Telegram Web Link
🌻 በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፥ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል🌻
(መዝሙረ ዳዊት 65:11)
አዎ ገቢና ወጪያችን ሳይመጣጠን ተመግበን የኖርነው በቸርነቱ ነው። የተደገፍንባቸው ሁሉ ተሰብረው ገሚሶቹም እንደሸምበቆ ወግተውን ያልወደቅነው በቸርነቱ ነው። የሚዝቱብን በዝተው ያልጠፋነው በቸርነቱ ነው። "አለቀለት/ላት/" እየተባልን እንደገና አዲስ የሆነው በቸርነቱ ነው። ያለ ቀልባችን ሁነን ስንበርና ስንዋከብ አደጋውን ያለፍነው በቸርነቱ ነው።
በረሃብ ዘመን በልተን ያደርነው በቸርነቱ ነው። ተምረን የተመረቅነው፣ ነግደን ያተረፍነው፣ ተናግረን የተሰማነው ፣አግብተን የወለድነው ፣ ወልደንም የሳምነው፣ አርሰን የሰበሰብነው ፣በፊቱ ለአገልግሎት የቆምነው በቸርነቱ ነው። ጊዜአችንን በኃጢአትና በበደል ጭርስ አድርገን ደግሞ እንደገና ለንስሃ ዘመን የተቀዳጀነው በቸርነቱ ነው።
ለዚህ ያደረሰን ቸር አምላካችን እግዚአብሔር እናመሰግነዋለን🙏🙏🙏 !!!
ሰዎች ዓመት ለንስሃ ተጨመረልንኮ እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን አደረሳችሁ🙏🌻😍 !!!

05/13/2014
ሊቀ ዲ/ን መባ
👇👇👇👇👇👇
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
ስላለህ አለሁ!

እኔ አለሁ ጌታዬ፣ አንተስ እንደምን አለህ? ድሆች በረከትን፣ ግፉዓን ፍርድን ፣ ብቸኞች የመኖር ጉልበትን ይለምኑሃል። ቀኑ ያደከማቸው "ልበ ሰፊ ፣ ነገር አላፊ አርገኝ" ይሉሃል። ጥሩ ኑሮ ሳይሆን ጥሩ ሞት በሚናፈቅበት ዘመን መኖር ገራሚ ነው። ካንተ ካልሆነ ይህ ከወዴት ይገኛል? ሁሉ የሚገኝብህ መዝገብ ሆይ በመኖር ስለባረከኝ ተመስገን! ስጠራጠርህ እየታመንህልኝ ፣ በጠላቶች ጉልበት ልክ ስለካህ አንተ አልተቀየምከኝም። ፈራጅ የለም ስልህ አንተ ግን በማይናወጥ ዙፋን አለህ! ምን እልህ ይሆን? የፈጠርከውን ላልፈጠረ ጨካኝ አሳልፈህ አትስጠው። ዘመኑን ብቻ ሳይሆን እኛንም ለውጠን። ልብ ለልብ መገናኘት ተረት እንዳይሆንብን አስበን። ዓመቱን በሰላም አስፈጽመን! ምስጋናችን ይኸው ይድረስህ!
01/01/2015
👇👇👇👇👇👇
@Yahiwenesei
➥60k በላይ ተከታይ ያለው
➥ከ850k በላይ like ያለው
➥ከ8M በላይ view ያለው Tik Tok አካውንት መግዛት የሚፈልግ ያናግረኝ።

@YILE_ORTODOX
ንጉሥ ፈርኦን ለ ያዕቆብ ሐበሻ በጣም የሚጠላውን ጥያቄ ጠየቀው:: "ዕድሜህ ስንት ነው?"

ከባሕላችን እጅግ ሊላቀቀን ያልቻለ ጥያቄ ቢኖር ዕድሜን መናገር መፍራት ነው:: "ኸረ ዕድሜዬን አልደብቅም" የምንል ሰዎች እንኳን ከመናገራችን በፊት "ዕድሜ ጸጋ ነው" የሚል ትንሽ የመግቢያ ንግግር እናደርጋለን:: በሰው ፊት ዕድሜ የጠየቁ ሕፃናትም “ዕድሜ አይጠየቅም እሺ ማሙሽዬ" የሚል ምክር ከትንሽ ቁንጥጫ ጋር ይቀምሳሉ::
ንጹሐኑ ሕፃናት ትምህርት ቤት "How old are you?”ን ሲያነቡ ስለሚውሉ ለምን እንደማይጠየቅ ግራ ግብት ይላቸዋል:: ብቻ በአጭሩ "ዕድሜህ ስንት ነው?" ተብለን ስንጠየቅ "ሰዓት ስንት ነው?" ስንባል በምንመልስበት ፍጥነት አንመልስም::

ያዕቆብ ግን ፈርኦን ሲጠይቀው የሐበሻ ደም የለበትምና "የእንግድነቴ ዘመን መቶ ሠላሳ ዓመት ነው" ብሎ ቀልጠፍ ብሎ መለሰ:: የሚገርመው በምድር ላይ የኖረበትን ዘመን "የእንግድነት ዘመን" አለው:: እውነትም ይህች ዓለም ሁላችንም ለጊዜው በእንግድነት የመጣንባት ናት እንጂ ሀገራችንስ በሰማይ ነው:: በእንግድነት መጥተን ዘላለም እንደሚኖር እንነካከሳለን እንጂ እንግዶች ነን:: እንደ ያዕቆብ ያሉ ቅዱሳን ግን "በምድሪቱም እንግዶችና መጻተኞች እንዲሆኑ ታመኑ" (ዕብ 11:13) ሁሉን ትተው የተከተሉት ሐዋርያቱም "በእንግድነታችሁ ዘመን በፍርሃት ኑሩ" ብለው አስተማሩ:: (1ኛ ጴጥ 1:17)

ያዕቆብ ዕድሜዬ 130 ነው ካለ በኁዋላ ጥቂትም ክፉም ሆነብኝ አለ:: እንግዲህ መቶ ሠላሳ አንሶት ነው:: እርግጥ ነው ሰው ዕድሜ አይጠግብም:: ማቱሳላንም ብንጠይቀው "ባጭር ተቀጨሁ" ማለቱ አይቀርም:: የተፈጠርነው ከዘላለማዊት ነፍስ ጋር ስለሆነ ለመኖር እንጂ ለመሞት መቼም ዝግጁ አንሆንም:: እንደ ያዕቆብ ያለ ብዙ ነገር ያየ ሰው ደግሞ ዕድሜህ ያንስብሃል:: ከእናትህ ሆድ ጀምረህ የሕይወት ትግል ከጀመርክ ለብኩርና ከተሽቀዳደምክ : ከፈጣሪህ ጋር ትግል ከገጠምክ : ድንጋይ ተንተርሰህ ሰማይ ድረስ ከተመለከትክ : ለራሔል ዓሥራ አራት ዓመት ደጅ ከጸናህ : በዮሴፍ ለዓመታት ካለቀስክ ዕድሜህ ቢያጥብርህ አይፈረድብህም::

ያልተኖረ ዕድሜ ግን ይሰለቻል:: ሰው ሥራ ሲኖረው ቀኑ እንዴት ይሮጣል? ይላል:: ሥራ የፈታ ደግሞ "ኸረ የዛሬው ቀን አልሔድ አለ እኮ" ይላል:: በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪካቸው ከተጻፈ ሰዎች የሚያሳዝኑት "ኖረ ሞተም" የተባለላቸው ሰዎች ናቸው:: መኖርህ ካልፈየደ መሞትህ አይጎዳም ከመባል በላይ ምን አስከፊ ነገር አለ::

ወዳጄ አንተ ወደዚህች ምድር የመጣ አንተን የሚመስል ብቸኛው ሰው ነህ:: የማያልቅበት ፈጣሪ የአንተን ዓይነት ሰው ፈጥሮ አያውቅም ድጋሚም አይፈጥርም:: ምድርም የአንተ ዓይነት ሰው አይታ አታውቅም:: ዕድሜ የተሠጠህ ለአንተ ብቻ የተሠጠህን ነገር አበርክተህ እንድትሔድ ነው:: በአንተ ብቻ የሚፈታ ችግር በአንተ ብቻ የሚፈጠር ብዙ መፍትሔ አለ::

ሌሎች ከአንተ በሀብት በእውቀት በሥልጣን ወዘተ በልጠው ልታይ ትችላለህ:: ሕይወት ፍትሐዊ አይደለችም:: ፈጣሪ ያደላል ወይ ልትል ትችላለህ::
ከሀብታሙም ከአዋቂውም ከኃያሉም እኩል ለአንተ የተሠጠህ ፍትሐዊ ሥጦታ ግን ጊዜ ነው:: ለሁሉም ሰው ቀንና ሌሊቱ ሃያ አራት ሰዓት ነው:: በብራቸው ሰዓት ያስጨመሩ የሉም:: አጠቃቀምህ ነው እንጂ ጊዜ ለአንተም በእኩልነት ተሠጥቶሃል::

ዐዲስ ዓመት ሊገባ ነው:: ፀሐይ እያየችን ስታልፍ ሌላ አንድ ዓመት ሆናት:: 2012 አይቻልም እንጂ በድንጋይ ፈንክተን ብንሸኘው ደስ የሚለን ዓይነት ከባድ ዓመት ነበር:: አሁን ደግሞ ፈጣሪ በቸርነቱ ሌላ ዘመንን አቀዳጀን:: ፈጣሪ የሠጠን ያልተጻፈበት አዲስ ደብተር ነው:: ብዕሩ እጃችን ላይ ነው:: ምን እንጽፍበት ይሆን? ካለፈው ደብተር የቀጠለ ታሪክ እንጽፍ ይሆን? ወይስ አዲስ ነገር?

መልካም አዲስ ዓመት

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
👇👇👇👇👇👇
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፥ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ። "
(ትንቢተ ኢሳይያስ 41:10)

የዘንድሮ 12ኛ ክፍል ተፈታኞች እህት ወንድሞቼ :-
የጥበብ ፣የዕውቀት፣ የማስተዋል ሁሉ ምንጭ የሆነው እግዚአብሔር ላለፉት ጊዜያት ደክማችሁ ፣ለፍታችሁ፣ ያነበባችሁትን ፣ ያጠናችሁትን በፈተናችሁ ወቅት አስተውላችሁ ትሰሩ ዘንድ ማስተዋልን ያድላችሁ🙏

እግዚአብሔር መንፈስቅዱስ በዚህ ጊዜ ፍጹም መረጋጋትን ያድላችሁ🙏
በሽታ፣ ህመምን፣ ጭንቀትን ክፉውን ሁሉ ከእናንተ ያርቅላችሁ🙏

ለፈተና ስትቀመጡ በማማተብ አቡነ ዘበሰማያትን ጸልያችሁ በስመ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ የፍርሃትና የጭንቀት መንፈስን አስወግዳችሁ ጀምሩ "እርሱን ያስቀደመ አያፍርምና" በርቱ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን🙏

👇👇👇👇👇👇
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
ኃጢአት አንገዳግዶት፣ ለተወላገደው
ከማዕዱ ቀርቦ ፣ ጽድቅን ለተራበው
ወንዝ ዳር ተተክሎ ፣ፍሬን ላላፈራው
ቅጠሉም እረግፎበት፣ ምልምሉን ለቀረው
እስክትመጣ ድረስ ፣ አትርፎ እንዲያፈራ
የቸርከውን መክሊት ፣ ብለኸው "አደራ"
በዝንጋዔ መንፈስ ፣አደራህን በልቶ
ቸል ላለው ባርያህ ፣ስራውን ዘንግቶ
ሰማዩን ለረሳ፣ ያ'ለም ተድላን ሽቶ
እኮ ምኑን አይተህ ፣ምን ቢያደርግልህ
ዘመን የሰጠኸው........
ቸሩ የኔ ጌታ ፣ ዓመትን ያደልከው
አውቃለሁ አምላኬ ፣ምናልባት ቢለወጥ፣እንደሆን ብለህ፣ ዓመት እንደቸርከው
በመቆረጥ ፈንታ ፣በሕይወት ያኖርከው
አደራ ጌታ ሆይ ፣አደራን የማትበላው
ዳግም እንዲያፈራ፣ ዕድል ከሰጠኸው
ዋጋ የከፈልክበት፣ ያበጀኸው ሸክላህ ፣
ዛሬም በእጆችህ ነው
ካንተ የሆነውን ሕይወት፣ ላንተው እንዲኖረው
አሮጌው ውድህን፣ በመንፈስህ ጋርደህ፣እንደገና ሥራው
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ።" ዮሐ 14:18

የዛሬ ሳምንት ዕለተ ዓርብ 04/02/2015 ዓ/ም በጠዋት ወደማገለግልበት ጪጩ ደ/ኃ/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ የሰበካ ጉባኤ ስብሰባ ስለነበረብኝ ወደዛ አቀናሁ የመወያያ አጀንዳው ተጀምሮ አርፍጄ ገባሁ ሰዓቱ ወደ 1:30 አካባቢ ነበር ።

የስብሰባው የመጨረሻ ሀሳብ አካባቢ ዲላ ጪጩ አብራኝ የምትኖረዋ ታላቅ እህቴ ደወለችልኝ ደጋግማ ስትደውል አነሳሁኝና "ምነው" አልኳት "ወንድሜ አባታችን በጠና ታሞ አምቡላንስ እየፈለግን ነው" ብለው ደወሉልኝ አለች ሰዓቱ 3:10 አካባቢ ነው እንጃ በጣም ደነገጥሁ በትውልድ አካባቢዬ የማውቃቸውን የጤና ባለሙያዎች ጋር ደወልኩ አባታችሁ አሞታል ብለውኝ ወደዛው እየሄድኩኝ ነው አለኝ አንደኛው ወዳጄ።

በዚህ መሃል ከትውልድ አካባቢዬ በተደጋጋሚ ስልክ ይደወልልኝ ጀመር "በጣም አሞታልና ና" የሚል ነው ሁሉም ደነገጥኩኝ የተወያየንበትን ቃለ ጉባኤ መፈረም አቃተኝ አብረውኝ የነበሩት አገልጋዮች ተረጋጋ ምን ሆነህ ነው ብለው ያረጋጉኝ ጀመር አባቴን ካየሁት 1 ወር ሞልቷል ድምጹን ከሰማሁ ደግሞ 2 ቀናት ያክል ቆይቻለሁ ምንም አልሆነም ነበር ደህና ነበር ምን ነካው ውስጤ እየተብሰለሰለ ከቤ/ክ ተፈትልኬ ወጣሁ ሞተር ጠራሁና ወደ ቤት ሄድኩ ስሄድ እህቴ ታነባለች ምን እንደሆነ ሳላውቅ እንባ በአይኔ ሞልቶ ይፈስ ጀመር ከዚያም ተያይዘን በሞተር ወደ ትውልድ መንደሬ አመራን።

ገና ወደ ከተማዋ ስንገባ አንዳንድ ነጠላ አዘቅዝቀው የለበሱ እናቶችን ተመለከትኩኝ ልቤ ይበልጥ ይመታ ጀመር ጉልበቴ ሁሉ ተንቀጠቀጠ "አይሆንም መቼም ቢያመው ብቻ ነው" አልኩኝ ለራሴ ከዚያም የከተማዋን አደባባይ ሳልፍ ፊት ለፊት ቤታችን አካባቢ ይታያልና አማተርኩኝ ድንኳን ተደኩኗል አፌ ደም ደም አለኝ ከሞተሩ ላይ ልንወድቅ ደረስን እህቴ ጩኸቷን አቀለጠችው እኔም ተከተልኳት ሞተሩን ይነዳ የነበረው ልጅ ወደ ቤታችን አቅራቢያ ደርሶ ቆመ ወረድኩኝ እህቴ ልትወድቅ ስትል ሰዎች ሮጠው እንደ ደገፏት አስታውሳለሁ "ልጆችህ መጡ"እያለች እናቴ እያለቀሰች ከቤት ስትወጣ ብዙ ሰዎች አብረዋት እያነቡ ወጡ እያለቀስኩ ገባሁ ለካ አሞታል ያሉኝ ውሸታቸውን ነበር አባቴ ግን ላይመለስ አሸልቧል።
ያ ጀግና ለሀገር ሉዓላዊነትና ህልውና ሲል 13 ዓመታት ያክል በዐውደ ጦር የተዋደቀው 1ጊዜ በፈንጅ 8 ጊዜ በጥይት የቆሰለው መቶ አለቃ አሳምነው ሽፈራው
በእምነቱ የማይደራደረው ቅ/ቤ/ክንን ያገለገለው እየለመነ ረጴ ማርያምን ያሳነጸው፣ አጸድ የተከለው አሳምነው ( ስመ ጥምቀቱ ኃ/ማርያም )

ሁሉ ዘመዱ የሆነ፣ ሰው ወዳዱ ፣የሀገር ሽማግሌው ግን ደግሞ እርጅና ያልተጫጫነው የሁሉ ታዛዥ ፣ትሁቱ ፣ አስታራቂው ከደጅ የማይታጣው፣እንግዳ ተቀባዩ አባባ አባቴ
ዛሬ ግን ከደጅ ጠፋ አጣሁት 😭😭የለም ወደ ዘላለም ዕረፍቱ ቻው ሳይለኝ አቅንቷል። 😭ቅርብ መንገደኛ እንኳ ይሰናበታል ሳይሰናበተኝ ወደ ሩቅ መንገድ ወዳገለገለው አምላኩ ሄዷል ያማል በእርግጥ እንደሰውኛው "አይዞህ ልጄ፣ አባዮ ኪያ" የሚለኝ አባቴ አይዞህ ሳልለው ፣ ሳላሳርፈው ለዘላለሙ አረፈብኝ አሸለበብኝ እነሆ 8 ቀናት ደጅ ደጁን ባየው የለም ምን አደርጋለሁ እንግዲህ የጌታ ፈቃድ ነው አሜን ብዬ ተቀብየዋለሁ🙏 ምንም እንኳ አባቴን በሕይወተ ሥጋ ባጣውም የማላጣው የዘላለም አባት አምላክ ስላለኝ ወላጆች እንደሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም ባለን አምላክ በእርሱ እጽናናለሁ።ስላደረገው ነገር ሁሉ እያመሰገንኩኝ የአባቴን ነፍስ በአጸደ ገነት እንዲያኖርልኝ ፣ እናቴንና እህቶቼን እንዲጠብቅልኝ እማጸነዋለሁ።🙏🙏🙏🙏
ሰላም ይሁን !

ይህ ዓለም በሰላም መኖር ብቻ ሳይሆን በሰላም መቀበርም የሚናፈቅበት ዓለም ነው ። በፍጹም እርጅና ላይ የነበረው ስምዖን አረጋዊ እንኳ ጌታን ታቅፎ የለመነው “ጌታ ሆይ ፥ አሁን እንደ ቃልህ ባሪያህን በሰላም ታሰናብተዋለህ” ብሎ ነው ። /ሉቃ. 2፡29 ።/ በዚህ ዕድሜ ላይ በሰላም መሰናበት ምን ያሳስባል? ቢሉ የሰው ልጅ እስከ ሞት ከአቋሙ የመውረድ ፣ ከምግባሩ የመዋረድ ፣ በሃይማኖቱ የመወራረድ ጠባይ አለውና ነው ። ስለዚህ በሰላም መሰናበትን ለመነ ። ጌታ አስቀድሞ “በሰላም አሰናብትሃለሁ” ቃል ገብቶለት ነበር ። በርግጥም ጌታን በሥጋዊ ዓይኖቹ አይቶ ፣ በሽምግልና ክንዶቹ ታቅፎ ነበርና ነገር ሳይበላሽ እንዲህ እንዳማረበት መሞትን ለመነ ።

አባቶቻችን፡- “አሟሟቴን አሳምረው ፣ ቀባሪ አታሳጣኝ” የሚለው ጸሎታቸው መጽሐፋዊና በኑሮ የተፈተነ ነው ። አሁንም፡- “ከሞቱ የአሟሟቱ” ይባላል ። የዕብራውያን መልእክት ፀሐፊም ስለ ሃይማኖት አርበኞች በተናገረበት ድርሳኑ፡- “እነዚህ ሁሉ አምነው ሞቱ” ይላል ። /ዕብ. 11 ፡ 13 ።/ ፈያታዊ ዘየማን ክዶ ኖሮ አምኖ እንደ ሞተ ፣ እነ ቀያፋ አምነው ኖረው ክደው ሞተዋል ። ሰማይ ምሥጢር ነው ፤ ወንበዴ ገብቶበት ፣ ሊቀ ካህናት የሚቀርበት ነውና ። ሰማይ ማልደው የተጠሩ ቀርተው ፣ የሠርክ ተጠሪዎች የሚካፈሉት ዋጋ ነው ። ይህን ዓለም ጨረስኩት የሚባለው ከሞትን ከሦስት ቀን በኋላ ፣ ሠልስት ከተለቀሰ ወዲያ ነው ።

እግዚአብሔር አምላክ ጻድቁ አብርሃምን፡- “አንተ ግን ወደ አባቶችህ በሰላም ትሄዳለህ በመልካም ሽምግልና ትቀበራለህ” አለው ። ዘፍ. 15 ፡ 15 ። በሰላም ትሄዳለህ ማለቱ ዘሩ የሆኑት እስራኤል ዘሥጋ በግብጽ ምድር የሚያገኛቸውን መከራ አታይም ሲለው ነው ። በሕፃናት ደም የጡብ ጭቃ ሲቦካ አታይም ሲለው ነው ። ደም እንደ ዝናብ ሲወርድ ፣ በክፉ አገዛዝ ልጆችህ ሲሰቃዩ አታይም ማለቱ ነው ። አለማየትም ለካ በረከት ነው ! “እንኳን ይህን ሳያዩት ሞቱ” የተባለላቸው ብፁዓን ናቸው ። ለአንዳንድ ሰው መኖር ብዙ ሐሣር ያሳየዋል ። የትውልድን ፣ የወገንን ስቃይ ማየት እጅግ ክፉ ነው ።

የዓለም መከራ የጀመረው በልጅ ሞት ነው ። አዳም ተቀምጦ ወጣቱ አቤል ሞተ ። ቃየን ክፉው እያለ ደጉ አቤል ተወገደ ። በሕይወት ውስጥ እጅግ አድካሚው ጥያቄ ፣ መላሽ መምህር ያጣው ሙግት “ለምን?” የሚለው ነው ። አቤል የሞት ማሟሻ ነበር ። የተሟሸ ጀበና ፣ የተሟሸ ወፍጮ ከዚያ በኋላ ሥራ አይፈታም ። ታዲያ ባለ ቅኔው እንዲህ አለ፡-

“ሞት ፊደል ተምሮ ያነባል ስንል፣
እንኳን ሊያነብና ገና ያግዛል ።”

“ሀ” ግእዝ “ሁ” ካዕብ የትምህርት መጀመሪያ ነው ። ሞት ገና ያግዛል ፣ ገና “ሀ” ግእዝ ወይም ሀ መጀመሪያ ፊደል ይላል ማለቱ ነው ። ምሥጢሩ ሞት በአቤል ሥራ ጀምሮ ገና በአዲስ ጉልበት ዛሬም እየሠራ ነው የሚል ይመስላል ። ሟች እየበዛ ነው ማለቱ ነው ። የመጨረሻውን ሟች ባናውቀውም የመጀመሪያውን ሟች ግን እናውቀዋለን ። የምንሞትበትን ቦታ ባናውቀውም የተወለድንበትን ቦታ ግን እናውቀዋለን ። ሰው በሰዎች እርዳታ ተወልዶ ፣ በሰዎች ጥይት መሞቱ ይገርማል ። ሽማግሌው፡- “ሰው አለ እንዳንል ሰው የለም ፣ ሰው የለም እንዳንል ሰው አለ” ያሉት ለካ ለዚህ ነው ።

ጻድቁ አብርሃም፡- “በመልካም ሽምግልና ትቀበራለህ” ተባለ ። ክፉ ሽምግልና የደከሙለት አገር ሲፈርስ ፣ የኖሩለት ራእይ ሲከሰከስ ፣ ያሳደጉት ልጅ ደሙ ሲፈስስ ማየት ነው ። አንዳንድ ልበ ደንዳና ፣ የዕድሜ ሳይሆን የማስተዋል ደሀ የሆኑ ይህ አይገርማቸውም ።

“የወንድሙ ሞት ወንድሙን ካልከፋው ፣
ቅበሩት ከደጁ በድኑ እንዲከረፋው ፤”

ደግሞም እንዲህ ተብሏል፡-

“ከስምንተኛው ሺህ እኛም ደረስንበት ፣
አባት ተቀምጦ ልጅ ከፈረደበት
ምድር እንደ ዳቦ ከተቆረሰበት ።”…

አዎ አዋቂውን ሊቅ ያልተማረ ሲያርመው ፣ አባቶች ዝም ብለው ልጆች ሲለፈልፉ ፣ ምድር ተከፋፍላ የእኔ የእኔ ሲበዛ ስምንተኛው ሺህ መድረሱን ፣ የመጽሐፉ በዓይን መታየቱን ያስረዳል ። ጻድቁ አብርሃም፡- “በመልካም ሽምግልና ትቀበራለህ” ተባለ ። ለመኖር ብቻ ሳይሆን ለመቀበርም ሰላም ያስፈልጋል ። “ተጣልቶ ለመታረቅም አገር ያስፈልጋል” ያሉት አባት በእውነት የመንፈስ ቅዱስ ክስተት መጥቶላቸው ነው ። ሰላም ይሁን ለአገሩ !
👇👇👇👇👇👇
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
በሰላም መሄድ

“አንተ ግን ወደ አባቶችህ በሰላም ትሄዳለህ” ዘፍ. 15 ፡ 15 ።

ይህ ዓለም የርክክብ ዓለም ነው ። አረካካቢዎቹም ልደትና ሞት ናቸው ። ልደትና ሞት ወሳኝ ኩነት ናቸው ተብለዋል ። ሰው ላያገባ ፣ ላይመረቅ ይችላል ። ሰው ሁኖ ግን ያልተወለደና ሰው ሁኖ የማይሞት የለም ። ልደት ባይኖር ኖሮ ሞት ይህን ዓለም ባዶ ያደርገው ነበር ። ሞት ባይኖርም የሰው ልጅ እንደ ንብ ተነባብሮ ለመኖርም ይሳነው ነበር ። ወደ ትልቁ አዳራሽ ለመግባት ልደት መግቢያ በር ነው ። ሞትም የመውጫ በር ነው ። የተወለድንበት ቅርጽ በር ሲሆን ስንሞትም የሚጠብቀን መቃብር የበር ቅርጽ ያለው ነው ። በመግቢያ በር የሚገቡ ምንም ያልያዙ ሊሆኑ ይችላሉ ። ወደዚህ ዓለም ስንመጣም ባዶ እጃችንን ፣ ዕራቁት ገላችንን ይዘን መጥተናል ። ደግነትም ክፋትም ያልነበረን ፣ ባለማወቃችንና በእርዳታ ፈላጊነታችን ሁሉ የሚወደን ማሙሽ ነበርን ። በመውጫ በር የሚወጡ ብዙ ዓይነት መልክ አላቸው ። ባዶ እጃቸውን የሚወጡ አሉ ። የሚፈልጉትን ሳያውቁ ፣ የሚፈልጉትን ሳያገኙ ፣ ገንዘብ ሳይዙ ሰዎች ባዶ እጃቸውን ይወጣሉ ። በዚህ ዓለም ኑሮ ተስፋ ቆርጠው ፣ እንደ እርጉዝ በሚያቅበጠብጥ ምኞት ሲጎመዡ ኖረው ፣ ሁሉንም ነገር በዜሮ በሚያባዛ ፍልስፍና ተወጥረው ባዶ እጃቸውን የሚሰናበቱ አሉ ።

የሚያስፈልጋቸውን ይዘው የሚወጡ ሰዎችም አሉ ። እነዚህ ሰዎች የሚፈልጉትን ከሚያስፈልጋቸው ነገር የለዩ ናቸው ። ቀኑን የኖሩበት ቀኑ ያልኖረባቸው ብልሆች ናቸው ። በዓላማ እንደ ተፈጠሩ በዓላማ ኖረው ያለፉ ናቸው ። እነዚህ ሰዎች አስቀድመው የሚፈልጉትን ጽፈው የገቡ ሲሆኑ አቅማቸውን በትክክል የተጠቀሙ ፣ የሚፈልጉትን ብድግ ብድግ አድርገው ጊዜአቸውን ያተረፉ ፣ አላስፈላጊ ወጪዎችን ያስወገዱ ናቸው ። የሚያዩት ሁሉ ዓይን አዋጅ ሳይሆንባቸው ፣ ሁሉም የእኔ ይሁን የሚል ስግብግብነት ሳይጫናቸው ፣ የቱን ልምረጥ ብለው ሳይምታቱ በሥርዓት ኖረው የሚያልፉ ናቸው ።

ዛሬ እንደ ተወለዱ ሕፃናት እኛም ተወልደናል ። ትላንት እንደ ሞቱት አባቶች ደግሞ እንሞታለን ። በእርሻ ላይ የተዘራው ስንዴ በመኸር ይሰበሰባል ። እንዲሁም በዚህ ዓለም ላይ የተዘራን የእግዚአብሔር ስንዴ ነን ። የጀመርነው በስንዴነት ነው ፤ መኸር የተባለው ሞት ሲመጣ ወደ ጎተራው ወደ ሰማይ እንሰበሰባለን ። ምድር የዘር ፣ የመኸር ቦታ ናት ። ሰማይ ጎተራ ነው ። በምድር ያላፈራ ወደ ሰማይ ጎተራ አይገባም ። ይህችን ጊዜያዊ ምድር ውድ የሚያደርጋት ዘላለማዊ ውሳኔ የምናደርግባት መሆንዋ ነው ። ሞት ከዚህ ዓለም ካሉት ወዳጆች ጋር ሲለየን በሰማይ ካሉት ወዳጆች ጋር ያገናኘናል ። በሰማይ ያሉት ደግሞ አባቶቻችን ናቸው ። የሚታየው ዓለም መንፈስ ሲሆን የማይታየው ዓለም ደግሞ የሚታይ ይሆናል ። በምድር ላይ አካላችን ሲታጣ መንፈሳዊ ተግባራችን ሲናገር ይኖራል ። በሰማይ ደግሞ አካላችን ይገኛል ፣ ሥራችንም ይከተለናል ።

የዚህ ዓለም ጉዞአችንን ስንፈጽም ለትውልድ ጥለን ስለምንሄደው ነገር ማሰብ አለብን ። ያን ጊዜ በሰላም መሞት ይቻላል ። ወደ ኋላ ያሳለፍነውን ጊዜ እያሰብን ፣ በባከነው ዘመን እንዳናዝን እያንዳንዱን ቀን ልንኖርበት ይገባል ። መወለዱን የሚጠራጠር እንደሌለ መሞቱንም የሚጠራጠር የለም ። መቼ እንደምንሞት እንጠራጠር ይሆናል ። መሞታችንን ግን አንጠራጠርም ። እርግጥ ስለሆነው ነገር ችላ ብለን እርግጥ ስላልሆኑ ነገሮች እንተጋለን ። ሞት ያለው በጦር ሜዳ ወይም በሆስፒታል ሳይሆን ሞት ይዘነው የምንዞረው ነው ። ሞት ከታላላቅ ጥሪዎች አንዱ ነው ። ልደት ጥሪ ነው ፣ ክህነት ጥሪ ነው ፣ ሹመት ጥሪ ነው ፣ ሞትም ጥሪ ነው ። ጥሪ ነውና ሰው በዕድሜ ፣ በበሽታ ላይሞት ይችላል ። አረጋዊው ተቀምጦ ሕፃኑ ፣ በሽተኛው ሳለ ጤነኛው ይሞታሉ ። ሞት አንዱ ላንዱ የማይከፍለው ባለቤቱ ራሱ የሚወራረደው ዕዳ ነው ። የማይቀረውን የሞት ዕዳ ከመክፈላችን በፊት በክርስቶስ መንገድነት መጓዝ ፣ በእውነትነቱ ነጻ መውጣት ፣ በሕይወትነቱ መዳን ያስፈልገናል ።

“አንተ ግን ወደ አባቶችህ በሰላም ትሄዳለህ” ዘፍ. 15፡15 ።

በሰላም መሄድን ምን አመጣው ? ጠጥቶ የሰከረ ሰው ሰላምታ እየሰጠ ገብቶ እየተሳደበ ይወጣል ። በኃጢአት አረቄ የሰከረ ሰውም አሟሟቱን ያበላሻል ። በመጨረሻ ሰዓት ለእግዚአብሔር ክብር ፣ ለሰው ጥቅም የማይበጅ ሥራ ይሠራል ። በሰላም መሄድ ራሱን ለሚገዛ ፣ አገኘሁ ብሎ ለማይሻማ ሰው የተመደበ ዕድል ነው ። በሰላም መሄድን ካነሣን ዓለሙ ነገረኛ ነው ማለት ነው ። ነገር ይፈልገናል ፣ ይተነኳኮለናል ። በሽታው ፣ አግኝቶ ማጣቱ ፣ ከብሮ መዋረዱ ፣ ነግቶ መጨለሙ እነዚህ ሁሉ ነገረኞች ናቸው ። በሰላም መሄድ በረከት ነው ። በሰላም መሄድ የከፈቱትን ዘግቶ ፣ ያስቀየሙትን ይቅርታ ጠይቆ ፣ የበደሉትን ክሶ ፣ የቀሙትን መልሶ ነው ። ወደ አባቶችህ ትሄዳለህ ማለቱም ሞትህ አድራሻ አለው ሲለው ነው ። የአብርሃም አባቶቹ እነ አዳም ፣ አቤል ፣ ሄኖክ ፣ ኖኅ ... ነበሩ ።

እግዚአብሔር አምላክ ሆይ በሰላም መሄድን አድለን ! የነፍሳችንን አድራሻ አንተው አሳውቀን! ሠርቶ አፍራሽ ፣ ለግሞ ፈራሽ ከመሆን ጠብቀን ! አሜን !

👇👇👇👇👇👇
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
📚
1, እመጓ
2, ዝጎራ
3, መርበብት
4, ዴርቶጋዳ
5, ዮራቶራድ
6, ዣንቶዣራ
7,መጽሐፈ ሄኖክ
8, ቤተክርስቲያንህን እወቅ እንዳትሆን መናፍቅ
9, ፍኖተ አእምሮ
9, አዳም እና ጥበቡ
10, ዝክረ መስቀል
11, ሰይፈ ሥላሴ
12, ፍትሐ ነገስት
13, መጽሐፈ መነኮሳት
14, ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና
16, ህግጋተ ወንጌል
17, ነገረ ማርያም በጥንታዊቷ ቤተከርስቲያን
18, ድርሳነ ሚካኤል ወ ገብርኤል
19, ውዳሴ ማርያም በግእዝ
20, ግድለ ተክለሃይማኖት
21, ገድለ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሰጫ
22, የወጣቶች ህይወት
23, መጽሐፈ ገድለ ሐዋርያት
24, ኦርቶዶክስ መልስ አላት
25, የዋልድባ ገዳም ታሪክ
26, መጽሐፈ አክሲማሮስ
27, 14ቱ ፍሬ ቅዳሴያት ከነ አንድምታው
28, መልክዓ መለኮት
29, መጽሐፈ አሚን ወ ሥርዓት
30, ሰባቱ ምስጢራተ ቤተከርስቲያን
31, ሐይማኖተ አበው
32, ራዕየ ማርያም
34, የመናኝ ጉዞ
35, መልክዓ እግዚአብሔር
36, ታብተ ጽዮንን ፍለጋ
37, ፍካሬ ኢየሱስ ወትንቢተ ሳቤላ
38, መጽሐፍ ቅዱስ እና የህክምና ሳይንስ
39, መርበብተ ሰሎሞን
40, የ ቶ መስቀል ትርጉም
41, መጽሐፈ ፈውስ
42, ባሕረ ሐሳብ
43, ሞታ የተነሳችው ኦርቶዶክሳዊት ካትሪን
44, ቅዱስ ማርቆስ ኢትዮጵያዊ
45, ትንሳኤ ዘኢትዮጵያ
46, የ 666 ሳይንሳዊ ምስጢር
47, ቅኔ
48, ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ
49, ህይወተ ቅዱሳን
50, ነገረ ቅዱሳን

📚📚📚የቱን ኦርቶዶክሳዊ መፅሀፍ ማንበብ ይፈልጋሉ የሚፈልጉትን መፅሀፍ በመንካት ያንብቡ መልካም ንባብ📖

📕█▓▒░► 𝑶𝑷𝑬𝑵 ░ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ▒▓█📕
📕█▓▒░► 𝑶𝑷𝑬𝑵 ░ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ▒▓█📕
📕█▓▒░► 𝑶𝑷𝑬𝑵 ░ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ▒▓█📕
📕█▓▒░► 𝑶𝑷𝑬𝑵 ░ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ▒▓█📕
📚
1, እመጓ
2, ዝጎራ
3, መርበብት
4, ዴርቶጋዳ
5, ዮራቶራድ
6, ዣንቶዣራ
7,መጽሐፈ ሄኖክ
8, ቤተክርስቲያንህን እወቅ እንዳትሆን መናፍቅ
9, ፍኖተ አእምሮ
9, አዳም እና ጥበቡ
10, ዝክረ መስቀል
11, ሰይፈ ሥላሴ
12, ፍትሐ ነገስት
13, መጽሐፈ መነኮሳት
14, ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና
16, ህግጋተ ወንጌል
17, ነገረ ማርያም በጥንታዊቷ ቤተከርስቲያን
18, ድርሳነ ሚካኤል ወ ገብርኤል
19, ውዳሴ ማርያም በግእዝ
20, ግድለ ተክለሃይማኖት
21, ገድለ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሰጫ
22, የወጣቶች ህይወት
23, መጽሐፈ ገድለ ሐዋርያት
24, ኦርቶዶክስ መልስ አላት
25, የዋልድባ ገዳም ታሪክ
26, መጽሐፈ አክሲማሮስ
27, 14ቱ ፍሬ ቅዳሴያት ከነ አንድምታው
28, መልክዓ መለኮት
29, መጽሐፈ አሚን ወ ሥርዓት
30, ሰባቱ ምስጢራተ ቤተከርስቲያን
31, ሐይማኖተ አበው
32, ራዕየ ማርያም
34, የመናኝ ጉዞ
35, መልክዓ እግዚአብሔር
36, ታብተ ጽዮንን ፍለጋ
37, ፍካሬ ኢየሱስ ወትንቢተ ሳቤላ
38, መጽሐፍ ቅዱስ እና የህክምና ሳይንስ
39, መርበብተ ሰሎሞን
40, የ ቶ መስቀል ትርጉም
41, መጽሐፈ ፈውስ
42, ባሕረ ሐሳብ
43, ሞታ የተነሳችው ኦርቶዶክሳዊት ካትሪን
44, ቅዱስ ማርቆስ ኢትዮጵያዊ
45, ትንሳኤ ዘኢትዮጵያ
46, የ 666 ሳይንሳዊ ምስጢር
47, ቅኔ
48, ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ
49, ህይወተ ቅዱሳን
50, ነገረ ቅዱሳን

📚📚📚የቱን ኦርቶዶክሳዊ መፅሀፍ ማንበብ ይፈልጋሉ የሚፈልጉትን መፅሀፍ በመንካት ያንብቡ መልካም ንባብ📖

📕█▓▒░► 𝑶𝑷𝑬𝑵 ░ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ▒▓█📕
📕█▓▒░► 𝑶𝑷𝑬𝑵 ░ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ▒▓█📕
📕█▓▒░► 𝑶𝑷𝑬𝑵 ░ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ▒▓█📕
📕█▓▒░► 𝑶𝑷𝑬𝑵 ░ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ▒▓█📕
⛪️የኢኦተቤክ አስተምህሮ ና ስርአትን የጠበቁ የትኞቹን መዝሙራት ማግኝት ይፈልጋሉ⁉️

👏 የቸብቸቦ መዝሙራት
          📖▓⇨→vido    ⇨ግጥም
🎻 የበገና መዝሙራት  
         📖▓⇨→vido     ⇨ግጥም
👑 የቅዱሳን መዝሙራት
          📖▓⇨→vido    ⇨ግጥም
⛪️ የንግስ መዝሙራት
          📖▓⇨→vido    ⇨ግጥም
🤲 የምስጋና  መዝሙራት
          📖▓⇨→vido    ⇨ግጥም
🙏 የንስሐ  መዝሙራት
         📖▓⇨→vido   ⇨ግጥም
💍 የሠርግ መዝሙራት
          📖▓⇨→avido   ⇨ግጥም
🌦 ወቅታዊ መዝሙራት
          📖▓⇨→vido    ⇨ግጥም
🇪🇹 ለአገር የተዘመሩ

          📖▓⇨→vido   ⇨ግጥም
          👇👇
https://youtu.be/74f62hDwSA4

          👇🏽ከእስልምና ወደ ክርስትና በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ በYOUTUBE👇🏽

         👇🏽🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔻👇🏽
   https://www.youtube.com/channel/UCy1JtUNzSqHW-91lAHXN-NA

           👆🏽🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔺‌‌👆🏽
⛪️የኢኦተቤክ አስተምህሮ ና ስርአትን የጠበቁ የትኞቹን መዝሙራት ማግኝት ይፈልጋሉ⁉️

👏 የቸብቸቦ መዝሙራት
          📖▓⇨→vido    ⇨ግጥም
🎻 የበገና መዝሙራት  
         📖▓⇨→vido     ⇨ግጥም
👑 የቅዱሳን መዝሙራት
          📖▓⇨→vido    ⇨ግጥም
⛪️ የንግስ መዝሙራት
          📖▓⇨→vido    ⇨ግጥም
🤲 የምስጋና  መዝሙራት
          📖▓⇨→vido    ⇨ግጥም
🙏 የንስሐ  መዝሙራት
         📖▓⇨→vido   ⇨ግጥም
💍 የሠርግ መዝሙራት
          📖▓⇨→avido   ⇨ግጥም
🌦 ወቅታዊ መዝሙራት
          📖▓⇨→vido    ⇨ግጥም
🇪🇹 ለአገር የተዘመሩ

          📖▓⇨→vido   ⇨ግጥም
          👇👇
https://youtu.be/74f62hDwSA4

          👇🏽ከእስልምና ወደ ክርስትና በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ በYOUTUBE👇🏽

         👇🏽🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔻👇🏽
   https://www.youtube.com/channel/UCy1JtUNzSqHW-91lAHXN-NA

           👆🏽🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔺‌‌👆🏽
+"በምድር ያለች ሰማይ"+

ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤ/ክ የክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ናት የምንላት የእኛ ስለሆነች በደጋፊነት አይደለም። እርሱ ክርስቶስ የሰማዩን ስርዓት ያዥ እንዳላት የሰማዩን ሥርዓት የያዘች ፣ #ፈቃዱ_የሚመራት#ውዴታው_የሳባት#ከዚሁ ፍቅር_ገመድ_ያልወጣች ፣ #የሰማዩን_በምድር የምትኖር ፣ በምድር_ያለች_ሰማይ ስለሆነች ነው እንጂ።

እርሱ የሰማዩን እወዳለሁ እንዳለ እንስሳዊ ጠባይዕን ለመልዐካዊ ጠባይዕ አስገዝቶ መኖርን ፣ ሥጋዊነትን ገዝቶ ፣ መንፈሳዊ ኑሮን ለልጆቿ የምታስተምር ስለሆነች ነው እንጂ ከዚህም ፈቃዱ እንዳትወጣ ማለዳ በኪዳኑ ጸሎቷ "ሀበነ ንሑር በትዕዛዝከ - #አቤቱ_በትዕዛዝህ_በፈቃድህ_እንኖር_ዘንድ_ምራን" እያለች ትማልደዋለች ። ሰርክም በቅዳሴው "እወ እግዚኦ አምላክነ በእንተ ዐቢይ ስምከ ንጉደይ እምኩሉ ሕሊና ዘኢያሰምረከ - አዎን አቤቱ አምላካችን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ስለ ግሩም ልዑል ስምህ ብለህ አንተን #ከማያስደስት#ከፈቃድህ_ከወጣ_ክፉ_አሳብ_እንሸሽ_ዘንድ_መሸሹንስጠን" እያለች ትለምነዋለች ። እንዲሁም በንስሃ ጸሎቷ "ሀበነ እግዚኦ ንግበር ፈቃድከ ወሥምረትከ ኩሎ ጊዜ - #አቤቱ ሁልጊዜ #ፈቃድህን_ውድህን_እንሰራ_ዘንድ_ልብንና_ልቡናን_ጥበብን_ስጠን" እያለች ለፈቃዱም ፈቃዱን በትህትና ትጠይቃለች። በትህትና የመሠረታት የትሁት ክርስቶስ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤ/ክ ግለሰብ አቋቁሞ የማይመራት መንፈስቅዱስ የሚመራት እንከን የሌላት ምልዕተ ትህትና በምድር ያለች ሰማይ ናትና።
አባ ገ/ኪዳን ግርማ
👇👇👇👇👇👇
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
📚
1, እመጓ
2, ዝጎራ
3, መርበብት
4, ዴርቶጋዳ
5, ዮራቶራድ
6, ዣንቶዣራ
7,መጽሐፈ ሄኖክ
8, ቤተክርስቲያንህን እወቅ እንዳትሆን መናፍቅ
9, ፍኖተ አእምሮ
9, አዳም እና ጥበቡ
10, ዝክረ መስቀል
11, ሰይፈ ሥላሴ
12, ፍትሐ ነገስት
13, መጽሐፈ መነኮሳት
14, ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና
16, ህግጋተ ወንጌል
17, ነገረ ማርያም በጥንታዊቷ ቤተከርስቲያን
18, ድርሳነ ሚካኤል ወ ገብርኤል
19, ውዳሴ ማርያም በግእዝ
20, ግድለ ተክለሃይማኖት
21, ገድለ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሰጫ
22, የወጣቶች ህይወት
23, መጽሐፈ ገድለ ሐዋርያት
24, ኦርቶዶክስ መልስ አላት
25, የዋልድባ ገዳም ታሪክ
26, መጽሐፈ አክሲማሮስ
27, 14ቱ ፍሬ ቅዳሴያት ከነ አንድምታው
28, መልክዓ መለኮት
29, መጽሐፈ አሚን ወ ሥርዓት
30, ሰባቱ ምስጢራተ ቤተከርስቲያን
31, ሐይማኖተ አበው
32, ራዕየ ማርያም
34, የመናኝ ጉዞ
35, መልክዓ እግዚአብሔር
36, ታብተ ጽዮንን ፍለጋ
37, ፍካሬ ኢየሱስ ወትንቢተ ሳቤላ
38, መጽሐፍ ቅዱስ እና የህክምና ሳይንስ
39, መርበብተ ሰሎሞን
40, የ ቶ መስቀል ትርጉም
41, መጽሐፈ ፈውስ
42, ባሕረ ሐሳብ
43, ሞታ የተነሳችው ኦርቶዶክሳዊት ካትሪን
44, ቅዱስ ማርቆስ ኢትዮጵያዊ
45, ትንሳኤ ዘኢትዮጵያ
46, የ 666 ሳይንሳዊ ምስጢር
47, ቅኔ
48, ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ
49, ህይወተ ቅዱሳን
50, ነገረ ቅዱሳን

📚📚📚የቱን ኦርቶዶክሳዊ መፅሀፍ ማንበብ ይፈልጋሉ የሚፈልጉትን መፅሀፍ በመንካት ያንብቡ መልካም ንባብ📖

📕█▓▒░► 𝑶𝑷𝑬𝑵 ░ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ▒▓█📕
📕█▓▒░► 𝑶𝑷𝑬𝑵 ░ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ▒▓█📕
📕█▓▒░► 𝑶𝑷𝑬𝑵 ░ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ▒▓█📕
📕█▓▒░► 𝑶𝑷𝑬𝑵 ░ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ▒▓█📕
📚
1, እመጓ
2, ዝጎራ
3, መርበብት
4, ዴርቶጋዳ
5, ዮራቶራድ
6, ዣንቶዣራ
7,መጽሐፈ ሄኖክ
8, ቤተክርስቲያንህን እወቅ እንዳትሆን መናፍቅ
9, ፍኖተ አእምሮ
9, አዳም እና ጥበቡ
10, ዝክረ መስቀል
11, ሰይፈ ሥላሴ
12, ፍትሐ ነገስት
13, መጽሐፈ መነኮሳት
14, ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና
16, ህግጋተ ወንጌል
17, ነገረ ማርያም በጥንታዊቷ ቤተከርስቲያን
18, ድርሳነ ሚካኤል ወ ገብርኤል
19, ውዳሴ ማርያም በግእዝ
20, ግድለ ተክለሃይማኖት
21, ገድለ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሰጫ
22, የወጣቶች ህይወት
23, መጽሐፈ ገድለ ሐዋርያት
24, ኦርቶዶክስ መልስ አላት
25, የዋልድባ ገዳም ታሪክ
26, መጽሐፈ አክሲማሮስ
27, 14ቱ ፍሬ ቅዳሴያት ከነ አንድምታው
28, መልክዓ መለኮት
29, መጽሐፈ አሚን ወ ሥርዓት
30, ሰባቱ ምስጢራተ ቤተከርስቲያን
31, ሐይማኖተ አበው
32, ራዕየ ማርያም
34, የመናኝ ጉዞ
35, መልክዓ እግዚአብሔር
36, ታብተ ጽዮንን ፍለጋ
37, ፍካሬ ኢየሱስ ወትንቢተ ሳቤላ
38, መጽሐፍ ቅዱስ እና የህክምና ሳይንስ
39, መርበብተ ሰሎሞን
40, የ ቶ መስቀል ትርጉም
41, መጽሐፈ ፈውስ
42, ባሕረ ሐሳብ
43, ሞታ የተነሳችው ኦርቶዶክሳዊት ካትሪን
44, ቅዱስ ማርቆስ ኢትዮጵያዊ
45, ትንሳኤ ዘኢትዮጵያ
46, የ 666 ሳይንሳዊ ምስጢር
47, ቅኔ
48, ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ
49, ህይወተ ቅዱሳን
50, ነገረ ቅዱሳን

📚📚📚የቱን ኦርቶዶክሳዊ መፅሀፍ ማንበብ ይፈልጋሉ የሚፈልጉትን መፅሀፍ በመንካት ያንብቡ መልካም ንባብ📖

📕█▓▒░► 𝑶𝑷𝑬𝑵 ░ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ▒▓█📕
📕█▓▒░► 𝑶𝑷𝑬𝑵 ░ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ▒▓█📕
📕█▓▒░► 𝑶𝑷𝑬𝑵 ░ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ▒▓█📕
📕█▓▒░► 𝑶𝑷𝑬𝑵 ░ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ▒▓█📕
2024/10/01 18:51:04
Back to Top
HTML Embed Code: