Telegram Web Link
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
አሜሪካዊው ፓስተርና ፕሮፌሰር ጌራልድ ድሬክስ በቲዮሎጂ የማስተርስ ዲግሪ
ባለቤት ሲሆን በሳይኮሎጂ ደግሞ የፒ ኤች ዲ ባለቤት ነው።
እናም ኢስላምን በመቀበል ሸሐዳውን ከያዘ በኋላ እንዲህ ሲል ምስክርነቱን
ሰጠ ፦ "እነዚያ ሁሉ በሳይኮሎጂ ያነብኳቸው መፅሐፍቶችም ቲዮሪዎችም ሆኑ
ትምህርቶቼ በአላህ ብቻ ለሚያምን አንድ ሙስሊም ጥቅም አልባ ናቸው።
አልሐምዱሊላህ ለዓለማቱ ጌታ አላ ኒዕመተል ኢስላም!ሱብሀነላህ!
American pastor Professor Gerald Drakes
Holds a master's degree in theology,
and a PhD in Psychology,
Who said after his conversion to Islam:
All the books and theories that I have studied in psychology
are of no value to a Muslim who trusts in Allah .
Praise be to Allah Lord of the worlds, for the blessing of Islam.
Subhan Allah
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
ብቻህን አይደለህም ሁሉም ሰው ይፈራል፤ ጥቂቶች ግን ማንም ለማድረግ የፈራውን ጨከን ብለው ያደርጉታል። ባለህበት ቆመህ መቅረት ከፈለክ ምንም አታድርግ፤ ወዳጄ ምርጫህ ራስህን ማሳደግ ከሆነ ለማድረግ ያስፈራህን ወይ ያስጠላህን ነገር ተነስና አድርገው! ያኔ ህይወት ጣዕም ይኖራታል!

ውድ የቻናሌ ቤተሰቦች ሰሞኑን ሀጃ ላይ ስለነበርኩኝ ነው post ማረግ ያልቻልኩት 🙏 ከዚ ቡሀላ እናንተን ሚያነቃቁ ሚያስተምሩ እና ትኩስ መረጃዎችን ይዤላቹ እከሰታለሁ 😉

T.me/hebre_muslim
T.me/hebre_muslim
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
👨‍🦳አንድ ሽማግሌ ወደ አንድ የሞባይል መጠገኛ ሱቅ ሄዱና "ስልኬ ተበላሽቷል ስራልኝ" ብለው ሰጡት። ሞባይል ጠጋኙ ስልኩን አገላብጦ ከፈተሸው በኋላ "አባባ ስልክዎ እኮ ምንም አልሆነም ፤ይሰራል" አላቸው ሽማግሌው አይናቸው እንባ አቀረረና......."ስልኩ ካልተበላሸ...... ልጆቼ የማይደውሉልኝ ለምንድነው? አሉ በደከመ ድምጽ።

ለወላጆቻቸን የምናደርገው ትልቁ ስጦታ ቢኖር በቂ ጊዜ መስጠት ብቻ ነው። የመኖራችን ትርጉም የሚገባን ሲለዩን ነው። እድለኛ ሆነን ወላጆቻችን በህይወት ካሉ እንከባከባቸው። እርቀንም ከሆነ እንደውልላቸው። ይሄን ያህል አመት ጊዜ ሰጥተው እንዳሳደጉን እኛም ጊዜ አንስጣቸው።

ለወላጆቻችን እንዲሁም ለአሳዳጊዎቻችን ፍቅር እና ጊዜ እንስጣቸው !!!

ABDI @hebre_muslimbot
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
ስለ ሰላተል ጀናዛ
አሰጋገድ 🚿
📂 #የጀናዛ_ሶላትየሶላቱል_ጀናዛ_ማእዘናት

➧➀ - ቅያም - ለሚችል ሰው መቆም፡፡
➧➁ - አ ራቱ ተክቢራዎች፡፡
➧➂- ፋቲሓን መቅራት፡፡

➧➃- በነቢዩ ﷺ ላይ ሶላት ማውረድ፡፡
➧➄ - ለሟቹ ዱዓእ ማድረግ፡፡
➧➅- ቅደም ተከተሉን መጠበቅ፡፡
➧➆ - ተስሊም (ሰላምታ)፡፡

💢#የሶላቱል_ጀናዛ_ሱንናዎች

➧➀- ከቅራኣ በፊት እስትዓዛ ማለት፡፡
➧➁ - ለራሱና ለሙስሊሞች ዱዓእ ማድረግ፡፡
➧➂ - ድምጽ ሳያሰሙ መቅራት፡፡

➧➃ - የሶላቱን ሶፍ ሦስት ረድፍ እንዲሆን ማብዛት፡፡

🕌 ➨የሶላቱል_ጀናዛ_አሰጋገድ

#ሟች #ወንድ ከሆነ ኢማሙ በአስከሬኑ ራስ አቅጣጫ፣
#ሴት ከሆነች ደግሞ በአስከሬኑ መሀል አቅጣጫ ይቆማል፡፡ ተከትለው የሚሰግዱት እንደ ሌላው ሶላት ከኢማሙ ጀርባ ይቆማሉ፡፡ ኢማሙ አራት ተክቢራዎች በሚከተለው ዝርዝር መሰረት ያደርጋል፡-

❶ - የእሕራም ተክቢራ አድርጎ እስትዓዛና በስመላ ካለ በኋላ ፋቲሓን ይቀራል፡፡ የእስትፍታሕ ዱዓእ ግን አይደረግም፡፡

❷ - ሁለተኛውን ተክቢራ አድርጎ በመደበኛው ሶላት የመጨረሻው ተሸሁድ የሚደረገውን ዓይነት ሶላት በነቢዩ ﷺ ላይ ያወርዳል፡፡

➌ - ሦስተኛውን ተክቢራ ካለ በኋላ ለሟቹ ለራሱና ለሙስሊሞች ዱዓእ ያደርጋል፡፡

#ከዱዓእ_ዓይነቶች_የሚከተለውን_እናገኛለን፡-

‹‹አልሏሁም’መ እግፍርለሁ ወርሐምሁ፣ወዓፍህ ወዕፉ ዐንሁ፣ወአክሪም ኑዙለሁ፤ወወስ’ሲዕ ሙድኸለሁ፤ወግሲልሁ ብልማእ ወሥ’ሠልጅ ወልበረድ፤ወነቅ’ቂህ ምነልኸጣያ ከማ ነቅ’ቀይተ አሥ’ሠውበል አብየደ ምነድ’ደነስ፤ወአብድልሁ ዳረን ኸይረን ምን ዳሪሂ፣ወአህለን ኸይረን ምን አህሊሂ፤ወዘውጀን ኸይረን ምን ዘውጅህ፤ወአድኽልሁ አልጀን’ነተ ወአዕዝሁ ምን ዐዛበል ቀብር ወምን ዐዛብ አን’ናር፡፡››

#ትርጉሙ፡-
‹‹አላህ ሆይ! ምሕረት አድርግለት፤እዘንለትም፡፡ ከቅጣትም አድነው፤ይቅር በለውም፡፡ መስተንግዶውንም አሳምርለት፤ ማረፊያውንም አስፋለት፡፡ ከኃጢአቱ በውኃ በበረዶና በአመዳይ (በረድ) እጠበው፡፡ ነጭ ልብስ ከቆሻሻ እንደሚጠራ ሁሉ ከኃጢአቱ አጥራው፡፡ ከመኖሪያው የተሸለ መኖሪያ፣ከቤተሰቡ የተሻለ ቤተሰብ፣ከሚስቱ የተሸለች ሚስት ቀይርለት፡፡ ወደ ጀነትም አስገባው፤ከመቃብር ውስጥ ስቃይና (ወይም) ከእሳት ቅጣትም ጠብቀው፡፡››
[📚በሙስሊም የተዘገበ] ማለት ነው፡፡

🌂 ሟች ሴት ከሆነች ዱዓኡ ተውላጠ ስሙ በሴቴ ጾታ ይለወጣል፡፡ ሟች ሕጻን ወይም ጭንጋፍ ከሆነ ‹‹አልሏሁም’መ እጅዐልሁ ዙኽረን ልዋሊደይህ፣ ወፈረጠን፣ወአጅረን፣ወሸፊዐን ሙጃበን››

‹‹አልሏሁም’መ ሰቅ’ቅል ብሂ መዋዚነሁማ፣ወአዕዝም ብሂ ዋጁ ብሷሊሕ ሰለፍልሙእምኒን፣ወጅዐልሁ ፊከፋለት ኢብራሂመ፣ ወቅህብረሕመትከ ዐዛበል ጀሒም፡፡›› ይላል፡፡

#ትርጉሙ ፡-
‹‹አላህ ሆይ! ለወላጆቹ አለኝታ፣(ወደ ጀነት) ቀድሞ የሚጠብቃቸው አጅር፣(አላህ ዘንድ) ተቀባይነት ያለው አማላጅም አድርግላቸው፡፡››
[📙በቡኻሪ የተዘገበ]

[አላህ ሆይ! የመልካም ሥራዎቻቸው ሚዛን ማክበጃም አድርገው፡፡ ምንዳቸውን በርሱ ትልቅ አድርግላቸው ፡፡ ከደጋግ አበው ሙእሚኖች ተርታም አሰልፈው፤በችሮታህም ከገሀነም ሥቃይ ጠብቀው፡፡›› ማለት ነው፡፡

➍ - ከዚያም አራተኛውን ተክቢራ አድርጎ ትንሽ ዝም ይልና ወደ ቀኝ ብቻ ሰላምታ ያደርጋል፣ወይም ሁለት ሰላምታ ያደርጋል!!!
✹••••━━✿✿━━••••✹
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
የቻናላችን አባላት ሊያውቋቸው የሚገቡ ነገሮች | ለጥንቃቄ ___ 🚸  

❗️በቴሌግራም Bitcoin የሚባል ነገር አትሞክሩ | ሰዓታችሁን አታባክኑ
❗️Telegram እና Facebook አካውንት በቀላሉ Hack አይደረግም
❗️Final Corrupt ያደረገ ሚሞሪ አይስተካከልም
❗️Wifi Password በስልክ App ሀክ ይደረጋል ብላችሁ አታስቡ
❗️የሚሞሪ ካርድን የመያዝ አቅም መጨመር አይቻልም | 2GB ወደ 4GB never
❗️ኢትዮጵያ ውስጥ ለጊዜው ነፃ ኢንተርኔት መጠቀም አይቻልም | ቴሌ አንዳንድ ኮንፊገሬሽኖችን Block አርጓቸዋል | ሲሰራ እናሳውቃለን
❗️ቴሌግራም ላይ ያሉ ያለምንም Description የሚለቀቁ አፖችን install አታድርጉ
❗️Online ብር መስራት የምትፈልጉ በመጀመሪያ Verified የሆነ Paypal Account ያስፈልጋችኋል | በWestern Union ምናምን የሚባለው Totally Scam
❗️ብር እንከፍላለን የሚሉ ዌብሳይቶችን ሳታረጋግጡ ጊዜአችሁን አታባክኑ
❗️በቴሌ Package ሲስተም አትጠቀሙ | ከባድ የዘረፋ ሲስተም ነው
❗️በአሁን ሰዓት Bitcoin በቀላሉ ማግኘት አይቻልም | ቢትኮይን ከ Diamond በልጧል
❗️ያገኛችሁትን አፕ ሁሉ ስልካችሁ ላይ install አታድርጉ | Auto Rooter የሆኑ Malicious Applicationኖች እየተበራከቱ ነው!
❗️ይህንን ቻናል Leave አታድርጉ ይጠቅማችኋል😂😎

➤ | @hebre_muslim ➤ |
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
የአላህ ስሞች እና ትርጉማቸው!!!!!
💫💫💫💫💖💫💫💫💫
💞1💫👉🏼 አላህ ፦ አምላክ ።
💞2💫👉🏼 እራህማን ፦ በጣም አዛኝ ።
💞3💫👉🏼 እረሒም ፦ በጣም ሩህ ሩህ ።
💞4💫👉🏼 አል- ወሃቡ ፦ ሰጪ ።
💞5💫👉🏼 አል- ጀዋዱ ፦ ቸር ።
💞6💫👉🏼 አል- ሱቡሁ ፦ ንጹህ ።
💞7💫👉🏼አል -ዋሪሱ ፦ ወራሽ ቀሪ ።
💞8💫👉🏼 አል- ረቡ ፦ ጌታ ።
💞9💫👉🏼 አል- አእላ ፦ ከሁሉ በላይ ።
💞10💫👉🏼አል- ኢላሁ ፦ አምላክ ።
💞11💫👉🏼አል- መሊክ ፦ ንጉስ ።
💞12💫👉🏼አል- ቁዱስ ፦ ከጉድለት ሁሉ የጠራ ።
💞13💫👉🏼አሰላሙ ፦ የሰላም ባለቤት ።
💞14💫👉🏼አል- ሙእሚኑ ፦ ፀጥታን ደህንነትን ሠጪ ።
💞15💫👉🏼አል -ሙሀይሚኑ ፦ ባሮቹን ጠባቂ ።
💞16💫👉🏼አል- አዚዙ ፦ አሸናፊ ።
💞17💫👉🏼አል - ጀባሩ ፦ ሃያል ጠጋኝ ።
💞18💫👉🏼አል - ሙተ ከቢሩ ፦ ኩሩ ።
💞19💫👉🏼አል- ኻሊቁ ፦ ፈጣሪ ።
💞20💫👉🏼አል - ቃዲሩ ፦ ታጋሽ ።
💞21💫👉🏼 አል - ሙሰዊሩ ፦ ላሻው ነገር ያሻውን ቅርስ ሰጭ ።
💞22💫👉🏼አል - አወሉ ፦ ፊት ያለ ።
💞23💫👉🏼አል- አኺሩ ፦ ኅላ ቀር ።
💞24💫👉🏼አል ዟሂሩ ፦ ግልፅ ።
💞25💫👉🏼አል- ባጢኑ ፦ ስውር ።
💞26💫👉🏼አል - ሰሚዑ ፦ ሰሚ ።
💞27💫👉🏼አል - በሲሩ ፦ ተመልካች ።
💞28💫👉🏼አል - መውላ ፦ ወዳጅ/ረዳት ።
💞29💫👉🏼አል - ነስሩ ፦ ረዳት ።
💞30💫👉🏼አል - ዐፍው ፦ ይቅር ባይ ።
💞31💫👉🏼አል- ቀዲሩ ፦ ቻይ ።
💞32💫👉🏼አል- ለጢፍ ፦ ሩህሩህ ።
💞33💫👉🏼አል - ኸቢር ፦ ውስጥ አዋቂ ።
💞34💫👉🏼አል- ዊትሩ ፦ ብቸኛ ።
💞35💫👉🏼አል- ጀሚሉ ፦ መልካም ።
💞36💫👉🏼አል - ሀዩ ፦ አክባሪ/ትሁት ።
💞37💫👉🏼አል - ሲትር ፦ ሸፋኝ ።
💞38💫👉🏼አል - ከቢር ፦ ትልቅ ።
💞39💫👉🏼አል- ሙተአል ፦ የላቀ ።
💞40💫👉🏼አል - ዋሂድ ፦ ብቸኛው ።
💞41💫👉🏼አል - ቀሃሩ ፦ አሸናፊ ።
💞42💫👉🏼አል - ሃቁ ፦ እውነት ።
💞43💫👉🏼አል- አል ሙቢኑ ፦ ሁሉንግልጽ አድራጊ ።
💞44💫👉🏼አል - ቀዊዩ ፦ ብርቱ ።
💞45💫👉🏼አል - መቲኑ ፦ ብርቱ ።
💞46💫👉🏼አል - ሃዩ ፦ ህያው ።
💞47💫👉🏼አል - ቀዩም ፦ ራሱን ቻይ ።
💞48💫👉🏼አል - አልዩ ፦ የበላይ ።
💞49💫👉🏼አል- ዐዚሙ ፦ ታላቅ ።
💞50💫👉🏼አል - ሸኩር ፦ ውላታ መላሽ ።
💞51💫👉🏼አል- ሀሊሙ ፦ ታጋሽ ።
💞52💫👉🏼አል - ዋሲሁ ፦ ችሮታው ሰፊ ።
💞53💫👉🏼አል - አሊሙ ፦ አዋቂ ።
💞54💫👉🏼አል - ተዋቡ ፦ ፀፀትን ተቀባይ ።
💞55💫👉🏼አል - ሀኪሙ ፦ ጥበበኛ ።
💞56💫👉🏼አል - ገንዩ ፦ ሀብታም ።
💞57💫👉🏼አል - ከሪሙ ፦ ቸሩ ።
💞58💫👉🏼አል - አሃዱ ፦ ብቸኛ ።
💞59💫👉🏼አል - ሶመዱ ፦ እሱን አስጠጊ ።
💞60💫👉🏼አል -ቀሪብ ፦ ቅርብ ።
💞61💫👉🏼አል - መጂቡ ፦ ተቀባይ ።
💞62💫👉🏼አል - ገፋሩ ፦ መሀሪ ።
💞63💫👉🏼አል - ውዱዱ ፦ ወዳጅ/ወዳድ ።
💞64💫👉🏼አል - ወልዩ ፦ ውዳጅ ።
💞65💫👉🏼አል - ሐሚዱ ፦ ምስጉን ።
💞66💫👉🏼አል - ሀፊዙ ፦ ጠባቂ ።
💞67💫👉🏼አል - ሙጅድ ፦ ለጋስ ።
💞68💫👉🏼አል - ፈታሑ ፦ የሚከፈት /ድልን አጎናጻፊ ።
💞69💫👉🏼አል- ሸሂዱ ፦ አስቀዳሚ /የሚቀርብ ።
💞70💫👉🏼አል - ሙቀዲሙ ፦ አስቀዳሚ ።
💞71💫👉🏼አል - መአኪሩ ፦ አዘገይ /የሚያርቅ ።
💞72💫👉🏼አል - ሙአኪሩ ፦ የመጨረሻው ቀሪ ጌታ ።
💞73💫👉🏼አል - ሙስዒሩ ፦ ዋጋ አውጪ ።
💞74💫👉🏼አል - ቃቢዱ ፦ ሲሳይን የሚጨብጥ ።
💞75💫👉🏼አል - ባሊፋ ፦ ሲሳይን የሚዘረጋ ።
💞76💫👉🏼አል - ራዚቁ ፦ መጋቢ ።
💞77💫👉🏼አል - ቃሂሩ ፦ አሸናፊ ።
💞78💫👉🏼አል - ሐቁ ፦ በእውነት እውነተኛ ጋታ ።
💞79💫👉🏼አል - ሸኩሩ ፦ አመስጋኝ ።
💞80💫👉🏼አል - መናኑ ፦ ለጋስ /ችሮታውሰፊ /ሰጪ ።
💞81💫👉🏼አል - ቃዲር ፦ ቻይ ።
💞82💫👉🏼ማሊከል ሙልክ ፦ ሹም የዟሂሩ /የባጢ ።
💞83💫👉🏼ዙል ጀላሊ ወልኢክራም ፦ የልቅና/የልግስ ባለቤት ።
💞84💫👉🏼አል- ራዚቁ ፦ መጋቢ ።
💞85💫👉🏼አል - ወኪሉ ፦ ተወካይ ።
💞86💫👉🏼አል- ረቂቡ ፦ ተጠባባቂ ።
💞87💫👉🏼አል - ሙህሲነ ፦ ደግ ሰሪ ።
💞88💫👉🏼አል - ሀሲቡ ፦ ተሳሳቢ /ተቆጣጣሪ ።
💞89💫👉🏼አል - ሻፊ ፦ አዳኝ /ፈዋሽ ።
💞90💫👉🏼አል - ረፊቁ ፦ አዛኝ ።
💞91💫👉🏼አል - ሙዕጢ ፦ ሰጪ ።
💞92💫👉🏼አል - ሙቂቱ ፦ ቻይ ።
💞93💫👉🏼አል - ሠይዱ ፦ የበላይ ።
💞94💫👉🏼አል - ጦይቡ ፦ ጥሩ ።
💞95💫👉🏼አል - ሐከሙ ፦ ዳኛ ።
💞96 . አል - አክረሙ ፦ ሸፋኝ /ጠጋኝ ።
💞97💫👉🏼አል - በሩ ፦ ደግ ሠሪ ።
💞98💫👉🏼አል - ገፋሩ ፦ መሐሪ ።
💞99💫👉🏼አል - ረኡፍ ፦ አዛኝ

🍇 ከሙስሊሞች መሃል የገባውን የጥላቻን የምቀኝነትና የመናናቅን ነቀርሳን በሽታን ከመሀላችን ነቅለ አጥፋልን!!! አርቅልን!!! ያአላህ ያረብ

🍇ያ አላህ በአለማችን ላይ ሙስሊም በመሆናቸው ብቻ እየታሰሩ፣ እየተንገላቱ፣ እየተጨቆኑ ላሉት ሁላ እዝነትህን አውርድልን፣ አውርድላቸው!!!

ያአላህ ያረብ የተሻለ ኑሮን ፈልጎ ሕይወቴን አሻሽላለው፣ ቤተሰቤን እረዳለው ብሎ ከሀገር የተሰደዱትን {የራቁትን} ሁሉ ወደ ቤተሰቦቻቸው በሰላምና በጤና መልሳቸው

እንዲሁም ውድ እና ተናፋቂ የአገራችን ኡስታዟቻችንንም እንዲሁም በአለም ላይ ያሉ አሊሞችን አንተው በያሉበት ጠብቅልን!!! ሰላምና ጤናቸውንም አብዛልን!!! ለሙስሊሙ ኡማ ሉሁ ሰላምና እዝነትህን አውርድልን!!!

🍇አላህ ተውበት ካላረጉ በስተቀር ከማይምረው ወንጀል ~~>ከሽር ክም አላህ ይጠብቀን!!! ይጠብቃቹ!!!

🪐 @hebre_muslim 🪐

🪐 @hebre_muslim 🪐

🪐 @hebre_muslim 🪐
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
📌 ሀይድ ላይ እያለች ግኑኝነት መፈፀም⁉️
#በውስጥ_መስመር_ከተላኩ_ጥያቄዎች

📌ጥያቄ📌
📌 የወር አበባ ላይ ያለች ሴት ከባሏ ጋር #ግኑኝነት መፈፀም ትችላለችን፣ ከነ #ማስረጃው ቢብራራልኝ⁉️

መልስ
#የወር_አበባም ላይ ይሁን #የወሊድ ደም ላይ ያለች ሴት ከዚህ ደም #እስክትጠራ ድረስ ግኑኝነት ማድረግ ፈፅሞ አይፈቀድላትም‼️ ለዚህም አላህ በቁርአኑ እንዲህ ይላል;—

🔵"ስለ #ወር_አበባ ይጠይቁሀል፣ እንዲህም በላቸው፣ እርሱ የተበከለ ነው፣ ሴቶችን በወር አበባ ጊዜ (ከግኑኝነት) #ራቋቸው፣ ንፁህ እስከሚሆኑ ድረስ #አትቅረቧቸው፣ ንፁህ በሆኑም ጊዜ አላህ ባዘዛችሁ ስፍራ ተገናኟቸው፣ አላህ ከ(ሀጢአት) ተመላሾችን ይወዳል፣ ተጥራሪዎችንም ይወዳል።"
⚫️ ሱረቱል በቀራ ፣ 222

📌 በዚህም ወቅት ከሚስቱ ጋር ግኑኝነት ያደረገ ባል ከባድን #ወንጀል ፈፅሟል፣ ወደ አሏህ #ተፀፅቶ ሊመለስ ይገባዋል። አንደንድ ኡለሞችም እንደሚሉት በዚህ ሰው ላይ የአንድ ወይም የግማሽ ዲናር #ከፋራ (ወንጀል ማሳበሻ ቅጣት) አለበት። ሁለቱም አላህን ሊፈሩ ይገባል።

♻️ ምንጭ :— 📚ኢብኑ ባዝ ረሂመሁሏህ ፣ መጅሙዑል ፈታዊ
@abduljilal
https://www.tg-me.com/hebre_muslim
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
#በውስጥ_መስመር_ከተላኩ_ጥያቄዎች

📌አንድ #ህፃን ልጅ #ምግብ ከመመገቡ በፊት #ሽንቱ ይነጅሳል ወይስ አይነጅስም #ከሴትና_ወንድ ምግብ እስኪጀምሩ ሽንታቸዉ የሚነጅሰው ማንኛቸው ናቸው⁉️

መልስ
አብዛህኛው የኡለሞች አቋም #የሰው ሽንት ህፃንም ይሁን አዋቂ ወንድም ይሁን ሴት ጡት ብቻ #የሚጠባም ይሁን #ምግብም የጀመረ ይሁን ሁሉም ሽንቱ #ነጃሳ ነው‼️ ለዚህም ሀዲስ 👇👇👇

⭕️አንድ ጊዜ ኡሙ ቀይስ ቢንት ሚህሶን ምግብ #መብላት_ያልጀመረ ልጇን ወደ ነብዩ (ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም) ይዛው መጥታ በጉያቸው ሲያስቀምጡት ሸናባቸው፣ ከዛም #ውሀ እንዲያመጡላቸው አዘዙና ባያጥቡትም በላዩ ላይ ዉሀውን #አፍስሰውበታል
⚫️ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል

ነገር ግን በዚህ ዙሪያ #የተግራራ ነገር ቢኖሩ #የወንድ ህፃን ልጅ ሽንትን ማጠብ ግዴታ አለመሆኑ ነው። ልክ ከላይኛው ሀዲስ እንደተመለከተው ውሀን በላዩ ላይ #ማፍሰሱ ብቻ በቂ ነው። ለዚህም ሀዲስ 👇

⭕️ሉባባ ቢንቱል ሀሪስ አንዲህ ትላለች:— "አንድ ጊዜ ሑሰይን ቢን ዓሊይ ነብዩ (ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም) ጉያ ውስጥ ሆኖ አያለ ልብሳቸው ላይ #ሸናባቸው። ከዛም ልብስ ልበሱና ሽርጥዎን ስጡኝ #ልጠበው ስላቸው እንዲህ አሉኝ; "የሚታጠበውኮ የህፃን #ሴት ልጅ ነው #የወንድ ልጅ ደግሞ በላዩ ላይ ውሀ #ማፍሰስ ነው።"
⚫️አህመድ፣ አቡ ዳውድና ኢብኑ ማጃህ ዘግበውታል

♻️ማጣቀሻ ምንጭ :— 📚 ሸይኽ ኢብኑ ባዝ ረሂመሁሏህ
@abduljilal
★★★ https://www.tg-me.com/hebre_muslim ★★★
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
ውድና የተከበራችሁ የ ቻናላችን ተከታዩች ስለ ምትከታተሉን ከልብ እያመሰገንን መልካም ምንዳችሁን አላህ ያብዛላችሁ እያልን መጠየቅ የምትፈልጉትን ማንኛውንም አይነት የ #ፈትዋ_ጥያቄ

@hebre_muslim ቻናል ይከታተሉን

ማንኛውም ጥያቄ ለመጠየቅ 👇👇👇👇

@abduljilal ላይ ይላኩልን
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
📌 ጫት መቃም ሀላል ወይስ ሀራም⁉️
#በውስጥ_መስመር_ከተላኩ_ጥያቄዎች
♻️ : ክፍል 91

📌ጥያቄ📌
📌 #ጫት መቃም ብዙ ጊዜ #ሀራም ነው ይባላል ፣ አንዳንዶች ደግሞ #የሚፈቀድ ነው ይላሉ እና የተሻለው የትኛው ነው⁉️

መልስ
በሸሪዓችን #አእምሮን መጀመሪያ ከነበረበት ሁኔታ ትንሽ እንኳን ቢሆን #የሚቀይር ማንኛውም መጠጥና #ምግብ በሸሪዓችን በጥብቅ የተከለከለ ነው። ጫት ደግሞ በተለምዶ እንደሚታወቀውና #በላቦራቶሪ ህክምና ውጤትም እንደተረጋገጠው አእምሮን የሚቀይርና ጎጂ #ንጥረ_ነገር ስላለው በሸሪዓችን በሁለት 2⃣ መልኩ የሚከለከል ይሆናል።

1⃣📌 መጠኑና አይነቱ እንደየሰው ቢለያይም አእምሮን ካለበት ሁኔታ #የሚቀይር መሆኑ #ከአስካሪ ነገራቶች ያስገባዋል።
2⃣📌 #በጤንነት#በገንዘብ#በቤተሰብ እና #በስነ_ልቦና ላይም ጉዳት ስላለው በሸሪዓችን ውስጥ ደግሞ ራስን #መጉዳት ሀራም ስለሆነ የሚከለከል ይሆናል።

♻️ ምንጭ :— 📚ኢብኑ ባዝ ፣ ሸይኽ ፈውዛን ፣ ሸይኽ ሙቅቢልና ከሌሎች ኡለሞች የድምፅ ፈይል የተወሰደ
@abduljilal
https://www.tg-me.com/hebre_muslim
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
ቴሌግራም የክፍያ ማስታወቂያዎችን ለመጀመር በሙከራ ላይ ነኝ ብሏል።

የመልዕክት መለዋወጫ መተግበሪያ የሆነው ቴሌግራም የክፍያ ማስታወቂያ ሥርዓት ለመጀመር በሙከራ ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል። ይህ ሥርዓትም ቢያንስ ከ1000 በላይ ተከታይ ባላቸው ቻናሎች ላይ እንደሚጀመር ነው የገለጸው።

ከዚህ ቀደም የክፍያ ማስታወቂያ ሥርዓት የሌለው ቴሌግራም አሁን ላይ ተጠቃሚዎች ቻናላቸውንና ቡታቸውን በክፍያ እንዲያስተዋውቁ የሚያስችላቸውን አሰራር መዘርጋቱን ነው ይፋ ያደረገው።

የቴሌግራም መስራች እንዲሁም ዋና ስራ አስኪያጅ ፓቬል ዱሮቭ እንደጠቀሰው በሙከራ ላይ የሚገኘው የክፍያ ማስታወቂያ ሥርዓቱ የቴሌግራም ተጠቃሚዎችን የግል መረጃን አይጠቀምም ብሏል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ ማስታወቂያዎቹ በግል እና በቡድን መልዕክት መለዋወጫ ሰሌዳዎች ላይ የማይታዩ መሆናቸውንና በክፍያ የሚቀርቡት ማስታወቂያዎች በቻናሎች ላይ ብቻ እንደሚቀርቡ ገልጿል።

ማስታወቂያ ማስነገር የሚፈልጉ አስተዋዋቂዎች ቻናላቸውን ወይም ቡታቸውን ከ160 ባልበለጡ ፊደላት ገለጻ ማድረግ የሚችሉ ሲሆን በቋንቋ፣ በይዘት እንዲሁም በልዩነት ማስታወቂያው እንዲተላለፍላቸው የሚፈልጉትን ቻናል መርጠው ማስተዋወቅ ይችላሉ ተብሏል።
ቴሌግራም ከቻናል ባለቤቶች ጋር የትርፍ ክፍፍል የማድረግ እቅድ እንዳለውም ያስታወቀ ሲሆን ይህ የሚሆነው ግን መሰረታዊ ወጪዎቹን ከሸፈነ በኋላ እንደሆነ ገልጿል።

@hebre_muslim@Hebre_muslimbot
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد) via @BestApps1bot
ይህ #አማርድ_ፈርኒቸር_ነው
የሚፈልጉትን አይነት የቢሮ እና የቤት እቃዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ እንሠራለን ጥራት እና ጥንካሬ መለያችን ነው ቻናላችንን በመቀላቀል የሚፈልጉትን አይነት ዲዛይን ይምረጡ
#ለበለጠ_መረጃ
በስልክ #ቁ.#0913715785_አማርድ_ፈርኒቸር_ብለው_ይደውሉ
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
😐 ጥረትህን አይቶ ማንም አይገረምም፤ ውጤትህ አሪፍ ከሆነ ሰዎች ያደንቁሀል ካልሆነ ግን ይንቁሀል፤ አየህ ይቺ አለም ውጤትን እንጂ ጥረትን አትሸልምም።

ካቆምክ መውደቅህን አረጋግጠሀል፤ ከቀጠልክ ለማሸነፍ እየተቃረብክ ነው፤ እርግጠኛ የምሆንልህ ግን ይቺ አለም ያከበረቻቸው ሰዎች በሙሉ ጥረታቸውን ያላቆሙት ናቸው! ስለዚህ አናቆምም!💪

@hebre_muslim
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد) via @BestApps1bot
ይህ #አማርድ_ፈርኒቸር_ነው
የሚፈልጉትን አይነት የቢሮ እና የቤት እቃዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ እንሠራለን ጥራት እና ጥንካሬ መለያችን ነው ቻናላችንን በመቀላቀል የሚፈልጉትን አይነት ዲዛይን ይምረጡ
#ለበለጠ_መረጃ
በስልክ #ቁ.#0913715785_አማርድ_ፈርኒቸር_ብለው_ይደውሉ
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
🔴 የሀይድ መከላከያ መጠቀም 🔴

ፈትዋ

📮 #ጥያቄ

📮ረመዳን ፆም ለመፆም ፣ ሀጅ ለማድረግ ወይም ለሌላ ነገር ሲባል ሀይድ እንዳይመጣ የሚያደርግ መድሀኒት መጠቀም ይፈቀዳልን⁉️

#መልስ

በመጀመሪያ ደረጃ ረመዷን ፣ ሀጅም ሆነ ማንኛውም ዒባዳ መስፈርቱ ለተሟላለት #እንጅ ካልተሟላ ግዴታ አይደለም። በዚህም መሰረት ሀይድ ላይ ያለች ሴት ማንኛውም ዒባዳ #ስለማይመለከታት ያንን ዒባዳ በወቅቱ ባለመፈፀሟ #አትጠየቅም። በመሆኑም አሏህ ለሷ ያገራላትን ነገር #ባለመጠቀምና በራሷ ላይ በማጥበቅ #መጨናነቅ የለባትም።

ሆኖም የወርአበባ መፍሰስን #የሚከላከል መድሀኒት መጠቀም ባሏ #አስከፈቀደላት እና በጤናዋ ላይ ገዳት #እስካላስከተለ ድረስ ብትጠቀም ችግር የለውም። ምክንያቱም የወርአበባ መፍሰስ #ተፈጥሮአዊ ኡደት ሲሆን ይህን ኡደት በሆነ ነገር #ስታሰናክለው ጤናዋ ላይ ችግር መፍጠሩ አይቀርም። በዚህም የተነሳ የወር አበባ መምጫው ሊዛባና #በግኑኝነትም ወቅት ችግር ሊያስከትል ይችላል። በመሆኑም እነዚህ ነገራቶች ከሌለ #የሚፈቀድ ሲሆን አለያ ግን የሚጠላ እንደ ሁኔታው ደግሞ የሚከለከል ይሆናል።

•┈┈•◈◉❒❒◉◈•┈┈•

📚 #ምንጭ

📙 መጅሙዑል ፈታዊ ፣ ለኢብኑ ዑሰይሚን ፣ 11/273
📔 ፈታዊ ኢስላሚያህ ፣ ለኢብኑ ባዝ ፣ 2/185

◈•┈┈·•┈┈·•┈┈·•┈┈·•┈┈·•◈
🖋abduljilal
[] 👇 ለሌሎችም ይጋብዙ👇
✒️https://www.tg-me.com/hebre_muslim
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
━━━━━━✦✿✦━━━━━━
አንደሉስ ክፍል 1
━━━━━━✦✿✦━━━━━━


አንደሉስ የአሁኖቹ የስፔንና ፖርቹጋል ድምር ወይም አይቤሪያን ፔኒንሱላን ያጠቃልል ነበር። "አንደሉስ" የሚለውን ስያሜ ያገኘው በአካባቢው የኖሩትን ህዝቦች አውሬነት ለመግለፅ ከእንሊዝኛው "Vandalism" ከሚለው ቃል እንደሆነ ተራኪዎች ይጠቅሳሉ።
አንደሉስ ኢስላም ሳይደርሳት በፊት እጅግ ኋላቀር የነበሩ ህዝቦች ሀገር ነበረች። አምባገነናዊ አስተዳደር የሰፈነበት፣ ድንቁርና ያየለበት፣ ንፅህና የማይታወቅበት (ገላቸውን በዓመት አንዴ ወይም ሁለቴ ብቻ ይታጠቡ እንደነበር ታሪክ አስፍሮታል) ፍፁም ኋላቀር ማህበረሰብ የተከማቸበት የድቅድቅ ጨለማ ሀገር ነበረች። አንዳንድ ማህበረሰቦቿ ደግሞ እንኳንስ መፃፍና ማንበብ ይቅርና ቋንቋ ያልነበራቸው በምልክት ብቻ የሚግባቡ ነበሩ። አንደሉስ ከኢስላማዊው ድል በፊት የመሀይምነት ጥግ ላይ የደረሰች ኋላቀር አህጉር ነበረች። ኢስላም ወደ ስፔን ከመድረሱ ቀደም ብሎ ሮደሪክ የተባለ ሰው በስፔኑን ንጉስ ዊትዛ ላይ መፈንቅለ መንግስት በማድረግ ስልጣኑን ያዘ። ከሙስሊሞች ጋር ፍልሚያ ውስጥ የገባውም ይኸው ሮደሪክ ነበር። ስፔን በጊዜው ሰላም ያልተረጋጋበት አየር ይስፈን እንጅ በወታደራዊ ብቃቱ ብርቱና ኃያል የነበረ ሰራዊት ባለቤት ነች።

★★★ ጉዞ ወደ አንደሉስ ★★★
ሙስሊሞች በ91ዓ.ሒ የሰሜን አፍሪካን ሀገሮች ባጠቃላይ ድል አድርገው ጨርሰዋል። ደዕዋቸውንና ጂሃዳቸውን ለመቀጠል ያላቸው አማራጮች ከሁለት መንገዶች አንዱን መምረጥ ነበር። ወደ ሰሜን ተጉዘው ስፔንና ፖርቹጋል (የጊዜው አንደሉስን) መክፈት፣ አሊያም ጥቂት የሰው ብዛትና ሰፊ መሬት ባለቤት ወደ ሆነው ወደ አፍሪካ በረሀ መዝለቅ ነበር። ሙስሊሞች የጂሃዳቸው ዓላማ ሰፋፊ ግዛቶችን መያዝና የሙስሊሞችን ግዛት ማስፋት አልነበረም፤ ይልቁንስ የአላህን ዲን ለሰዎች ማድረስ እንጂ። ስለዚህ ወደ አፍሪካ በረሀ ከመስመጥ ይልቅ በጣም በርካታ ሰዎች ወደሚገኙበት ወደ ሰሜን መጓዛቸው ፍፁም ትክክለኛ ውሳኔ ነበር።
በጊዜው የሰሜን አፍሪካ ገዢ የነበረው ታላቁ ሙጃሂድ ሙሳ ኢብኑ ኑሰይር ብልህ፣ አስተዋይና አርቆ አሳቢ፣ የተካነ የጦር መሪ ነበር። የሠሜን አፍሪካ ነዋሪዎች የነበሩትን የበርበር ሰዎች እስልምናን በደንብ ካስተማራቸው በኋላ አንደሉስን ለመክፈት ብዙ ሙጃሂዶችን መለመለ። በርበሮቹ ለእስልምና ከነበራቸው ጥልቅ ፍቅር በፍላጎት ሰራዊቱን ይቀላቀሉ ጀመር። ሙሳ ኢብኑ ኑሰይር አንደሉስን የመክፈት ህልሙ ድንገተኛ አልነበረም፤ የቆየ ዓላማ ነበረው። ስለሆነም በወቅቱ ከነበረው ኸሊፋ ወሊድ ኢብኑ ዐብዱል መሊክ ፍቃድ እንዳገኘ ቀጥታ ወደ አንደሉስ ዘመቻ ዝግጅት ገባ። ሙሳ አንደሉስን ለመክፈት የሚያግዱትንና ዘመቻውን ከባድ አድርገው የሚያሰናክሉበትን ነገሮች ሁሉ አንድ በአንድ መፍትሔ መስጠት ጀመረ።
-የመጀመሪያው አቀበት የመርከቦች እጥረት ነበር። ወደ አንደሉስ የሚደረገው ጉዞ ከ13ኪ.ሜ ያላነሰ የባህር ላይ ጉዞ ይኖረዋል። ለዚህም መርከቦችን በብዛት ማምረት ጀመረ።
- ከአንደሉስ በቅርብ ርቀት የምትገኘው ቤልያር ደሴት በአንደሉስ ዘመቻ ወቅት ከጀርባው እንዳታጠቃው ስለሰጋ ደሴቷን በቁጥጥሩ ስር አደረገ።
- ሌላኛው የሙስሊሞች ቁጥር ማነስና የክርስቲያኖች ብዛት ግዝፈት ነበር። ሙሳ ይህን ችግር ለመቅረፍ በርበሮችን ስለ ኢስላም በሰፊው አስተማራቸው። በርበሮችም ኢስላም በልባቸው ሰፈረ። ለጂሃድ ያላቸው ፍቅር አየለ። በዚህም የሰራዊቱ ቁጥር ከፍ አለ።
َ- ሌላኛው አስቸጋሪው አቀበት በአንደሉስ መሻገሪያ መንገድ ላይ ተጋርጣ በዩሊያን ስር የምትገኘው የሰብታ ወደብ ጉዳይ ነበር። ሙስሊሞች ሰብታን ለመቆጣጠር ፍፁም አይችሉም። ሰብታን ካልያዙ ደግሞ አንደሉስ ብሎ ነገር የለም። አስቸጋሪ አቀበት! ከዚህ በተጨማሪ ሙስሊሞች የአንደሉስን ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥና የአየር ንብረት የሚያውቁት ነገር አለመኖር የአንደሉስን መከፈት ጥያቄ ምልክት ውስጥ የሚያስገባ ሌላ አቀበት።
በዚህ መሀል ነበር የአላህ ጣልቃ የገባው። ፍፁም ያልተጠበቀ እርዳታ!
ነገሩ እንዲህ ነው:- የሰብታ ወደብ መሪ የነበረው ዮሊያንና በሮድሪጎ (ሮድሪክ) ስልጣኑን የተቀማው ዊትዛ ወዳጅነትና ጓደኝነት ነበራቸው። ታዲያ ሮድሪጎ ዊትዛን ከስልጣን ላይ ፈንቅሎ በመግደል ስልጣኑን በመያዙ ዮሊያንን አስቆጥጦታል።





________\\\_____________

ለሌሎችም ሼር በማድረግ ተደራሽነቱን እናስፋ

@hebre_muslim
@hebre_muslim
═════════════════
#ኢኽላስ_ታማኝነት_ትጋት_ስኬት
╚═══════════════╝
ምንጭ mahi
━━━━━━✦✿✦━━━━━━
አንደሉስ ክፍል 2
━━━━━━✦✿✦━━━━━━


በተጨማሪም ሮድሪጎ የዊትዛ ከተማን ገንዘብ በሙሉ ከልጆቹ በመመንጠቅ ለግሉ አድርጓል። ከዚህ አልፎ የአንደሉስን ህዝብ የማይችሉትን ግብር በማሸከም ጫንቃቸውን አክብዶታል። እሱ በቤተመንግስቱ ሲንፈላሰስ ህዝቡ በከባድ ድህነትና ችግር ይማቅቃል። ይህን ሁሉ ሀሳብ በአዕምሮው ሲያሰላስል የከረመው ዮሊያን ሮድሪጎን ለመበቀል አቅሙ እንደማይፈቅድ ተረድቷል።
እናም ይህን እቅዱን እንዲፈፅሙለት ከሙስሊሞች ጋር ለመስማማት ወሰነ። ሙሳ ኢብኑ ኑሰይር ከዮሊያን ድርድር ሲቀርብለት ፍፁም አላመነታም። የአላህ እርዳታ እንደሆነ አምኖ በደስታ ተቀበለ። የድርድሩ መስፈርቶች እኚህ ነበሩ።
- የሰብታን ወደብ ለሙስሊሞች ሊፈቅዱና ሊያስረክቡ
- ስለ አንደሉስ አስፈላጊ መረጃዎችን ሊያቀብሉ በምትኩ ሙስሊሞች አንደሉስን ሲከፍቱ የዊትዛን ሙሉ ሀብትና ንብረት እንዲሰጧቸው የሚጠይቅ ነበር።
ሙሳ ኢብኑ ኑሰይር መስፈርቶቹን ያለማንገራገር ተቀበለ። የሙስሊሞች ዓላማ የዊትዛ ወይም የሮድሪክ ገንዘብ አልነበረም። የዮሊያን ንብረትም አይደለም። የሚከፍቱት ሀገር ሀብት አስጨንቋቸው አያውቅም። ሀብት ፍለጋ ቢሆን ኖሮ በወርቅ የታጨቀውን የአፍሪካ መሬት ለምን ብለው ይተው ነበር?
የሙስሊሞች ህልምና ዓላማ ለሰዎች የአላህን ዲን ማስተዋወቅ ከሰዎች ባርነት አላቀው የታላቁ ጌታ አላህ አገልጋይ ማድረግ ነው። ሙሳ ኢብኑ ኑሰይር በፍጥነት ለኸሊፋው ወሊድ ደብዳቤን በመላክ የዘመቻ ፈቃድ ጠየቀ።
ኸሊፋውም ፈቀደለት አያይዞም ያለ ፍተሻና ሙከራ ሰራዊቱን ሁሉ እንዳይልክ አዘዘው። ሙሳ ይህን ጉዳይ እሱም አስቦበት ነበር። ዮሊያን የሚያቀርብለት መረጃ እውነት ይሁን ሀሰት ማን ያውቃል? ስለሆነም ጊዜ ሳያጠፋ ለሙከራና ለፍተሻ ያክል ጦሪፍ ኢብኑ ማሊክ በተባለ በርበራዊ የጦር መሪ የሚመራ አምስት መቶ አባላት ያሉት ብርጌድ ወደ አንደሉስ ላከ።
ጦሪፍም በአራት መርከቦች ተሳፍሮ በረመዷን ወር 91ኛው ዓ.ሒ አንደሉስ ደረሰ።ጦሪፍም በአራት መርከቦች ተሳፍሮ በረመዷን ወር 91ኛው ዓ.ሒ አንደሉስ ደረሰ። የተላከበትን ተልዕኮ በሚገባ በመወጣት ወደ ሙሳ ኢብኑ ኑሰይር በመመለስ ስለአንደሉስ ያጠናቀረውን ጥናት በግሩም ሁኔታ አቀረበ።
ሙሳ በጣም የበሰለና በጦር ስትራቴጂ የተካነ ሰው ነበር። ከጦሪፍ ተልዕኮ መልስ በኋላ ፍፁም በመረጋጋት ለአንድ ዓመት ሙሉ አስፈላጊ ዝግጅት በማድረግ አሳለፈ። ሰባት ሺህ የተደራጀ ሰራዊት አዋቀረ። በነዚህ ሰባት ሺህ ወታደሮች ነበር ዘመቻውን የጀመረው።

የአንደሉስ ድል መጀመሪያ
በ92 ዓ.ሒ [ 711 ] በሸዕባን ወር ከጦሪፍ የተሳካ ስለላ ከአንድ ዓመት በኋላ ሙሳ ኢብኑ ኑሰይር ጧሪቅ ብኑ ዚያድ የተባለውን የበርበር ተወላጅ በሰባት ሺዎቹ ወታደሮች ላይ ሾሞ ወደ አንደሉስ ላከው።
ጧሪቅ ኢብኑ ዚያድ ፈሪሀ አላህ፣ ዛሂድ፣ ጀግናና ለጂሃድ የተፈጠረ ሸሂድነትን የሚናፍቅ የተዋጣለት የጦር መሪ ነበር። በሰሜን አፍሪካ አህጉር በዛሬዋ አልጄሪያ ሀገር (ኦድ ታፍና) በሚባል መንደር በ670 ዓ.ል የበርበራ ሙስሊም ከሆንው የኡመያድ ዘመን ጄኔራል በመሆን የቪዚኮቲክ ሂስፓኒያ ግዛትን በ711 ዓ.ል ከተቆጣጠረው ኧሊፋ አል ወሊድ ተወለደ።
ኢብን ኸልዱን የተባሉት የሙሰሊም ታሪክ ፀሐፊ እንዳሚሉት ጧሪቅ ኢብኑ ዚያድ በስፔን ዜጎች ዘንድ ኤልቱኤርቶ (አንድ ዓይን) በሚል ቅፅል ስሙ ነበር የሚታወቀው ። በአይቤርያን ፔኒሱላ ከታዩ ስመ ገናና የሙስሊም ጄኔራሎች መሃል ግንባር ቀደም ተጠቃሸ ነበር።

ኢንሻ አላህ ይ





═════════════════
#ኢኽላስ_ታማኝነት_ትጋት_ስኬት
_\\\____________
ሼር
@hebre_muslim
@hebre_muslim
╚═══════════════╝
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
━━━━━━✦✿✦━━━━━━
አንደሉስ ክፍል 3
━━━━━━✦✿✦━━━━━━



ታላቁ የሙስሊም ታሪክ ፀሐፊ የሆነው አልመካር የተባለ የታሪክ ምሁር እንደዘገበው ጧሪቅ ኢብን ዚያድ ወታደሮችን በማንቀሳቀስ ወደ ስፔን ካቀና በኋላ ለታላቁ ዘመቻ ለተሰናዱ ሙስሊም ወታደሮች ፊት ቆሞ ዝንት ዓለም በኢስላም ታሪክ ሲታወስ የሚቆይ ታሪካዊ ንግግርን በማድረግ የወታደሮችን ወኔ መገንባት ቻለ። ሁሌም ሲታወስበት የሚቆይበትን ንግግር እንዲህ በማለት ጀመረ:- "እናንተ የተከበራችሁ ምርጥ የአላህ ወታደሮች ወደ ኋላ ብትንቀሳቀሱ ከጀርባቹ ያለው ባህር ነው፤ ወደ ፊት ብትጓዙ ከፊት ለፊታችሁ የጠላት ጦር ወታደሮች አሰፍስፈው ይጠብቋቹኋል። በአሁኑ ሰዓት ህይወታችሁን ለመታደግ ከእናንተ ጋር የቀረ ነገር ቢኖር ውስጣቹ ያመቃችሁት ወኔና መንፈሳዊ ጥንካሬያቹ ብቻ መሆኑን ተረዱ። እናንተ ውድ የአላህ ባሮች ከውስጣቹ በመንጨ ወኔ እና ፍጹም በሆነ ጀግንነት በተሞላበት ሹጃእ በአላህ ተውኩላችሁ በመታገዝ ሠይፋችሁን ወደፊት በመምዝዝ ለዲነል ኢስላም ዝብ ቁሙ። አስታውሱ እናንተ በዚህች ባዕድ ሀገር ያላችሁ ዕድል አንድ ወላጅ አልባና ተንከባካቢ ያጣ የቲም ህፃን ልጅ የከፋ እድልና ያነሰ ዕጣ ነው፣ ጠላቶቻችሁ ከፊት ላፊታችሁ ቆመዋል ፤ እጅግ በተዋቀረ ሁኔታ በህብረት ሊያጠቋችሁ ተሰናድተዋል። ቁጥራቸው ከኛ ወታደሮች እጅግ የላቁ ናቸው። ነገር ግን በእጆቻቹ ያሉ ሠይፎች ሕይወታችሁን ለመታደግ ያላችሁ ብቸኛ አማራጮች ናቸው። ሠይፎቻችሁን በመጠቀም በጠላት እጅ ያሉ ሠይፎችን በማስጣል ነፍሶቻችሁን መታደግ ትችላላችሁ። ነገር ግን ይህን ማድረግ አቅቷችሁ ከተቀደማችሁ ነብሳችሁን ለመታድግ የሚኖራችሁ አጋጣሚ ያከትማል። ሠይፎችሁን በብልሃት በመጠቀም ጠላትን ካንበረከካችሁ በዚች ምድር የመንገስ ህልማችሁን የምታረጋግጡ ሲሆን ይህ የምትመለከቱት በታላቅ አጅብ የታጀበ የጠላት ጦር በጀግንነታችሁ ፍርሃት ተውጦ በፈሰሰ ውስጥ ሰጥሞ ይጠብቃችኋል። ወኔያችሁ ይበርታ። ጀግንነት ከናንተ ጋር ይሁን። የማሸንፍ ብርታትን ብቻ በውስጣችሁ አኑሩ። በርቱና ሠይፋችሁን ምዘዙ። የጠላትን ጦር ተጋፈጡ። የማሸንፍ እድላችሁን ለጠላት አሳልፋቸወሁ አትስጡ። ይህን ንግግሬን ከልብ አድምጡ። በችሎታችሁ ላይ ፍፁም እርግጠኛ ሁኑ ላአደገኛ ጠላት አሳልፌ ምሰጣችሁ አድርጋችሁ አታስቡ በልበ ሙሉዕነት የጠላት ጦርን ለማጥቃት እኔ እራሴ በመጀመሪያ ረድፍ ላይ በመሰላፍ የጠላት ጦርን ለማጥቃት ዝግጁ ነኝ" በማለት የሙጃሂዶቹ ልብ በተውኩልና በወኔ እንዲሞላ፤ ጉልበታቸው እንዲበረታ ልባቸው
እንዲደነድን አድርጎ በአላህ ላይ እንዲፀኑ በማድረግ በክረምት ወቀት በ8ኛው ክፍለ ዘመን በ711 ዓ.ል ወደ አንደሉስ በማቅናት በንጉስ ሮድሪክ የሚመራዉን የቪሲጎቲክ ግዙፍ ወታደርን በመደምሰስ አመርቂ ድልን በመቀዳጀት በጁለይ 19 በጉዳሌት አውደ ውጊያ ንጉስ ሎድሪክን አንገቱን በመቀንጠስ ወደር ባልተገኘለት ጅብድ ቃሉን የጠበቀው ጧሪቅ ኢብኑ ዚያድ በጥቂት ወታደሮቹ በአላህ ተውኩል እየታጀበ በግዙፉና አስፈሪው የቪሲጎቲኮችን ጦር ገጠመ።
ጧሪቅ ወደ አንደሉስ ሲሄድ ሙሳ ኢብኑ ኑሰይር አላህ እንዲረዳቸው በለቅሶ ይማፀን ነበር።
ኢስላማዊው ሰራዊት በመርከብ ተሳፍረው የባህሩን ወሽመጥ አለፉ። ወሽመጡን ሲያልፉ በዳርቻ ከነበረው ተራራ ስር ጧሪቅ ሰራዊቱን አሳርፎ ስለነበር እስከዛሬ ድረስ "የጧሪቅ ተራራ ወሽመጥ" (Strait of Gibraltar) እየተባለ ይጠራል።
ከጧሪቅ ተራራ ወደ ኸድራእ (Algeciras) ደሴት በመጓዝ አረፉ። እዚያም የደቡብ አንደሉስ ወታደሮች ጋር ተፋጠጡ። ወታደሮቹ የክርስቲያኑ ጦር ጠባቂዎች ስለነበሩ ጠንካራ የሚባሉ አልነበሩም። በጂሃድ ህግ መሠረት ጧሪቅ እስልምናን እንዲቀበሉ ጥሪ አደረገላቸው እምቢ ካሉ ግብር እንዲከፍሉ የሶስት ቀን ገደብ ሰጣቸው። ነገር ግን ጠባቂዎቹ ትዕቢት ወጠራቸውና ሁለቱንም ምርጫዎች አሻፈረኝ አሉ። ጦርነቱ ተካሄደ በጧሪቅ አሸናፊነትም ተጠናቀቀ። የጠባቂዎቹ አለቃ የነበረው ቱድሚር በጊዜው የአንደሉስ መናገሻ ከተማ ከነበረችው ጡለይጢላ (ቶሌዶ) ለሚገኘው ሮድሪጎ አስቸኳይ ደብዳቤ ላከ። "ሮድሪጎ ድረስልን! ከሰማይ ይሁኑ ከመሬት የማናውቃቸው ሰዎች መጥተውብናል። ራስህ መጥተህ ድረስልን!" በእርግጥም ልዩ ፍጡሮች ነበሩ ለነሱ። የለመዱት ወራሪ ኃይል ገንዘብ መዝረፍና ነፍስ ማጥፋት ባህሪው የሆነ ነው። ኃይማኖታቸውን የሚያቀርቡላቸውና ከተቀበሉ ሁሉንም ነገር የሚተውላቸው ካልሆነ የተወሰነ ግብር (ጂዝያ) ከፍለው ገንዘባቸውንም ሆነ ሙሉ ንብረታቸውን የማይነኩባቸው ከዚያም አልፎ የሚከላከሉላቸው ዘማቾች በርግጥም ለነሱ ግሩም ነበር። ከዚያም አልፎ በቀን ብቁ ተፋላሚ በሌሊት መነኩሴ የሆኑ እንግዳ ፍጡሮች ከሰማይ ይሁኑ ከመሬት ቢያደናግሩት አይደንቅም። በርግጥም ትክክል ነው። እነሱ የአላህ ሰራዊቶች ናቸው።
(( ﺃُﻭ۟ﻟَٰٓﺌِﻚَ ﺣِﺰْﺏُ ﭐﻟﻠَّﻪِ ۚ ﺃَﻟَﺂ ﺇِﻥَّ ﺣِﺰْﺏَ ﭐﻟﻠَّﻪِ ﻫُﻢُ ﭐﻟْﻤُﻔْﻠِﺤُﻮﻥَ ))
"እነዚያ የአላህ ሕዝቦች ናቸው፡፡ ንቁ! የአላህ ሕዝቦቸ እነርሱ ምኞታቸውን የሚያገኙ ናቸው"

ኢንሻ አላህ ይ





═════════════════

#ኢኽላስ_ታማኝነት_ትጋት_ስኬት
_\\\____________
ሼር
@hebre_muslim
@hebre_muslim
╚═══════════════╝
2024/10/01 16:43:34
Back to Top
HTML Embed Code: