Telegram Web Link
ጷጉሜ 01
" ሰላም ለሀገራችን ~ሰላም ለምድራችን "
+ ተንስኡ ለጸሎት +
ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣኸን የሕይወት ምንጭ አምላካችን ሆይ ማይክሮ ሰከንድ ለማይገባን አንተን እስትንፋሳችንን ቸል ላልንህ ቸል ሳትለን በፊትህ እንደገና የምናንጋጥጥበትን ጊዜ በምህረትህ ብዛት ስለቸርከን እናመሰግንሃለን🙏

የፍጥረት ሁሉ ጌታ ማዕበል ፣ ሞገዱ ፣ነፋሳቱ ሁሉ የሚታዘዙልህ ንውጽውጽታውን የምታረጋጋው የጸጥታ ወደባችን ሆይ ሰላም መረጋጋትን ለብዙ ዘመናት ብንሻም የነጭ እርግብ ምስል እየሰራን ከማሳየት ፣ ከመመኘት ውጪ ፍጹም ሰላምን ማምጣት አልቻልንም "ሰላሜን እሰጣችኋለሁ" ያልከን ሰላማችን ሆይ እውነተኛ ሰላም ካንተ ዘንድ ነውና ፣ ለእኛ ክቡድ የሆነውም በአንተ ዓይን ቀላልና ሀገራችንን እየናጣት ያለውን የጦርነት ፣ የጥላቻ ፣ የረሃብ፣ የቸነፈር ማዕበል ገስጸህ ፍጹም ሰላምህን ለሀገራችን ኢትዮጵያ ለምድራችን ታድል ዘንድ እኛም ሁል ጊዜ ቃልህን ለመስማት የነቃን የበቃን የዘተጋጀን እንድንሆን ማስተዋልን ትሰጠን ዘንድ እንለምንሃለን። ስልጣን ባለው ስምህ ለዘለዓለሙ አሜን 🙏

ሊ/ዲ/ን መባጽዮን (ኢ/ር)
ጳጉሜ 01/13/2015 ዓ/ም
ራጴ ~ኢትዮጵያ
👇👇👇👇👇👇
ሊንኩን ይንኩት
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
ጷጉሜ 02

" የሞትክለት ከቶ አይሙት "
+ ተንስኡ ለጸሎት +
ስለዓለም ሁሉ ድኅነት መስዋዕት ፣ መስዋዕት አቅራቢም ፣ መስዋዕት ተቀባይም ሆነህ ይህን ዓለም አንድ ጊዜ በደምህ ያዳንኸው ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ውለታህን ዕለት ዕለት ባናስታውስም እንኳ ዳግም ይህን ዕለት በበዛው ምህረትህ እንኩ ስላልከን የምንሰጥህ ሌላ የለንም ቀናችንን ፣ የከንፈራችንን ፍሬ ምስጋናችንን እንካ እንልሃለን🙏

ንጹሁ መስዋዕታችን ኢየሱስ ሆይ ጥንት አባቶቻችን እነ አቡነ ጴጥሮስ ለዘላለም ቤታቸው ለሃይማኖታቸው ፣ ለሃገር ነጻነት ለህዝባቸው ሲሉ አንዲት ነፍሳቸው ሳታሳሳቸው በጠላት ጥይት ተረፍርፈው መስዋዕት ሆኑ መስዋዕትነት ለብዙሃን ጥቅም ለብዙዎች ህልውና እራስን አሳልፎ ለመከራ ፣ ለሞት መስጠት ነውና ........ ዛሬ ዛሬ ግን ለማን መስዋዕት መሆን እንዳለብን እንኳ ግራ ገብቶን የምንሞትለትን ጉዳይ እንኳ በቅሉ ሳንረዳ በጠላት ወሬ ና ሴራ ተጠልፈን ለስልጣን፣ ለጥቅም ብለን ብዙዎቹን ይዘን እርስ በእርስ የምንተላለቅ ሆነናልና.......

ለዓለም ድኅነት በመስቀል ላይ መስዋዕት የሆንከው የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ሆይ የሞትክለት አይሙት የደማህለት አይድማ በደምህ በርነት ወደ አባትህ መግባት ይሆንለት ዘንድ አብርሆትን፣ ለማን መስዋዕት መሆን እንዳለብን ለሃገርና ፣ለሃይማኖት የሚከፈለውን መስዋዕትነት እውነት የምንረዳበትን ማስተዋል ታድለን ዘንድ ፣ ልባቸውን ከእውነት አርቀው ድብቅ አጀንዳ ሸክፈው ትውልድ እንዲማገድ ፣ የሃገር ኢኮኖሚ እንዲደቅ "በለው በለው" እያሉ የሚያቀጣጥሉትን እነ ሆድ አምላኩን ወደ ልባቸው ትመልስልን ዘንድ ተጸጽተውም የአንድነትን ሀሳብ ማፍለቅ ይሆንላቸው ዘንድ ፍጹም ሰላምህ ይከብበን ዘንድ እንማጸንሃለን በተወጋው ጎንህ ለዘለዓለሙ አሜን🙏

ሊ/ዲ/ን መባጽዮን (ኢ/ር)
ጷጉሜ 02/13/2015 ዓ/ም
ራጴ ~ኢትዮጵያ
👇👇👇👇👇👇
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
ጷጉሜ 02

+ ክብረ ክህነት +

ከጣሊያን ጦርነት በኋላ ንጉሱ ጃንሆይ ወደ መንበራቸው ከተመለሱ በኋላ ራስ ስዩም ከራስ ካሣ በታች ሲቀመጡ ንጉሡ ያያሉ ይህን ሁኔታ የተመለከቱት ንጉሡ ራስ ስዩምን "ምነው ከራስ ካሳ በታች ተቀመጥክ?" ብለው ጠየቁት (ራስ ስዩም የንጉሥ ዮሐንስ የልጅ ልጅ ስለነበሩ ቀድሞ ከራስ ካሳ ከፍ ብለው ነበርና የሚቀመጡት) ራስ ስዩምም ለንጉሡ "ራስ ካሳ ክህነት ስላላቸው ብዬ ነው" ብለው መለሱላቸው ንጉሡም አላወቁም ነበርና ከዚያ በኋላ ሁለቱንም በእሳቸው በቀኝና በግራ አስቀመጧቸው።

አዊ ከንግሥና ክብር የካህን ክብር ይበልጣል።በዚህ ዓለም ላይ ከታወቁ ክብሮች አንዱ የቤ/ክ አባቶችና አገልጋዮች ክብር ነው። የተቀቡትን ማክበር ቀቢውን ጌታ ማክበር ነው። የተቀቡትን መናቅም ቀቢውን ጌታ መናቅ ነው የተቀቡትንም የሚጠይቅ ቀቢው ጌታ ነው።የእኛ ድርሻ መጸለይና "እግዚአብሔር ካዱ" እስካላሉ ድረስ መታዘዝ ነው።የኖረው ክብር ይህ ነው የማያከብር ትውልድ ዕድሜም ፣ ክብርም የለውም የአባቶች ክብር ሊደምቅ እንጂ ሊወድቅ አይገባውም። የአባቶች ፣ የካህናት ክብር እስካልተመለሰ ድረስም ሀገር አይባረክም ምክንያቱም እኒህ አባቶች ወደ ቀባቸው ጌታ ስለሃገር ሰላም ፣በረከት ፣ አንድነት የሚጸልዩ ናቸውና።
ክብር ይመለስ !
ማስተዋል ይስጠን !
ጷጉሜ 02/13/2015 ዓ/ም
👇👇👇👇👇
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
ጳጉሜ 03
"በጎ ምግባር ከበጎ ህሊና ይመነጫል"

+ ለጸሎት እንነሳ +

ወሰን ፣ ገደብ በሌለው በጎነትህ እንደገና ዛሬን ያሳየኸን በሚያምንህም በሚክድህም ሰፈር እኩል ጸሐይ የምታወጣ ፣ ዝናብን የምታዘንብ ቸር አምላካችን ሆይ ተመስገን🙏

ይህን በጎነትህን ያለድንበር ያለአመክንዮ ለፍጥረቱ እንድናንጸባርቅ በመልክህ ፈጥረኸን ሳለ እኛ ግን
በጎነትን በቤተሰብ ፣ በብሄር ፣ በጎሳ ፣ በሰፈር አድርገነው እሱም ነጥፎብን ለራሳችን ስንኳ በጎ መሆን አቅቶን ታመናልና መድኃኔዓለም ሆይ አድነን !

ያለቅድመ ሁኔታ ለሰው ሁሉ በጎ በማድረግ የታመኑትን ግን እንደሰማይ የራቁትን ጥቂት በጎ ሰዎችን ስናይ የምንደነቅ "በዚህ ዘመን ይህን የሚያደርግ አለ?" የምንል ባህሪያችንን የዘነጋን ሆነናልና አቤቱ ታደገን

በጎነት የሌለው እምነት ፣ በጎነት የሌለው ስብዕና ከንቱ ስለሆነ "በእምነታችሁ በጎነት ጨምሩ" ብለህ በቅዱስ ቃልህ ያስተማርከን መምህራችን ሆይ ሃይማኖት ዕረፍት የሚሆነው ፣የሀገር ሰላምና መረጋገት የሚታወጀው በበጎ ህሊና በሰፊ ልብ መሆኑን ዘንግተናልና ወሰን አልባውን ያንተን በጎነት ተመልክተን መንቃትና መዳን ፣ ለቤተሰብ ለጎረቤት ለሀገር ለምድሪቷ መድረስ ይሆንልን ዘንድ ማስተዋልን ትሰጠን ዘንድ የእንደገና አምላክ ሆይ በጎ ምግባር ከበጎ ህሊና ይመነጫልና እንደገና በጎ ህሊናን ትሰጠን ዘንድ እንማጸንሃለን በማያልቀው በጎነትህ ለዘላለሙ አሜን 🙏

ሊ/ዲ/ን መባጽዮን
ጳጉሜ 03/2015 ዓ/ም
👇👇👇👇👇👇
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
ጳጉሜ 04
"ፍቅር ካለ..."
+ እንጸልይ ጸሎት ይለውጣል +

በቤታችን ፣ በሀገራችንና በምድራችን ልማትና ምርታማነት እንዲሆን የዘራነው ይበቅል ዘንድ ዝናብን በጊዜው የምታወርድ የበቀለውም ይበስል ዘንድ ጸሐይንም በጊዜዋ የምታወጣ የዘመን ሁሉ አፈራራቂ ቸር አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ ዛሬም ጠለ ምህረትህን ስለሰጠኸን እናመሰግንሃለን 🙏

ስንፍናን የምትቃወመው ሆይ በረከትን እናገኝ ዘንድ ምድርን ሰጠኸን አርሰን ፣ ጥረን ግረን እንበላ ዘንድ ሰጠኸን መሬት የጣሉለትን ሁሉ በእጥፍ አድርጎ ይሰጣልና ጥሩ ዕድገት አምራችነት የሚረጋገጠውም ዝቅ ብለን ስንሰራ ነው። መጣር ፣ማረስ የእኛ ድርሻ ሲሆን ማብቀል መባረክ ግን ያንተ ነው ያላንተ ያመረተም ብኩን ነው።

ድሮ አባቶቻችን አንተን እያስቀደሙ በፍቅር ተጓዙ የእጃቸውንም ፍሬ ባረክላቸውና ጠግቡ ዛሬ ግን "ፍቅር ካለ......." የሚለው ብሂላችንን ዘንግተን በስግብግብ ማንነት ለየብቻችን ስንጓዝ በልቶ ማደርም ጭንቅ ሆነብን ብዙ ብናከማችም በረከት አልባ ሆንን ጥቂቱን የምታበዛው ሆይ የበረከት ምንጭ አምላካችን ሆይ በጥረታችን ሁሉ ላይ በጸሎት ፣በኑሮ አንተን ማስቀደም ይሆንልን ዘንድ ጥረታችንን ፣ ስራችንን ሁሉ ባርከህልን የራቀንን ፍቅር እንደሸማ አልብሰኸን የምናፈራው ፍሬ ከእኛ አልፎ ብዙዎች የሚረኩበት ይሆን ዘንድ፣ ማስተዋልን ታበዛልን ዘንድ እንማጸንሃለን በሰፊው እጅህ አሜን 🙏

ሊ/ዲ/ን መባጽዮን
ጳጉሜ 04/2015 ዓ/ም
👇👇👇👇👇👇👇
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
⛪️የኢኦተቤክ አስተምህሮ ና ስርአትን የጠበቁ የትኞቹን መዝሙራት ማግኝት ይፈልጋሉ⁉️

👏 የቸብቸቦ መዝሙራት
          📖▓⇨→vido    ⇨ግጥም
🎻 የበገና መዝሙራት  
         📖▓⇨→vido     ⇨ግጥም
👑 የቅዱሳን መዝሙራት
          📖▓⇨→vido    ⇨ግጥም
⛪️ የንግስ መዝሙራት
          📖▓⇨→vido    ⇨ግጥም
🤲 የምስጋና  መዝሙራት
          📖▓⇨→vido    ⇨ግጥም
🙏 የንስሐ  መዝሙራት
         📖▓⇨→vido   ⇨ግጥም
💍 የሠርግ መዝሙራት
          📖▓⇨→avido   ⇨ግጥም
🌦 ወቅታዊ መዝሙራት
          📖▓⇨→vido    ⇨ግጥም
🇪🇹 ለአገር የተዘመሩ

          📖▓⇨→vido   ⇨ግጥም
          👇👇
https://youtu.be/74f62hDwSA4

          👇🏽ከእስልምና ወደ ክርስትና በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ በYOUTUBE👇🏽

         👇🏽🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔻👇🏽
   https://www.youtube.com/channel/UCy1JtUNzSqHW-91lAHXN-NA

           👆🏽🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔺‌‌👆🏽
እንኳን ከ 2015 ዓ.ም ዘመነ ሉቃስ ወደ 2016 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስ በሰላምና በጤና አሸጋገራችሁ!

ዓመቱን ሙሉ ኖረው ይህችን ቀን ሳያዩ ትላንት የሞቱ አሉ። የኖርነው ስለ ፈለግን ሳይሆን ስለ ተፈቀደልን ነው፡ ፡ ይህች ቀን ከሰው የምትሰጥ ብትሆን ኖሮ ባላገኘናት ነበር። እነዚያ የሞቱት በሞኝነት ፣ እኛ የቀረነው በብልጠት አይደለም:: መኖር የአንድ አምላክ ስጦታ ነው:: እንኳን ለዚህች ቀን አበቃን! ዓመቱን የሰላም ያድርግልን!
@meba
👇👇👇👇👇👇
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
" እኛን ለውጠን "

ማይክሮ ሰከንድ ለማይገባን ዘመንን በቸርነትህ የቸርከን አምላካችን ሆይ እናመሰግንሃለን🙏

ዘመን ያንተ ስጦታ እንጂ የማንም ጥረት ውጤት አይደለም ያንተ ስጦታ ደግሞ ሁል ጊዜም መልካም ነው እኛ ግን እኩይ ምግባራችንን ለዘመኑ እያላከክን "ክፉ ዘመን ደግ ዘመን" እያልን ያሳለፍንበትን ጊዜ ይቅር ብለኸን እንደገና ለንስሃ ይህን ዘመን ስለቸርከን ተመስገን🙏

ሰሪያችን ሆይ ባልተለወጠ ማንነት ዛሬም ዘመኑ መልካም እንዲሆን የምንመኝ ምስኪናን ነንና ስህተታችንን አውቀን በሰጠኸን ዘመን መልካሙን ብቻ እንሰራ ዘንድ እኛን ትለውጠን ዘንድ እንለምንሃለን በማያልቀው ምህረትህ አሜን🙏

ሊ/ዲ/ን መባጽዮን (ኢ/ር)
ጳጉሜ 6/2015 ዓ/ም
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
አዲሱ ዓመት

በጎ ነገሮቻችን ሁሉ የሚከናወኑበት ፣ በደስታ ሳቅ የምንፈነድቅበት ፣ የቤተክርስቲያንም የሀገርም ሀዘን የማይሆንበት ፣ በኑሯችን የምንረካበት ፣ እግዚአብሔርን መፍራትና ትህትናን ገንዘብ የምናደርግበት ፣ ፍቅር እንደሸማ የምንለብስበት ፣ ሰላም በምድራችን የሚሰፍንበት፣ ከሰሜን እስከ ደቡብ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ የጦርነትና የሞት ዜና የማንሰማበት፣ ህጻናት ያለሰቀቀን የሚቦርቁበት ፣ ወጣቶች በስራ የሚበረቱበት አዛውንቶች የሚከበሩበት ፣በሀገራችን ባይተዋር የማንሆንበት ፣ የእናቶቻችን ዕንባ የሚገታበት ፣ እንደድሮአችን በመልካም ምግባር ና በአንድነት የምንዋብበት ዓመት ይሁንልን🙏
እንኳን አደረሳችሁ ኢትዮጵያዊያን !
መልካም ርዕሰ አውደ ዓመት🌻!
ሊ/ዲ/ን መባጽዮን (ኢ/ር)
👇👇👇👇👇👇
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
+የስኬታማና የሚያስቀና ትዳር መርህ +

ይድረስ ለባለትዳሮችና ልትጋቡ ለወሰናችሁ እጮኛሞች.........

ሴቶች መወደድን ፍቅርን ይሻሉና ባል ሆይ ሚስትህን ውደዳት ፣ ፍቅር ስጣት ይኸ ማለት ዕንቁ ከመስጠትህ በፊት ጊዜ ስጣት ፣ በቁልምጫ ስም ጥራት

ወንዶች መከበርን ይሻሉና ሚስት ሆይ ባልሽን አክብሪው በጓደኞቹ በወዳጆቹ ፊት ክብር ስጪው ጌታዬ በይው ያኔ በትዳራችሁ ላይ ስትተዋወቁ የነበረው ፍቅር እንደሞቀ እንዳስቀና ይቀጥላል ....ደሞ እኔ አይደለሁም ይህን ያልኹት ታላቁ የሕይወት መዝገብ ነው ያለው👇👇👇

(ወደ ኤፌሶን ሰዎች ምዕራፍ 5)
----------
22፤ ሚስቶች ሆይ፥ ለጌታ እንደምትገዙ ለባሎቻችሁ ተገዙ፤

23፤ ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ እርሱም አካሉን የሚያድን እንደ ሆነ ባል የሚስት ራስ ነውና።

24፤ ዳሩ ግን ቤተ ክርስቲያን ለክርስቶስ እንደምትገዛ እንዲሁ ሚስቶች ደግሞ በሁሉ ለባሎቻቸው ይገዙ።

25-26፤ ባሎች ሆይ፥ ክርስቶስ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤ በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት ስለ እርስዋ ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤

27፤ እድፈት ወይም የፊት መጨማደድ ወይም እንዲህ ያለ ነገር ሳይሆንባት ቅድስትና ያለ ነውር ትሆን ዘንድ ክብርት የሆነችን ቤተ ክርስቲያን ለራሱ እንዲያቀርብ ፈለገ።

28፤ እንዲሁም ባሎች ደግሞ እንደ ገዛ ሥጋቸው አድርገው የገዛ ሚስቶቻቸውን ሊወዱአቸው ይገባቸዋል። የገዛ ሚስቱን የሚወድ ራሱን ይወዳል፤
አምላከ አብርሃም ወሳራ እንደቃሉ እንድትኖሩና በትዳራችሁ እንድትባረኩ ይርዳችሁ !
ሰናይ ምሽት !
ሊ/ዲ/ን መባጽዮን (ኢ/ር)
13/01/2016 ዓ/ም
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
+ መስቀል የድል አርማ +
" ከቀስት ፊት ያመልጡ ዘንድ፥ ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠሃቸው።"
(መዝሙረ ዳዊት 60:4)
ክርስቶስ ለዓለሙ ሁሉ ቤዛ ሆኖ ከመሰቀሉ አስቀድሞ መስቀል የወንጀለኞች መቅጫ ፣ መሰቀያ ፣ የሰቃዮች መዘባበቻ ማላገጫ ነበር 1ኛ ጴጥ 2:24 ጠላት ሊዘብትበት መስቀል ላይ ቢሰቅለው አምላካችን ግን መስቀሉን(መከራውን) የሰውና የእግዚአብሔር መታረቂያ ድልድይ አድርጎ ፣የጥልን ግድግዳ ንዶበት ጠላትንም ራስ ራሱን ቀጥቅጦ አሳፍሮበት ለምናምንበት ሁሉ ዕጸ መስቀሉን የድል ፣ የነጻነት አርማ ፣ ምልክት አድርጎ ሰጠን ክብር ለመድኃኔዓለም ይሁን።

ለዚህ ነው በክርስቶስ አዳኝነት የሚያምኑ አብያተክርስቲያናት ሁሉ በቤተክርስቲያናቸው ላይ ከፍ አድርገው የመስቀል ምልክትን ያስቀምጣሉ ምክንያቱም የድል ዓርማ ስለሆነ በተለይም የጸጋው ግምጃ ቤት የሆነችው ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያናችን ደግሞ በቤተመቅደሶቿ ጉልላት ላይ ፣ በንወየቅድሳቶቿ ላይ በማማተብ ፣በልጆቿ አንገት በማሰር ፣ ብሎን ቀን ሰጥታ መስቀሉን በልዩ ክብር ታከብረዋለች ምክንያቱም ሙሽራዋ ፣ ጌታዋ ክርስቶስ ለእርስዋ ሲል ፣ደሙ የተንጠበጠበበት ተሰቅሎ ጠላትን ድል የነሳበት የነጻነት ፣ የድል አርማ ስለሆነ አሁን ልጆቿ ከጠላት ቀስት የሚያመልጡበት ምልክት ስለሆነ።

ይህን መስቀል አይሁድ ስላፈሩበት ቀበሩት እውነት ተቀብሮ አይቀርምና በጊዜው ወጣ .... ወገኖቼ ጥንት በአይሁዶች አድሮ ያን ሲያደርግ የነበረው የተሸነፈው መንፈስ ዛሬም ይህ አርማ ከፍ ብሎ ሲታይ ያንገፈግፈዋልና በሰዎች እያደረ መስቀሉን በመዘቅዘቅ ፣ "ለመስቀል ክብር መስጠት አያስፈልግም" በሚል ተቃውሞ ለመቅበር ሲሞክር እናያለን ግን አይችልም ክርስቶሳዊያኑ የዳኑበት ፣ የመርገም ዘመንን የተሻገሩበት ነውና ከፍ አድርገው ያከብሩታል እናከብረዋለን። ምክንያቱ የክርስቶስ መስቀል(መከራው) ኃይላችን ፣ ክብራችን ፣ ትምክህታችን ፣ ቤዛችን ምልክቱም የድል አርማችን ነውና እናከብረዋለን አይሁድ ቢክዱትም እኛ እናምንበታለን ምክንያቱም ድነንበታልና 1ኛ ቆሮ 1:18!!!
እንኳን አደረሳችሁ ክርስቶሳዊያን !

ሊ/ዲ/ን መባጽዮን (ኢ/ር)
16/01/2016 ዓ/ም
ዲላ ኢትዮጵያ
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
በኢየሱስ ልደት ወቅት ስጦታ ይዘው የመጡት የሶስቱ ጠቢባን ሰዎች ስም____ነው።
"የመጨረሻ post" ....የዚህ ሳምንት

"ብንሄድ ይሻለናል"

ሰው ወዶ እራሱን በማጥፋት እራሱ ላይ ከባዱን እርምጃ አይወስድም ይህን የመሰለ ከባድ ውሳኔ የሚወስነው ምናልባት የሆነ የሕይወት አጣብቂኝ ውስጥ ሲገባ ፣ የሚኖርለት ነገር ሲያጣ ፣ ተስፋ የሚያደርግበት ነገር ሲጠፋው ፣ በዚህ ዓለም መኖር ትርጉሙ ሲጠፋው ያኔ "ብሄድ ይሻለኛለኛል" ብሎ የጉዞ ቲኬቱን ይቆርጣል ....[ለዚህም ነው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ "ብንሄድ ይሻለናል"በሚል የመጨረሻ የመሰናበቻ ቃል ብዙዎች እራሳቸውን ያፈረሱት]
እናም.....

ምናልባት ዛሬም በዚህ ሰዓት ቀን ሳለ የመሸባችሁ፣ የሚያስጠጋ ወዳጅ ያጣችሁ፣ ጉልበታችሁ የከዳችሁ፣ አልቅሳችሁ እንባ አልቆባችሁ እዥ እያነባችሁ ያላችሁ፣ የሚረዳ ወዳጅ አይዞህ(ሽ) የሚል ቤተሰብ ያጣችሁ፣ የሚፈርድባችሁ እንጂ የሚፈርድላችሁ ያጣችሁ፣ሁሉም ጀርባውን ያዞረባችሁ የመሰላችሁ ፣ በምንም ነገር ተስፋ ያጣችሁ ፣ ጠላት አንድ መፍትሔ ያውም እራስን የማጥፋት መፍትሔ ብቻ የሚያሳያችሁ፣ አንድ መፍትሔ ልጠቁማችሁ ስብሐተ እግዚአብሔር ወደ ሚደርስበት ቃለ እግዚአብሔር ወደሚሰማበት ወደ እግዚአብሔር ቤት(ወደ ቤ/ክ) ብትሄዱ ይሻላችኋል አዎ እሱ ይሻላችኋል።

ለጥቂት ቀናት እራሳችሁን ከዓለም ጫጫታ ሰውራችሁ ሳትናገሩ የልባችሁን ከሚረዳችሁ የልብ አውቃ አምላካችሁ ጋር በጸሎት ፣ በጾም ተነጋገሩ ከቃሉ ጋር ህብረት አድርጉ፣ በተስፋ፣በደስታ ተሞልታችሁ ፣ታሪካችሁ ተቀይሮ ትመለሳላችሁ የማይሆን ይመስላል ግን ይሆናል የቀመስኩትን ነው ቅመሱ የምላችሁ እርሱ መድኃኔዓለም የጽልመታችን ንጋት ፣ በደከመን ሰዓት ብርታት ፣ ስንወድቅ ትንሳኤያችን ፣ የበረሃ ጥላችን ነው ቢመሽም ቢጨላልምብንም እርሱን ተስፋ በማድረግ ወደ ቤቱ ብንሄድ ይሻለናል ሌሊቱን ያነጋዋልና። ለዚህ ነው ንጉሱ ዳዊት ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ ያለው መዝ 122 :1 እናም ወደ እግዚአብሔር ቤት ብንሄድ ይሻለናል።

01/03/2016 ዓ/ም
ሊ/ዲ/ን መባጽዮን (ኢ/ር)
ዲላ_ኢትዮጵያ
👇👇👇👇👇👇
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
ብዙ የምትማሩበት የምትባረኩበት የFacebook ቻነል እነሆ 👇👇👇

https://www.fb.com/l/6lp1kJRRR
2024/06/26 01:54:32
Back to Top
HTML Embed Code: