Telegram Web Link
Foreign Currency Exchange Rates for 15 July 2024

For more updates please visit our website:
https://www.abaybanksc.com/
#abaybank
ባንካችን በ17ኛው የአውሮፓ እግር ኳስ ዋንጫ የስፔን እና እንግሊዝ የፍጻሜ ጨዋታ ውጤት በ“ይገምቱ ይሸለሙ” መርሐግብሩ በማኅበራዊ ሚዲያዎቹ ትክክለኛ ግምት የሰጡ አሸናፊዎችን ለመሸለም ጥያቄ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡

በዚህ መሰረት ለመሸም የሚያስችሉ የውድድሩን ሕጎች ተግባራዊ በማድረግ (ስፔን 2 : እንግሊዝ 1) በሚል ትክክለኛ ግምት ሰጥተው የነበሩ ሶስት አሸናፊዎችን የለየን ሲሆን አሸናፊዎቹ የተመረጡት፡-

⚽️ ትክክለኛ ግምት በመስጠት፣
⚽️ቀድሞ በመመለስ፣
⚽️ግምቱን በባንካችን የፌስቡክ ገጽ የውስጥ መልዕክት (Inbox) በመላካቸው እንዲሁም
⚽️ የፌስቡክ ገጻችንን ለሌሎች ሰዎች በማጋራታቸው መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ባንካችን ውድድሩ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ በይገምቱ ይሸለሙ ፕሮግራማችን የውጤት ግምት በመስጠት ንቁ ተሳትፎ ላደረጉ የማኅበራዊ ሚዲያ ቤተሰቦቻችን ከፍ ያለ ምስጋና ያቀርባል፡፡
ጥሪት የጎልማሶች የቁጠባ ሒሳብ
-----------------------------
ዓባይ ባንክ ለሀገር ባለውለታዎች ታላቅ አክብሮት አለው!
ባንካችን ዕድሜያቸው 50 ዓመት እና በላይ ለሆኑ ደንበኞች ወደፊት ለሚኖራቸው ሕይወት ዋስትና እንዲሆናቸው ጥሪት የጎልማሶች የቁጠባ ሒሳብን ከልዩ የደንበኞች አገልግሎት እና ጠቀም ካለ ወለድ ጋር በማቅረብ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይጋብዛል፡፡
አገልግሎቱን ለማግኘት በአቅራቢያዎ የሚገኙ ቅርንጫፎቻችንን ይጎብኙ፤ በአክብሮት እናስተናግድዎታለን፡፡

ዓባይ - የታላቅነት ምንጭ!
#abaybank #tirit #seniorcitizens
https://www.abaybanksc.com/abay/tirit-saving/
የዓባይ ባንክ የሞባይል ባንኪንግ በሚሰጣቸው ዘርፈብዙ አገልግሎቶች በመጠቀም ኑሮዎን ያቅልሉ፤ ያዘምኑ!
መተግበሪያውን ከአፕስቶር እና ፕሌይስቶር አውርደው ወይም *812# በመደወል በምቾት ይገልገሉ፡፡

#abaybank #mobilebanking
https://www.abaybanksc.com/mobile-banking-abay/
የሃላል ካርድዎ በየትኛውም ቦታ 24/7 ያገለግልዎታል፡፡
በካርድዎ ግብይትዎን ያቀላጥፉ፣
ክፍያዎን ይፈጽሙ፣
ድካምዎን ያቅልሉ፣
ኑሮዎን ያዘምኑ!

ዓባይ - የታላቅነት ምንጭ!
#abaybank #sadiiq #halal
https://www.abaybanksc.com/abay-card-banking/
Foreign Currency Exchange Rates for 19 July 2024

For more updates please visit our website:
https://www.abaybanksc.com/
#abaybank
አሁናዊ ሁነት
......................
ዓባይ ባንክ የ2016 ዓ.ም ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ እያካሄደ ይገኛል።


ስብሰባውን በንግግር የከፈቱት የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ የኋላ ገሠሠ በባለፈው በጀት ዓመት (እ.ኤ.አ 2023/24) ባንኩ በርካታ ስኬቶችን ማስመዝገቡን ገልፀዋል።

በስብሰባው ላይ ከፍተኛ የሥራ አመራር አባላት የተገኙ ሲሆን ስብሰባው በአዲስ አበባ ኃይሌ ግራንድ አዲስ ሆቴል በመካሄድ ላይ ይገኛል።
ጎጆ - የቁጠባ ሒሳብ
--------------------------
ትዳር ለመመስረት አቅደው የሠርግ ወጪ ካሳሰብዎ፥ ዓባይ ባንክ ጥሩ መላ አቅርቦልዎታል!
ዓባይ ባንክ ለእጮኛሞች እና ለባለትዳሮች ጎጇቸውን ለማሞቅና የተለያዩ ጉዳዮቻቸውን ማከናወኛ ከመደበኛው የቁጠባ አገልግሎት በተጨማሪ በርካታ የማበረታቻ ጥቅሞች ያለው የቁጠባ አገልግሎት  "ጎጆ" በሚል ስያሜ በማቅረብ ደንበኞቹን ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑን በደስታ ይገልጻል።   

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በአቅራቢያዎ ከሚገኝ የዓባይ ባንክ ቅርንጫፍ በመቅረብ ቢጠይቁ በትህትና ይስተናገዳሉ፡፡ 

ዓባይ - የታላቅነት ምንጭ!
#abaybank #gojjo #saving
https://www.abaybanksc.com/abay/gojjo-saving/
ዓባይ ባንክ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ሥራ አፈጻጸም የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ዕውቅና ሰጠ

ባንኩ ሐምሌ 15 እና 16፣ 2016 ዓ.ም ባካሄደው ዓመታዊው የሥራ አመራር ስብሰባ እ.ኤ.አ በ2023/24 በጀት ዓመት በአጠቃላይ ሥራ አፈፃፀም የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ቀጠና ጽ/ቤቶች እና ቅርንጫፎች እውቅና ተሰጥቷል ።

የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ የኋላ ገሠሠ በዕውቅና አሰጣጥ ስነ-ስርዓቱ ላይ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ቀጠና ጽ/ቤቶች እና ቅርንጫፎች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት በቀጣይም መላው የባንኩ ማኅበረሰብ ባንኩ አመርቂ ውጤት ያስመዘገብ ዘንድ ጥረት እንዲያደርግ መልዕክት አስተላልፈዋል።
2024/09/30 13:24:36
Back to Top
HTML Embed Code: