Telegram Web Link
ዓባይ ባንክ ለይቆጥቡ፣ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ መርሀግብር ዕጣ ዕድለኞች ሽልማት ሰጠ
------------------------------
ዓባይ ባንክ ከነሀሴ 26 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ ጥር 18 ቀን 2016 ዓ.ም ሲካሄድ የነበረው የ7ኛ ዙር የይቆጥቡ፣ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ መርሀግብር ዕጣ ለወጣላቸው ባለዕድለኞች በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል በተከናወነ መርሀግብር ሽልማቶችን ሰጠ፡፡

በስነ - ስርዓቱ ላይ አቶ ወንድይፍራው ታደሰ የዓባይ ባንክ የስትራቴጂ ዋና መኮንን እንደገለጹት የማህበረሰባችንን የቁጠባ ባህል ለማጎልበት እንዲሁም የአገራችን የውጭ ምንዛሪ ግኝት ላይ የራሱን አስተዋጽኦ ለማበርከት ላለፉት ሰባት ተከታታይ ዓመታት ባንኩ ደንበኞችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የሽልማት መርሀግብሮችን ሲያከናውን እንደነበር ጠቅሰው÷ ባንኩ አዲስ የብራንድ መለያ እና መሪ ቃል ይፋ ባደረገ ማግስት ዕድለኛ ለሆኑ ተሸላሚዎች እንኳን ደስ አላችሁ በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የይቆጥቡ፣ ይቀበሉ፣ ይመንዘሩ መርሀ ግብር የመጀመሪያው ዕጣ የሆነው የቤት አውቶሞቢል መኪና የዕጣ ቁጥር 46527286 ሲሆን አሸናፊ የሆኑት የባንኩ የገንዳ ውሃ ቅርንጫፍ ደንበኛ የሆኑት አቶ ባዘዘው ተሻገር ናቸው፡፡

ባንኩ ያዘጋጀው የይቆጥቡ፣ ይቀበሉ፣ ይመንዘሩ መርሀግብር አንደኛ ዕጣ የአንድ ዘመናዊ መኪና፣ ሁለተኛ ዕጣ የ10 ፍሪጆች፣ ሶስተኛ ዕጣ 10 ላፕቶፖች፣ አራተኛ እጣ 10 ስማርት ቴሌቪዥኖች እና አምስተኛ ዕጣ 20 ስማርት ሞባይል ቀፎዎች በአጠቃላይ 51 የሽልማት ዓይነቶችን ለባለእድለኞች አቅርቧል፡፡
ሸሪዓውን መርህ ተከትለው በሚሰጡት ሰዲቅ የዓባይ ባንክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት፡-
ዋዲያህ የቁጠባና ተንቀሳቃሽ ሂሳብ፣
ሙዳራባህ የቁጠባና በጊዜ ገደብ የሚቀመጥ ሂሳብ፣
የሀጅ ጉዞዎን ለማከናወን የተዘጋጀ የቁጠባ አገልግሎት፣
ካፋላህ የዋስትና አገልግሎት፣
ሀዋላ ገንዘብ የማስተላለፍ አገልግሎት
እንዲሁም የተለያዩ የፋይናንስ አገልግሎቶች፡-
ሙራባህ፣ ቀርድ እና ሌሎችም ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት እንዲጠቀሙ እንጋብዝዎታለን፡፡

ዓባይ - የታላቅነት ምንጭ!
#ዓባይባንክ
https://www.abaybanksc.com/sadiiq-banking
Foreign Currency Exchange Rates for 15 April 2024

For more updates please visit our website:
https://www.abaybanksc.com/
#abaybank
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዓባይ - የታላቅነት ምንጭ!
የዓባይ ባንክ ካርድዎ በየትኛውም ቦታ 24/7 ያገለግልዎታል፡፡
በካርድዎ ግብይትዎን ያቀላጥፉ፣
ክፍያዎን ይፈጽሙ፣
ድካምዎን ያቅልሉ፣
ኑሮዎን ያዘምኑ!

ዓባይ - የታላቅነት ምንጭ!
#abaybank #cardbanking
https://www.abaybanksc.com/abay-card-banking/
ዓባይ ባንክ በትንሣዔ የንግድ ባዛር በመሳተፍ ላይ ይገኛል
--------------------------------------------                                                              
ዓባይ ባንክ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል በተዘጋጀው የ2016 የትንሣዔ የንግድ ባዛር ላይ በመሳተፍ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

ጎብኝዎች በባዛሩ ላይ የሚያስፈልጋቸውን ማንኛውም የባንክ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ  ሲሆን መጥተው እንዲጎበኙን ጋብዘንዎታል፡፡

በኤግዚቢሽን ማዕከል እና ሴንቸሪ ፕሮሞሽንና ኤቨንትስ አዘጋጅነት በደማቅ ሁኔታ የተከፈተው የትንሤዔ ባዛር እስከ ሚያዚያ 26/2016 ዓ.ም ለጎብኝዎች ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዓባይ
ዓባይ የታሪክ፣ የሀይማኖት፣ የባህል፣ የሥልጣኔ እና የጥበብ መፍለቂያ፣ የበጎ እሴቶች መታያና መገኛ፣ በዘመን ብራና በጊዜ ዐውድ ላይ የነገሠ፣ የኢትዮጵያዊነት ልክና መልክ!

ዓባይ - የታላቅነት ምንጭ!
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በግብይትዎ ወቅት ከዓባይ ባንክ በቀረበልዎ የክፍያ ካርድ ጊዜና ቦታ ሳይገድብዎ 24/7 በመጠቀም ምቾትዎን ይጠብቁ፣ ኑሮዎን ያዘምኑ!

ዓባይ - የታላቅነት ምንጭ!
#abaybank  #cardbanking
https://www.abaybanksc.com/abay-card-banking/
ይጠንቀቁ!

ውድ ደንበኞቻችን አንዳንድ ግለሰቦች ከዓባይ ባንክ የተደወለ በማስመሰል የሞባይል እና ኦንላይን ባንኪንግ የይለፍ ቃል (PIN) እና የአንድ ጊዜ የይለፍ ቃል (One Time Password) በመጠየቅ መረጃ ለመውሰድ እየሞከሩ መሆኑን ከደንበኞቻችን በደረሰን መረጃ አረጋግጠናል፡፡

ባንካችን የሞባይል እና ኦንላይን ባንኪንግ የሚስጢር የይለፍ ቃል መረጃዎችን ከደንበኞች የማይጠይቅ እንዲሁም በምንም መልኩ ከተጠቃሚው ደንበኛ ውጭ መጋራት የሌለባቸው መሆኑን በመገንዘብ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እንዲሁም ተመሳሳይ ሙከራ ሲያጋጥምዎ ወደ ባንካችን የጥሪ ማዕከል 8834 በመደወል እንዲያሳውቁን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡

ዓባይ - የታላቅነት ምንጭ!
ሰዲቅ- የዓባይ ባንክ ከወለድ-ነጻ የባንክ አገልግሎት የሸሪዓውን ሃይማኖታዊ ዕሴት መርህ በማድረግ የሚሰጥ የፋይናንስ አገልግሎት ነው፡፡
የባንካችን ቅርንጫፎችን በመጎብኘት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንጋብዝዎታለን!

ዓባይ - የታላቅነት ምንጭ!
#abaybank
https://www.abaybanksc.com/sadiiq-banking
2024/09/29 21:23:28
Back to Top
HTML Embed Code: