder/2063
P31➭https://www.tg-me.com/abuhyder/2055
P30➭https://www.tg-me.com/abuhyder/2048
P29➭https://www.tg-me.com/abuhyder/2045
P28➭https://www.tg-me.com/abuhyder/2041
P27➭https://www.tg-me.com/abuhyder/2039
P26➭https://www.tg-me.com/abuhyder/2030
P25➭https://www.tg-me.com/abuhyder/2028
P24➭https://www.tg-me.com/abuhyder/2026
P23➭https://www.tg-me.com/abuhyder/2025
P22➭https://www.tg-me.com/abuhyder/2023
P21➭https://www.tg-me.com/abuhyder/2021
P20➭https://www.tg-me.com/abuhyder/2017
P19➭https://www.tg-me.com/abuhyder/2014
P18➭https://www.tg-me.com/abuhyder/2011
P17➭https://www.tg-me.com/abuhyder/2003
P16➭https://www.tg-me.com/abuhyder/2001
P15➭https://www.tg-me.com/abuhyder/1999
P14➭https://www.tg-me.com/abuhyder/1997
P13➭https://www.tg-me.com/abuhyder/1996
P12➭https://www.tg-me.com/abuhyder/1991
P11➭https://www.tg-me.com/abuhyder/1989
P10➭https://www.tg-me.com/abuhyder/1985
P9➭https://www.tg-me.com/abuhyder/1983
P8➭https://www.tg-me.com/abuhyder/1981
P7➭https://www.tg-me.com/abuhyder/1980
P6➭https://www.tg-me.com/abuhyder/1975
P5➭https://www.tg-me.com/abuhyder/1972
P4➭https://www.tg-me.com/abuhyder/1969
P3➭https://www.tg-me.com/abuhyder/1965
P2➭https://www.tg-me.com/abuhyder/1961
P1➭https://www.tg-me.com/abuhyder/1957

⇊ኪታቡ_ኡሱሉል ኢማን ⇊
Pdf➭ https://www.tg-me.com/abuhyder/2034
P25➭https://www.tg-me.com/abuhyder/2106
P24➭https://www.tg-me.com/abuhyder/2105
P23➭https://www.tg-me.com/abuhyder/2104
P21➭https://www.tg-me.com/abuhyder/2102
P20➭ https://www.tg-me.com/abuhyder/2082
P19➭https://www.tg-me.com/abuhyder/2081
P18➭https://www.tg-me.com/abuhyder/2078
P17➭https://www.tg-me.com/abuhyder/2077
P16➭https://www.tg-me.com/abuhyder/2076
P15➭https://www.tg-me.com/abuhyder/2075
P14➭https://www.tg-me.com/abuhyder/2072
P13➭https://www.tg-me.com/abuhyder/2071
P12➭https://www.tg-me.com/abuhyder/2067
P11➭https://www.tg-me.com/abuhyder/2066
P10➭https://www.tg-me.com/abuhyder/2061
P9➭https://www.tg-me.com/abuhyder/2060
P8➭https://www.tg-me.com/abuhyder/2059
P7➭https://www.tg-me.com/abuhyder/2058
P6➭https://www.tg-me.com/abuhyder/2054
P5➭https://www.tg-me.com/abuhyder/2053
P4➭https://www.tg-me.com/abuhyder/2051
P3➭https://www.tg-me.com/abuhyder/2043
P2➭https://www.tg-me.com/abuhyder/2037
P1➭https://www.tg-me.com/abuhyder/2035

ተጨማሪ የኡስታዝ ትምህርቶችን ለማግኘት⇊
Join us ➤➤ http://www.tg-me.com/abuhyder
Like ➤➤https://bit.ly/39TA18B
Subscriber ➤➤https://bit.ly/2MLLQF0
ለወዳጅ ዘመድዎ ሼር በማድረግ የሂዳያ ሰበብ ይሁኑ!
አሰላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ

ውድና የተከበራችሁ ወንድምና እሕቶቼ!

አምላካችን አላህ ፈቃዱ ከሆነ: በረመዷን ወር ተቋርጦ የነበረውን የቀጥታ ስርጭት ፕሮግራም ማታ 3:30 እንቀጥላለን ኢንሻአላህ።
«መጅሊስ ዋጋ የከፈልኩበት ተቋሜ ነው»
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
T.me/ahmedin99

ነገ ጠዋት ከ 3 ሰዓት ጀምሮ «መጅሊስ ዋጋ የከፈልኩበት ተቋሜ ነው» በሚል በርካታ የአዲስ አበባ ሙስሊሞች ከጦርሃይሎች በላይ ሆላንድ ኢንባሲ ጋር በሚገኘው የፌደራል መጅሊስ ቅጥር ጊቢ በመገኘት የመጅሊስ አመራሮች የተሰጣቸውን ህዝባዊ አማና በተመለከተ ጥያቄ ለማቅረብ መዘጋጀታቸው ታውቋል። ከሚያነሷቸው ጥያቄዎችና ሀሳቦች መካከል:

1) «አማናችሁን በ6 ወራት እንድትወጡ ተሰጥቷችሁ ከ 2 ዓመታት በላይ ባለመወጣት ህዝበ ሙስሊሙን የበደላችሁበት ምክንያት በግልጽ ንገሩን»፣

2) «የመጅሊስ ምርጫ ቁርጥ ቀኑ ይነገረን»፣

3) «መጅሊስ የህዝበ ሙስሊሙ እንጂ የግለሰቦች አይደለም»

4) ፣«ሕዝበ ሙስሊሙን የበደሉት የመጅሊስ አባላት በአስቸኳይ ለፍርድ ይቅረቡ»፣

5) «የጠቅላላ ጉባኤውን ዉሳኔ ያደናቀፉ አካላት በአስቸኳይ ለህግ ይቅረቡልን»

6) ፣«የፌደራል መጅሊስ የክልል መጅሊሶችን ተወካይ ሆኖ ሳላ ስለምን ከነርሱ ፍላጎት በተቃራኒ ቆመ?»

7) በ2004 ህዝበ ሙስሊሙ ለመብቱ ሲታገል የትግሉ መነሻ የሆነውን የአወሊያ ተቋምን መጅሊስ በማዳከም ለማፈራረስ የጀመረው ተግባር በአስቸኳይ ይቁም»

8) ፣ «እኛ ሙስሊሞች ነን።ሱፊ-ሰለፊ ጫወታ አይመለከተንም። መጫወት የፈለገም አካል ዋጋ በከፈልንበት ተቋማችን ሳይሆን በቤቱ ሄዶ ይጫወት»፣

9)«ህዝበ ሙስሊሙ ላይ እየደረሰ ላለው ትንኮሳ የፌደራል መጅሊስ ሚናውን ካለመወጣት አልፎ ተባባሪ ነው እስክንል ድረስ እየበደለን በመሆኑ ከተጠያቂነት አያመልጥም»፣

10) «በሀጅና በፋይናንስ ክፍል ሆነው ህዝበ ሙስሊሙን ለዓመታት የዘረፉ የቀድሞ የመጅሊስ አባላትን በህግ ተጠያቂ ማድረግ ሲገባችሁ ከተባረሩበት መልሳችሁ እንዴት ሾማችሁ?»፣

11) «ከህወሃት መራሹ መንግስት ጋር ዉድ ዋጋ ከፍለን የታገልነው መጅሊስ የናንተ መጫወቻ እንዲሆን አይደለም»፣

12) «ዑለማ ሆናችሁ በቃል በመገኘትና አማናን በመጠበቅ ለህዝቡ ምሳሌ መሆን ሲገባችሁ እንዴት የዑለማን ስም የሚያሰድብ ተግባር ትፈጽማላችሁ? »፣

13) አህለል ከይሮች እንስራ በማለት እየለመኑ ጭምር ሲጠይቁ መስጊዱ እንዲሰራ ፈቃደኛ ባለመሆን የነጃሺ ኢስላማዊ ማዕከልን መሬት ለማስነጠቅ የጀመራችሁት አካሄድን በአስቸኳይ በማቆም እንዲገነባ ይደረግ።

14) የተሰጣችሁን አማናንን ቶሎ እንወጣ በማለታቸው በሌላችሁ ስልጣን ቦርዱን በማገዳችሁ በይፋ ይቅርታ ጠይቁ። ወደ መጅሊስ እንዳይገቡ ያዘዘው አካል ላይ በአስቸኳይ እርምጃ ይወሰድበት።

15) «መጅሊስ በአስቸኳይ ህወሃት ካሰማራቸው ካድሬዎችና ተላላኪዎች ነፃ የሆነ ህዝባዊ ተቋም እንዲሆን እንጠይቃለን»፣«የሚሉ ይገኙበታል።

የዑለማ ምክር ቤት አባላት ነገ ወደ ቢሮ እንደሚገቡ የታወቀ ሲሆን በቢሮዋቸው ሳይገኙ የሚቀሩ ከሆነ ሰኞ እለት ጀምሮ በመጅሊስና በመኖሪያ ቤቶቻቸው በመመላለስ ጥያቄ ለማቅረብ መታሰቡ ታውቋል። የመጅሊስ ጉዳይ ይመለከተኛል፣ «ተቋሜን አሳልፌ አልሰጥም» የሚል የአዲስ አበባ ሙስሊም በስፍራው ሲገኝ ጥያቄዎቹን በኢስላማዊ አደብ በሰላማዊ መንገድ ብቻ ማቅረብ እንደሚገባው አሳስበዋል።
ሱብሐነላህ ሲገርም!!

ቢስሚላህ ወሶላቱ ወሰላሙ ዐላ ረሱሊላህ

عندما نخاف من شخص نهرب منه. و عندما نخاف الله نقترب منه

عندما نطلب حاجة من شحص ننزل رؤوسنا. عندما نطلب من الله نرفع رؤوسنا للسماء سبحانه الله ما اكرمه.

አንድን ሰው ስንፈራው ከሱ እንሸሻለን። አላህን ስንፈራው ግን ወደሱ እንቀርባለን።

ከሆነ ሰው ጉዳያችንን ይፈፅምልን ዘንድ እርዳታን ስንጠይቅ እራሳችንን ዝቅ እናደርጋለን። ከአላህ የምንፈልገውን ነገር ለማግኘት ሲሆን ግን እጃችንን ራሳችንንም ወደ ሰማይ ቀና እናደርጋለን።

ጌታችን ምንኛ ቸር ነው!! ሱብሐነከ ያ ከሪም!

Join ➤➤ www.tg-me.com/abuhyder
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
እውርን እውር ቢመራው….
በአቡ ሀይደር
በአላህ ሥም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን (አል-ፋቲሓ 2)፡፡ የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡
ከላይ ስክሪን ሹት የተደረገውን ጽሑፍ ካነበባችሁት፡ አንዷ ክርስቲያን (ስሟን የሙስሊም አካውንት ያደረገች) የለጠፈችው ነው፡፡ እኔም ዋና ትኩረት ያደረግሁት እሳ ለለጠፈችው መልስ መስጠቱ ላይ ሳይሆን፡ ምን እየተደረገ እንዳለ ልጠቁማችሁ ነው፡፡ ወደ ገደለው…..
1ኛ/ ከላይ ሐዲሥ ተብሎ የቀረበው ተረት-ተረት ፈጽሞውኑ የሐዲሥ መጻሕፍት ላይ የለም፡ አይገኝምም፡፡ ይህ የኢስላም ጠላቶች ያቀነባበሩት ዐረብኛ ነው፡፡ ከሐዲሥ ላይ የሶሓቢዩን ሥም፣ የመልክተኛውን ሥም ይወስዱና፡ ከዚያም ከመጽሐፍ ቅዱስ አንድን ቃል በመውሰድ፡ ቀሪውን ከዐረብኛ ቋንቋ ዘርፈው በማዳቀል የደረሱበት ከንቱ ልፋት ነው፡፡ እንዴት እንደሆነም በቁጥር ሶስት ላይ አብራራዋለሁ፡፡
2ኛ/ ለሐዲሡ ምንጭ የጠቀሱ ለመምሰል፡ ዑምደቱል-አሕካም የሚል ሥም ሰጥተውታል፡፡ ጥራዝና ገጹም ተጠቅሷል፡፡ የሐዲሱ ቁጥር ግን ተዘልሏል፡፡ ምክንያቱም ቁጥር ከተጠቀሰ በቀላሉ ቅጥፈታቸው ስለሚጋለጥ፡ እሱን ባላየ አልፈውታል፡፡
3ኛ/ ይህ ሐዲሥ ተብዬ ፈጽሞ ምንም መሠረት የሌለው፡ እንኳን ሶሒሕ ሐዲሥ ሊሆን ይቅርና ዶዒፍ ሊሆን እንኳ መስፈርቱ ያልተሟላለት፡ ከላይ በተጠቀሰው መጽሐፍ ላይም ሆነ በሌሎች የሐዲሥ መጻሕፍት ውስጥ ፈጽሞ የማይገኝ፡ ነገር ግን
http://kontra-balik-islam.blogspot.ae/
2017/06/si-satanas.html እዚህ ሊንክ ውስጥ ባለው መሠረት እዚሁ የተፈበረከ ቅጥፈት መሆኑን ቀጥሎ ባሉት መረጃዎች ማወቅ ይቻላል፡-
ሀ/ ሐዲሡ ሲጀምር ‹‹ረዋሁ አነስ ኢብኑ ማሊክ›› ይላል፡፡ እኔ የምለው፡- ከመቼ ጀምሮ ነው የሐዲሥ ጅማሬ ላይ ረዋሁ ፉላን መባል የተጀመረው? የሐዲሥ መጻሕፍትን ካያችሁ ይህ ‹ረዋሁ› የሚለው ቃል የሚጠቀሰው በሐዲሡ መጨረሻ ላይ እንጂ፡ ጅማሬው ላይ አይደለም፡፡ እነዚህ ለፊዎች ግን ከየት ያመጡት ሐዲሥ ቢሆን ነው ሲጀምር ‹ረዋሁ› ብሎ የጀመረው?
ለ/ ‹‹ሰሚዕቱ ሚን ረሱል ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አነሁ ይልና ካነላሁ›› ብሎ ይቀጥላል፡፡ የእንግሊዘኛውን ትርጉም ብትመለከቱት ‹‹"I heard from the Apostle of Allah (Peace and blessing be upon him) that he said "Allah was ›› ይላል፡፡ that he said የሚለው የእንግሊዘኛው ትርጉም ከየት የተወሰደ ነው? ከዐረብኛው ከሆነ ዐረብኛው ላይ እንደዛ የሚል ቃል የለም፡፡ ወይስ አላህ ሊያጋልጣቸው ሲፈልግ፡ እነሱ ሲያቀናብሯት የዘለሏት ነች?
ሐ/ በጣም የሚደንቀው ደግሞ ‹‹ሚላክ›› የሚለው ቃል መጠቀሱ ነው፡፡ በቁርኣንም ሆነ በሐዲስ የአላህ መልአክ በዐረብኛው ‹መለክ› ለብዙ ከሆነ ደግሞ ‹መላኢከህ› ተብሎ እንጂ፡ ሚላክ ተብሎ ተጠቅሶ አያውቅም፡፡ አልለ የሚል ሰው ማስረጃ ይዞ መቅረብ ይችላል፡፡ እንደውም ‹ሚላክ› የሚለው ቃል የሚመጣው፡ የነገሮች ሁሉ ዋና፡ ሁሉንም የሚቆጠጠር በሚለው ትርጉም ነው፡፡ እዚህ ሐዲሥ ተብዬው ላይ ግን angel ለሚለው የእንግሊዘኛ ትርጉም ዐረብኛው ላይ ሚላክ ብሎት እርፍ፡፡ ደስ የሚለው ግን ‹ሚላክ› የሚለውን ቃል ለመልአክ የሚጠቀመው መጽሐፍ ቅዱስ ሆኖ መገኘቱ ነው፡
ﻭَﻓِﻲ ﺍﻟﺸَّﻬْﺮِ ﺍﻟﺴَّﺎﺩِﺱِ ﺃُﺭْﺳِﻞَ ﺟِﺒْﺮَﺍﺋِﻴﻞُ ﺍﻟْﻤَﻼَﻙُ ﻣِﻦَ ﺍﻟﻠﻪِ ﺇِﻟَﻰ ﻣَﺪِﻳﻨَﺔٍ ﻣِﻦَ ﺍﻟْﺠَﻠِﻴﻞِ ﺍﺳْﻤُﻬَﺎ ﻧَﺎﺻِﺮَﺓُ
In the sixth month the angel Gabriel was sent from God to a city of Galilee named Nazareth, luke 1:26
ﻭَﺍﻛْﺘُﺐْ ﺇِﻟَﻰ ﻣَﻼَﻙِ ﺍﻟْﻜَﻨِﻴﺴَﺔِ ﺍﻟَّﺘِﻲ ﻓِﻲ ﺳَﺎﺭْﺩِﺱَ : ‏« ﻫَﺬَﺍ ﻳَﻘُﻮﻟُﻪُ ﺍﻟَّﺬِﻱ ﻟَﻪُ ﺳَﺒْﻌَﺔُ ﺃَﺭْﻭَﺍﺡِ ﺍﻟﻠﻪِ ﻭَﺍﻟﺴَّﺒْﻌَﺔُ ﺍﻟْﻜَﻮَﺍﻛِﺐُ . ﺃَﻧَﺎ ﻋَﺎﺭِﻑٌ ﺃَﻋْﻤَﺎﻟَﻚَ، ﺃَﻥَّ ﻟَﻚَ ﺍﺳْﻤﺎً ﺃَﻧَّﻚَ ﺣَﻲٌّ ﻭَﺃَﻧْﺖَ ﻣَﻴِّﺖٌ .
"And to the angel of the church in Sardis write: 'The words of him who has the seven spirits of God and the seven stars. "'I know your works. You have the reputation of being alive, but you are dead. Revelation 3፡1
ታዲያ የሐዲሡ ቅንብር ከነዚሁ ሰፈር አይመስላችሁምን?
መ/ የሐዲሥ ተብዬው መጨረሻ ላይ ‹‹ወአና-ነቢይ›› ይላል፡፡ እንግሊዘኛው ላይ ደግሞ፡- ‹‹I' am his prophet›› ተብሏል፡፡ የዐረብኛው ትርጉም ግን እኔ ነብይ ነኝ ነበር፡፡ እንግሊዘኛው ግን እኔ የሱ ነቢይ ነኝ ይላል፡፡ የሱ የሚለውን ተወላጠስም የሚያመለከት ነገር ዐረብኛው ላይ የለም፡፡ ይህ በቅንብር ወቅት ያመለጣቸው ስህተት ነው፡፡
ድብቁ ዓላማ፡-
እነዚህ የኢስላም ጠላቶች በሐዲሥ ላይም ሆነ በቁርኣን አንድን ጥያቄ ሲያነሱ፡ ዓላማቸው ያልገባቸው ነገር ኖሮ፡ ለማወቅና ለመረዳት ሳይኾን፡ ዕውቀቱ በሌለውና ኢማኑ ደካማ በኾነው ሰው ላይ ጥርጣሬን ለመፍጠር ነው፡፡ በዚህ መሐል እውነቱን ማወቅ የሚሹ ወገኖች ግን በሚሰጠው መልስ የመምህራኖቻቸውን ቅጥፈትና የኢስላምን እውነት ይረዱበታል፡፡ አማኞችም በእምነታቸው ይጠነክሩበታል፡፡ አዲስ ዕውቀትንም ይገበዩበታል፡፡ እኛም አቅማችን በቻለ መጠን ለምላሹ የምንለፋው ይህን ታሳቢ በማድረግ እንጂ፡ ለሁሉም ግለሰብ መልስ መስጠቱ ተገቢ ነው ብለን አምነንበት አይደለም፡፡
ወገኖቻችን ሆይ!፡-
ፈጣሪ አምላካችሁ አላህ፡ በመልአክ ቅርጽ ያለ ሰይጣን ሳይኾን፡ የመላእክትና የሰይጣናት ፈጣሪና አምላካቸው ነው፡፡ አላህ መላእክትን፣ ጂንኒዎችን፣ ሰዎችን፣ እንሰሳትን፣ ነፍሳትን፣ በራሪዎችን፣ እጽዋትንና ግኡዛን ፍጥረታትን በጠቅላላ ብቻውን ያለ-ረዳት እና ያለ አማካሪ የፈጠረ አምላክ ነው፡፡ ሰይጣናትም ሆኑ መላእክት ፍጥረትና ግኝት በመሆናቸው ከአምልኮ ምንም ድርሻ የላቸውም፡፡ ዛሬ በፍጹም ጥላቻ የተሞላ ልብ ይዛችሁ፡ በጥፋት መምህራኖቻችሁ እየተመራችሁ፡ አምላካችሁን ብትክዱና ብትሳደቡም፡ በፍርዱ ቀን ግን ማንም ነቢይ ሆነ መልአክ ከአላህ ቁጣ አያድናችሁም፡፡ ጊዜው ሳያልፍባችሁ ቶሎ ብላችሁ ወደ አምላካችሁ አላህ መንገድ ተመለሱ፡፡ ይህ አምላክ፡- በፍጹማዊ አንድነቱ ልዩ ሶስትነት የሌለበት፣ በፍጹም መለኮታዊ ባሕሪው፡ ሰዋዊነት ያልታየበት፣ በዘላለማዊ ሕያውነቱ ለቀናት እንኳ ያልሞተና ያላንገላጀ፣ በአንተነቱ ብቻ የሚለመንና የሚጥጠራ፣ በእሱነቱ እንጂ በእነሱነቱ ለሰው የማይሰበክ፣ በእኔነቱና በእኛነቱ እራሱን የሚገልጥና የሚናገርቨ ስእልና ምስል ተበጅቶለት በሽማግሌ ቅርጽ በመጽሐፍ ጀርባ ላይ የማይለበድ የኾነ አንድ አምላክ ነው፡፡
"የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በእኛና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ኾነች ቃል ኑ፡፡ (እርሷም) አላህን እንጅ ሌላን ላንገዛ፣ በርሱም ምንንም ላናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርጎ ላይይዝ ነው፤ በላቸው፡፡ እምቢ ቢሉም፡- እኛ ሙስሊሞች መኾናችንን መስክሩ በሏቸው፡፡" (ሱረቱ አሊ-ዒምራን 3፡64)፡፡
ወሰላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱላህ
Click and Like ➤➤ https://
www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
Join ➤➤
www.tg-me.com/abuhyder
የዱዓእ አዳቦች (ስነ-ስርአት)
በ አቡ ሀይደር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ምስጋና የዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ የተገባ ነው፡፡ የአላህ ውዳሴና ሰላም፡ የሰላም አለቃና መምህር ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ ይሁን፡፡ ድልና የበላይነት ሐቅን ለማንገስና ሀሰትን ለማርከስ፡ በደልን አጥፎቶ ፍትህን ለማስፈን ዕውቀታቸውን፣ ንብረታቸውን፣ ጉልበታቸውን፣ ጊዜያቸውንና ህይወታቸውን መስዋእት በማድረግ ለሚታገሉት ይሁን፡፡
"አድ-ዱዓእ" (ተማጽኖ):- ልብ ከመላስ ጋር በመጣመር ከሚፈጸሙ የዒባዳ ዘርፎች ውስጥ የሚመደብና ተቀዳሚ ተግባርም ነው፡፡ ዱዓእ በዱዓነቱ ብቻ ለባለቤቱ አጅር ያስገኛል፡፡ ሶላት የሰገደ በሶላቱ፣ ዘካት ያወጣ በዘካው፣ ሶደቃህ የሰጠ በሶደቃው አጅር እንደሚያገኘው እጁን ወደላይ አንስቶ ያ አላህ! ያ ረቢ! የሚል፡ ጌታውን የሚማጸን ባርያም የዱዓውን ምላሽ ወዲያው ቢያገኝ፡ ወይም ምላሹ ቢዘገይ እንኳ በዱዓው ብቻ አጅርን ያገኛል፡፡ ምክንያቱም ዱዓእ ዒባዳ (አምልኮ) ነውና! ዱዓእ ከዒባዳ ዘርፎች ውስጥ እንደሚካተት የሚያመላክቱ ቅዱስ ቁርኣናዊና ነቢያዊ ሐዲሦች አሉ፡፡ ከነዚህም መካከል፡-
" وَقَالَ رَبُّكُمُ ادْعُونِي أَسْتَجِبْ لَكُمْ إِنَّ الَّذِينَ يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِي سَيَدْخُلُونَ جَهَنَّمَ دَاخِرِينَ " سورة غافر 60
"ጌታችሁም አለ፦ ለምኑኝ እቀበላችኋለሁና፤ እነዚያም እኔን ከመገዛት የሚኮሩት ተዋራጆች ሆነው ገሀነምን በእርግጥ ይገባሉ።" (ሱረቱ ጋፊር 60)፡፡
በዚህ አንቀጽ ላይ ጌታችን ይቀበለን ዘንድ እንድለምነው ካዘዘን በኋላ፡ ጀሀነምን ግን እኔን ከመገዛት ለኮሩት ነች አለ እንጂ፡ እኔን ከመለመን ለኮሩት አላለም፡፡ ይህም አላህን መለመን እርሱን መገዛት፤ አላህን ከመለመን መሸሽ እሱን ከመገዛት መኩራት መሆኑን ፍንትው አድርጎ ያስረዳናል፡፡ ስለሆነም ዱዓእ የአምልኮ አካል ነው፡፡ በተለይ ጉዳዩን ይበልጥ ግልጽ የሚያደርገው ተከታዩ የነቢያችን (ዐለይሂ ሶላቱ ወስ-ሰላም) ሐዲሥ ነው፡-
ኑዕማን ኢብኑ በሺር(ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዳስተላለፈልን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "ዱዓእ እራሱ ዒባዳህ ነው፡፡" ከዛም ይህን አንቀጽ አነበቡ፡ ‹‹"ጌታችሁም አለ፦ ለምኑኝ እቀበላችኋለሁና፤ እነዚያም እኔን ከመገዛት የሚኮሩት ተዋራጆች ሆነው ገሀነምን በእርግጥ ይገባሉ››" (አሕመድ 18933፣ቲርሚዚይ 3247፣ አቡ ዳዉድ 1479፣ኢብኑ ማጀህ 3828፣ሐኪም አል-ሙስተድረክ 1802)፡፡
ዱዓእ፡- አላህ ዘንድ እጅግ የተከበረ ነው፡- አቢ ሁረይራህ(ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዳስተላለፈው የአላህ መልክተኛ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "ከዱዓእ የበለጠ ሁኖ አላህ ዘንድ የተከበረ ምንም ነገር የለም" (አሕመድ 8733፣ቡኻሪይ፡ አደቡል ሙፍረድ 712፣ኢብኑ ማጀህ 3829፣ቲርሚዚይ 3370)፡፡
- ዱዓእ፡- አላህ የሚወደው ተግባር ነው፡- ዐብዱላህ ኢብኑ-መስዑድ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ከአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሰምተው እንደነገሩን፡- "አላህን ከችሮታው (ከጸጋዎቹ) ለምኑት፤ አላህ መልለመንን ይወዳልና" (ቲርሚዚይ 3571፣አሕመድ 8050)፡፡
- ዱዓእ፡- የአላህን ቁጣ ይከላከላል፡- አቢ ሁረይራህ(ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዳስተላለፈው የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "አላህን የማይለምን ሰው አላህ ይቆጣበታል" (ቡኻሪይ፡ አደቡል ሙፍረድ 658፣ ቲርሚዚይ 3373)፡፡ ከቁጣው መትረፍ የፈለገ ሰው በዱዓእ ይበርታ፡፡
- ዱዓእ፡- የተወኩል መገለጫ ነው፡፡ አላህን ሁሌም የሚማጸን ሙስሊም በአላህ ላይ ያለው ተወኩል ጠንካራ መሆኑን ያሳያል፡፡ ምክንያቱም ማንም ሰው አንድን ነገር የሚጠጋው በዛ ነገር ላይ እምነት ሲኖረው ነው፡፡ የተጠራጠረውን ነገር ግን ይሸሸዋል እንጂ አይቀርበውም፡፡ አንድ ሙስሊም አላህ ለሱ የተሻለውን እንደሚመርጥለትና እንደሚያግዘውም ስለሚያውቅ ወደ አላህ ከመጠጋትና አላህን ከመማጸን አይቦዝንም ማለት ነው፡፡
- ዱዓእ፡- የድክመት ማጥፊያ መሳሪያ ነው፡- ከሰዎች መሐል ሰነፍ መባልን የማይፈልግ በዱዓእ ላይ ይበርታ፡፡ ዱዓእ ጉልበትን፣ ገንዘብን፣ የተራዘመ ወቅትን፣ ወይም የተወሰነ ቦታና ሰዓትን ወጪ ማድረግ አይጠይቅም፡፡ በማንኛውም ሰዓትም ሆነ በየትኛውም ቦታ ላይ ብንሆን ከልብ የወሰነና ከአላህ ተስፋ ያደረገ ኒያን ብቻ ነው የሚፈልገው፡፡
አቢ ሁረይራህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዳስተላለፈው የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "ከሰዎች ሁሉ ደካማ ማለት በዱዓእ ላይ የሰነፈ ሰው ነው" (ኢብኑ ሒባን፡ አልባኒይ ሶሒሕ ብለውታል አስ-ሶሒሐህ 601)፡፡
- ዱዓእ፡- የማይሻር ዋስትና አለው፡፡ ማንኛውም ሙስሊም ሁለት እጁን አንስቶ ወደ አላህ ያ ረብ! ብሎ ከተጣራ፣ በወንጀልና ዝምድና መቁረጥ ላይ እስካልለመነ ድረስ ዱዓው በፍጹም ተመላሽ አይሆንም፡፡
አቢ ሁረይራህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዳስተላለፈው የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ሲሉ ሰማሁ አለ፡- "ማንም ሰው ከወንጀልና ዝምድና መቁረጥ ውጪ ባለ ነገር አላህን አይማጸንም፡ አላህ የጠየቀውን ነገር የሰጠው፡ ወይንም በምትኩ እንደ ዱዓው መጠን ክፉ ነገርን የሚከላከልለት ቢሆን እንጂ" (ቲርሚዚይ 3381)፡፡
- ዱዓእ፡- ቀደርን ይመልሳል፡፡ አላህ እንዲሆን የወሰነው ነገር ተፈጻሚ ከመሆን የሚያግደው ምንም ነገር የለም ከዱዓእ በስተቀር፡፡ ይህም የዱዓእን ተጽእኖ ፈጣሪነት አጉልቶ ያሳያል፡፡
ሠውባን (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዳስተላለፈው የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "ቀደርን ዱዓእ እንጂ ሌላው አይመልሰውም" (አሕመድ 22386፣ኢብኑ ማጀህ 90፣ቲርሚዚይ 2139)፡፡
የምእመናን እናት አዒሻ (ረዲየላሁ ዐንሃ) እንደነገረችን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "ጥንቃቄ ከቀደር አያስጥልም፡፡ ዱዓእ ግን ለወረደም ላልወረደም (በላእ) ይጠቅማል፡፡ ከላይ በላእ ይወርዳል፤ ዱዓእ ደግሞ ይወጣል፤ ይገናኙና እስከ-ቂያም ቀን ድረስ ይታገላሉ" (ሐኪም አል-ሙስተድረክ 1813)፡፡
የሐዲሡ መልእክት፡- በሰዎች አመጽ ምክንያት ሊመጣባቸው የነበረው በላእ፡ እንዲሁ በዱዓእ አማካኝነት ደግሞ መሬት ሳይደርስ መከላከል እንደሚቻል ለመግለጽ ነው፡፡
ስለ ዱዓእ በተወሰነ መልኩ ከተመለከትን፡ እንዲሁም የዒባዳ አንድ አካል መሆኑን ካወቅን፡ ሌላው ልንረዳ የሚገባው ነገር "ዱዓእ" በምናደርግበት ጊዜ መላበስ የሚገባንን ስነ-ምግባራት ነው፡፡ የተወሰኑትን ከዚህ በታች አቀርባቸዋለሁ፡-
1. የቂን (እርግጠኝነት)፡-
የመጀመሪያውና ዋናው መስፈርት ነው፡፡ የምንማጸነው አላህ፡ ዱዓችንን ሰሚና ተቀባይ ጌታ መሆኑን እርግጠኛ መሆን አለብን፡፡ አላህ ለኛ ማድረግ የፈለገውን ነገር እንዳያደርግ ሊከለክለው የሚችል ኃይል የለምና፡፡ ስለዚህም በዱዓችን ላይ እርግጠኞች መሆን ይጠበቅብናል፡፡ እስኪ ዱዓዬን ከሰማኝ! ምን-አልባት ከተቀበለኝ! እና በመሳሰሉት ጥርጣሬን በተሞሉ ልቦች አላህን መለመን የዱዓእን ተቀባይነት ከሚያሳጡት ነገራት አንዱ ነው፡፡
عن أبي هريرة رضي الله عنه عن النبي صلى الله عليه وسلم قال : " ادعو الله وأنتم موقنون بالإجابة... " صحيح الجامع 245.
አቢ ሁረይራህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዳስተላለፈው የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "አላህን ስትማጸኑት እንደሚቀበላችሁ እርግጠኛ ሆናችሁ (ለምኑት)…" (ሶሒሑል ጃሚዕ 245)፡፡
2. ንቃት (ተንቢህ)፡-
ሌላው ሁለተኛው መስፈርት ነው፡፡ አላህን በምንማጸን ጊዜ በዘነጋ ልብ (ቀልቡን-ጋፊል) መሆን የለበትም፡፡ ልብ የተመኘውንና መጠየቅ የምንፈልገውን ነገር በአንደበታችን ስንገልጸው እያስተዋልን መሆን አለበት፡፡ አንዳንድ ጊዜ (ወይንም ብዙ ጊዜ) ዱዓእ ስናደርግ፡- ‹ረበና አቲና ፊ-ዱንያ ሐሰናህ፣ ወፊል-አኺረቲ ሐሰናህ፣ ወቂና አዛበ-ናር› እንላለን፡፡ ግን ሁለት ጥያቄዎችን መመለስ አለብን፡-
ሀ. አሁን ያልከውን ዱዓእ ትርጉሙን ታውቀዋለህ? አንተስ ይህን ዱዓእ ስታደርግ በዛን ወቅት እነዚህን ሶስት ነገሮች ከልብህ ፈልገሀቸው ነው? ወይንስ የመስጂዱ ኢማም ብዙ ጊዜ በተደጋጋሚ ስለሚያደርገው አንተም በቃልህ ሐፍዘኸው ነው?
ያንተ ምላሽ፡- ትርጉሙን አላውቅም ከሆነ፡ ወንድሜ ሆይ! ታዲያ በምታውቀውና በምትችለው ቋንቋ ጌታህን መለመን ማን ከለከለህ? ቋንቋዎችን ሁሉ የፈጠረው እሱ አይደለምን? ደግሞስ በቁርኣንና በሐዲሥ የመጡ በዐረብኛ የተነገሩ የዱዓእ አይነቶችን ትርጉማቸውን ጠይቀህ ለመማር ማን ከለከለህ? ወደ ምድረ አሜሪካ ለመሄድ ዲቪ ስትሞላ (ይሳካ አይሳካ ገና ላልታወቀ ነገር) እንግሊዘኛውን የሚያውቁ ሰዎች ጋር ጠጋ ብለህ አይደል እንዴ በትህትና እያንዳንዱን ነገር እንዲተረጉሙልህ የምትጠይቀው? ታዲያ ከአላህ ጋር ይበልጥ የሚያቃርብህን ዱዓእ በግል ቋንቋህ ለማድረግ፣ እንዲሁም በቁርኣንና በሐዲሥ የመጡትን ደግሞ ትርጉማቸውን ጠይቀህ ለመማር ማን ከለከለህ?
ለ. ደግሞስ ይህን ዱዓእ ስታደርግ በዘነጋ ልብ ሁነህ ነው ወይስ ዱዓህን እያሰብከው? ብዙ ሰዎች እጃቸው ወደላይ ተነስቷል፡፡ አንደበታቸው ዱዓእ ያደርጋል፡፡ ልባቸው ግን ሌላ ቦታ ነው፡፡ ዱዓውን ከጨረሱ በኋላ እንኳ፡ አሁን ያደረጋችሁት ዱዓእ ስለምን ነበር? ቢባሉ፡ ከፊሉን ይረሱታል፡፡ ስለዚህ በዱዓእ ወቅት ከመዘንጋት ልንቆጠብ ይገባል፡-
عن أبي هريرة رضي الله عنه عن النبي صلى الله عليه وسلم قال : " ادعو الله وأنتم موقنون بالإجابة، و اعلموا أن الله لا يستجيب دعاء من قلب غافل لاه " صحيح الجامع 245.
አቢ ሁረይራህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዳስተላለፈው የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "አላህን ስትማጸኑት እንደሚቀበላችሁ እርግጠኛ ሆናችሁ (ለምኑት፡፡ አላህ ከዘነጋና ከረሳ ልብ ዱዓን እንደማይቀበልም ዕወቁ" (ሶሒሑል ጃሚዕ 245)፡፡
3. በውዳሴ መጀመር (ሠናእ)፡-
ቀጥታ ወደ ሐጃችን ገብተን፡- ያ ረቢ! ይሄን አሳካልኝ፣ ከዚህ ደግሞ ጠብቀኝ ከማለታችን በፊት ጌታችንን በማወደስ፣ በሳቸውም ላይ ሶላዋት በማውረድ እንክፈተው፡፡ ቢስሚላህ፡ አልሐምዱ ሊላህ፣ ወስ-ሶላቱ ወስ-ሰላሙ ዐላ ረሱሊላህ… ይበል፡፡
ወላሁ አዕለም
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
Audio
በዙልሒጃ ወር መደረግ ያለባቸው ኢባዳዎች

🎙 አዘጋጅ⇊
በኡስታዝ አቡ ሀይደር

Join ➤➤ www.tg-me.com/abuhyder
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
በአላህ ፈቃድና እገዛ ከፊታችን ቅዳሜ ጀምሮ ገበያ ላይ ይውላል
አስ-ሓበል የሚን
🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟

🌕 በሀገራችን ኢትዮጵያ በገጠር አካባቢ ኢስላማዊ (መማሪያ ክፍል) መድረሳን በመገንባት ልጆችን እያስተማረ ይገኛል።

🌕 የእስልምና ብርሃን ለሁሉም ይደርስ ዘንድ አሻራውን እያሳረፈ የሚገኘው በአባላቶቹ ጥረት በአላህ እገዛ የኸይር ስራ ጉዞውን ቀጥሏል።

🌕 የቲሞችን በመንከባከብ መሳኪኖችን ሠለምቴዎችን በመርዳት የወገኑ ደጀን ለመሆን ሰበብ እያደረሰ የሚገኘው አስ-ሓበል የሚን የአሏህ ፍቃድ ከሆነ ትልቅ መስጂድ የመገንባት እቅድ ይዘናል ።

🌕 በብዙ መከራና ስቃይ ውስጥ የሚገኙ ሚስኪኖችን እንባ እያበሰ፤ የበርካታ የቲሞችን እንግልት እየቀነሰ፤ የተቸገሩ ወገኖቹን ችግር ለማቃለል ሰበብ እያደረሰ የሁለት ሀገር ደስታን ለማግኘት እየተጋ የሚገኘው አስ-ሓቡል የሚን ጀመዓ እየሰራቸው የሚገኙትን በርካታ የበጎ ስራ ፕሮጀክቶች ሁሉም ይሳተፍበት ዘንድ እነሆ ጥሪውን አቅርቧል።

🌕 በረበና ፍቃድ በአባላቶቹ መልካም ኒያ፤ በኸይር ፈላጊዎች ጥንካሬ፤ ገንዘባቸውን እውቀታቸውን ጊዜአቸውን ሳይሰስቱ በሚደክሙ አባላት እዚህ የደረሰው አስ-ሓቡል የሚን ጀመዓ በርካቶችን በማሳተፍ የኢስላምን ጮራ የዲኑን ብርሃን ለሁሉም ለማዳረስ በርካቶችን አባል ለማድረግ እድሉን አመቻችቷል።

🌕 በመሆኑም ጥሪው የደረሳችሁ የአስ-ሓቡል የሚን አባል በመሆን የመልካም ሥራው ተካፋይ እንዲሆኑ እየጋበዝን ለሌሎችም መልእክቱን በማድረስ የኸይሩ ተካፋይ ይሁኑ።።

የአስ-ሓቡል የሚን ቋሚ ቤተሰብ ሲሆኑ በቋሚነት ወርሃዊ ክፍያ በአቅሞ በመሸፈን የመልካም ተግባራት ተሳታፊ ይሁኑ
💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥

ኢትዮጵያዊ ውስጥ ነዋሪ ለሆነ 50 ብር

ሳዑድ-አረቢያ እና የመሳሰሉ አረብ ሃገራት ለሚኖሩ 30 ሪያል

በአውሮፓ እና መሰል ሃገራት ለሚኖሩ ወንድምና እህቶች ሲመነዘር ከ50 ( ሃምሳ ) ብር በላይ ሊሆን የሚችል ገንዘብ በየወሩ መነየት ይፈቀዳል።


ለበለጠ መረጃ
⚡️
+966554225870
+971544106845
+966503917209
+251926142009

በቴሌግራም ¶
https://www.tg-me.com/joinchat-Th93dNNUa7fV1c79

በዋስት-አፕ ¶
https://chat.whatsapp.com/6O1nFgi4oKHLgB1fdY0Air

አስ-ሓቡል የሚን ከሚሰራቸው የኦላይን ስራም ለምሳሌ ያህል

የሰለምቴዎችን ማራኪ ታሪክ በእንዴት ሰለምኩኝ በተሰኘው ፕሮግራም ያቀርባል ።
ሰለምቴዎችን ከአንደበታቸው ታሪካቸውን ለማድመጥ
https://youtube.com/channel/UCGL4i2pl7eV7sWA3yvsno_Q

በጹሑፍ ይቀርባል ¶
https://www.tg-me.com/AshaBuleyamine/5125

አስተያየት ለመስጠት ¶
http://www.tg-me.com//Ashabulyeminbot

አስ-ሓቡል የሚን የዑማው ብርሃን 💡
በቀዷ ወል-ቀደር ማመን ማለት፡- በዚህ ዓለም ላይ የሚከሰት ማንኛውም ክስተት ጥሩም ሆነ መጥፎ፡ ከሰውም ይገኝ ከእንሰሳት፣ ከመላእክትም ይገኝ ከጂንኒዎች (አጋንንት)፣ ከበራሪዎችም ይሁን ከነፍሳት፣ በፈቃድና በምርጫም የተገኘ ይሁን በግዳጅ፡ አጠቃላይ ጉዳዩ አስቀድሞ አላህ ዘንድ የታወቀ፡ መጀመሪያውኑም በለውሐል መሕፉዝ (ጥብቅ ሰሌዳ) ላይ ተወስኖ የተጻፈ፡ የተጻፈለት ጊዜ በደረሰ ሰአት በአላህ ፈቃድና ይሁንታ የሚከናወን ነው ብሎ ማመን ማለት ነው፡፡

ከመፅሀፉ የተወሰደ

ከነገ ጀምሮ መፅሀፉ ገበያ ላይ ይውላል።
ዐረፋ ደረሰ

በአቡ ሀይደር

በአላህ ሥም እጅግ በጣም ሩህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን (አል-ፋቲሓ 2) ፡፡ የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡

የዐረፋ ቀን የሚባለው የዙል-ሒጃ 9ኛ ቀን ነው፡፡ ሓጅ አድራጊዎች ያለ ፆም በዐረፋ ተራራ ላይ ከእኩለ-ቀን (ዙህር) አንስቶ መግሪብ እስኪደርስ ይቆያሉ: በዱዓም ጌታቸውን ይማጸናሉ፡፡ ዙህርንና ዐሱርንም በአንድ ላይ ወደ ዙህር በማምጣት አሳጥረው ይሰግዳሉ፡፡ ጌታቸውም ወደነሱ ይቀርባል፡፡ በዚያም ቀን ብዙዎች በክፉ ተግባራቸው እሳት የተገባቸው: በአላህ ቸርነት ከእሳት ነጻ ይባላሉ፡፡ ሓጅ ያላደረጉት ደግሞ ቀኑን በፆምና በተለያየ ዒዳባህ ያሳልፉታል፡፡
ይህ ቀን ከሌሎች ቀናት ከሚለይባቸው ውስጥ፡-

1. ዲኑ የተሟላበት ቀን መሆኑ፡-

"...الْيَوْمَ أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ وَأَتْمَمْتُ عَلَيْكُمْ نِعْمَتِي وَرَضِيتُ لَكُمُ الْإِسْلَامَ دِينًا..." سورة المائدة 3
"…ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ። ጸጋዬንም በናንተ ላይ ፈጸምኩ። ለናንተም ኢስላምን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ…" (ሱረቱል ማኢዳህ 5:3)፡፡

ይህ ቅዱስ አንቀጽ የወረደው በዙል ሒጃ ወር፡ ሐጀተል ወዳዕ(የመሰናበቻው ሐጅ) በ 9ኛው ቀን: በዕለተ ጁምዓ በዐረፋ ተራራ ላይ ነበር፡፡

2. የሙስሊሞች ዒድ መሆኑ:–

ዑቅበተ ኢብኑ ዐሚር (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "የዐረፋ ቀን፣ የእርዱ ቀን፣ ቀጣዮቹም 3ቱ ቀናት የኛ ዒዳችን ነው" (ሶሒሑል ጃሚዕ 8192)።

3. ፆሙ የሁለት አመት ኃጢአት ያስምራል:–

አቢ ቀታዳህ እንዳሉት የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "የዐረፋ ቀን ጾም የሁለት ዐመት (ያለፈውንና የሚመጣውን) ኃጢአት ያስምራል" (ከቡኻሪ በስተቀር ሁሉም የዘገበው)፡፡

4. ብዙ ሰው ከእሳት ነጻ የሚባልበት ቀን መሆኑ:–

እናታችን ዓኢሻህ (ረዲየላሁ ዐንሃ) እንደነገረችን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "ከዐረፋ ቀን ተሸሎ ብዙ ሰው ከእሳት ነጻ የሚባልበት ቀን የለም" (ሙስሊም)፡፡

5/ ከዱዓኦች ሁሉ በላጩ በዚህ ቀን መሆኑ:–

በማንኛውም ቀንና ለሊት፣ በማንኛውም ስፍራና ሁኔታ ወደ አላህ የሚደረገው ዱዓ በሩ ክፍት ነው። ተመላሽነት የለውም። ሆኖም በዐረፋ ቀን የሚደረገው ዱዓእ ግን ከየትኛውም ቀን የተሻለ ነው። ከዐብዱላህ ኢብኑ አምሩ ኢብኑል–ዓስ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ:– "ከዱዓዎች ሁሉ በላጩ የዐረፋ ቀን ዱዓእ ነው፡፡ እኔና ከበፊቴ የነበሩት ነቢያት ከተናገርነው ቃላት ሁሉ በላጩ፡- ‹‹ላ ኢላሀ ኢልለሏሁ፡ ወሕደሁ፡ ላ-ሸሪከ ለህ፣ ለሁል-ሙልኩ፡ ወለሁል-ሐምድ፣ ወሁወ ዐላ-ኩሊ ሸይኢን ቀዲር›› የሚለው ነው" (ቲርሚዚይ 3585፣ ሶሒሑል-ጃሚዕ 3274)፡፡

6/ ለአምስት ቀናት የሚቆየው ተክቢራም የሚጀምረው በዚሁ በዐረፋ በዘጠነኛው ቀን ፈጅር ሶላት ጀምሮ ስለሆነ: በዚሁ ቀን ከፈርድ ሶላት በኋላ ሶስት ጊዜ አስተግፊሩላህ እንበልና ከዛም አላሁመ አንተ–ሰላም ...... ካልን በኋላ በቀጥታ ወደ ተክቢሩ በመግባት:– "አላሁ አክበር፣ አላሁ አክበር፣ አላሁ አክበር። ላ ኢላሀ ኢልለሏህ፣ አላሁ አክበር፣ አላሁ አክበር፣ ወሊላሂል ሐምድ" እንበል።

ዑዝር ላይ ላሉ ወንድም/እሕቶች:–

የዐረፋን ቀን ፆም ከልቡ ለመፆም የወሰነ ወንድም/እሕት፣ ነገር ግን በዑዝር ሰበብ (በሽታ፣ ሰፈር፣ ሐይድ፣ የወሊድ ደም፣ ወዘተ) ቀኑን መፆም ባይችልስ? ለሚለው ሸይኽ ስዑድ ከረመዷን ዐሽሩል አዋኺር ጋር ተመሳሳይ ጥያቄ ቀርቦላቸው መልስ ስለሰጡበት: መልሱን እንዲህ አቅርበነዋል:–

ተጠያቂው ሸይኽ ኻሊድ ቢን ሱዑድ

ጥያቄ፡- አሰላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ ያ ሸይኽ! በሐይድ ላይ ያለች ሴት ወይም የወለደች እንዴት አድርጋ የረመዷንን የመጨረሻ አስር ቀናት መጠቀም ትችላለች? ያ ሸይኽ! እኔ በጣም በመጨናነቄ ሰበብ እርሶ እንዲረዱኝና እንዲሁም ሀሳቡና ጭንቀቱ እንዲቀልልኝ እፈልጋለሁ፡፡ አላህም የለይለቱል-ቀድርን ምንዳ እንዳይከለክለኝ ዱዓእ እንዲያረጉልኝ እማጸንዎታለሁ፡፡

ምላሽ፡- ወዐለይኩሙ-ሰላሙ ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ የተከበርሽ እህቴ! ከሁሉ በፊት ቀድመሽ ልታውቂው የሚገባ ነገር፡- የወር አበባና የወሊድ ደም አላህ እሱ ብቻ ለሚያውቀውና ለፈለገው ጥበብም በአንቺ ላይ የወሰነው የተፈጥሮ ህግ መሆኑን ነው፡፡ መልካም ነገር ደግሞ አላህ ላንቺ የመረጠልሽ ነገር እንጂ አንቺ ለራስሽ የመረጥሽው አይደለም፡፡ አላህ ለወሰነው (ቀዷ ወል-ቀደር) እጅ ስጪ፡፡ ደግሞም አንቺ ለነፍሲያሽ ከጓጓሽው በላይ አላህ ላንቺ አዛኝ ጌታ መሆኑን እርግጠኛ ሁኚ፡፡

በተጨማሪም ልታውቂው የሚገባ ነገር፡- አንድ ሰው በዑዝር ወቅት በሰላም ጊዜ ይፈጽመው የነበረውን ነገር መቀጠል ቢያቅተው እንኳ አጅሩ ግን እንደማይቋረጥበት ነው፡፡ ተወዳጁ የአላህ ነቢይም (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) እንዲህ ብለዋል፡- "አንድ የአላህ ባሪያ ከታመመ ወይም ከመኖሪያ ክልል ርቆ (ሙሳፊር የሚሰኝበትን ያህል) ከተጓዘ: ጤነኛና የአካባቢው ነዋሪ ሆኖ ይፈጽመው የነበረው (መልካም ስራ) ሳይቋረጥ ይጻፍለታል" (ቡኻሪይ 2996)፡፡

አንቺ ደግሞ በሐይድ ወቅት ያለ ጥርጥር ዑዝር ያለሽ ነሽ፡፡ ምክንያቱም፡- ያለ ምርጫሽና ፍላጎትሽ የመጣ በመሆኑ፡፡ እንዲሁም ልትከላከዪውና ልታስቀሪው የማትችዪው ነገር ስለሆነ፡፡ በድጋሚም ማወቅ ያለብሽ ነገር፡- አንድ የአላህ ባሪያ አንድን ነገር ለመስራት ከልብ የቆረጠ ኒያ ካለው ከዛም ያንን የነየተውን ነገር ለመስራት ድንገተኛ ሁኔታና ክስተት ቢከለክለውና ቢያግደው፤ አላህ ግን እንደሰራው በመቁጠር ሙሉ አጅሩን የሚጽፍለት መሆኑን ነው፡፡ ይህንን አስመልክቶ የአላህ ነቢይም (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) እንዲህ ብለዋል፡-

"በመዲና ውስጥ ሰዎች አሉ፡፡ እናንተ አንድንም ሸለቆ አታቋርጡም መንገድንም አትዘልቁም እነሱ በአጅር ቢጋሯችሁ እንጂ፡፡ ከናንተው ጋር አብረው እንዳይጓዙ ዑዝር ከለከላቸው" (ቡኻሪይ)፡፡

በሌላ ቅዱስ ትምህርታቸው ላይ ደግሞ እንዲህ አሉ፡- "አላህን በፍጹም ልቡ ሸሂድነትን (ለዲን ሰማእት ሆኖ መሞትን) እንዲወፍቀው የለመነ ሰው ቀኑ ደርሶ በፍራሹ ላይ እንኳ ቢሞት(በኒያው ሰበብ) የሸሂዶችን (ሰማእታት) ደረጃ ያጎናጽፈዋል" (ሙስሊም)፡፡

ታዲያ አንቺም እንደ ሌሎቹ ሙስሊም እህቶችሽና ወንድሞችሽ እነዚህን አስር ቀናት በዒባዳ ለማሳለፍ ገና ከመጀመሪያው የነየትሽና የጓጓሽለት ከነበር ጌታሽ ኒያሽን ከንቱ እንደማያረግብሽ ባለሙሉ ተስፋ ሁኚ አብሽሪ፡፡

ሌላው ደግሞ ይህ የወር አበባ ወይም የወሊድ ደም ሶላት ከመስገድ፣ ጾም ከመጾምና መስጂድ ከመግባት ቢያግድሽም ሌሎች ያልተከለከልሻቸው ዒባዳዎች መኖራቸውንም አትዘንጊ፡፡ ከነዚም መካከል፡- (ሱብሐነላህ፣ አልሐምዱ ሊላህ፣ ላኢላሀ ኢለላህ፣ አላሁ አክበር…) አዝካሮችን ማለት፣ ዱዓእ ማድረግ፣ በነቢያችን (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) ላይ ሶላዋት ማውረድ፣ ሶደቃ ማውጣት፣ ኢስቲግፋር ማብዛት፣ በአላህ ስሞችና በሱ ስራዎች ማስተንተንን የመሳሰሉት፡፡
በመጨረሻም ማወቅ ያለብሽ ነገር፡- እነዚህ አስር ቀናት በዑዝር ሰበብ ሊያመልጠኝ ነው ብለሽ ማሰብና መጨነቅሽ በራሱ የሚያመላክተው የኢማንሽን ታላቅነት፣ ወደ አላህ ለመቃረብ ያለሽን ጉጉት ነው ኢንሻአላህ፡፡ ስለዚህም የቻልሽውን ያህል ኸይር ስራ ለመስራት ታገዪ፣ ተረጋጊ አትጨናነቂ፣ አይዞሽ፣ አላህ ላይ ያለሽን ተስፋ ከፍ አድርጊ እሱ ኒያሽንም ሆነ መልካም ስራሽን አያባክነውም ምንዳውንም አይከለክልሽም፡፡ የሱ እዝነት አንቺን ብቻ ሳይሆን ዓለሙን ሁሉ የሰፋና ያካለለ ነውና፡፡ ወሰሊላሁመ ወሰለም ዓላ ነቢዪና ሙሐመድ ወዓላ ኣሊሂ ወሰሕቢሂ ወሰለም፡፡

ስለዚህ መጪው ሰኞ የዐረፋ ቀን ነውና ይህን ቀን እንጹመው እንዳያመልጠን፡፡ በእስር ያሉ ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንንም እንዲሁም ዓለም ላይ ያሉ የሚሰቃዩትን ሙስሊሞችን በዱዓ እንዳንረሳቸው፡፡ አላህ ይወፍቀን አሚን፡፡

Click and Like ➤➤ http://fb.com/Ustaz.Abuhyder
አሰላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ

እንኳን ለ1442ኛው የተከበረው ዒዱል አድሓ በዓል አላህ በሰላም አደረሳችሁ!

ተቀበለላሁ ሚንና ወሚንኩም ዒዱኩም ሙባረክ
ዐሹራእ ደረሰ

አቡ ሀይደር

በአላህ ሥም እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ክብርና ምሥጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን (አል-ፋቲሓ 2)፡፡ የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡

#ዐሹራእ ምንድነው?

ዐሹራእ ማለት (የሙሐረም ወር) አሥረኛው ቀን ማለት ነው፡፡ አሁን ያለንበት ወር ሙሐረም አንደኛው ወር ተብሎ ይጠራል፡፡

#ይህ ወር ክብር ያለው ወር ነው፡-

አቢ ሁረይራህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ከነቢያችን (ዐለይሂ ሶላቱ-ወስ-ሰላም) እንዳስተላለፈልን የአላህ መልክተኛ እንዲህ ብለዋል፡- "ከረመዷን ቀጥሎ ከጾሞች ሁሉ በላጩ የአላህ ወር የሆነው ሙሐረም ነው" (ሙስሊም 2812)፡፡
ከሙሐረም ወር ውስጥ ደግሞ አሥረኛው የዐሹራእ ቀን በላጭ ቀን ነው፡፡

#ለምን ይጾማል?

ዐብደላህ ኢብኑ-ዐባስ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንዲህ አሉ፡- "የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ወደ መዲና ሲገቡ አይሁዶችን በዐሹራእ ቀን ሲጾሙ አገኟቸው፡፡ ይህን ቀን የምትጾሙት ለምንድነው? ብለው ሲጠይቋቸው፡ እነሱም፡- ይህ ታላቅ ቀን ነው! አላህ ሙሳንና ተከታዮቹን ከፊርዐውንና ሰራዊቱ በማዳን እነሱን በባሕር ያሰጠመበት ቀን ስለሆነ ሙሳም ለአላህ ምስጋናን ለማድረስ ጾሞታል እኛም እንጾመዋለን ብለው መለሱ፡፡ የአላህ መልክተኛውም (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ፡- ለሙሳ (ወዳጅነት) ከናንተ ይልቅ እኛ የቀረብንና የተገባን ሰዎች ነን እኮ! በማለት እሳቸውም ጾሙት ሶሓባዎቻቸውንም እንዲጾሙ አዘዙ" (ሙስሊም 2714)፡፡
ከዛ በፊት ግን በመካ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ዐሹራእን ይጾሙ ነበር ነገር ግን ማንንም አላዘዙም፡፡

#ጥቅሙስ ምንድነው?

አቢ ቀታዳህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተናገረው የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "የዐረፋ ቀን ጾም አላህ ዘንድ ያለፈውንና የሚመጣውን (የሁለት) ዓመት (ትናንሽ) ኃጢአቶችን ያስምራል፣ የዐሹራእ ቀን ጾም ደግሞ ያለፈውን አንድ ዓመት (ትናንሽ) ኃጢአት ያስምራል" (ሙስሊም 1976)፡፡
ዐብደላህ ኢብኑ ዐባስ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንዲህ አለ፡- የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የዐሹራእን ቀን የጾሙና ሶሓቦቻቸውን ያዘዙ ጊዜ፡- "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ይህን ቀን እኮ አይሁዶችና ክርስቲያኖች ያከብሩታል ሲሏቸው፡ እሳቸውም፡- በቀጣዩ ዓመት አላህ ካደረሰን ዘጠነኛውን ቀን እንጾማለን አሉ፡፡" (ሙስሊም 2722)፡፡
በሌላ ዘገባ ላይ ደግሞ "ከ(ዐሹራእ) ቀን ከፊቱ ወይም ከኋላው አንድን ቀን ጹሙ" ብለዋል (አሕመድ የዘገቡት)፡፡ ሐዲሡ ዶዒፍ ነው የሚሉም አሉ ወላሁ አዕለም፡፡
ያ ዓመት ሳይደርስ የአላህ መልክተኛ ከዚህ ዓለም ተለዩ፡፡ የኢስላም ሊቃውንትም ከዚህ ሐዲሥ በመነሳት የሁዳዎችን ላለመመሳሰል ዘጠነኛውንም ቀን ጨምሮ መጾም ነቢያዊ ሱንና መሆኑን ገለጹ፡፡

#መጾሙ ዋጂብ ነው ወይስ ሱንና?

የዐሹራእን ቀን መጾም ሑክሙ ሱንና ነው፡፡ በሒጅራ 2ኛው ዓመት የመጀመሪያው ወር ሙሐረም ላይ ስለነበር የተደነገገው የረመዷን ጾም እስኪደነገግ ድረስ ዋጂብ ነበር፡፡ ከ7 ወር በኋላ ግን በሒጅራ 2ኛው ዓመት 8ኛው ወር ሻዕባን ላይ የረመዷን ጾም ግዳጅነት ሲደነገግ፡ ዐሹራእ ግዳጅነቱ ተሰረዘ፡፡ ይህን በተመለከተ ቀጣዩ ሐዲሥ እንዲህ ይላል፡-

እናታችን ዓኢሻህ (ረዲየላሁ ዐንሃ) እንዲህ አለች፡- "የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ረመዷን ሳይደነገግ በፊት ዐሹራእን ይጾሙ ነበር፡፡ ካዕባም የሚሸፈንበት ቀን ነበር፡፡ አላህ ረመዷንን በደነገገበት ጊዜ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- የፈለገ ሰው (ዐሹራእን) ይጹመው ለመጾም ያልፈለገ ደግሞ ይተወው" (ቡኻሪይ 1489)፡፡

#መቼ እንጀምር?

የሙሐረም አስረኛው ቀን (ዐሹራእ) የፊታችን ረቡእ ነው የሚውለው፡፡ ስለዚህ አላህ ወፍቆት ይህን ዐሹራእን መጾም የፈለገ ከአራቱ መንገዶች አንዱን መርጦ ይጹም፡-
ሀ. ረቡእን ብቻ፡- 10ኛውን ቀን መጾም ማለት ነው፡፡ ዋናው ዐሹራእ ተብሎ የሚጠራውም ይህ ቀንነው፡፡
ለ. ማቅሰኞና ረቡእን፡- 9ኛውንና 10ኛውን ቀን መጾም ማለት ነው፡፡ ይህም በላጭና ሱንና ነው፡፡
ሐ. ከ ማቅሰኞ-ሀሙስ፡- 9ኛ፣10ኛና 11ኛውን ቀን ማለት ነው፡፡ ይህም በላጩ ነው፡፡
መ. ረቡእና ሀሙስን፡- 10ኛውና 11ኛውን ቀን መጾም ማለት ነው፡፡ 9ኛውን ቀን ጁምዓህ ለመፆም ያልተመቸው 10ኛውና 11ኛውን ቀን መጾም ይችላል፡፡
አላህ ይወፍቀን፡፡
Click and Like ➤➤
https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
2024/09/28 09:33:36
Back to Top
HTML Embed Code: