Telegram Web Link
እንኳን ለታላቁ ኢድ - አል ፈጥር በዓል አደረስዎ!
ባንካችን የኢድ- አል ፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ ከወዳጅ ዘመድ ከውጭ አገር የሚላክልዎትን ከ50 ዶላር በላይ እና የ50 ዶላር ተመጣጣኝ የሆኑ ተቀባይነት ያላቸውን ገንዘቦች በባንካችን ሲቀበሉ እንዲሁም በእጅዎ የሚገኝ የውጭ አገር ገንዘብ ሲመነዝሩ ለደንበኝነትዎ ስጦታዎችን አዘጋጅቷል፡፡ አቅራቢያዎ የሚገኙ ቅርንጫፎቻችንን ይጎብኙ፡፡

ኢድ ሙባረክ!
ዓባይ - የታላቅነት ምንጭ!
እንኳን ለ1445ኛው ታላቁ የዒድ ዓልፈጥር በዓል በሠላም አደረስዎ!

ዒድ ሙባረክ!
ዓባይ - የታላቅነት ምንጭ!
ዓባይ ባንክ ለይቆጥቡ፣ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ መርሀግብር ዕጣ ዕድለኞች ሽልማት ሰጠ
------------------------------
ዓባይ ባንክ ከነሀሴ 26 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ ጥር 18 ቀን 2016 ዓ.ም ሲካሄድ የነበረው የ7ኛ ዙር የይቆጥቡ፣ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ መርሀግብር ዕጣ ለወጣላቸው ባለዕድለኞች በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል በተከናወነ መርሀግብር ሽልማቶችን ሰጠ፡፡

በስነ - ስርዓቱ ላይ አቶ ወንድይፍራው ታደሰ የዓባይ ባንክ የስትራቴጂ ዋና መኮንን እንደገለጹት የማህበረሰባችንን የቁጠባ ባህል ለማጎልበት እንዲሁም የአገራችን የውጭ ምንዛሪ ግኝት ላይ የራሱን አስተዋጽኦ ለማበርከት ላለፉት ሰባት ተከታታይ ዓመታት ባንኩ ደንበኞችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የሽልማት መርሀግብሮችን ሲያከናውን እንደነበር ጠቅሰው÷ ባንኩ አዲስ የብራንድ መለያ እና መሪ ቃል ይፋ ባደረገ ማግስት ዕድለኛ ለሆኑ ተሸላሚዎች እንኳን ደስ አላችሁ በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የይቆጥቡ፣ ይቀበሉ፣ ይመንዘሩ መርሀ ግብር የመጀመሪያው ዕጣ የሆነው የቤት አውቶሞቢል መኪና የዕጣ ቁጥር 46527286 ሲሆን አሸናፊ የሆኑት የባንኩ የገንዳ ውሃ ቅርንጫፍ ደንበኛ የሆኑት አቶ ባዘዘው ተሻገር ናቸው፡፡

ባንኩ ያዘጋጀው የይቆጥቡ፣ ይቀበሉ፣ ይመንዘሩ መርሀግብር አንደኛ ዕጣ የአንድ ዘመናዊ መኪና፣ ሁለተኛ ዕጣ የ10 ፍሪጆች፣ ሶስተኛ ዕጣ 10 ላፕቶፖች፣ አራተኛ እጣ 10 ስማርት ቴሌቪዥኖች እና አምስተኛ ዕጣ 20 ስማርት ሞባይል ቀፎዎች በአጠቃላይ 51 የሽልማት ዓይነቶችን ለባለእድለኞች አቅርቧል፡፡
ሸሪዓውን መርህ ተከትለው በሚሰጡት ሰዲቅ የዓባይ ባንክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት፡-
ዋዲያህ የቁጠባና ተንቀሳቃሽ ሂሳብ፣
ሙዳራባህ የቁጠባና በጊዜ ገደብ የሚቀመጥ ሂሳብ፣
የሀጅ ጉዞዎን ለማከናወን የተዘጋጀ የቁጠባ አገልግሎት፣
ካፋላህ የዋስትና አገልግሎት፣
ሀዋላ ገንዘብ የማስተላለፍ አገልግሎት
እንዲሁም የተለያዩ የፋይናንስ አገልግሎቶች፡-
ሙራባህ፣ ቀርድ እና ሌሎችም ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት እንዲጠቀሙ እንጋብዝዎታለን፡፡

ዓባይ - የታላቅነት ምንጭ!
#ዓባይባንክ
https://www.abaybanksc.com/sadiiq-banking
Foreign Currency Exchange Rates for 15 April 2024

For more updates please visit our website:
https://www.abaybanksc.com/
#abaybank
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዓባይ - የታላቅነት ምንጭ!
የዓባይ ባንክ ካርድዎ በየትኛውም ቦታ 24/7 ያገለግልዎታል፡፡
በካርድዎ ግብይትዎን ያቀላጥፉ፣
ክፍያዎን ይፈጽሙ፣
ድካምዎን ያቅልሉ፣
ኑሮዎን ያዘምኑ!

ዓባይ - የታላቅነት ምንጭ!
#abaybank #cardbanking
https://www.abaybanksc.com/abay-card-banking/
ዓባይ ባንክ በትንሣዔ የንግድ ባዛር በመሳተፍ ላይ ይገኛል
--------------------------------------------                                                              
ዓባይ ባንክ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል በተዘጋጀው የ2016 የትንሣዔ የንግድ ባዛር ላይ በመሳተፍ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

ጎብኝዎች በባዛሩ ላይ የሚያስፈልጋቸውን ማንኛውም የባንክ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ  ሲሆን መጥተው እንዲጎበኙን ጋብዘንዎታል፡፡

በኤግዚቢሽን ማዕከል እና ሴንቸሪ ፕሮሞሽንና ኤቨንትስ አዘጋጅነት በደማቅ ሁኔታ የተከፈተው የትንሤዔ ባዛር እስከ ሚያዚያ 26/2016 ዓ.ም ለጎብኝዎች ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
2024/09/29 21:24:30
Back to Top
HTML Embed Code: