Telegram Web Link
የዓባይ ባንክ ከፍተኛ የሥራ አመራሮች አዲስ የባንኩን ሕንጻ የግንባታ ሒደት ጎበኙ
-----------------------------------------
የዓባይ ባንክ አ.ማ. ከፍተኛ የሥራ አመራሮች በግንባታ ላይ የሚገኘውን የባንኩን ግዙፍ ሕንጻ ግንባታ ጎበኙ፡፡

በጉብኝቱ ላይ አቶ የኋላ ገሠሠ የዓባይ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚን ጨምሮ ሌሎች የባንኩ ከፍተኛ የሥራ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

አቶ የኋላ በጉብኝቱ ላይ እንደተናገሩት የሕንጻው ግንባታ በወሳኝ ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ ጠቅሰው፣ ግንባታውን በፍጥነት ለማጠናቀቅ ግንባታውን እያከናወነ ካለው ቻይና ው ይ ኃ/የተ ተቋራጭ ድርጅት እና ዠቅአለ የኮማ አማካሪ ድርጅት ጋር የባንኩ የፕሮጄክት ጽሕፈት ቤት ሠራኞች በትጋት እየሠሩ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

የሕንጻው ግንባታ ተጠናቅቆ ሥራ ሲጀምር ለባንኩ ይበልጥ ውጤማነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት አቶ የኋላ ገልጸዋል፡፡

ሕንጻው ከዋና ዋና አገልግሎቶቹ በተጨማሪ ካፊቴሪያ፣ ጂምናዚየም፣ የሕጻናት ማቆያ፣ የእሳት አደጋ እና የደህንነት መቆጣጠሪያ እንዲሁም የውሃ እና ኃይል ቆጣቢ ቴክኖሎጂዎች እንደሚኖሩት በጉብኝቱ ተጠቅሷል፡፡

33 ወለሎች የሚኖሩት ይህ ዘመናዊ ሕንጻ ሜክሲኮ አደባባይ አካባቢ የሚገኝ ሲሆን ግንባታው በአሁኑ ሰዓት 20ኛው ወለል ላይ ይገኛል፡፡
ካፋላህ - የዓባይ ሰዲቅ ዋስትና የመስጠት አገልግሎት

ባንካችን የሸሪዓ የፋይናንስ መርሆችንና አሠራሮችን መሰረት በማድረግ ካፋላህ - የዓባይ ሰዲቅ የተለያዩ ዋስትናዎች የመስጠት አገልግሎት በማቅረብ በርካቶችን ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑን በደስታ ይገልጻል፡፡

ዓባይ - ታማኝ አገልጋይ!

#abaybank
https://abaybank.com.et/kafalah-and-halal-atm-cards/
Foreign Currency Exchange Rates for 15 December 2023
For more updates please visit our website:
https://www.abaybank.com.et/exchange-rates
#abaybank #exchangerates
ይገምቱ ይሸለሙ!
------------------
በእንግሊዝ የፕሪሚየር ሊግ ከሚካሄዱ ጨዋታዎች መካከል እሑድ ምሽት 1:30 ላይ የሚደረገው የሊቨርፑል እና ማንችስተር ዩናይትድ ጨዋታ የስፖርት ቤተሰቡን ትኩረት አግኝቷል።

ባንካችን የዚህን ጨዋታ ውጤት በትክክል ለገመቱ የመጀመሪያዎቹ አምስት የማኅበራዊ ሚዲያ ቤተሰቦቻችን ሽልማት አዘጋጅቷል።

የውድድሩ ሕጎች፣
1. ይህን መልዕክት ለሌላ ሰው ያጋሩ፡፡
2. ግምትዎን መስጠት የሚችሉት ጨዋታው ከመጀመሩ በፊት በይፋዊ የባንካችን የፌስቡክ ገጽ የውስጥ መልዕክት (Inbox) በመላክ ብቻ መሆኑን ከወዲሁ ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡

የዓባይ ባንክ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾች እና ድረገጽ ቤተሰብ እንዲሆኑ ጋብዘንዎታል!

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/abaybanksharecompany
ቴሌግራም፡ https://www.tg-me.com/abaybanksharecompany
ትዊተር፡ https://twitter.com/AbayBank
ሊንክድኢን፡ https://www.linkedin.com/company/abaybank/
ዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/@abaybank4665
ድረገጽ፡ https://abaybank.com.et

መልካም ጨዋታ!
መልካም ዕድል!
Foreign Currency Exchange Rates for 18 December 2023
For more updates please visit our website:
https://www.abaybank.com.et/exchange-rates
#abaybank #exchangerates
ባንካችን ቀደም ሲል ሽልማት የሚያስገኝ የ“ይገምቱ ይሸለሙ” ጥያቄ በማኅበራዊ ሚዲያዎቻችን ማቅረቡ ይታወሳል፡፡

ትክክለኛውን ግምት በባንካችን የፌስቡክ ገጽ የውስጥ መልዕክት (Inbox) ቀድመው የሰጡ እንዲሁም ጥያቄዎቹን ለሌሎች ሰዎች ያጋሩ አምስት ተሸላሚዎችን ለይተናል፡፡

መልስ ለመስጠት በርካታ የማኅበራዊ ሚዲያ ቤተሰቦቻችን ላደረጋችሁት ንቁ ተሳትፎ ምስጋና እያቀረብን፣ በቀጣይም ተመሳሳይ የሚያሸልሙ ጥያቄዎችን እንደምናቀርብ ከወዲሁ እንገልጻለን፡፡

የዓባይ ባንክ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾች እና ድረገጽ ቤተሰብ እንዲሆኑ ጋብዘንዎታል!

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/abaybanksharecompany
ቴሌግራም፡ https://www.tg-me.com/abaybanksharecompany
ትዊተር፡ https://twitter.com/AbayBank
ሊንክድኢን፡ https://www.linkedin.com/company/abaybank/
ዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/@abaybank4665
ድረገጽ፡ https://abaybank.com.et

ዓባይ - ታማኝ አገልጋይ!
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለዘመናት በዓለም ዙሪያ ዝናው እንደናኘው
ከዓመት ዓመት ያለማቋረጥ እየገሰገሰ የጥንካሬ ምልክት ሆኖ የዘለቀ
ኃያልነቱን እያስመሰከረ ታላቅ ተስፋን ያቀበለ
አገር ምድሩን እንደሚያርሰው ወንዛችን
ኑ አብረን እንግዘፍ የሚልዎ እነሆ ባንካችን!
ከዓባይ ባንክ ጋር እየሠሩ የኑሮዎን ከፍታ ያስውቡ!

ዓባይ - ታማኝ አገልጋይ!
በዓባይ ባንክ ይቆጥቡ፤ ራዕይዎን ዕውን ያድርጉ!

ባንካችን እንደፍላጎትዎ ያቀረበልዎትን ዘርፈብዙ የቁጠባ አማራጮች በመጠቀም ከገቢዎ ላይ አነሰ በዛ ሳይሉ ዛሬውኑ መቆጠብ ይጀምሩ፤ ራዕይዎን ዕውን ያድርጉ!

ዓባይ - ታማኝ አገልጋይ!
#abaybank
https://abaybank.com.et/other-saving-accounts/
ወዳጅ ዘመዶችዎ ለፍቅራቸው መግለጫ ከውጭ አገር የሚልኩትን የበዓል ስጦታ ገንዘብ ከባንካችን ጋር ከሚሠሩ ፈጣን ዓለምአቀፍ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች በተላከልዎት ፍጥነት ሲቀበሉ እና ሲመነዝሩ ይሸለማሉ፡፡

#abaybank
https://abaybank.com.et/money-transfer-services-2/
VACANCY ANNOUNCEMENT
-------------------------------------

Abay Bank S.C. invites interested and qualified applicants for Customer Service Officer -II (CSO – II) position.

Interested and qualified applicants fulfilling the criteria can apply in person at Abay Bank Dire Dawa District office, Jigjiga, Kebridahir, Gode and Shebelle Branches. 
Only short listed candidates will be contacted.

Please use the link below to read full content of the vacancy.  
(https://abaybank.com.et/career-opportunities/

Good Luck!
ዓባይ ባንክ ተደራሽነቱን ይበልጥ በማስፋፋት ከደጅዎ ደርሷል!

ባንካችን 516ኛ ቅርንጫፉን በገንደውሃ ከተማ “ነጭወርቅ ቅርንጫፍ”፣
517ኛውን በአዲረመጥ ከተማ “ወልቃይት ቅርንጫፍ”፣
518ኛውን በጎንደር ከተማ “ምንትዋብ ቅርንጫፍ” እንዲሁም
519ኛውን በጎንደር ከተማ “ህዳሴ ቅርንጫፍ” በሚሉ ሥያሜዎች ከፍቶ ከዘርፈ ብዙ የባንክ አገልግሎቶች ጋር ይጠብቅዎታል፡፡

ዓባይ - ታማኝ አገልጋይ!
#abaybank
https://abaybank.com.et/branch-locator
ዓባይ ባንክ በገና ኤግዚቢሽን እና ባዛር ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛል
--------------------------------------------
ዓባይ ባንክ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል በተዘጋጀው የ2016 የገና ባዛር ላይ በመሳተፍ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

ጎብኝዎች በባዛሩ ላይ የሚያስፈልጋቸውን ማንኛውም የባንክ አገልግሎቶች በመስጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን መጥተው እንዲጎበኙን ጋብዘንዎታል፡፡

በኤግዚቢሽን ማዕከል እና ሴንቸሪ ፕሮሞሽንና ኤቨንትስ አዘጋጅነት በደማቅ ሁኔታ የተከፈተው ባዛር እስከ ታኅሣሥ 27/2016 ዓ.ም ለጎብኝዎች ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
ጁሙዓ ሙባረክ!

ዓባይ ባንክ የሸሪዓ የፋይናንስ መርሆችንና አሰራሮችን መሰረት አድርጎ ባዘጋጀው ሰዲቅ - ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት እንዲጠቀሙ ጋብዘንዎታል!

ዓባይ - ታማኝ አገልጋይ!
#abaybank
https://abaybank.com.et/about-abay-sadiiq/
Foreign Currency Exchange Rates for 22 December 2023
For more updates please visit our website:
https://www.abaybank.com.et/exchange-rates
#abaybank #exchangerates
ዓባይ ባንክ በሚሊኒየም አዳራሽ የገና ኤግዚቢሽን እና ባዛር ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛል
--------------------------------------------
ዓባይ ባንክ በሚሊኒየም አዳራሽ በተዘጋጀው የ2016 የገና ባዛር ላይ በመሳተፍ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

ጎብኝዎች በባዛሩ ላይ የሚያስፈልጋቸውን ማንኛውም የባንክ አገልግሎቶች በመስጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን መጥተው እንዲጎበኙን ጋብዘንዎታል፡፡

በባሮክ ኤቨንት ኦርጋናይዘር አዘጋጅነት በደማቅ ሁኔታ የተከፈተው ባዛር እስከ ታኅሣሥ 27/2016 ዓ.ም ለጎብኝዎች ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
2024/09/30 05:30:56
Back to Top
HTML Embed Code: