Telegram Web Link
ወንድማችንን እንደግፈው

እዚሁ መንደር ያለ ወንድማችን ነው።ታታሪ ሰራተኝነት መገለጫው ነው።ከአመት በፊት ሸገር ሲቲ ቤት ፈረሳ ሲጀምር ብዙ አመት ለፍቶ የገነባው ቤት ፈረሰ።ወንድማችን በወቅቱ ሀዘኑን ዋጥ አድርጎ ቤት ፈረሳውን ተከትሎ አደባባይ የወጡ ወገኖቹን ከችግር ለመታደግ የተከራየው ቤት ላይ ሰዎችን ከማስጠለል ጀምሮ የሚያውቃቸውን ሰዎች እያስቸገረ የሚቋቋሙበትን ስራ ለማስጀመር ደፋ ቀና ይል ነበር።ወራት ነጎዱ ወንድማችን በአላህ ፈቃድ የፈረሰብኝን ቤት ነገ በላቤ ሰርቼ እተካዋለሁ ብሎ መልፋቱን ቀጠለ።አሁን ደግሞ የቤተሰቡን ህይወት የሚያናጋ ሌላ ዱብ እዳ መጣበት።ለኮሊደር ልማቱ ይፈለጋል በሚል የስራ ቦታው ፈረሰ።ለአመታት እረፍት የማያውቁ እጆቹ ስራ ፈተው ቤት መቀመጥ እጣቸው ሆነ።
ስራ ፈቶ ቤት ከመቀመጡ በላይ ሰርቼ እከፍለዋለሁ ብሎ የተበደረውን የ650 ሺህ ብር እዳ መክፈል ዳገት ሆነበት።እጁ ላይ የቀረውን 400 ሺህ ብር ለአበዳሪው ከፍሎ 250 ሺህ ብሩን ለመክፈል የአንድ ሳምንት ተጨማሪ ጊዜ ጠየቀ። ነገር ግን እጁ ላይ ቤሳቤስቲ እንኳ አልቀረውም።ወንድማችን ለቀናት እንቅልፍ አጥቶ ከባድ ጭንቀት ውስጥ ገብቷል። በዚህ ከቀጠለ የጤናውም ነገር አሳሳቢ ነው።

ለሰዎች ደራሽ የሆነውን ወንድማችን ከጭንቀት መታደግ የሁላችንም ኃላፊነት ነው።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000651036406
ሹክራየ ሱልጣን(የባለቤቱ አካውንት ነው)
2024/09/28 17:26:24
Back to Top
HTML Embed Code: