Telegram Web Link
RAMDAN KERIM
#profile_pic

@abubekersidik
💞💞💞💞💞💞
አላህ ለይለተል ቀድርን ይወፍቀን

አሚን🙌
🌙 #ረመዳን 23

ለይለተል-ቀድር መሆኑን ባውቅ ምን ብዬ ዱዓእ ላድርግ?

እናታችን ዓኢሻ ረዲ አላሁ ዐንሀ እንዲህ ብለዋል:-
የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ለይለተል ቀድርን ባገኝ (ያቺ ለሊት
ለይለተል-ቀድር መሆኗን ባውቅ) ምን ብዬ ዱዓእ ላድርግ?
ብዬ ጠየቅኳቸው።
እሳቸውም:- «አላሁመ ኢነከ ዓፉዉን ቱሂቡ አል-ዓፍው ፈዕፉ ዓኒ »
(አላህ ሆይ! አንተ ይቅር ባይ ነህ ይቅርታንም ትወዳለህ ይቅር በለኝ) በይ አሉኝ። (ቲርሚዚይ፣ኢብኑ ማጃህ፣ ኢማሙ አህመድ እና ሃኪም ዘግበውታል)

#በዱዓእንበርታ 🤲
ዘካቱል‐ፊጥር
=========
ለጾም ፍቺ የሚሰጥ ዘካ ስለሆነ ዘካቱል‐ፊጥር ይባላል። እንደሌሎች ዘካዎች በሀብት ላይ ሳይሆን በጾመኛ አካል ላይ የሚያርፍ ዘካ በመሆኑ ደግሞ ዘካቱል‐በደን ይባላል።
:
ከሂጅራ በኋላ በሁለተኛው ዓመት ላይ የተደነገገ የዘካ ዓይነት ነው። የረመዳን ጾም በተደነገገበት ዓመት ማለት ነው። ዘካቱል‐ፊጥር ግዴታ መሆኑ በበርካታ ሐዲሶች ተረጋግጧል።
ከአቡ ሰዒድ አል‐ኹድሪይ [ረዐ] እንደተዘገበው: ‐ «የአላህ መልክተኛ [ﷺ] በመካከላችን እያሉ ዘካቱል‐ፊጥርን እንሰጥ ነበር።» ብለዋል።» ሙስሊም ዘግበውታል።
ከኢብኑ ዐባስ [ረዐ] እንደተዘገበው "የአላህ መልክተኛ [ﷺ] ዘካቱል‐ፊጥርን ግዴታ አድርገው ደንግገውታል።" አቡዳዉድ እና ሌሎችም ዘግበውታል።
:
የድንጋጌ ጥበብ
==========
ዘካቱል‐ፊጥር የተደነገገው በጾም ላይ የተከሰቱ ጉድለቶችን ለመጠገን እና በዒድ ቀን ድሆችን ከልመና ለመጠበቅ ነው። የአላህ መልክተኛ [ﷺ] ዘካቱል‐ፊጥር የተደነገገበትን ምክንያት ሲገልፁ እንዲህ ብለዋል: ‐ "ለጾመኛ ንፅህና ለምስኪን ምግብ እንዲሆን የተደነገገ ነው።" ኢብኑ ዐባስ (ረዐ) ዘግበውታል።
በሌላ ሐዲስ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል: ‐ "[ድኾቹን] በዚያን እለት ለልመና እንዳይዞሩ አብቃቋቸው።"
ዘካቱል‐ፊጥር በሶላት ውስጥ ለሚከሰቱ አንዳንድ ስህተቶች እንደተደነገገው ሰጅደቱ‐ሰህዉ (የመርሳት ሱጁድ) የሚታይ ነው። ሰጅደቱ ሰህው ሶላትን እንደሚጠግነው ዘካቱል‐ፊጥርም ጾምን ይጠግናል።
ዘካቱል‐ፊጥር በማህበረሰቡ መሀል የመተባበርና የመረዳዳት መንፈስን ያሳድጋል። መተዛዘን እንዲሰፍን፣ የሀዘን እና የደስታ ስሜትን የሚጋራ ህዝብ ለመፍጠርና የማህበረሰብ ትስስርን ለማጥበቅ ያግዛል።

@abubekersidik 👈
ግዴታ የሚሆነው በማን ላይ ነው?
=====================
ዘካቱል‐ፊጥር ማውጣት የእያንዳንዱ ሙስሊም ግዴታ ነው። ወንድን ከሴት፣ ህፃንን ከዐዋቂ፣ እብድን ከጤነኛ አይለይም። ዐብዱላህ ኢብኑ ዑመር [ረዐ] እንደዘገቡት: ‐ "የአላህ መልክተኛ [ﷺ] የረመዳን መግደፊያ ዘካን ግዴታ አድርገዋል። መጠኑ አንድ ቁና ተምር ወይም አንድ ቁና ገብስ ነው። ባሪያም ሆነ ጨዋ፣ ወንድም ሆነ ሴት፣ ህፃንም ሆነ ዐዋቂ በሙስሊሞች ላይ ሁሉ ግዴታ ተደርጓል።" ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ኢብኑል‐ሙንዚር እንዲህ ብለዋል: ‐ "ዘካቱል‐ፊጥር ግዴታ መሆኑ ላይ የምናውቃቸው ዐሊሞች በሙሉ ተስማምተዋል።"
:
የግዳጅ መስፈርቶች
============
ዘካቱል‐ፊጥር ግዴታ ይሆን ዘንድ መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች ተከታዮቹ ናቸው: ‐
❶ ሙስሊም መሆን: ‐ ሙስሊም ያልሆነ ሰው ዘካቱል‐ፊጥር ቢያወጣ ተቀባይነት የለውም። አላህ እንዲህ ብሏል: ‐ «ልግስናዎቻቸውን ከነሱ ተቀባይ የሚያገኙ ከመኾን እነሱ በአላህና በመልክተኛው የካዱ… መኾናቸው እንጂ ሌላ አልከለከላቸውም፡፡»
❷ ችሎታ: ‐ በዒድ ሌሊትና በቀኑ ላይ ከራሱና ከቤተሰቡ ቀለብ እና መሰረታዊ ወጪ የተረፈ ገንዘብ መኖር።
:
ሰውየው ከራሱ በተጨማሪ ወጪያቸውን ሸፍኖ ማኖር ግዴታ የሚሆንበትን ሰዎች ዘካ መስጠትም ግዴታ አለበት። የህፃናት ልጆቹን፣ የሚስቱን እና [በርሱ ስር የሚተዳደሩ] ወላጆቹን ማለት ነው።
:
ኢብኑ ዑመር [ረዐ] በዘገቡት ሐዲሰ የአላህ ነቢይ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «ለምትቀልቧቸው ሰዎችም ዘካቱል‐ፊጥር አውጡላቸው።» ዳረቁጥኒ ዘግበውታል።
:
አንዲት ሴት ባሏ ዐቅም ከሌለው ዘካቱል‐ፊጥር ማውጣት በርሷ ላይ ግዴታ በመሆኑ ላይ የዐሊሞች ልዩነት አለ። ዘካዋን በራሷ መክፈል ግዴታ ይሆንባታል የሚለው ሃሳብ ግን የአብዝሃኞቹ ዐሊሞች ነው።
ሰውየው በዕዳ የተያዘ ሰው መሆኑ ዘካቱል‐ፊጥርን ለመተው ምክንያት አይሆንም።
:
ግዴታ የሚሆንበት ጊዜ
==============
ዘካው ግዴታ የሚሆንበት ጊዜ የሚጀምረው በዒድ ዋዜማ ፀሀይ ከመጥለቋ አንስቶ ነው። ምክንያቱም ዘካቱል‐ፊጥር የተደነገገበት ምክንያት ጾም ነበር። እርሱ ደግሞ ፀሀይ በመጥለቋ ምክንያት አብቅቷል። ይህ የኢማም ሻፊዒይና የኢማም አሕመድ ሃሳብ ነው።
በዚህ መሰረት የዒድ ሌሊት ፀሀይ በምትጠልቅበት ሰዓት ዘካቱል‐ፊጥር ግዴታ ከሚሆንባቸው ሰዎች መካከል ሆኖ የተገኘ ዘካውን የመስጠት ግዴታ ይኖርበታል። ፀሀይ ከጠለቀች በኋላ ወዲያው ቢሞትም ግዴታው እንዳለ ነው። በተቃራኒው ፀሀይ ከመጥለቋ ከደቂቃዎች በፊት የሞተ ሰው ዘካ የለበትም።
:
አቡ ሐኒፋ እና ማሊክ በበኩላቸው ግዳጁ የሚጀምረው ንጋት ከቀደደ አንስቶ ነው ባይ ናቸው። ምክንያቱም ዘካቱል‐ፊጥር የተደነገገበት ምክንያት ዒዱ ነው። ስለዚህ እንደማናቸውም የዒድ ቀን ድንጋጌዎች፣ እንደ ኡድሒያ፣ እንደ ጁሙዐ ሶላት ድንጋጌዎች… ከእለቱ ቀድሞ ግዴታ ይሆንም።…
:
የሚሰጥበት ጊዜ
===========
ዘካውን የዒድ ሶላት ከመሰገዱ አስቀድሞ ማውጣት ይወደዳል። ሻፊዒዮች ዘንድ በዒዱ ቀን ፀሀይ እስከምትጠልቅ ድረስ መስጠት ግን ይፈቀዳል። አብዝሀኞቹ ዐሊሞች ደግሞ ከሶላት በኋላ ማውጣት ይጠላል ብለዋል። አንዳንድ ዐሊሞች ከሶላት በኋላ አዘግይቶ መስጠት ሐራም ነው ይላሉ። እለቱን ማሳለፍ ግን ያለ ልዩነት ሐራም ነው። ነገርግን ቀኑ ቢያልፍም ዘካው ከሰውየው ጫንቃ ላይ አይነሳም። ጫንቃውን ከድሆች ሐቅ ለማፅዳት መቼም ቢሆን ዘካውን መክፈል አለበት። ከዚያም ማዘግየቱ የአላህ ሐቅን መጣስ በመሆኑ አላህን ምህረት መለመን አለበት።
:
አቡ ሰዒድ አል‐ኹድሪ [ረዐ] እንዲህ ብለዋል: ‐ "በአላህ መልክተኛ [ﷺ] ዘመን በዒዱል‐ፊጥር ቀን አንድ ቁና እህል እንሰጥ ነበር።"
ከኢብኑ ዑመር [ረዐ] እንደተዘገበው የአላህ መልክተኛ [ﷺ]: ‐ "ዘካቱል‐ፊጥር ሰዎች ለሶላት ከመውጣታቸው አስቀድሞ እንዲሰጥ አዘዋል።"
የዘካው ዓላማ ድሆች ከሀብታም ጎረቤቶቻቸው ጋር የዒዱን ቀን በደስታ እንዲያሳልፉ ከመሆኑ አንፃር በጠዋት ከሶላት በፊት መስጠቱ ተገቢ ነው።
:
ዘካውን ሳይሰጥ የዘገየው በአሳማኝ ምክንያት ከሆነ ግን ችግር የለውም። ለምሳሌ: ‐ ሰውየው የሚሰጠው ነገር በሌላ ቦታ ላይ እያለ የዘካው ጊዜ ከደረሰበት፣ ዘካ የሚቀበል ተገቢ አካል ሳያገኝ በመቅረቱ ካዘገየው፣ የዒዱ አዋጅ በድንገት ተነግሮ ከሶላት በፊት ዘካ ለማውጣት የሚመች ጊዜ በማጣቱ፣ ሌላ ሰው ዘካውን ያወጣልኛል ብሎ ተዘናግቶ ባለበት ሰውየው ከረሳው ወ.ዘ.ተ. ዘካውን ያለ ምንም ችግር ከዒድ በኋላም መስጠት ይችላል። ምክንያቱም በነዚህ ሁኔታዎች በሙሉ ሰውየው ምክንያታዊ ነው።
:
ማስቀደም
======
ሻፊዒዮቹ ዘንድ ከረመዳን አንደኛው ቀን ጀምሮ ግዴታ ከመሆኑ አስቀድሞ ዘካውን መስጠት ይፈቀዳል። ምክንያቱም ዘካው በሁለት ምክንያቶች የተደነገገ ዘካ ነው። አንደኛው ጾም ሲሆን ሌለኛው ፊጥር ነው። ረመዳን አንድ ሲል አንዱ ምክንያት ተገኝቷል። ስለዚህ ዘካውን ከረመዳን አንድ ጀምሮ መስጠት ይቻላል።
ኢማም ማሊክ እና አሕመድ ዘንድ ደግሞ ከሁለት ቀን አስቀድሞ መስጠት ይቻላል። አንዳንዶቹ ሦስት ቀን ማስቀደም ይፈቀዳል ይላሉ። ሐንበሊዮች በከፊሉ ከረመዳን አጋማሽ ጀምሮ አስቀድሞ መስጠት ይቻላል ይላሉ። ነገሩ ሰፊ ነው። የፈለጉትን ዐሊም ሀሳብ ተንተርሶ መፈፀም ይቻላል።
:
ቡኻሪ እንደዘገቡት "ኢብኑ ዑመር [ረዐ] ሶደቀቱል‐ፊጥርን ይሰጡ ነበር። ከዒዱ እለት አንድ ወይም ሁለት ቀን አስቀድመውም ያወጡ ነበር።"
የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ "ከሶላት በፊት ከሰጠ ዘካው ተቀባይነት ያለው ነው። ከሶላት በኋላ ከሰጠ ደግሞ እንደማንኛውም ምፅዋት የሚቆጠር ነው።" አቡዳዉድ ዘግበውታል።
:
የእህል ዓይነቶች
==========
ዘካቱል‐ፊጥር የሚወጣባቸው የእህል ዓይነቶች ተዘርዝረው አያልቁም። በአጭሩ በሀገሩ ላይ አብዝሀኛው ሰው የሚመገበውን የምግብ [የእህል] ዓይነት ማውጣት ግዴታ ነው። ኢብኑ ዑመር [ረዐ] እንዲህ ይላሉ: ‐ "የአላህ መልክተኛ [ﷺ] የረመዳን ፍቺ ዘካን ግዴታ አድርገው ደንግገዋል። መጠኑም አንድ ቁና ተምር ወይም አንድ ቁና ገብስ ነው።" ያን ጊዜ ገብስ ይመገቡ ስለነበር ነው።
:
አቡ ሰዒድ አል‐ኸኹድሪይ [ረዐ] እንዲህ ብለዋል: ‐ "በነቢዩ [ﷺ] ዘመን በዒዱል‐ፊጥር ቀን አንድ ቁና ምግብ ዘካ እናወጣ ነበር። በዚያን ጊዜ ምግባችን ገብስ፣ ዘቢብ፣ ደረቅ ወተት [አይብ] እና ተምር ነበር።" ቡኻሪ ዘግበውታል።
:
የእህል ዋጋን መስጠት
==============
የዘካቱል‐ፊጥር መጠን በሀገሩ እንደቀለብ ከሚበሉ የእህል ዓይነቶች አንድ ቁና ነው። ይኸውም ለአንድ ሰው ሁለት ኪሎ ከአርባ ግራም (2.4 ኪ.ግ.) ይሆናል። እህሉን መስጠት ድንጋጌው የተዘገበበት ተቀዳሚ አፈፃፀም ነው። ሻፊዒዮቹን ጨምሮ በአብዝሃኞቹ ዓሊሞች መዝሀብ መሰረት በዋጋው መስጠት አይፈቀድም።
:
በእርግጥ ዋጋውን መስጠት እንደሚፈቀድ የሚያምኑ አንዳንድ ዐሊሞች አሉ። ኢማም አቡ ሐኒፋ፣ የአቡ ዩሱፍ፣ የሐሰኑል‐በስሪይ እና ሰውሪይ ከነዚህኞቹ ናቸው። የዘካ ዓላማው የድኾችን ችግር መቅረፍ እስከሆነ ድረስ ነገሩ ሰፊ ተደርጎ መታየት አለበት።
:
ዶ/ር ሙሐመድ አዝ‐ዙሐይሊ "አል‐ሙዕተመድ" በተሰኘው መፅሀፋቸው ላይ እንዲህ ብለዋል: ‐ «በዚህ ዘመን የአቡ ሐኒፋን ሃሳብ ከመያዝ የሚያግድ ነገር የለም። ምክንያቱም በዚህ ዘመን ለድኾች የሚጠቅመው ይህ ስለሆነ ነው። ዘካ የተደነገገበትን ድኾችን የማብቃቃት ትልምንም ያሳካል።»
ከትላንቱ የቀጠለ 👇

"አል‐ፊቅሁል‐ሚንሀጂይ ዐላ መዝሀቢሽ‐ሻፊዒይ" በተሰኘው የሻፊዒዮቹ ድንቅ መፅሀፍ ላይም እንዲህ የሚል አለ: ‐ «በዚህ ጉዳይ ላይ የኢማም አቡሐኒፋን መዝሀብ መከተል ችግር የለውም። ስለዚህ ዋጋውን መስጠት ይፈቀዳል። በዚህ ዘመን ዋጋውን መስጠት እህሉን ከመስጠት የበለጠ ለድኻው ይጠቅማል። ከዘካው ድንጋጌ የሚጠበቀውን ግብም ያሳካል።»
:
ዘካቱል‐ፊጥር ለማን ይሰጣል?
===================
ዘካቱል‐ፊጥርን ዘካ ለሚሰጣቸው ስምንቱ ቡድኖች ማከፋፈል ይፈቀዳል። ነገርግን ለድሆችና ምስኪኖች ማከፋፈል ተመራጭ ነው። ሰውየው ራሱ ሊቀልባቸውና ወጪያቸውን መሸፈን ግዴታ ለሚሆንበት ቤተሰቦቹ መስጠት አይፈቀድለትም። ነገርግን ከዚህ ውጪ ለሆኑ ዘመዶቹ መስጠት ሁለት ምንዳ ያስገኝለታል። አንድም ምፅዋት ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ዝምድናን መቀጠል ነው።
:
አላህ ዒባዳችንን ይቀበለን። ረመዳኑንም አመት አመት ይድገመን!

@abubekersidik 👈
ረመዷን ቀን 23 ሀቢብ ኑሩ
فضل الاجتماع على التلاوة والذكر
1, በህብረት ቁርአን መቅራትን በሚመለከት
2, በጋራ በህብረት ዚክርና አውራድ ማለትን በሚመለከት
3, ኢዕቲካፍ ስለማድረግ
4, ምክር እና ጥቆማ

🍂🌺🌾🍀🌸🌹💘🌴🌷🌻🍁🌼

@abubekersidik

🌼🍁🌻🌷🌴💘🌹🌸🍀🌾🌺🍂
Forwarded from Warida islamic tube
#ብዙ_እንዳትስቁ!!!

ለፈገግታ




ከቀዶ ሕክምና በኀላ፡በሆስፒታል ውስጥ በማገገም ላይ ያለውን
ጓደኛውን ሊጠይቅ የመጣው ሰው፡<<ቀዶ ህክምናው እንዴት ነበር እባክህ?
>>ይለዋል፡፡
በሽተኛው፡<<ምኑ ይነሳል፡የመጀመሪያው ቀዶ ሕክምና
እንዳለቀጥጥ ይሁን እስፖንጅ ረስተው ኖሮ በነጋታው እንደገና
ተቀደድኩ፡፡አሁንም ሰፍተን ጨርሰናል ብለው ከሄዱ በኀላ፡ መቀስ
ሆዴ ውስጥ ረስተው ኖሮ እንደገና ቀደውኝ አወጡት >>እያለ
በማውራት ላይ እያለ ከሐኪምቹ አንዱ ብቅ አለና፡>>ጓንቴን
አይታቹዋል?ትናንት እዚህ አካባቢ የተውኩት ይመስለኛል>>ሲል
ስለሰማው ታካሚው አእምሮውን ሳተ፡፡

በዚህ ይቀላቀሉን👇 @WaridaIslamicTube
Forwarded from Warida islamic tube
ረመዷን - 24
******
ዱንያ የዉድድር ሜዳ ናት። አሯሯጩ ሳይሆን የጨረሰው ነው
ሚሽለመው። ያቋረጠው ሳይሆን በጽናት ያጠናቀቀው ነው ትልቅ
ስኬት የሚጎናፀፈው።
ከረጅም ሩጫ በኋላ ተወዳዳሪዎች ይዳከማሉ። ወደ መዳረሻው
እየቀረቡ በመጡ ቁጥር በርካቶች ይንጠባጠባሉ። የሥራዎች
ፍፃሜያቸው ነዉና ሚታየው ብልሆች ግን ስለ ፍፃሚያቸው ነው
የሚጨነቁት። ከዛሬው ድካም ይልቅ የነገን እርካታ ነው አሻግረው
የሚያዩት። ስለሆነም ጽኑ ናቸው፣ ብርቱ ናቸው፣ ጠንካሮች ናቸው፣
ትጉሃን ናቸው።
ረመዷን አሁንም አለ። ከረመዷን በጥሩ ዉጤት ለመውጣት
ማለቂያው አካባቢ መበርታት አስፈላጊ ነው።
የዉድድር ፈረሶች ለማሽነፍ ያለየሌለ ሀይላቸዉን ነው የሚጠቀሙት
በመጨረሻ ዙር ላይ ነው። በዉድድሩ መጨረሻ አካባቢ ከሚሳነፉት
እንዳንሆን እንጠንቀቅ። አላህ ረመዷናቸው ተቀባይነታቸው አግኝቶ፣
ኻቲማቸው አምሮ፣ ዉጤታቸው ሰምሮ ረመዷንን ከሚሰናበቱት
ያድርገን።
እስከመጨረሻው መስመር ድረስ በርቱ።


#በዚህ_ተቀላቀሉን👇
@WaridaIslamicTube
#የፆም_ህግጋት

#ክፍል_ሰባት

በፆም ውስጥ ምን ምን ነገራቶች ይወደዳሉ
ምንስ ይጠላሉ

👉በፆም ውስጥ የሚወደዱ ነገሮች አሉ። እነሱም፦👇

1⃣#ማፍጠርን_ማፋጠን
(በጊዜ ቶሎ ማፍጠር)

ይኸውም ፀሀይ መጥለቋን ካረጋገጥን በኋላ ነው። ምክንያቱም #ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋልና፦

*لا يزال الناس بخير ما عجلو ا الفطر* رواه مسلم

#ትርጉም ፦ «ሰዎች ማፍጠርን እስካፋጠኑ ድረስ መልካም ላይ ናቸው»ሙስሊም ዘግበውታል።

√ የሚወደደውም በቴምር ማፍጠር ነው። ካልተገኘ ደግሞ በውሀ ። ይኸውም መግሪብን ከመስገድ በፊት ሲሆን ምክንያቱም #ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋልና፦

*إذا أفطر أحدكم فليفطر على تمر فإن لم يجد فليفطر على الماء فإنه طهور* رواه أبو داود

#ትርጉም፦ « ከመካከላቹህ አንዳቹህ ካፈጠረ በቴምር ያፍጥር ፣ካላገኘ በውሀ ያፍጥር ፣እሱ ጠሁር ነውና» አቡ ዳውድ ዘግበውታል።


#ሲያፈጥርም_እንዲህ_ይበል👇

"اللهم لك صمت وعلى رزقك أفطرت"
#ትርጉም
" #አሏህ_ሆይ! ላንተ ብየ ፆሜአለሁ ፣በሲሳይህም አፍጥሪያለሁ"

√ ከማፍጠር በፊት ፀሀይ መጥለቋን ማረጋገጥ ግዴታ ነው።በአዛን ብቻ መመካት በቂ አይደለም። ምክንያቱም አዛን ጊዜው ከመግባቱ በፊት በመቻኮል ሊደረግ ይችላልና።

2⃣#ሱህርን_ማዘግየት

ይኸውም እስከ መጨረሻው ለሊት፤ ፈጅር ከመግባቱ በፊት እስካለው ጊዜ ድረስ ሲሆን ውሀን በመጎንጨትም ቢሆን ተስሂር ማድረጉ ይወደዳል።

አነስ ባወሩት ሀዲስ #ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
*تسحروا فإن في السحور بركة*

#ትርጉም
በሱሁር ተመገቡ፣ በሱሁር ምግብ በእርግጥ በረካ አለዉና* ሙስሊም ዘግበውታል።


3⃣ኛ አንድ የሚፆም ሰው ከውሸት ፣ከሐሜት፣ ከአፀያፊ ንግግርና እነዚህን ከመሳሰሉ ሀራም ነገሮች ከወትሮው በላይ ምላሱን መጠበቅ አለበት።

#ሙስሊም_ወንድም_ሆይ!!
በማፍጠሪያ ሰአት ሀራም ከሆኑ ነገሮች ሆድህን ቆጥብ ። ሀራም ከሆነ እይታም አይንህን ቆጥብ። እንደ ውሸትና ሐሜት ከመሳሰሉ ሃራምና አስቀያሚ ንግግሮች ምላስህንም ቆጥብ። ሐሜት ሲባል ሙስሊም ወንድምህን በሚጠላውና ባለበት ነገር ያለ ሸሪዓዊ ፍቃድ በሌለበት ቦታ ማውሳት ነው።* እንዲሁም ከአፀያፊ ነገሮች፣ ከጥል፣ ከመዘጋጋትና ከፋይዳ ቢስ ክርክሮችም ተቆጠብ።

*روى البخاري ومسلم من حديث أبي هريرة رضي الله عنهما عن الرسول الله صلى الله عليه وسلم قال:*
*إنما الصيام جنة فإذا كان أحدكم صائما فلا يرفث ولا يجهل وإن امرؤ قاتله أو شاتمه فليقل إني صائم إني صائم)*
#ትርጉም
ቡኻሪይና ሙስሊም ከአቡ ሁረይራ ሀዲስ እንደዘገቡት #ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል።
«ፆም እርግጥ መከላከያ ነው። አንዳቹህ የፆማቹህ ከሆነ አፀያፊ ነገር እንዳይፈፅም ፣የመሀይማን ንግግርም አይናገር፣ አንድ ሰው ቢጋደለውም ፣ቢሰድበውም እኔ ፆመኛ ነኝ ፣እኔ ፆመኛ ነኝ ይበል። »

ጆሮአችንንም ቢሆን መስማቱ ሃራም ከሆኑ ነገራቶች በሙሉ መቆጠብ አለብን።

እንደ እጅና እግር ያሉ የሰውነት ክፍለ አካሎችንም ከጥፋት፣ከሀጢያትና ፣ከተጠሉ ነገሮች መቆጠብ አለብን።
إن شاء الله
#ክፍል_ስምንት_ይቀጥላል ......

@abubekersidik 👈
25ኛ የተራዊህን ለይል☞ የዛሬውን ተራዊህ ለአሏህ ብሎ የሰገደ ሰው አሏህ የቀብርን ቅጣት ያነሳለታል

ሼር ማድረግ አይርሱ
👇👇👇👇👇👇
@abubekersidik
➣ዛሬ የመጨረሻው ጁምኣ ሰለሆነ ሁላችንም ረመዳን ስላሳለፍን ዱአ በማድረግ አንርሳ ጁሙዓ ነው ፤ ሰለዋት እናብዛ

🔻የአላህ መልእክተኛ - ﷺ - እንዲህ ይላሉ ፦ [ በኔ ላይ አንድ ሰለዋትን ያወረደ ሰው ፤ አላህ በሱ ላይ አስር ሰለዋትን ያወርድበታል። ]
💌. (ሙስሊም ዘግቦታል).
____
اللهم صل على محمد وعلى آل محمد كما صليت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد، اللهم بارك على محمد وعلى آل محمد كما باركت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد.
#ሼር
የረመዷን የመጨረሻው ጁምዐ!🥺

አሏህ ሆይ በረመዳን ከተጠቀሙት አድርገን!🤲

#መልካም_ጁምዐ #በዱዐ_ተበራቱ!
#የፆም_ህግጋት

#ክፍል_ስምንት


4⃣👉 ቸርነትን ማብዛት ፣ ዘመድን መጠየቅ ፣ቁርአንን በብዛት መቅራት ይወደዳል።
*عن ابن عمر أن النبي -صلى الله عليه وسلم-كان يعتكف في العشر الأواخر من رمضان* رواه مسلم

#ትርጉም፦ "ኢብን ዑመር እንዳወሩት #ነብያችን ﷺ በረመዷን" የመጨረሻው አስርቱ ቀናት ኢዕቲካፍ(በመስጊድ ውስጥ መቆየት) ያደርጉ ነበር።" ሙስሊም ዘግበውታል።

5⃣👉ጊዜውን በመፆም ያሳለፈ ምእመናንን ማስፈጠርም ይወደዳል።

#ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፦

*من فطر صائما كان له مثل أجره 1غيرأنه لا ينقص من أجر الصائم شيء* رواه الترمذي وقال حديث حسن صحيح.

#ትርጉም፦ "የፆመን ሰው ያስፈጠረ የሱን መሳይ አጅር ይኖረዋል፣ ከሚፆመውም አጅር ምንም ሳይቀነስ"ቲርሚዚይ ዘግበውታል ሀዲሱም ሶሒህ ነው ብለውታል።

የሐዲሱ ትርጉም እንደ ሚያመላክተው ለሚያስፈጥረው ሰው ትልቅ አጅር እንደሚኖረው ነው።ይኸውም የፆመውን ሰው አጅር የሚመስል ማግኘቱ ሲሆን በሁሉም ረገድ የሱን አጅር ያክል ያገኛል ማለት ግን አይደለም። ለዚህም ማብራሪያ #ነብያችን ﷺ በሌላ ሐዲስ እንዲህ ብለዋል ፦

"من قرأ قل هو الله أحد. فكأنما قرأ ثلث القرآن"

#ትርጉም
ሱረቱ አል ኢኽላስን አንድ ጊዜ
የቀራ ሰው የቁርአንን አንድ ሶስተኛ እንደቀራ ይታይለታል።

ይህም ማለት የቁርአንን 1/3 ቀርቶ የሚሰጠውን የሚመስል አጅር ይሰጠዋል ማለት ነው።

6⃣👉በአንድ ሰው ሲሰደብ አቻ መልስ በመስጠት ሳይሆን "እኔ ፆመኛ ነኝ ፣እኔ ፆመኛ ነኝ" የሚል ምላሽ መስጠቱ ይወደዳል።*
إن شاء الله
#ክፍል_ዘጠኝ_ይቀጥላል ........

@abubekersidik 🌹
#የፆም_ህግጋት

#ክፍል_ዘጠኝ

#ልንፆማቸው_ክልክል_የሚሆኑብን_ቀናቶች

1⃣👉 የዒድ አል-ፈጥር ዕለት (ሸዋል 1)
2⃣👉የዒድ አል-አድሀ አረፋ ዕለት
3⃣👉አያመ ተሽሪቅ(ሶስቱ የተሽሪቅ ቀናት)
(ዒድ አልአድሀ አረፋን ተከትለው የሚመጡ 3
ቀናት)
4⃣👉 የውመ ሸክ(የጥርጣሬ ዕለት)*

በነዚህ ቀናት መፆም ክልክል ነው።

የጥርጣሬ ዕለት ሲባል የሸዕባን 30ኛ ቀን ሆኖ በንግግራቸው ፆም መግባቱ የማይረጋገጥባቸው ሰዎች ማለትም ወንጀልን እንደሚያበዛ ሙስሊም (ፋሲቅ) ፣ሴትና ህፃናትን የመሰሉ የረመዷንን ጨረቃ አይተናል ቢሉ ንግግራቸውን መሰረት በማድረግ ጨረቃ ታይታለች እና ፁሙ ስለማይባል ይችን ዕለት መፆም ክልክል ነው። #ነብዩ ﷺ ይችን ቀን መፆምን ከልክለዋል።
*"لا تقدموا رمضان بيوم أو يومين صوموا لرؤيته وأفطروا لرؤيته فإن غم عليكم فأكملوا عدة شعبان ثلاثين يوما "* رواه البخاري

#ትርጉም ፦ "ረመዷንን በአንድ ቀን ወይም በሁለት ቀን አታስቀድሙ ፣ ጨረቃን ያያቹህ እንደሆነ (በሸዕባን 29 ማታ ላይ) ፁሙ ፣ጨረቃን አይታችሁ እንደሆነም(በረመዷን 29 ማታ) አፍጥሩ ፣ ደመና ከሆነባቹሁ (ጨረቃ ካልታያችሁ) የሸዕባንን ወር 30 ሙሉ" 📚ቡኻሪይ ዘግበዉታል

#እንደዚሁም
5⃣👉የሸዕባን ወር የመጨረሻውን አጋማሽ
መፆም አይቻልም።* ከእርሱ በፊት ከተጀመረ
ፆም ጋር የሚቀጥል ካልሆነ በስተቀር
ወይም ቀዷእ ወይም የነዝር ፆም ወይም
ያስለመደው ፆም" ከሆነ(ለምሳሌ ሰኞ እና
ሀሙስ) ከሆነ ግን መፆም ይቻላል።

የሸዕባንን 15ኛ ቀን መፆም ሱና ነው። #ነብያችን ﷺ ቀኗን በፆም ለይሏን በዒባዳ አሳልፏት ብለውናል።

#እንደዚሁም ከሸዋል ወር ውስጥ 6 ቀን መፆም ሱና ነው። ከዒድ ቀን በኋላ በተከታታይ ማድረጉ ይወደዳል። ቢፈራረቅም ሱናው ይገኛል።

#አሏህ سبحانه وتعالى ኸይሩን ሁሉ ይወፍቀን🙏🙏🙏
أمين اللهم أمين يارب العالمين

#ሼር በማፍረግ የአጅሩ ተካፋይ ሁኑ!

@abubekersidik 👈
Forwarded from Deleted Account
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
2024/11/16 13:49:05
Back to Top
HTML Embed Code: