Telegram Web Link
ጾሙን ከመጀመራችን በፊት ይህንን የእግዚአብሔር ሀሳብ በማስተዋል እናንብብ እና እንተግብር ክርስቶሳውያን

ይህን ሁሉ ዘመን እየጾምን ስለምንድነው መልስ ያጣነው?.... ይኸው መልሱ
👇👇👇👇👇👇👇
(ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ 58)
----------
3፤ ስለ ምን ጾምን፥ አንተም አልተመለከትኸንም? ሰውነታችንንስ ስለ ምን አዋረድን፥ አንተም አላወቅህም? ይላሉ። እነሆ፥ በጾማችሁ ቀን ፈቃዳችሁን ታደርጋላችሁ፥ ሠራተኞቻችሁንም ሁሉ ታስጨንቃላችሁ።

4፤ እነሆ፥ ለጥልና ለክርክር ትጾማላችሁ በግፍ ጡጫም ትማታላችሁ፤ ድምፃችሁንም ወደ ላይ ታሰሙ ዘንድ ዛሬ እንደምትጾሙት አትጾሙም።

5፤ እኔ የመረጥሁት ጾም ይህ ነውን? ሰውስ ነፍሱን የሚያዋርደው እንደዚህ ባለ ቀን ነውን? በውኑ ራሱን እንደ እንግጫ ዝቅ ያደርግ ዘንድ ማቅንና አመድንም በበታቹ ያነጥፍ ዘንድ ነውን? በውኑ ይህን ጾም፥ በእግዚአብሔርም ዘንድ የተወደደ ቀን ትለዋለህን?

መልስ የሚያሰጥ የተወደደ ጾም ምን ዓይነት ጾም ነው ?....አሁንም ይኸው መልሱ
👇👇👇👇👇👇
6፤ እኔስ የመረጥሁት ጾም ይህ አይደለምን? የበደልን እስራት ትፈቱ ዘንድ፥ የቀንበርንስ ጠፍር ትለቅቁ ዘንድ፥ የተገፉትንስ አርነት ትሰድዱ ዘንድ፥ ቀንበሩንስ ሁሉ ትሰብሩ ዘንድ አይደለምን?
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
(ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ 58)
----------
7፤ እንጀራህንስ ለተራበ ትቈርስ ዘንድ፥ ስደተኞቹን ድሆች ወደ ቤትህ ታገባ ዘንድ፥ የተራቈተውንስ ብታይ ታለብሰው ዘንድ፥ ከሥጋ ዘምድህ እንዳትሸሽግ አይደለምን?

8፤ የዚያን ጊዜ ብርሃንህ እንደ ንጋት ይበራል፥ ፈውስህም ፈጥኖ ይበቅላል፥ ጽድቅህም በፊትህ ይሄዳል፥ የእግዚአብሔርም ክብር በኋላህ ሆኖ ይጠብቅሃል።

9፤ የዚያን ጊዜ ትጠራለህ እግዚአብሔርም ይሰማሃል፤ ትጮኻለህ እርሱም። እነሆኝ ይላል። ከመካከልህ ቀንበርን ብታርቅ፥ ጣትህንም መጥቀስ ብትተው፥

10፤ ባታንጐራጕርም፥ ነፍስህንም ለተራበ ብታፈስስ፥ የተጨነቀውንም ነፍስ ብታጠግብ፥ ብርሃንህ በጨለማ ይወጣል ጨለማህም እንደ ቀትር ይሆናል።

11፤ እግዚአብሔርም ሁልጊዜ ይመራሃል፤ ነፍስህንም በመልካም ነገር ያጠግባል አጥንትህንም ያጠናል፤ አንተም እንደሚጠጣ ገነት፥ ውኃውም እንደማያቋርጥ ምንጭ ትሆናለህ።

12፤ ከዱሮ ዘመን የፈረሱት ስፍራዎች ይሠራሉ፥ የብዙ ትውልድም መሠረት ይታነጻል፤ አንተም። ሰባራውን ጠጋኝ፥ የመኖሪያ መንገድን አዳሽ ትባላለህ።

13፤ ፈቃድህን በተቀደሰው ቀኔ ከማድረግ እግርህን ከሰንበት ብትመልስ፥ ሰንበትንም ደስታ፥ እግዚአብሔርም የቀደሰውን ክቡር ብትለው፥ የገዛ መንገድህንም ከማድረግ ፈቃድህንም ከማግኘት ከንቱ ነገርንም ከመናገር ተከልክለህ ብታከብረው፥
" በዚያን ጊዜ በእግዚአብሔር ደስ ይልሃል፥ በምድርም ከፍታዎች ላይ አወጣሃለሁ፥ የአባትህንም የያዕቆብን ርስት አበላሃለሁ፤ የእግዚአብሔር አፍ ተናግሮአልና።
"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 58:14)
👆👆👆👆👆
ከላይ የተጻፈውን ከተገበርነው የበረከት ጾም ይሆንልናል እና ቀድመን ትዕዛዙን እናክብር
*ማስተዋል ይብዛልን* 🙏
👇👇👇👇👇👇
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
ቅድስት ሆይ !

በሔዋን ያዘኑ ባንቺ ካልተደሰቱ ይገርማል ። በሥጋ ድንግል በመሆንሽ በዚህ ብቻ አልተደነቅንም ። በኅሊናም ድንግል ነሽ ። ድንግል በክልኤ/በሁለት ወገን ድንግል ነሽና ለቅዱሱ ቅድስቲቱ አስፈልገሽዋል ። ሊቀ ካህናቱ ብቻ በዓመት አንድ ጊዜ የሚገባባት ያቺ ኅቱም መቅደስ ፣ ቅድስተ ቅዱሳን ትባላለች ። ሊቀ ካህናት ክርስቶስ ብቻ ያደረበት ያንቺ ማኅፀን ከዚያች መቅደስ ይበልጣል ። ከሊቀ ካህኑ ሌላ በዚያች መቅደስ የሚገባ ሰው በሞት ይቀጣል ። እሳተ መለኮት በተቀመጠበት ባንቺ ማኅፀንም ፍጡር ይቀመጥ ዘንድ አይቻለውም ። መጠን የሌለው ክብር ሳለሽ መጠን የሌለው መከራ ተቀበልሽ ። ክብሩ ባየለ ቍጥር መከራውም ብዙ ይሆናል ። ሁሉ ያንቺ ይሆን ሁሉን አጣሽ ። ልጅሽ ብቻ ሀብት እንዲሆንሽ “እፎ ቤተ ነዳይ ኀደረ ከመ ምስኪን” ተባለልሽ ።

ቅድስት ሆይ !

አንቺን የወደደ እግዚአብሔር አብ ቡሩክ ነው !
ካንቺ ሰው የሆነ እግዚአብሔር ወልድ ቡሩክ ነው !
ያጸናሽ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስም ቡሩክ ነው ። ለዘላለሙ አሜን
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
⛪️የኢኦተቤክ አስተምህሮ ና ስርአትን የጠበቁ የትኞቹን መዝሙራት ማግኝት ይፈልጋሉ⁉️

👏 የቸብቸቦ መዝሙራት
          📖▓⇨→vido    ⇨ግጥም
🎻 የበገና መዝሙራት  
         📖▓⇨→vido     ⇨ግጥም
👑 የቅዱሳን መዝሙራት
          📖▓⇨→vido    ⇨ግጥም
⛪️ የንግስ መዝሙራት
          📖▓⇨→vido    ⇨ግጥም
🤲 የምስጋና  መዝሙራት
          📖▓⇨→vido    ⇨ግጥም
🙏 የንስሐ  መዝሙራት
         📖▓⇨→vido   ⇨ግጥም
💍 የሠርግ መዝሙራት
          📖▓⇨→avido   ⇨ግጥም
🌦 ወቅታዊ መዝሙራት
          📖▓⇨→vido    ⇨ግጥም
🇪🇹 ለአገር የተዘመሩ

          📖▓⇨→vido   ⇨ግጥም
          👇👇
https://youtu.be/74f62hDwSA4

          👇🏽ከእስልምና ወደ ክርስትና በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ በYOUTUBE👇🏽

         👇🏽🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔻👇🏽
   https://www.youtube.com/channel/UCy1JtUNzSqHW-91lAHXN-NA

           👆🏽🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔺‌‌👆🏽
አለሁ !!!

ባሕረ ጥበባት በሆንከው ፣ ሁሉን እንደ መላህ በምታኖረው ባንተ አለሁ ። ደዌያትን በቃልህ ፣ አጋንንትን በሥልጣንህ በምትሸኘው ፤ ትላንትን ለመካስ ፣ ዛሬን ለማድረስ ፣ ነገን ለማውረስ አቅም ባለህ ባንተ አለሁ ። የሞትን አዋጅ በሕይወት ፣ የስቅላትን ደብዳቤ በሹመት በምትለውጠው ባንተ በመፍቀሬ ሰብእ/በሰው ወዳዱ ጌታ አለሁ ። የነበረው የነበረ እስከማይመስል ደብዛው ጠፍቷል ፣ ያለው የማያልፍ ይመስል ይሸልላል ። የሚታየው የማይታይ ሲሆን ፣ አፈር የላሰው እንጀራ ሲያገኝ ፣ ተስፋ ያጣው ቀን ሲወጣለት ባንተ ደስ ይለኛል ። እኔ ግን ባንተ አለሁ !

@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
++ አደራህን ሀገሬን ++
" የሁሉ ዓይን አንተን ተስፋ ያደርጋል፤ "
(መዝሙረ ዳዊት 145:15)

ሁሉ ወደ አንተ በማንጋጠጥ የዓይኑ አድራሻ ያደረገህ የማታሳፍረው የአገልጋዩ፣ የገበሬው ፣ የነጋዴው ፣ የተማሪው ፣ የሐኪሙ ፣ የጸሐፊው ፣ የአዛውንቱ ፣ የጎበዛዝቱ ፣ የሕጻናቱ ፣ የፍጥረቱ ሁሉ ተስፋ መፍቀሬ ሰብዕ (ሰው ወዳዱ) ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ተመስገን !

አቤቱ ያለፍንብህ ትናንትናችን ዛሬን ያየንብህ ብርሃናችን የነገም ተስፋችን አንተው ነህ!
ሰው ተስፋ ቢሰጥ ይረሳል አደራ ቢባል ይበላል የነገሩህን የማትረሳ የለመኑህን የማትነሳ አደራ የማትበላው መድኃኔአለም ሆይ ዘወትር እጆቿን ወደ አንተ የምትዘረጋው የሀገሬ ተስፋ አንተው ነህና በፍጹም ሰላምህ ትጎበኛት ለመኳንንቶቿ ማስተዋልን ታበዛ ዘንድ አደራ እንልሃለን አሁንም ተስፋችን አንተው ነህና ድል በሚነሳው ስምህ አሜን 🙏

ሊ/ዲ/ን መባጽዮን (ኢ/ር)
08/12/2015 ዓ/ም
ዲላ ኢትዮጵያ
👇👇👇👇👇👇
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
++ አደራህን ሀገሬን ++
" የሁሉ ዓይን አንተን ተስፋ ያደርጋል፤ "
(መዝሙረ ዳዊት 145:15)

ሁሉ ወደ አንተ በማንጋጠጥ የዓይኑ አድራሻ ያደረገህ የማታሳፍረው የአገልጋዩ፣ የገበሬው ፣ የነጋዴው ፣ የተማሪው ፣ የሐኪሙ ፣ የጸሐፊው ፣ የአዛውንቱ ፣ የጎበዛዝቱ ፣ የሕጻናቱ ፣ የፍጥረቱ ሁሉ ተስፋ መፍቀሬ ሰብዕ (ሰው ወዳዱ) ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ተመስገን !

አቤቱ ያለፍንብህ ትናንትናችን ዛሬን ያየንብህ ብርሃናችን የነገም ተስፋችን አንተው ነህ!
ሰው ተስፋ ቢሰጥ ይረሳል አደራ ቢባል ይበላል የነገሩህን የማትረሳ የለመኑህን የማትነሳ አደራ የማትበላው መድኃኔአለም ሆይ ዘወትር እጆቿን ወደ አንተ የምትዘረጋው የሀገሬ ተስፋ አንተው ነህና በፍጹም ሰላምህ ትጎበኛት ለመኳንንቶቿ ማስተዋልን ታበዛ ዘንድ አደራ እንልሃለን አሁንም ተስፋችን አንተው ነህና ድል በሚነሳው ስምህ አሜን 🙏

ሊ/ዲ/ን መባጽዮን (ኢ/ር)
08/12/2015 ዓ/ም
ዲላ ኢትዮጵያ
👇👇👇👇👇👇
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
"ለምን ያለቀኔ ልሙት? .... በቀኔ ይውሰደኝ እንጂ"

ዛሬ ነው ከሰዓት በኋላ የሆኑ ሰራተኞች ስራ ሰርተው በውላችን መሰረት ባለመስራታቸውና በሆኑ ምክንያቶች ጭቅጭቅ ተነስቶ ጸብ ካላነሳን ብለው "እምቧ ካራዮ" እያሉ ነው አንደኛው ግቶ ነው የመጣውና ሆዱ ያባውን ብቅሉ እያወጣለት የመጣለትን ሁሉ ይተፋል "እባካችሁ ነገ በጠዋት በቀና መንፈስ እንነጋገር" ተብለው ቢለመኑ ቢዘከሩ "አሻፈረን" ይሉ ጀመር ይባስ ብሎ አንደኛው (የጋተው) እየደጋገመ "ዛሬ ብሞትስ " እያለ ይፎክር ጀመር የቃሉ መደጋገም ሲገርመኝ "እንግዲህ ከሞት የሚቀር የለምና ሙታ !" አልኹት በዚህ ሰዓት የቅድሙ አይደለም በገነ(ተናደደ) ስካሩ እስኪለቀው እጅግ ተቆጣ መልሶ "እንዴት እንዲህ ትለኛለህ ለምን ያለቀኔ ልሙት? በቀኔ ልሙት እንጂ" እያለ በጥያቄ ያፋጥጠኝ ጀመር እኔም ጥያቄውን በጥያቄ "ምነው የምትሞትበትን ቀን ታውቃለህ እንዴ? ጌታ ቀንህን ነግሮሃል እንዴ?" ስለው በፍጥነት ረገበና ለደቂቃዎች ዝም አለ ከዚያም ይቅርታ ተባብለን ለነገ ተቀጣጥረን በሰላም ተለያየን።

ለደቂቃዎች ይህ ቃል በአዕምሮዬ ሲመላለስብኝ ላጋራችሁ ወደድኩኝ አዎ ብዙ ጊዜ በተለይ ሰው በድንገት ሲጠራ "ያለቀኑ ፣ ያለጊዜው ፣ ሞተ ምናም" እንላለን እንዴ ታሞ የሚሞት ብቻ በቀኑ የሚሞት በድንገት ደግሞ ሲሞት ያለቀኑ ሟች ያለው ማነው? መጽሐፍ ቅዱስ ግን እንዲህ ይለናል " ቀኒቱንና ሰዓቲቱን አታውቁምና እንግዲህ ንቁ።"
(የማቴዎስ ወንጌል 25:13) እንዲሁም
(የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 24)
----------
43፤ ያን ግን እወቁ፤ ባለቤት ከሌሊቱ በየትኛው ክፍል ሌባ እንዲመጣ ቢያውቅ ኖሮ፥ በነቃ ቤቱም ሊቈፈር ባልተወም ነበር።

44፤ ስለዚህ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፥ የሰው ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና። ስለዚህ ወገኖቼ ማናችንም የምንሞትበትን ቀን አናውቅምና ሁል ጊዜም በወንጌል በማመን፣ በንስሃ ተዘጋጅተን ልንኖር ይገባል።
ማስተዋል ይብዛልን 🙏
ሰናይ ጊዜ
ሊ/ዲ/ን መባጽዮን (ኢ/ር)
18/12/2015 ዓ/ም
👇👇👇👇👇👇
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
+ የብሽሽቅ ወንጌል +
ወገን ይህ የብሽሽቅ አገልግሎት መቼ ይሆን የሚያበቃው? እዛም እዚህም ቤት ሰው እውነት ብሎ የያዘውን ፣ የተረዳውን እውነት ብቻ በሥርዓቱ ለምን አያስኬደውም በዚህ የብሽሽቅ ስብከትስ ማንን ደስ ለማሰኘት ከማን ዘንድ ዋጋ ለማግኘት ነው? ማንንስ ለማጽናት ነው ለምንድነው ትውልዱ እንዲህ ልቅ የሆነው ?...... እንደው በቀና ልቦና አስቡት እስኪ ይኽች ልጅ ምን የቅድስት ቤተክርስቲያናችንን ስርዓት ባታውቅ እንኳ ቤተክርስቲያን እንደሆነ ግን ጠንቅቃ እያወቀች

1ኛ, ሰው ከራሱ ቤት ውጪ ግለሰብ ቤት እንኳ ሄዶ እንደፈለገ መሆን በሚታፈርበትና በማይቻልበት ሀገር እየኖረች የሰማይ ስርዓት በሚከናወንባት ታላቅና ትልቅ ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ ያውም ካሜራ ደግና እንዴት ልትጨፍር ቻለች ?
2ኛ , በሀገራችን ባህል በተለያዬ እንቅስቃሴና ሁኔታ የቀብር ስርዓት ይፈጸም ይሆናል ግን ቀብር ወጥቶ በደስታ እንቅስቃሴ ማድረግና መጨፈር ነውር ነው ካዘኑት ጋር እንድናዝን ከተደሰቱት ጋርም ሀሴት እንድናደርግ የሚያዝ መጽሐፍ ቅዱስ የምትናነብ ሆና እንዴት ቀብር ላይ ፈገግ እያለች ካሜራ ፊት ልትጨፍር ቻለች? ........ ሆን ብላ አብሽቆ ለመፈመስ ካልሆነ

ይህ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ትውልዱን የተጠናወተው ክፉ ነገር ትልቅ ትንሹ በየሚዲያው እየተነሳ እያቆሰለ "ይቅርታ ማሩኝ" ማለት ከዚያ ታዋቂ መሆን ደሞ በየቸርቹ በየአደባባዩ የሆነን አካባቢ የሚያስቆጣ ርዕስ እየተፈለገ መለፈፍና ማስጮኽ ማየት የተለመደ ሆኗል። .......በቃ ይብቃ ተው ይህች ቤ/ክ ውለታዋ ቢዘነጋ እንኳ ምን አደረገች ምንስ አጠፋች ? ደስ የማይል ዓመጽን የሚቀሰቅስ ነውና ይህ ዓይነቱ የብሽሽቅ ስብከት ይቅር በቃ !
ኧረ ጌታ ሆይ ቶሎ ናልን !
ሊ/ዲ/ን መባጽዮን (ኢ/ር)
Share ይደረግ

👇👇👇👇👇👇
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
+ የብሽሽቅ ወንጌል +
ወገን ይህ የብሽሽቅ አገልግሎት መቼ ይሆን የሚያበቃው? እዛም እዚህም ቤት ሰው እውነት ብሎ የያዘውን ፣ የተረዳውን እውነት ብቻ በሥርዓቱ ለምን አያስኬደውም በዚህ የብሽሽቅ ስብከትስ ማንን ደስ ለማሰኘት ከማን ዘንድ ዋጋ ለማግኘት ነው? ማንንስ ለማጽናት ነው ለምንድነው ትውልዱ እንዲህ ልቅ የሆነው ?...... እንደው በቀና ልቦና አስቡት እስኪ ይኽች ልጅ ምን የቅድስት ቤተክርስቲያናችንን ስርዓት ባታውቅ እንኳ ቤተክርስቲያን እንደሆነ ግን ጠንቅቃ እያወቀች

1ኛ, ሰው ከራሱ ቤት ውጪ ግለሰብ ቤት እንኳ ሄዶ እንደፈለገ መሆን በሚታፈርበትና በማይቻልበት ሀገር እየኖረች የሰማይ ስርዓት በሚከናወንባት ታላቅና ትልቅ ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ ያውም ካሜራ ደግና እንዴት ልትጨፍር ቻለች ?
2ኛ , በሀገራችን ባህል በተለያዬ እንቅስቃሴና ሁኔታ የቀብር ስርዓት ይፈጸም ይሆናል ግን ቀብር ወጥቶ በደስታ እንቅስቃሴ ማድረግና መጨፈር ነውር ነው ካዘኑት ጋር እንድናዝን ከተደሰቱት ጋርም ሀሴት እንድናደርግ የሚያዝ መጽሐፍ ቅዱስ የምትናነብ ሆና እንዴት ቀብር ላይ ፈገግ እያለች ካሜራ ፊት ልትጨፍር ቻለች? ........ ሆን ብላ አብሽቆ ለመፈመስ ካልሆነ

ይህ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ትውልዱን የተጠናወተው ክፉ ነገር ትልቅ ትንሹ በየሚዲያው እየተነሳ እያቆሰለ "ይቅርታ ማሩኝ" ማለት ከዚያ ታዋቂ መሆን ደሞ በየቸርቹ በየአደባባዩ የሆነን አካባቢ የሚያስቆጣ ርዕስ እየተፈለገ መለፈፍና ማስጮኽ ማየት የተለመደ ሆኗል። .......በቃ ይብቃ ተው ይህች ቤ/ክ ውለታዋ ቢዘነጋ እንኳ ምን አደረገች ምንስ አጠፋች ? ደስ የማይል ዓመጽን የሚቀሰቅስ ነውና ይህ ዓይነቱ የብሽሽቅ ስብከት ይቅር በቃ !
ኧረ ጌታ ሆይ ቶሎ ናልን !
ሊ/ዲ/ን መባጽዮን (ኢ/ር)
Share ይደረግ
@Yahiwenesei
" የእኛው መለያ ለእኛው እንግዳ ሆኖብን አስደነቀን"

ዛሬ አትሌቶቻችን የተቃቀፉት ፣ የተደጋገፉት በብሔራቸው ፣ በክልላቸው ፣ በጎሳቸው፣ በሰፈራቸው ምክንያት አይደለም እንደውም እንደ ጊዜው በሽታ ቢሆን ኖሮማ 3ቱም የተለያዩ ክልሎች ተወላጆች ነበሩ ግን ያደጋገፋቸው ፣ ያተቃቀፋቸው ፣ ያደመቃቸው፣ ኢትዮጵያዊነትና ኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው ዛሬ ትምህርት መውሰድ ለቻለ ሁሉ ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ ሩጫ ውድድር ነበር ብዙውን ተመልካች ዓይኑን በእንባ የመላ ፣ ዓለምን ያስደመመ ህብረት የታየበት ውድድር ! ይህ ነውና የናፈቀን የእኛው መለያ(አንድነታችን) ለእኛም እንግዳ ሆኖ አስደነቀን ! እናም አንድነታችን ይበጀናል !
ሊ/ዲ/ን መባጽዮን (ኢ/ር)
20/12/2015 ዓ/ም
ዲላ ኢትዮጵያ
👇👇👇👇👇👇
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
⛪️የኢኦተቤክ አስተምህሮ ና ስርአትን የጠበቁ የትኞቹን መዝሙራት ማግኝት ይፈልጋሉ⁉️

👏 የቸብቸቦ መዝሙራት
          📖▓⇨→vido    ⇨ግጥም
🎻 የበገና መዝሙራት  
         📖▓⇨→vido     ⇨ግጥም
👑 የቅዱሳን መዝሙራት
          📖▓⇨→vido    ⇨ግጥም
⛪️ የንግስ መዝሙራት
          📖▓⇨→vido    ⇨ግጥም
🤲 የምስጋና  መዝሙራት
          📖▓⇨→vido    ⇨ግጥም
🙏 የንስሐ  መዝሙራት
         📖▓⇨→vido   ⇨ግጥም
💍 የሠርግ መዝሙራት
          📖▓⇨→avido   ⇨ግጥም
🌦 ወቅታዊ መዝሙራት
          📖▓⇨→vido    ⇨ግጥም
🇪🇹 ለአገር የተዘመሩ

          📖▓⇨→vido   ⇨ግጥም
          👇👇
https://youtu.be/74f62hDwSA4

          👇🏽ከእስልምና ወደ ክርስትና በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ በYOUTUBE👇🏽

         👇🏽🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔻👇🏽
   https://www.youtube.com/channel/UCy1JtUNzSqHW-91lAHXN-NA

           👆🏽🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔺‌‌👆🏽
"ስለማርያም ብትዘምር ኖሮ ማንም አይናገራትም ነበር "

እንደነርሱ ያልተናገረ ፣እንደእነርሱ ያልተራመደ ፣ እንደእነርሱ ያላሰበ፣እንደእነርሱ ያለበሰ ፣ እንደእነርሱ ያልተጫማ ፣ በአጠቃላይ እንደእነርሱ ያልሆነ፣ የማይኖር ሰው ትክክል ያልሆነ የሚመስላቸው ምስኪናን ሰዎች አሉ።

እንደዚሁ ሁሉ ብዙዎች ይህችን ሐዋርያዊት ሥርዓት ያላት ታላቂቱን ቤተክርስቲያን ኢየሱስን አትሰብክም ፣ ሸፍናዋለች bla bla ሲሉ መስማት የተለመደ ሆኗል። በቅርቡም በድፍረት የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ሳትሆን በቤተክርስቲያኒቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ በሌሎች ቤተ እምነት መዝሙር እየጨፈረች ቪዲዮ በሰራችው ኤዶም በምትባለው ልጅ ምክንያት ብዙዎች "ስለኢየሱስ ስለዘመረች ነው ኦርቶዶክሳዊያን የተነሱባት ስለማርያም ዘምራ ቢሆን እንዲህ አይሆኑም ነበር" እያሉ ነገሩን ሲያራግቡ ሰምተናል።

እውን ግን ይህች ሐዋርያዊት ቤ/ክ ኢየሱስን አትሰብከውምን ?..በእርግጥ በኪፖርድና በጊታር ስላልጨፈረች ያልሰበከች ሊመስለው የሚችል ምስኪን አለ። ነገር ግን በቀና ልቦና ሥርዓተ አምልኮቷን ለተመለከተ አስተዋይ ሰው የዜማ ዕቃዎቿ ሳይቀር ኢየሱስ ክርስቶስን የሚሰብኩት ሆነው ነው የሚያገኘው።

ለምሳሌ በስርዓተ ማህሌቷ አባቶች ካህናት ግራና ቀኝ ተሰልፈው መቋሚያቸውን ትከሻቸው ላይ አድርገው፣ ጸናጽላቸውን ይዘው ፣ ወደ ፊት ወደ ኋላ ወደ ግራ ወደቀኝ እየተንቀሳቀሱ ሲወርቡ፣ ሲያመሰግኑ ለተመለከተ ምስኪን ሰው ተራ ትርኢት (show) ሊመስለው ይችላል ነገር ግን በማስተዋል ምሳሌውን ትርጉሙን ለጠየቀ የጌታን ሕማም የሚማርበት የስብከት ዐውድ ሆኖ ያገኘዋል የእንቅስቃሴው ምሳሌና ትርጉም ወደፊት ወደኋላ ወደ ግራና ቀኝ መንቀሳቀሳቸው በአራቱም ወንጌላት እንደተጻፈው ጌታ ስለሁላችን በደል ቤዛ ሊሆን በተያዘባት በዚያች ዕለት ከጌቴሰማኒ እስከ ጎልጎታ በነበረው ጉዞ ወደፊት ወደ ኋላ እየጎተቱት ወደ ግራና ቀኝ እገፉት የተጓዘውን ጉዞ እያሰቡ በአራቱም አቅጣጫ እንቅስቃሴ እያደረጉ ያመሰግናሉ....ስለዚህ ከማንም ዘመናዊ ጭፈራና ዳንስ ጋር የማይነጻጸረው ይህ በወረቡ የሊቃውንቱ እንቅስቃሴ እንኳ ሰፊውን የኢየሱስን ሕማም የሚሰብክ ነው ለዚህ ቤተክርስቲያንን ምስጢር ናት የምንለው..... ይቀጥላል

ሊ/ዲ/ን መባጽዮን (ኢ/ር)
24/12/2015 ዓ/ም
ራጴ ኢትዮጵያ
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
"ቆይ እንዴት ይህ አይሆን??"

ጦርነት ሲሆን ወንድም ወንድሙን ሲወጋ መደነቅ ፣መገረም ....ረሃብ ቸነፈር ሲሆን ... መገረም ፣መደነቅ ......ኑሮ ሲወደድ እንደገና መገረም መደነቅ ...... "ኧረ ጉድ ነው ዘንድሮ" ማለት ከቤተክህነት እስከ ቤተመንግስት ጆሮን ጭው የሚያደርግ ነገር ሲከሰት ፣ ሲከናወን ....በቃ ...... አመክንዮ ፍለጋ መዋከብ ፣ ማራገብ ...."ይገርማል እንዴት ይህ ሆነ" እያሉ .....መናደድ ፣ መቆጨት ፣ ደግሞ መገረም ደግሞ መደነቅ ........ኧረ ወገን ....ቆይ እንዴት ይህ አይሆን?? ሰማይ ምድር ያልፋል እንጂ ቃሉ'ኮ አያልፍም ይፈጸማል። ይህ ሁሉ እንደሚሆን'ኮ ቀድሞ ተነግሮናል.ማቴ 24 :25....ግን የትንቢቱ መፈጸምያ ሲኮን አያስገርምም እጅግ ያሳዝናል...... ገና መች አይተን ርኩሰት በተቀደሰው ስፍራ ቆሞ ልናይ እንችል ይሆናል ያኔ ግን ተደነቁ ተገረሙ አይደለም ያለን ቅዱስ ወንጌሉ "አንባቢው ያስተውል ! "ማቴ 24 :15 ብሎ ነው የነገረን ስለዚህ የዘመን ፍጻሜ መሆኑን አስተውለን በእግዚአብሔር ፊት ንስሃ እንግባ !
በወርሃ ጷጉሜን በ6ቱ ቀናትም ይህን እንድናደርግ ነው ቤ/ክ ያዘዘችን ማስተዋል ይብዛልን ሰናይ የጾም ፣የጸሎት ፣ የንስሃ ሰሞን ይሁንልን !
ሊ/ዲ/ን መባጽዮን (ኢ/ር)
30/12/2015 ዓ/ም
ዲላ_ጪጩ ኢትዮጵያ
👇👇👇👇👇👇
ሊንኩን ንኩት
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
ጷጉሜ 01
" ሰላም ለሀገራችን ~ሰላም ለምድራችን "
+ ተንስኡ ለጸሎት +
ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣኸን የሕይወት ምንጭ አምላካችን ሆይ ማይክሮ ሰከንድ ለማይገባን አንተን እስትንፋሳችንን ቸል ላልንህ ቸል ሳትለን በፊትህ እንደገና የምናንጋጥጥበትን ጊዜ በምህረትህ ብዛት ስለቸርከን እናመሰግንሃለን🙏

የፍጥረት ሁሉ ጌታ ማዕበል ፣ ሞገዱ ፣ነፋሳቱ ሁሉ የሚታዘዙልህ ንውጽውጽታውን የምታረጋጋው የጸጥታ ወደባችን ሆይ ሰላም መረጋጋትን ለብዙ ዘመናት ብንሻም የነጭ እርግብ ምስል እየሰራን ከማሳየት ፣ ከመመኘት ውጪ ፍጹም ሰላምን ማምጣት አልቻልንም "ሰላሜን እሰጣችኋለሁ" ያልከን ሰላማችን ሆይ እውነተኛ ሰላም ካንተ ዘንድ ነውና ፣ ለእኛ ክቡድ የሆነውም በአንተ ዓይን ቀላልና ሀገራችንን እየናጣት ያለውን የጦርነት ፣ የጥላቻ ፣ የረሃብ፣ የቸነፈር ማዕበል ገስጸህ ፍጹም ሰላምህን ለሀገራችን ኢትዮጵያ ለምድራችን ታድል ዘንድ እኛም ሁል ጊዜ ቃልህን ለመስማት የነቃን የበቃን የዘተጋጀን እንድንሆን ማስተዋልን ትሰጠን ዘንድ እንለምንሃለን። ስልጣን ባለው ስምህ ለዘለዓለሙ አሜን 🙏

ሊ/ዲ/ን መባጽዮን (ኢ/ር)
ጳጉሜ 01/13/2015 ዓ/ም
ራጴ ~ኢትዮጵያ
👇👇👇👇👇👇
ሊንኩን ይንኩት
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
ጷጉሜ 02

" የሞትክለት ከቶ አይሙት "
+ ተንስኡ ለጸሎት +
ስለዓለም ሁሉ ድኅነት መስዋዕት ፣ መስዋዕት አቅራቢም ፣ መስዋዕት ተቀባይም ሆነህ ይህን ዓለም አንድ ጊዜ በደምህ ያዳንኸው ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ውለታህን ዕለት ዕለት ባናስታውስም እንኳ ዳግም ይህን ዕለት በበዛው ምህረትህ እንኩ ስላልከን የምንሰጥህ ሌላ የለንም ቀናችንን ፣ የከንፈራችንን ፍሬ ምስጋናችንን እንካ እንልሃለን🙏

ንጹሁ መስዋዕታችን ኢየሱስ ሆይ ጥንት አባቶቻችን እነ አቡነ ጴጥሮስ ለዘላለም ቤታቸው ለሃይማኖታቸው ፣ ለሃገር ነጻነት ለህዝባቸው ሲሉ አንዲት ነፍሳቸው ሳታሳሳቸው በጠላት ጥይት ተረፍርፈው መስዋዕት ሆኑ መስዋዕትነት ለብዙሃን ጥቅም ለብዙዎች ህልውና እራስን አሳልፎ ለመከራ ፣ ለሞት መስጠት ነውና ........ ዛሬ ዛሬ ግን ለማን መስዋዕት መሆን እንዳለብን እንኳ ግራ ገብቶን የምንሞትለትን ጉዳይ እንኳ በቅሉ ሳንረዳ በጠላት ወሬ ና ሴራ ተጠልፈን ለስልጣን፣ ለጥቅም ብለን ብዙዎቹን ይዘን እርስ በእርስ የምንተላለቅ ሆነናልና.......

ለዓለም ድኅነት በመስቀል ላይ መስዋዕት የሆንከው የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ሆይ የሞትክለት አይሙት የደማህለት አይድማ በደምህ በርነት ወደ አባትህ መግባት ይሆንለት ዘንድ አብርሆትን፣ ለማን መስዋዕት መሆን እንዳለብን ለሃገርና ፣ለሃይማኖት የሚከፈለውን መስዋዕትነት እውነት የምንረዳበትን ማስተዋል ታድለን ዘንድ ፣ ልባቸውን ከእውነት አርቀው ድብቅ አጀንዳ ሸክፈው ትውልድ እንዲማገድ ፣ የሃገር ኢኮኖሚ እንዲደቅ "በለው በለው" እያሉ የሚያቀጣጥሉትን እነ ሆድ አምላኩን ወደ ልባቸው ትመልስልን ዘንድ ተጸጽተውም የአንድነትን ሀሳብ ማፍለቅ ይሆንላቸው ዘንድ ፍጹም ሰላምህ ይከብበን ዘንድ እንማጸንሃለን በተወጋው ጎንህ ለዘለዓለሙ አሜን🙏

ሊ/ዲ/ን መባጽዮን (ኢ/ር)
ጷጉሜ 02/13/2015 ዓ/ም
ራጴ ~ኢትዮጵያ
👇👇👇👇👇👇
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
ጷጉሜ 02

+ ክብረ ክህነት +

ከጣሊያን ጦርነት በኋላ ንጉሱ ጃንሆይ ወደ መንበራቸው ከተመለሱ በኋላ ራስ ስዩም ከራስ ካሣ በታች ሲቀመጡ ንጉሡ ያያሉ ይህን ሁኔታ የተመለከቱት ንጉሡ ራስ ስዩምን "ምነው ከራስ ካሳ በታች ተቀመጥክ?" ብለው ጠየቁት (ራስ ስዩም የንጉሥ ዮሐንስ የልጅ ልጅ ስለነበሩ ቀድሞ ከራስ ካሳ ከፍ ብለው ነበርና የሚቀመጡት) ራስ ስዩምም ለንጉሡ "ራስ ካሳ ክህነት ስላላቸው ብዬ ነው" ብለው መለሱላቸው ንጉሡም አላወቁም ነበርና ከዚያ በኋላ ሁለቱንም በእሳቸው በቀኝና በግራ አስቀመጧቸው።

አዊ ከንግሥና ክብር የካህን ክብር ይበልጣል።በዚህ ዓለም ላይ ከታወቁ ክብሮች አንዱ የቤ/ክ አባቶችና አገልጋዮች ክብር ነው። የተቀቡትን ማክበር ቀቢውን ጌታ ማክበር ነው። የተቀቡትን መናቅም ቀቢውን ጌታ መናቅ ነው የተቀቡትንም የሚጠይቅ ቀቢው ጌታ ነው።የእኛ ድርሻ መጸለይና "እግዚአብሔር ካዱ" እስካላሉ ድረስ መታዘዝ ነው።የኖረው ክብር ይህ ነው የማያከብር ትውልድ ዕድሜም ፣ ክብርም የለውም የአባቶች ክብር ሊደምቅ እንጂ ሊወድቅ አይገባውም። የአባቶች ፣ የካህናት ክብር እስካልተመለሰ ድረስም ሀገር አይባረክም ምክንያቱም እኒህ አባቶች ወደ ቀባቸው ጌታ ስለሃገር ሰላም ፣በረከት ፣ አንድነት የሚጸልዩ ናቸውና።
ክብር ይመለስ !
ማስተዋል ይስጠን !
ጷጉሜ 02/13/2015 ዓ/ም
👇👇👇👇👇
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
ጳጉሜ 03
"በጎ ምግባር ከበጎ ህሊና ይመነጫል"

+ ለጸሎት እንነሳ +

ወሰን ፣ ገደብ በሌለው በጎነትህ እንደገና ዛሬን ያሳየኸን በሚያምንህም በሚክድህም ሰፈር እኩል ጸሐይ የምታወጣ ፣ ዝናብን የምታዘንብ ቸር አምላካችን ሆይ ተመስገን🙏

ይህን በጎነትህን ያለድንበር ያለአመክንዮ ለፍጥረቱ እንድናንጸባርቅ በመልክህ ፈጥረኸን ሳለ እኛ ግን
በጎነትን በቤተሰብ ፣ በብሄር ፣ በጎሳ ፣ በሰፈር አድርገነው እሱም ነጥፎብን ለራሳችን ስንኳ በጎ መሆን አቅቶን ታመናልና መድኃኔዓለም ሆይ አድነን !

ያለቅድመ ሁኔታ ለሰው ሁሉ በጎ በማድረግ የታመኑትን ግን እንደሰማይ የራቁትን ጥቂት በጎ ሰዎችን ስናይ የምንደነቅ "በዚህ ዘመን ይህን የሚያደርግ አለ?" የምንል ባህሪያችንን የዘነጋን ሆነናልና አቤቱ ታደገን

በጎነት የሌለው እምነት ፣ በጎነት የሌለው ስብዕና ከንቱ ስለሆነ "በእምነታችሁ በጎነት ጨምሩ" ብለህ በቅዱስ ቃልህ ያስተማርከን መምህራችን ሆይ ሃይማኖት ዕረፍት የሚሆነው ፣የሀገር ሰላምና መረጋገት የሚታወጀው በበጎ ህሊና በሰፊ ልብ መሆኑን ዘንግተናልና ወሰን አልባውን ያንተን በጎነት ተመልክተን መንቃትና መዳን ፣ ለቤተሰብ ለጎረቤት ለሀገር ለምድሪቷ መድረስ ይሆንልን ዘንድ ማስተዋልን ትሰጠን ዘንድ የእንደገና አምላክ ሆይ በጎ ምግባር ከበጎ ህሊና ይመነጫልና እንደገና በጎ ህሊናን ትሰጠን ዘንድ እንማጸንሃለን በማያልቀው በጎነትህ ለዘላለሙ አሜን 🙏

ሊ/ዲ/ን መባጽዮን
ጳጉሜ 03/2015 ዓ/ም
👇👇👇👇👇👇
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
2024/07/01 01:12:00
Back to Top
HTML Embed Code: