Telegram Web Link
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
ዲን ማለት መልካም ሥነምግባር ነው። በመልካም ሥነምግባር የበለጠህ በዲን በለጠህ።
ጥሩ ፀባይ ሳይኖርህ ጥሩ ዲን አለኝ ማለት አትችልም።
ኢስላም መጥፎ ባህሪን ይሞርዳል፣ የተበላሸዉን ያስተካክላል።

@hebre_muslim

JOIN
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
ለመጀመሪያ ጊዜ ፍቅር ሲይዝህ የተሰማህ ልዩ ስሜት፣ የመኖር ጉጉት እና እሷን የራስህ ለማድረግ የነበረህን ጥልቅ ፍላጎት አስበው እስኪ....እርግጠኛ ነኝ የሆነ ውርር የሚየደርግ ደስታ እንደነበረው።

አየህ አሁንም እየኖርከው ያለውን ኑሮ የምታፈቅራትን ሴት አግኝተህ እንደመኖር ብታጣጥመው እንዳንተ በዚህ ምድር ደስተኛ አይኖርም። ወዳጄ አሁን ያለህበት ለመድረስ እኮ ብዙ ዋጋ ከፍለሀል፤ እመነኝ በየደቂቃው እጅህ ባለው ነገር እስከ ጥግ መደሰት አለብህ

ᴊᴏɪɴ ᴜs @hebre_muslim
@hebre_muslim
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
ዋጋ የምትከፍለው መጀመሪያ ላይ ነው፤ ጠዋት መነሳቱ፣ ስፖርት መስራቱ፣ ማንበቡ ማጥናቱ፣ ገንዘብ ማስቀመጡ ሌላውም ነገር የሚያስቸግርህ ስትጀምረው ነው። አንተ ጀምረው አዲሱ ማንነትህ ሲለምደው አቁም ብትባል እንኳን አታቆምም። ወዳጄ ጣዕሙን የምታውቀው ስትቀምሰው ብቻ ነው፤ ስለዚህ ለውጡን ቶሎ ጀምረው!


ᴊᴏɪɴ ᴜs @hebre_muslim
@hebre_muslim
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
በዚህ አለም ጠይቆ ያላገኘ ዘርግቶ ያልዘገነ የለም፤ የምትጠይቀውን ሁሉ ማግኘት ይገባሀል! ፈጣሪ ሁሉ የሞላው ሁሉ የተረፈው ሆኖ አንተ ጠይቀኸው የሚከለክልህ ነገር የለም!

ወዳጄ መጀመሪያ የምትፈልገውን አጥብቀህ መጠየቀህን እርግጠኛ ሁን....ከዛ ግን የምትፈልገው ካልተሰጠህ ጊዜው ስላልደረሰ ወይ የሚገጥምህን መጦፎ ነገሮች በ መልካም ሊቀይርልህ አልያም ደግሞ ከዛ የተሻለ ነገር ፈጣሪ ሊሰጥህ ስለሆነ ነው!


@hebre_muslim
@hebre_muslim
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
የሚያስገርም ለውጥ የምትፈልግ ከሆነ አይንህ ከገጠመህ ችግር ትልቀት ላይ አንሳውና የ #አላህን_ታላቅነት_አስብ፤ ከዛ አንተን መቼም እንደማይተውህ እመን!

ይሄን ስታደርግ የሚያቆምህ ነገር የለም! አሁን እስኪ ንገረኝ የትኛው ችግር ነው ካንተ አቅም በላይ የሆነው?!

@hebre_muslim
@hebre_muslim
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
የነብዩን መውሊድ (የልደት በአል ) ማክበር
➪➪➧➪➪➧➪➪➧➭➪➧➪➪➧➪➪
ክፍል ➊
እነዚያ የሚከሰቱ የሆኑት በአብዛኛዎቹ መውሊድ ላይ በውስጣቸው ከሚጠሉ ነገራቶች፣ከአዲስ መጤ(ከቢድአ)፣ከሙሓለፋዎች (ሸሪአው ከሚከለክላቸው) ክልክላቶች አይከለከሉም ለዚህም ሲባል ከመውሊድ እና ከመውሊድ ባልተቤቶች መራቅ ይገባናል።
መውሊድ ማክበር በመሰረቱ ነብያችን አልሰሩትም፣ሶሃቦችም፣ታቢዕዮችም፣አኢመቱል
አርበዓ (ኢማሙ ሃኒፋ፣ኢማሙ ሻፊዕይ፣ኢማሙ
ማሊክ፣ወኢማሙ አህመድ) ከእነሱም ውጪ በላጭ ከሆኑት የክፍለ~ዘመን ኡለሞችም አልሰሩትም፤ስሩም ብለው አላዘዙም አክብሩት
የሚልም የተደነገገ ማስረጃ የለም።
አብዛኞቹ የመውሊድ ባልተቤቶች ሽርክ ውሰጥ
የሚወድቁት ይህን ባሉ ጊዜ ነው።
➦አንቱ ነቢ እርዱን፣መደድን(ጭማሪን)ስጡን፤

➦አንቱ መልዕክተኛ ሆይ መደገፊያ እና መጠጊያ
ባንቱ ብቻ ነው፤
➦ነቢ ሆይ ችግራችንን ከኛ ግለፁልን (አባሩልን)፤

➦አንቱ ነቢ ሆይ ችግር አያቅህም ችግር ተብዬው
የሚበተን(የሚሸሽ ) ቢሆን እንጂ እያሉ ነብያችንን
በዚህ መልኩ እናመሰግቸዋለን እያሉ በእነሱ ላይ
ድንበር ያልፋሉ በማማመስገንም ስም ቢደዓ ውስጥ ሽርኪያት ውስጥ ይዘፈቃሉ ።
➦ነብያችን ﷺ እነዚህን የሽርክ ስንኞቻቸውን ቢሰሙ ኖሮ የሽርክ ስንኞቻቸውንም ሆነ መውሊድ
ተብዬውን ሽርከል አክበር (ከትልቁ ሽርክ) ነው ብለው በፈረዱ ነበር፦ምክንያቱም
➦ሊረዳንም የሚችለው፣
➦ችግርንም ከኛ የሚገፈትር፣
➦መደድን (ጭማሪን)የሚሰጠን፣
➦መጠጊያ ወይም መደገፊያ የሚሆነን ብቸኛ
የሆነው የአለማቱ ጌታ አላህ ሱብሃነ ወተአላ ብቻ እና ብቻ ስለሆነ ነው።
➦ከቁርአንም ለዚህ ማስረጃ አለን፦

أَمَّن يُجِيبُ الْمُضْطَرَّ إِذَا دَعَاهُ وَيَكْشِفُ السُّوءَ

(ሱረቱ አል-ነምል - 62)
ያ ችግረኛን በለመነው ጊዜ የሚቀበል፣ መከራንም የሚያስወግድ ማነው
➦አላህ ሱብሃነ ወተአላ መልዕክተኛወን ነብያችንን ﷺ ለሰዎች እንዲህ እንዲሉ አዟቸዋል፦

قُلْ إِنِّي لَا أَمْلِكُ لَكُمْ ضَرًّا وَلَا رَشَدًا

(አል-ጂን - 21)
«እኔ ለእናንተ ጉዳትንም ጥቅምን አልችልም» በላቸው፡፡
➦ከሃዲስም ማስረጃ አለን፦
ነብያችን ﷺ እንዲህ አሉ "በጠየቅህ ጊዜ አላህን
ብቻ ጠይቅ፤መታገዝም በፈለግህ ጊዜ በአላህ ብቻ ታገዝ"
[ ኢማሙ ቲርሚዝይ ዘግበውታል]

ምንጭ 📚📚📚[መንሃጁ ፊርቀቱ
ናጂያ
ወጧኢፈቱል መንሱራህ]

ክፍል➋ .........በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል !!!

🥀 https://www.tg-me.com/hebre_muslim 🥀
🥀 https://www.tg-me.com/hebre_muslim 🥀
🥀 https://www.tg-me.com/hebre_muslim 🥀
🥀 https://www.tg-me.com/hebre_muslim 🥀
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
[የነብዩ መውሊድ( የልደት በዓል) ማክበር]
➪➺➪➺➪➺➪➺➪➺➪➺➪➺➪

(ተከታታይ ዳሰሳ በአቡ የህያ)

╔════ ❁✿❁ ════╗
↪️ ክ ፍ ል ሁ ለ ት ↩️ ╚════ ❁✿❁ ════╝

ክፍል አንድን ለማግኘት ↙️↙️↙️
➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
https://www.tg-me.com/hebre_muslim

➦በክፍል ሁለት ደግሞ የምንመለከተው በመወሊዶች ውስጥ ያሉትን ቢድዕይ ተግባር ይሆናል።
አብዛኛዎቹን መውሊዶች ስንመለከት በውስጣቸው ➪ድንበር ማለፍ
➪ነቢን ﷺ በማወደስ ላይ ጭማሪን ይጨምራሉ( ከመጠን በላይ ያልፋሉ)
➺ከዚህ አይነቱ ተግባር ደግሞ ነብያችን ﷺ በንግግራቸው ከልክለውናል ፦ከፍ ከፍ አታድርጉኝ
ክርስቲያኖች የመሬምን ልጅ ኢሳ አለይሂሰላምን ከፍ ከፍ እንደሚያደርጉት እኔ እኮ የአላህ ባሪያ ነኝ ለዚህም ሲባል እንዲህ በሉ አሉን የአላህ ባሪያ እና መልዕክተኛ ነው በሉ።

[ ቡኻሪ ዘግበውታል ]

➦ሸኽ ሙሀመድ ቢን ጀሚል ዘይኑ የዚህ የፊርቀቱ ናጂያ መፅሐፍ ፀሐፊ አላህ ይማራቸውና
እንዲህ ይሉናል፦በአሩሲ መውሊድ እና ከዚህም ውጪ ያሉ መውሊዶችን በውስጣቸው ስላለው
ቢድአ ሲያወሱ ፦

➦አላህ ሱብሃነ ወተአላ ነቢ ሙሀመድ ﷺ ከእሱ
ከሆነ ኑር ፈጠራቸው ከነቢ ﷺ ኑር ሁሉንም ነገራቶች ፈጠረ ብለዉ ይቀጥፋሉ ይሉናል።
➦ቁርአን ደግሞ የእነሱን ንግግር አሰተባባይ ሆኖ እንዲህ ይላል፦

قُلْ إِنَّمَا أَنَا بَشَرٌ مِّثْلُكُمْ يُوحَىٰ إِلَيَّ أَنَّمَا إِلَـٰهُكُمْ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ ۖ

(ሱረቱ አል ከህፍ፥ - 110)
«እኔ አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው፤ ማለት ወደኔ ወህይ የሚወረድልኝ ቢጤያችሁ ሰው ብቻ ነኝ።
➦ስለዚህ እውነታው ግን ነቢያችን ﷺ ከአላህ
ሱብሃነ ወተአላ ከሆነ ኑር ሳይሆን የተፈጠሩት ከእናታቸው አሚናት እና ከአባታቸው አብደላህ ነው።ነብያችንም የእኛን አምሳያ ሰዉ ናቸዉ ነገር ግን እሳቸው ከእኛ ይለያሉ በምን ይለያሉ ካልን ለእሳቸው ወህይ ይወርድላቸዉ ነበር (ከአላህ ሱብሃነ ወተአላ የመጣ የሆነ) ነገር ግን እነዚህ የመውሊድ ባልተቤቶች በመውሊዳቸው ውስጥ እንዲህ ይላሉ
➦አላህ ሱብሃነ ወተአላ አለምን ለነብያችን ﷺ
ሲል ፈጠረ ይላሉ ፦ነገር ግን አላህ ሱብሃነ ወተአላ
አለምን የፈጠረበት አላማ ለተውሒድ እንጂ
ለነብዩ ﷺ አይደለም ቁርአንም የእነሱን ንግግር
በዚህ መልኩ ያስተባብላል ፦

وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ

(ሱረቱ አል-ዛሪያት - 56)
አጋንትምና ሰውንም ሊገዙኝ እንጅ ለሌላ አላማ አልፈጠርኳቸውም፡፡
በነገራችን ላይ ጉድ ተዘርዝሮ አያልቅም ለምሳሌ ፦ ክርስቲያኖች የነብዮሏህ ኢሳን አለይሂሰላም መወለድ አስመልክቶ መውሊድ (ልደት) ያከብራሉ፤እንዲሁም የመሪዎቻቸውን
መወለድ ቀን አስመልክቶ መውሊድ(ልደት) ያከብራሉ ፤ግን አንዳንድ ችግር ያለባቸው ሙስሊሞችም ደግሞ ይህንን ቢድዕይ
የሆነን ተግባር ከእነሱ ኮፒ አድርገው የነብዮን ﷺ
እና የመሪዎቻቸውን መወለድ ቀን አስመልክቶ
መውሊድ(ልደት) ማክበር ጀመሩ።ግን መሆን የነበረበት ከእነሱ ተቃራኒ መሆን ነው ።

ነብያችን ﷺ ደግሞ በንግግራቸው አሰጠንቃቂ ህነው እንዲህ ይላሉ፦
➦በህዝቦች ማለትም በክርስቲያኖች፤
በየሁዳዎች ........ወዘተ የተመሳሰለ እሱ
የተመሳሰለው ሰውዬ ከእነሱ ነው።

➺በአጭር ቃል ይህ ማለት ደግሞ ሰውዬው ከእስልምና ወጣ ማለት ነው።

[ ኢማሙ አቡ ዳውድ ወኢማሙ አህመድ
ዘግበውታል ]

አንድነት በተወሒድ ብቻ ሆኖ ሳለ አንዱ ይመጣና ምን ይልሃል መውሊድ አይለያየንም ይልሃል፦ስለዚህ መውሊድ ድብን ያለ ቢድዐ ስለሆነ በመውሊድ ላይ አንድነት የሚባል የለም ለዚህም ሲባል ከመውሊድ እና
ከመውሊድ ባልተቤቶች መራቅ እና መጠንቀቅ ይገባናል!!!!!

ምንጭ 📚📚📚[መንሃጁ ፊርቀቱ
ናጂያ
ወጧኢፈቱል መንሱራህ]


ክፍል➌ .........በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል !!!

➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
https://www.tg-me.com/hebre_muslim
https://www.tg-me.com/hebre_muslim
https://www.tg-me.com/hebre_muslim
https://www.tg-me.com/hebre_muslim
➹➹➹➹➹➹➹➹➹➹➹➹➹➹➹
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
የነብዩ መውሊድ( የልደት በዓል) ማክበር]
➪➺➪➺➪➺➪➺➪➺➪➺➪➺➪

(ተከታታይ ዳሰሳ በአቡ የህያ)

╔════ ❁✿❁ ════╗
↪️ ክ ፍ ል ሶ ስ ት↩️ ╚════ ❁✿❁ ════╝

ክፍል አንድን ለማግኘት ↙️↙️↙️
➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
https://www.tg-me.com/hebre_muslim

➦በክፍል ሶስት ደግሞ የምንመለከተው የመውሊድ ጥቅመ ቢስነት እና ጉዳቱ በሚል ይሆናል።
➦እሺ ወደ ጉዳዮ ስገባ እንግዲህ በአብዛኛዎቹ መውሊዶች ላይ ስንመለከት የሴት እና የወንድ መደባለቅ አለ እስልምናችን ደግሞ ወንድ እና ሴት ከመደባለቅ ይከለክለናል ፦ስለዚህ እዚህ ጋር ምን
እንገነዘባለን መውሊድ ሸሪአችንን የሚቃረን ቢድዕይ ተግባር እንጂ ሸሪአችንን የሚያጠነክር አይደለም ።
➦ከዚህም ውጪ ደግሞ በመውሊድ አማካኝነት ገንዘብ (ሐብት) ይባክናል ይህም ሲባል ለዚህ መውሊድ ተብዬው ቢድዕይ ተግባር አላማ ማሳኪያ ገንዘብ ፈሰስ ይደረጋል ለምሳሌ ፦
➊ለጌጣጌጦች የሚወጣ ወጪ
➋ለመብራት ወይም ለሶላር የሚወጣ ወጪ
➌ለተለያዩ ጥሩ ጥሩ ነገሮች የሚወጣ ወጪ
➍እንዲሁም ሶደቃ እናወጣለን እያሉ የሚያወጡት
ወጪ ለምሳሌ፦ለበርበሬ፣ለሽሮ፣ለፍየል መግዣ እና ለመሳሰሉት የሚወጣው ከዚህም ውጪ ያሉት ሲቆጠሩ ሚሊዮን ይደርሳሉ ። ታዲያ እንዚህ ጥሩ ጥሩ ገንዘቦች ያለምንም ጥቅም እዚያም
እዚያም ትበተናለች ።
እስልምናችን ደግሞ ያለምንም ምክንያት ወይም ያለምንም ጥቅም ገንዘብን ከማባከን ከልክሎናል። ስለዚህ መውሊድ የሸሪአችንን መመሪያ የሚቃወም ስለሆነ መውሊድን ከማክበር እንጠንቀቅ!!!!!!!!!!!
➦የመውሊድ ጉድ ተዘርዝሮ አያልቅም ይህም ሲባል በመውሊድ ሰበብ (ለመውሊድ የሚያስፈልጉ ነገራቶች) ሲሸምቱ ጊዜያቸውን ያጠፋሉ በከንቱ ያጠፋሉ ሲሸማምቱ ደግሞ ሰአቱ ከማለፉ የተነሳ ሶላትን እስከመተው ያቀርባቸዋል
➦በመውሊዶች መገባደጃ ለይ አንድ ነገር ልምድ
ሆኖ ሁሉም ሰው ይጣዳል፦ ይህም ልምዳቸው ለማመናቸው ሲባል ነው ምኑን ነው የሚያምኑት?ምኑን ነው ልምድ አርገው የያዙት ካላችሁ
ነብዮ ﷺ በመውሊዱ መጨረሻ ለሊት ላይ ይጣዳሉ ብለው ስለሚያስቡ ነው ። ይህም ማለት
ሁሉም የመውሊዱ ተካፋዮቹ ይሰበስቡና ይጣዳሉ አባጋር ተብዬው እና በመውሊዱ ላይ
የተጣዱት ሰዎች ቅጠላቸውን እንደፍየል በጉንጫቸው ያላምጣሉ ከዛም አበጋሩ አየቃሙ ሳለ መብራቱን አጥፉት ይልና ያዛል፤ከዛም ፀጥ ረጭ ብለው ጫታቸውን ያላምጣሉ ከዚያም አባጋሩ መብራቱን አብሩት ብሎ ያዛል ከዚያም
አባጋሩ ተብዬው እንዲህ እያለ ይቀጥፋል ነነብያችን ﷺ ያለፈውንም ወደፊት የሚመጣውንም ወንጀላችንን ምሮናል ይላል እዚህ ጋር ይሰመርበት ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን እንዴት የሞተ ሰው ሊረዳን ይችላል ።
➦የተከበረው የአላህ ቃል የሆነው ቁርአንም የእነሱን ንግግር አሰተባባይ ሆኖ በንግግሩ አንዲህ ይላል

وَمِن وَرَائِهِم بَرْزَخٌ إِلَىٰ يَوْمِ يُبْعَثُونَ

(ሱረቱ አል-ሙእሚኑን - 100)
« ከበስተሗላቸውም እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ ግርዶሽ አለ፡፡

➦ግርዶሽ የተባለው ደግሞ በዱንያ እና በአኼራ መካከል ያለነው ይህም ማለት የሞተ ሰው ወደ ዱንያ መምጣት አይችልም ምክንያቱም ግርዶሽ አለ!!!ታዲያ አበጋር ተብዬው ከየት አምጥቶት ነው ነብያችንን ﷺ መጥተው ያለፈውንም የሚመጣውንም ወንጀል ምሮልን ሄደ የሚለው ይህ ግልፅ የሆነ ቅጥፈት ነው ፦አላህ ሱብሃነ ወተአላ ከቢድአ እና ከቢድአ ባልተቤቶች ይጠብቀን!!!!!!!!!!

ምንጭ 📚📚📚[መንሃጁ ፊርቀቱ
ናጂያ
ወጧኢፈቱል መንሱራህ]
ክፍል➍ .........በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል !!!

🌹 https://www.tg-me.com/hebre_muslim 🌹
🌹 https://www.tg-me.com/hebre_muslim 🌹
🌹 https://www.tg-me.com/hebre_muslim 🌹
🌹 https://www.tg-me.com/hebre_muslim 🌹
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
🔴 የመውሊድ ምግብ መብላት 🔴

🕰 ፈትዋ ቁጥር

📮 #ጥያቄ

⭕️ አንድ ሰው መውሊድ እንደማይቻል እያወቀ ግን በአሉን #ሳያከብር ምግቡን #ቢበላ ምን ችግር አለው⁉️

#መልስ

☑️ እንደሚታወቀው በኢስላም ሸሪዓ #የመውሊድ በአል የሚባል ነገር አንዳንድ መሀይማን #የፈበረኩትና የፈጠሩት እንጅ ከሶሀቦች አንስቶ እስከ ታቢዕዬችም ድረስ #የማይታወቅ መጤ ቢድዓ ነው።ለዛም ነው ይህ ቢድአ ከታየበት ጊዜ #አንስቶ የዲኑ ሊቃውንቶች በቦታና በጊዜ ሳይገደቡ #ሲያጥላሉትና ከሰዎችም ሲያስጠነቅቁት የነበረው።

☑️ ታዲያ በዚህ መጤ በአል ላይ አንዳንዶች ስለ ረሱል - ﷺ - የውልደት #ታሪክና በዛ ዙሪያ የተዘጋጁ #ግጥሞች በማቅረብ ቢያሳልፉትም #አብዛህኞቹ ግን ለዚሁ ቀን ተብሎ #ከደሀውም ጭምር ከተለያዪ ሰዎች #በግዴታነትም ይሁን በውዴታነት ገንዘብ ሰብስበው #ምግብ እያዘጋጁ ለታዳሚው የሚያቀርቡበት ቀን ነው። ታዲያ እዚሁ በአል ላይ በርካታ #ሀራም የሆኑ ነገራቶች (ለምሳሌ የወንድና የሴት መቀላቀል ፣ ዘፈኖችና ጭፈራዎች) ከመፈፀማቸውም በላይ #ሽርክያቶችም ጭምር (ለምሳሌ ነብዪን - ﷺ - ድረሱልን ማለት ፣ መጣራት ፣ #መለመንና ቦታው ላይ #በአካል እንደተሳተፉ ማሰብ እና ሌሎችም) በሰፊው የሚስተናገዱበት በአል ነው።

☑️ ታዲያ በዚህ አይነቱ #የሽርክ_መነሀሪያ ላይ የሚዘጋጀውን ምግብ #መመገብም ሆነ ቦታው ላይ መገኘትና #መሳተፍ ብሎም በየትማውም ስራ ላይ #ማገዝ ቢድዓቸውን ህያው በማድረግ ላይ #እንደማገዝና እንደመተባበር ፣ አሏህንም #ከማመፅ ጭምር ነው። ምክንያቱም አሏህ እንዲህ ይላልና: "በመልካምና አሏህን በመፍራት ተባበሩም ፣ በወንጀልና በጠላትነት ላይ አትተባበሩም" ሱረቱል ማኢዳህ ፣ 4

•┈┈•◈◉❒❒◉◈•┈┈•

🗂 #ምንጭ

📗 አልቢዳያ ወንኒሀያ ለኢብኑ ከሲር ፣ 13 /137

📘 መጅሙዑል ፈታዊ ለኢብኑ ባዝ ፣ 9/74

📕 አልበያን ለአኽጧኢ በዕዱል ኩታብ ለሸይኽ ፈውዛን ፣ 270-268

◈•┈┈·•┈┈·•┈┈·•┈┈·•┈┈·•◈
https://www.tg-me.com/hebre_muslim
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
◽️ ብዙ ነገሮች በምትፈልገው ሰዓት ላይሆኑልህ ወይም ላይሳኩ ይችላሉ፤ አትዘን ወዳጄ ለምን እንደምፈልገው አልሆነም ብለህ ራስህንም አትውቀስ። ለኛ ይመስለናል እንጂ ምንም ነገር ከልኩ አያልፍም፤ አንድ ነገር ግን እወቅ 'ስትፈልገው ያጣኸውን ሲፈልግህ ታገኘዋለህ'።


𝐉𝐨𝐢𝐧 𝐔𝐬 @hebre_muslim
Abdi 𝚢𝚘𝚞𝚛 𝙱𝚎𝚜𝚝 𝙵𝚛𝚒𝚎𝚗𝚍
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
ምንም ነገር ለመስራት ሳይሞክሩ ከተሳካላቸው ይልቅ አንድ ነገር ለማረግ ሞክረው ያልተሳካላቸው ሰዎች ያለጥርጥር የተሻሉ ናቸው ።

ድልን ከመፈለግህ በፊት የማያቋርጥ ጥረትና ፍላጎት ያስፈልጋል ከዛ አትተራጠር የድሉ ባለቤት አንተው ነህ (አንቺው ነሽ)

@hebre_muslim
𝙰bdi - ከፈለክ ትሆናለህ 💪
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
ፌስቡክ የስያሜ ለውጥ ሊያደርግ መሆኑ ተነገረ፡፡

ግዙፉ የማሕበራዊ ትስስር ድረ-ገጽ ኩባንያ ፌስቡክ በቅርቡ የስያሜ ለውጥ ሊያደርግ እንደሚችል የሚጠቁሙ መረጃዎች እየወጡ ነው፡፡

ሬውተርስ የቴክኖሎጂ መረጃ ምንጭ የሆነውን ዘ ቨርጅ ድረ-ገጽ ዋቢ አድርጎ ባወጣው መረጃ ፌስቡክ በቀጣዮቹ ሳምንታት የስያሜ ለውጥ በማድረግ በአዲስ መልክ የመቅረብ እቅድ እንዳለው ተገልጿል፡፡

በአዲሱ ስያሜ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ በጥቅምት ወር መጨረሻ በሚደረገው ዓመታዊ የኩባንያው ጉባኤ ላይ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ማርክ ዙከርበርግ ማብራሪያ እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡

ኩባንያው በአዲስ ስያሜ እና አወቃቀር ሲቀርብ ፌስቡክ፣ ዋትስአፕ፣ ኢንስታግራም ኦኩለስ እና ሌሎች የኩባንያው መተግበሪያና አገልግሎቶች በአዲስ መልክ በሚደራጀው ኩባንያ እንደሚተዳደሩ ይጠበቃል ሲል መረጃው አትቷል፡፡

T.me/hebre_muslim
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
Telegram የምጠቀመው👇
💝አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» 💝የሚለው ነብያዊ ትእዛዝ ለማድረስና ሡናን ለማስፋፋት ነው 🇪🇹🇪🇹

እናም ይህ ከስር ያለውን የ ቦት ሊንክ ለ እናንተ ስናዘጋጅ ታላህ ደስታ ይሰማናል ኢንሻ አላህ ሌሎችም ተጨማሪ የ እውቀት ማበልፀጊያዎችን እናዘጋጃለን
እርሶም ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩልን


www.tg-me.com/hebre_muslimbot
www.tg-me.com/hebre_muslimbot
www.tg-me.com/hebre_muslimbot

JOIN US and Share
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
ይህን ጀባ ብለናል 👇
✿ ያንተ ወንጀል የቱንም ያህል ቢገዝፍ ከ አላህ ምህረት አይበልጥም
✿ አንተ ሺ ጊዜ ድንበር ብታልፍ አላህ አንድም ቀን ቃሉን አያጥፍም
✿የሠው ልጅ እያፈቀርከው ጥሎህ ይሄዳል፣ አላህ ግን እያመፅከው ይጠብቅሃል
✿ የወንጀለኛነት ስሜት ከተሰማህ የኢማን ብርሃን ልብህ ውስጥ አለ ማለት ነው ምክንያቱም ያ ብርሃን ባይኖር የጥፋተኝነት ስሜት ባልተሰማህ ነበር፡፡
✿አንተ ለመመለስ እስካልሰለቸህ ድረስ አላህ ለማርታ ዝግጁ ነው፡፡

✿ ሸይጣን ሁለት ጊዜ እንዲያሸንፍህ አትፍቀድለት አንደኛ ወንጀል አሰርቶ ሁለት በአላህ ላይ ያለህን ተስፋ አስጠፍቶ

💡የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡-

🌴«የጁምዓ ሰላት ገላውን ታጥቦ በጊዜ ወደ ጁምዓ የሄደ፤ ከዚያ በኃላ በሰዎች መካከል ሳይለያይ አላህ የወሰነለትን የሰገደ፤ በዕለቱና በሚቀጥለው ጁምዓ መካከል የሚፈፅመው ኃጢዓቶች ይሰረዝለታል።»

📚 (ቡኻሪ ዘግበውታል)
👉👉 https://www.tg-me.com/hebre_muslim
👉👉 https://www.tg-me.com/hebre_muslim
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
አንድ ጫካ በዛፍ ለመሞላት ብዙ አመት ይጠይቃል፤ ለማውደም ግን አንድ ክብሪት በቂ ናት። የለፋህበትን ነገር ለመናድ አንድ የችኮላ ውሳኔ በቂ ነው፤ ታግሰህ የምትገነባው ነገር ግን አሁን ዋጋ ሊያስከፍልህ ይችላል ውጤቱ ግን አንጀትህን ነው የሚያርስህ። ታገስ ወዳጄ!


T.me/hebre_muslim
T.me/hebre_muslim
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
📚አርባ ሀዲሶች (ከኢማም ነወዊ)
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺»̶̥✽̶┉┉┄┄
الحديث الأول
(አንደኛ ሐዲስ)
┉✽̶»̶̥☀️»̶̥✽̶┉
إنما الأعمال بالنيات
ስራ የተባለ ሁሉ በኒይያህ ነው
┄┄┉┉✽̶»̶̥ 📚»̶̥✽̶┉┉┄┄

عَنْ أَمِيرِ الْمُؤْمِنِينَ أَبِي حَفْصٍ عُمَرَ بْنِ الْخَطَّابِ رضي الله عنه قَالَ: سَمِعْت رَسُولَ الله ﷺ يَقُولُ: " إنَّمَا الْأَعْمَالُ بِالنِّيَّاتِ، وَإِنَّمَا لِكُلِّ امْرِئٍ مَا نَوَى، فَمَنْ كَانَتْ هِجْرَتُهُ إلَى اللَّهِ وَرَسُولِهِ فَهِجْرَتُهُ إلَى اللَّهِ وَرَسُولِهِ، وَمَنْ كَانَتْ هِجْرَتُهُ لِدُنْيَا يُصِيبُهَا أَوْ امْرَأَةٍ يَنْكِحُهَا فَهِجْرَتُهُ إلَى مَا هَاجَرَ إلَيْهِ". رَوَاهُ إِمَامَا الْمُحَدِّثِينَ أَبُو عَبْدِ اللهِ مُحَمَّدُ بنُ إِسْمَاعِيل بن إِبْرَاهِيم بن الْمُغِيرَة بن بَرْدِزبَه الْبُخَارِيُّ الْجُعْفِيُّ، وَأَبُو الْحُسَيْنِ مُسْلِمٌ بنُ الْحَجَّاج بن مُسْلِم الْقُشَيْرِيُّ النَّيْسَابُورِيُّ رَضِيَ اللهُ عَنْهُمَا فِي "صَحِيحَيْهِمَا" اللذِينِ هُمَا أَصَحُّ الْكُتُبِ الْمُصَنَّفَةِ.

የአማኞች መሪ ከሆኑት አቡ ሐፍስ ዑመር ኢብኑል ኸጧብ رضي الله عنه ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ አሉ፦ "ሰራዎች በኒያዎች ነው የሚታሰቡት። ለሁሉም ሰው ደግሞ ያሰበው ነው ያለው። ስደቱ ወደ አላህና ወደ መልእክተኛው የሆነ ሰው ስደቱ ወደ አላህና ወደ መልእክተኛው ነው። ስደቱ ሊያገኛት ወደሚያስባት አዱኛ ወይም ሊያገባት ወዳሰባት ሴት የሆነ ስደቱ ወደተሰደደለት ነው።"

#1(ሐዲሡን) የሙሐዲሦች መሪዎች የሆኑት አቡ ዐብዲላህ ሙሐመድ ኢብኑ ኢስማዒል ኢብኑ ኢብራሂም ኢብኑ ሙጊራ ኢብኑ በርዲዝባህ አልቡኻሪይ አልጁዕፊይ እና አቡል ሑሰይን ሙስሊም ኢብኑል ሐጃጅ ኢብኑ ሙስሊም አልቁሸይሪይ አንነይሳቡሪይ አላህ ይውደድላቸወውና በትክክለኛ መድብሎቻቸው ዘግበውታል። እነዚያ በዘርፉ ከተዘጋጁ መፃሕፍቶች ሁሉ ይበልጥ ትክክለኛ በሆኑት። [ቁ. 1] [ቁ. 1907]
#ሐዲሡ_ያለው_የላቀ_ደረጃ
ሐዲሡ ቡኻሪና ሙስሊም የዘገቡት ትክክለኛ ሐዲሥ ሲሆን ኢስላም ከሚሽከረከርባቸው ዛቢያዎች አንዱ ነው ተብሏል። በርካታ ቀደምት ምሁራን ይሄ ሐዲሥ ከሃይማኖት እውቀት ውስጥ ሲሶውን ይዟል ብለዋል።

ከቀደምት ዑለማዎች ውስጥ ኪታብ ሲፃፍ መጀመሪያ ላይ በዚህ ሐዲሥ ሊከፈት እንደሚገባ የጠቆሙ አሉ። ለዚህም ምክንያቱ ተማሪው ገና ከመነሻው ኒያውን እንዲፈትሽ ማስታወሻ ይሆነዋል በማለት ነው። ታላቁ ሰለፍ ዐብዱርረሕማን ኢብኑ መህዲ ረሒመሁላህ "ኪታብ ባዘጋጅ እያንዳንዱን ርእስ የምጀምረው በዚህ ሐዲሥ ነበር" ብለዋል። [ሸርሑል አርበዒን፣ ነወውይ፡ 6] ኢማሙል ኸጧቢም እንዲሁ "ቀደምት ሸይኾቻችን አንገብጋቢ ከመሆኑ የተነሳ በእያንዳንዱ በሚጀምሩት ዲናዊ ስራ ላይ 'አልአዕማሉ ቢንኒያት' የሚለውን ሐዲሥ ማስቀደምን ይወዱ ነበር" ይላሉ። [ፈትሑል ቀውዩል መቲን፣ 9] ምናልባትም ይህን በማስተዋል ይመስላል ኢማሙል ቡኻሪ ሶሒሓቸውን፣ ዐብዱል ገኒይ አልመቅደሲ "ዑምደቱል አሕካም" የተሰኘ ኪታባቻውን፣ በገዊ ሁለት ስራዎቻቸውን እና ሌሎችም ምሁራን ኪታቦቻቸውን በዚህ ሐዲሥ የከፈቱት።
ኢማም ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ በዚህ ሐዲሥ ላይ ብቻ የምታጠነጥን "ሸርሑ ሐዲሡ ኢንነመል አዕማሉ ቢንኒያት" የተሰኘች አንዲት ቀለል ያለች ኪታብ አለቻቸው።
#ከሐዲሡ_የሚወሰዱ_ቁም_ነገሮች

ስራዎች የሚታሰቡት እንደሚፈፀሙበት እሳቤ
(ኒያ) እንደሆነ
የሰው ልጅ የሚያገኘው ያሰበውን ብቻ እንደሆነ፡
መልካም ካሰበ መልካም፤ መጥፎ ካሰበ መጥፎ፣
ተመሳሳይ ስራዎች በኒያ መለያየት ምክንያት
የተለያዩ ዋጋዎችን ሊያስገኙ እንደሚችሉ፣
አላህን እና መልእክተኛውን ﷺ በማሰብ መልካም
ስራን የሰራ ሰው ዋጋውን እንደማያጣ፣
አለማዊ ጥቅም ብቻ አስቦ ኢስላማዊ ስራን የሰራ
ሰው በዚያ ስራው ያሰበውን ምድራዊ ጥቅም ብቻ
እንጂ ለአኸራው የሚሆን ምንዳ እንደማያገኝ፣
ሰው በኒያው ብቻ ወይ መልካምን ስራ ወይ ደግሞ
ወንጀልን ሊያስመዘግብ እንደሚችል፣
ለኢስላም ብሎ መሰደድ (ሂጅራ) የላቀ ስራ
እንደሆነ (ምሳሌ ተደርጎ መቅረቡ ያለ ምክንያት
አይደለምና። ነብዩ ﷺ "ሂጅራ ቀድሞ ያለን
ወንጀል ያወድማል" ማለታቸው ይታወስ።
[ሙስሊም፡ 192])፣ #2
በትምህርት ላይ ምሳሌ ማቅረብ ይበልጥ
እንደሚያስችል ከሐዲሡ እንማራለን።

#ማሳሰቢያ

1. ኒያ ማለት አንድን ተግባር ለመፈፀም ከልብ የሚታሰብ ቁርጠኛ ውሳኔ እንጂ በምላስ ማነብነብ አይደለም። ስለሆነም በሶላትም ይሁን በፆም ወይም በሌላ ዒባዳ መግቢያ ላይ በምላስ የሚደረጉ ኒያዎች ከነብዩ ﷺ አስተምህሮት ያልተገኙ መሰረት የሌላቸው ፈጠራዎች ናቸው።
2. መጥፎ ስራ በጥሩ ኒያ ጥሩ ሊሆን አይችልም። በቅርቡ ከሚመጣው 5ኛው ሐዲሥ እንደምንረዳው እያንዳንዱ ስራ ዋጋ ይኖረው ዘንድ ከኒያ በተጨማሪ ከመልእክተኛው ﷺ አስተምህሮት መሰረት ያለው ሊሆን ይገባል።
_
#1
በሶሐቦች ዘመን አንድ ሰው "ኡሙ ቀይስ" የምትባልን ሴት ለማግባት ያጫል። እሷ ግን አብሯት ካልተሰደደ በስተቀር ልታገባው ፈቃደኛ እንዳልሆነች ስታሳውቀው ተሰዶ አገባት።

ነብዩ ﷺ ከላይ ያለውን ንግግር የተናገሩት በዚህ ሰው ምክንያት እንደሆነ የገለፁ በርካታ የኋለኛው ዘመን ፀሀፊዎች ቢኖሩም የእውነት እሳቸው የተናገሩት እሱን መነሻ አድርገው መሆን አለመሆኑን የሚያስረግጥ ትክክለኛ ማስረጃ ግን የለም ይላሉ ኢብኑ ረጀብ እና ኢብኑ ሐጀር አላህ ይማራቸውና። [ጃሚዑል ዑሉም፡ 15] [ፈትሑል ባሪ፡ 1/16]

#2
ሂጅራ ለዲን ብሎ መሰደድ በነብዩ ﷺ ዘመን በሁለት መልኩ ተከስቷል። አንዱ፦ ከስጋት ሃገር ወደ ሰላም ሃገር መሰደድ ነው። ይህም ከመካ ወደ ሐበሻ እንዲሁም የመጀመሪያው ወደ መዲና የተደረገው ስደት ነው።

ሁለተኛው፦ ከክህደት ሃገር ወደ ኢስላም ሃገር መሰደድ ነው። ይህም ነብዩ ﷺ መዲና ላይ ከተረጋጉ በኋላ የተደረገው ስደት ነው። [አልአፍናኑ አንነዲያ፡ 9]

የነወውይ አርባ ሐዲሥ ከኢብኑ ረጀብ ጭማሪ

#ኢንሻአላህ_ይቀጥላል............


https://www.tg-me.com/hebre_muslimbot
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
📚{አርባ ሀዲሶች (ከኢማም ነወዊ}
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺»̶̥✽̶┉┉┄┄
الحديث الثاني
ሁለተኛ ሐዲስ
┉✽̶»̶̥☀️»̶̥✽̶┉
مراتب الدين
#የእስልምና_ሃይማኖት_ደረጃዎች
┄┄┉┉✽̶»̶̥ 📚»̶̥✽̶┉┉┄┄
عَنْ عُمَرَ رضي الله عنه أَيْضًا قَالَ: " بَيْنَمَا نَحْنُ جُلُوسٌ عِنْدَ رَسُولِ اللَّهِ ﷺ ذَاتَ يَوْمٍ، إذْ طَلَعَ عَلَيْنَا رَجُلٌ شَدِيدُ بَيَاضِ الثِّيَابِ، شَدِيدُ سَوَادِ الشَّعْرِ، لَا يُرَى أَثَرُ السَّفَرِ، وَلَا يَعْرِفُهُ مِنَّا أَحَدٌ. حَتَّى جَلَسَ إلَى النَّبِيِّ ﷺ . فَأَسْنَدَ رُكْبَتَيْهِ إلَى رُكْبَتَيْهِ، وَوَضَعَ كَفَّيْهِ عَلَى فَخْذَيْهِ، وَقَالَ: يَا مُحَمَّدُ! أَخْبِرْنِي عَنْ الْإِسْلَامِ. فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ ﷺ ፡ الْإِسْلَامُ أَنْ تَشْهَدَ أَنْ لَا إلَهَ إلَّا اللَّهُ وَأَنَّ مُحَمَّدًا رَسُولُ اللَّهِ، وَتُقِيمَ الصَّلَاةَ، وَتُؤْتِيَ الزَّكَاةَ، وَتَصُومَ رَمَضَانَ، وَتَحُجَّ الْبَيْتَ إنْ اسْتَطَعْت إلَيْهِ سَبِيلًا. قَالَ: صَدَقْت . فَعَجِبْنَا لَهُ يَسْأَلُهُ وَيُصَدِّقُهُ! قَالَ: فَأَخْبِرْنِي عَنْ الْإِيمَانِ. قَالَ: أَنْ تُؤْمِنَ بِاَللَّهِ وَمَلَائِكَتِهِ وَكُتُبِهِ وَرُسُلِهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ، وَتُؤْمِنَ بِالْقَدَرِ خَيْرِهِ وَشَرِّهِ. قَالَ: صَدَقْت. قَالَ: فَأَخْبِرْنِي عَنْ الْإِحْسَانِ. قَالَ: أَنْ تَعْبُدَ اللَّهَ كَأَنَّك تَرَاهُ، فَإِنْ لَمْ تَكُنْ تَرَاهُ فَإِنَّهُ يَرَاك. قَالَ: فَأَخْبِرْنِي عَنْ السَّاعَةِ. قَالَ: مَا الْمَسْئُولُ عَنْهَا بِأَعْلَمَ مِنْ السَّائِلِ. قَالَ: فَأَخْبِرْنِي عَنْ أَمَارَاتِهَا؟ قَالَ: أَنْ تَلِدَ الْأَمَةُ رَبَّتَهَا، وَأَنْ تَرَى الْحُفَاةَ الْعُرَاةَ الْعَالَةَ رِعَاءَ الشَّاءِ يَتَطَاوَلُونَ فِي الْبُنْيَانِ. ثُمَّ انْطَلَقَ، فَلَبِثْنَا مَلِيًّا، ثُمَّ قَالَ: يَا عُمَرُ أَتَدْرِي مَنْ السَّائِلُ؟. قَلَتْ: اللَّهُ وَرَسُولُهُ أَعْلَمُ. قَالَ: فَإِنَّهُ جِبْرِيلُ أَتَاكُمْ يُعَلِّمُكُمْ دِينَكُمْ ". رَوَاهُ مُسْلِمٌ
በድጋሜ ከኡመር رضي الله عنه ተይዞ እንዲህ ይላሉ፦ "ከእለታት አንድ ቀን እኛ ከአላህ መልእክተኛ ﷺ ዘንድ ተቀምጠን ሳለን አንድ ልብሱ በጣም የነጣ፣ ፀጉሩ በጣም የጠቆረ ሰው ወደ እኛ መጣ። የጉዞ ምልክት አይታይበትም። ከኛ ደግሞ አንድም አያውቀውም። ከነብዩ ﷺ ዘንድ ተቀመጠ። ጉልበቶቹን ከጉልበቶቻቸው ጋር አስጠጋ። መዳፎቹን ከጭኖቻቸው ላይ አስቀመጠ። #3 ከዚያም፦ 'ሙሐመድ ሆይ! ስለ ኢስላም ንገረኝ' አላቸው። እሳቸውም 'ከአላህ በስተቀር (እውነተኛ) አምላክ እንደሌለ እና ሙሐመድ ደግሞ የአላህ መልእክተኛ እንደሆነ ልትመሰክር፤ ሶላትን ባግባቡ ልትሰግድ፤ ዘካንም ልትሰጥ፤ ረመዳንንም ልትፆም እና ወደ እሱ መንገድን (መጓዝን) ከቻልክ ቤቱን (ከዕባን) ልትጎበኝ ነው' አሉት። 'እውነት አልክ' አላቸው። ስለሱ ተደነቅን። (እንደ አላዋቂ) ይጠይቃቸውና ልክነታቸውን ያረጋግጥላቸዋል። ከዚያም 'ስለ ኢማን ንገረኝ' አላቸው። 'በአላህ፣ በመላእክቱ፣ በመፃህፍቱ፣ በመልእክተኞቹ፣ በመጨረሻው ቀን እና በቀደር ልታምን ነው' አሉት። 'እውነት ብለሃል' አላቸው። ከዚያም 'ስለ ኢሕሳን ደግሞ ንገረኝ' አላቸው። 'አላህን ልክ አንተ እንደምትመለከተው ሆነህ ልታመልከው ነው። የምታየው ባትሆንም እንኳን እሱ ያይሃልና' አሉት። 'እውነት አልክ' አላቸው። ከዚያም 'ስለቂያማ ንገረኝ' አላቸው። 'ተጠያቂው (እኔ) ከጠያቂው (ካንተ) ይበልጥ የሚያውቅ አይደለም' አሉት። 'ስለ ምልክቶቿ ንገረኝ' አላቸው። 'ባሪያ እመቤቷን ልትወልድ ነው። #4 እንዲሁም ጫማ የሌላቸው፣ የታረዙና ድሃ የሆኑ የፍየል እረኞችን በህንፃ (ግንባታ) ሲፎካከሩ ልታያቸው ነው' አሉት።

ከዚያም ሄደ። ረዘም ያለ ጊዜንም ቆየን። ከዚያም 'ዑመር ሆይ! ጠያቂው ማን እንደሆነ ታውቃላችሁን?' አሉ። 'አላህና መልእክተኛው ይበልጥ አዋቂዎች ናቸው' አልኩ። 'ይሄ ጂብሪል ነው። የሃይማኖታችሁን ጉዳይ ሊያስተምራችሁ ነው ወደ እናንተ የመጣው" አሉ። ሙስሊም ዘግበውታል። [10] #5

➲"ሐዲሡ_ያለው_የላቀ_ደረጃ

ኢብኑ ረጀብ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦ "ይሄ ሃይማኖትን በሙሉ የሚተነትን ትልቅ ክብር ያለው ሐዲሥ ነው። ለዚህም ነው ነብዩ ﷺ የኢስላምን ደረጃ፣ የኢማንን ደረጃ እና የኢሕሳንን ደረጃ ከተነተኑ በኋላ 'ይሄ ጂብሪል ነው። ዲናችሁን ሊያስተምራችሁ ነው' የመጣው ማለታቸው። ይህንን ባንድ ላይ ዲን (ሃይማኖት) ሲሉ ጠሩት።" [ጃሚዑል ዑሉም፡ 26-27]
➲"ከሐዲሡ_የሚወሰዱ_ቁም_ነገሮች

✔️" ታላላቆች ዘንድ ስንቀርብ አለባበሳችንና ገፅታችን
የተዋበ ቢሆን እንደሚመረጥ
✔️ "ተማሪ ከመምህሩ ቀረብ ብሎ ቢቀመጥ የተሻለ
እንደሆነ፣
✔️ "ሌሎች እንዲማሩ በማሰብ የሚያውቁትን ነገር
መጠየቅ እንደሚወደድ፤
✔️" የኢስላም ሃይማኖት ኢሕሳን፣ ኢማንና ኢስላም
የሚሉትን ሶስቱን እርከኖች ከነ ምሰሶዎቻቸው
እንደሚያካትት፣
✔️" ከሶስቱ የዲነል ኢስላም እርከኖች ኢሕሳን
እንደሚበልጥ፣ ከዚያም ኢማን ከዚያም ኢስላም
እንደሚከተል፣
✔️" አንድ ሰው የማያውቀውን ከተጠየቀ "አላውቅም"
ማለቱ ነብያዊ ሱንና እንደሆነና ይህን ከማለት
ሊያፍር እንደማይገባ፣
✔️ "አንድ ሰው የማያውቀውን "አላውቅም" ማለቱ
የሚያስመሰግነው እንጂ ደረጃውን የሚያወርደው
እንዳልሆነ፣
✔️" ቂያማ መቼ እንደሆነ የሚያውቀው አላህ ብቻ
እንደሆነ፣
✔️"የስነ-ምግባር መዝቀጥ፣ የወላጆችን ሐቅ መጣስ፣
የገንዝብ መትረፍረፍ፣ በህንፃ መፎካከር፣ በሀብት
መኮፈስ፣... ከቂያማ ምልክቶች ውስጥ
እንደሆኑ፣ #6
✔️" በጥያቄና በመልስ መልኩ ማስተማር ጥሩና
አሳታፊ የሆነ የማስተማር ስልት እንደሆነ፣
✔️" መላእክት ከተፈጠሩበት ቅርፅ ውጭ በሰው ተመስለው መቅረብ እንደሚችሉ።


https://www.tg-me.com/hebre_muslimbot
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
አሜሪካዊው ፓስተርና ፕሮፌሰር ጌራልድ ድሬክስ በቲዮሎጂ የማስተርስ ዲግሪ
ባለቤት ሲሆን በሳይኮሎጂ ደግሞ የፒ ኤች ዲ ባለቤት ነው።
እናም ኢስላምን በመቀበል ሸሐዳውን ከያዘ በኋላ እንዲህ ሲል ምስክርነቱን
ሰጠ ፦ "እነዚያ ሁሉ በሳይኮሎጂ ያነብኳቸው መፅሐፍቶችም ቲዮሪዎችም ሆኑ
ትምህርቶቼ በአላህ ብቻ ለሚያምን አንድ ሙስሊም ጥቅም አልባ ናቸው።
አልሐምዱሊላህ ለዓለማቱ ጌታ አላ ኒዕመተል ኢስላም!ሱብሀነላህ!
American pastor Professor Gerald Drakes
Holds a master's degree in theology,
and a PhD in Psychology,
Who said after his conversion to Islam:
All the books and theories that I have studied in psychology
are of no value to a Muslim who trusts in Allah .
Praise be to Allah Lord of the worlds, for the blessing of Islam.
Subhan Allah
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
ብቻህን አይደለህም ሁሉም ሰው ይፈራል፤ ጥቂቶች ግን ማንም ለማድረግ የፈራውን ጨከን ብለው ያደርጉታል። ባለህበት ቆመህ መቅረት ከፈለክ ምንም አታድርግ፤ ወዳጄ ምርጫህ ራስህን ማሳደግ ከሆነ ለማድረግ ያስፈራህን ወይ ያስጠላህን ነገር ተነስና አድርገው! ያኔ ህይወት ጣዕም ይኖራታል!

ውድ የቻናሌ ቤተሰቦች ሰሞኑን ሀጃ ላይ ስለነበርኩኝ ነው post ማረግ ያልቻልኩት 🙏 ከዚ ቡሀላ እናንተን ሚያነቃቁ ሚያስተምሩ እና ትኩስ መረጃዎችን ይዤላቹ እከሰታለሁ 😉

T.me/hebre_muslim
T.me/hebre_muslim
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
👨‍🦳አንድ ሽማግሌ ወደ አንድ የሞባይል መጠገኛ ሱቅ ሄዱና "ስልኬ ተበላሽቷል ስራልኝ" ብለው ሰጡት። ሞባይል ጠጋኙ ስልኩን አገላብጦ ከፈተሸው በኋላ "አባባ ስልክዎ እኮ ምንም አልሆነም ፤ይሰራል" አላቸው ሽማግሌው አይናቸው እንባ አቀረረና......."ስልኩ ካልተበላሸ...... ልጆቼ የማይደውሉልኝ ለምንድነው? አሉ በደከመ ድምጽ።

ለወላጆቻቸን የምናደርገው ትልቁ ስጦታ ቢኖር በቂ ጊዜ መስጠት ብቻ ነው። የመኖራችን ትርጉም የሚገባን ሲለዩን ነው። እድለኛ ሆነን ወላጆቻችን በህይወት ካሉ እንከባከባቸው። እርቀንም ከሆነ እንደውልላቸው። ይሄን ያህል አመት ጊዜ ሰጥተው እንዳሳደጉን እኛም ጊዜ አንስጣቸው።

ለወላጆቻችን እንዲሁም ለአሳዳጊዎቻችን ፍቅር እና ጊዜ እንስጣቸው !!!

ABDI @hebre_muslimbot
2024/09/21 11:01:09
Back to Top
HTML Embed Code: