Telegram Web Link
⛪️የኢኦተቤክ አስተምህሮ ና ስርአትን የጠበቁ የትኞቹን መዝሙራት ማግኝት ይፈልጋሉ⁉️

👏 የቸብቸቦ መዝሙራት
          📖▓⇨→vido    ⇨ግጥም
🎻 የበገና መዝሙራት  
         📖▓⇨→vido     ⇨ግጥም
👑 የቅዱሳን መዝሙራት
          📖▓⇨→vido    ⇨ግጥም
⛪️ የንግስ መዝሙራት
          📖▓⇨→vido    ⇨ግጥም
🤲 የምስጋና  መዝሙራት
          📖▓⇨→vido    ⇨ግጥም
🙏 የንስሐ  መዝሙራት
         📖▓⇨→vido   ⇨ግጥም
💍 የሠርግ መዝሙራት
          📖▓⇨→avido   ⇨ግጥም
🌦 ወቅታዊ መዝሙራት
          📖▓⇨→vido    ⇨ግጥም
🇪🇹 ለአገር የተዘመሩ

          📖▓⇨→vido   ⇨ግጥም
          👇👇
https://youtu.be/74f62hDwSA4

          👇🏽ከእስልምና ወደ ክርስትና በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ በYOUTUBE👇🏽

         👇🏽🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔻👇🏽
   https://www.youtube.com/channel/UCy1JtUNzSqHW-91lAHXN-NA

           👆🏽🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔺‌‌👆🏽
DH ብሎኬት

ባለ 10 💵28
ባለ 15 💵31
ባለ 20 💵33

አድራሻ ፦ ጀሞ 1 , መስታወት ፋብሪካ አጠገብ ,
ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ግቢ

☎️ ስልክ ፦ +251902405737
*ችግርህ ኃይል ማጣት ነው
ዘላቂ መፍትሔው ደግሞ እነሆ*

ወዳጄ :-
ፈልገህም ይሁን ሳትፈልግ በድንገት "ሀ....." ብለህ የጀመርከው ክፉ ነገር እንደቀልድ ደግመህ ደጋግመኸው አጉል ልማድ ሱስ ሆኖብህ አቅምህን ፣ ዕድሜህን ፣ ገንዘብህን ፣ ወጣትነትህን ፣ አንተነትህን እየበላብህ ተቸግረህ ይሆናል ስትገባበት የቀለለህ መውጫው ከብዶህ ጠፍቶብህ እየዳከርክ ይሆን ? ሲሰበክ ፣ ቃሉ ወደ ጆሮህ ሲመጣ ደግሞም ስትመከር ወይንም *ስልጠና* ስትወስድ አልያም የማትፈልገውን እያደረግህ ስላለህ ውስጥህ ሲወቅስህ በጸጸት አልቅሰህ ፣ አንብተህ "ከዚህ በኋላማ በቃኝ" ብለህ ተገዝተህ ሳይውል ሳያድር "እንቢ" የምትልበት አቅም አጥተህ ተመልሰህ ከበፊቱ በከፋ ሁኔታ ራስህን እዛው በማትወደው አጉል ልማድ ውስጥ ተዘፍቀህ ስታገኘው እንደገና ደግሞ በጸጸት "እኔማ በቃ ካለዚህ ነገር መኖር አልችልም ፣ አልረባም" ምናምን እያልክ ተወዛግበህ ተቸግረህ ፣ተጨንቀህ ይሆን?

እንግዲያውስ ዘላቂ መፍትሄውን ልንገርህ ስማኝ ያንተ ችግር ኃይል ፣ አቅም ማጣት ስለሆነ ለአንድ ሰባት ቀን አልያም ከዚያም በላይ ከአምላክህ ጋራ ቀጠሮ ያዝ ከዚህ ከሁካታ ከጫጫታ መንደር ከዓለም ራቅ ስልክህን አስቀምጠው ቅዱሳት መጻህፍትን አንሳ ወደ ሰራህ አምላክ ተንበርክክ ፣ አልቅስ ፣ ለምነው "ለውጠኝ ኃይል ሁኔኝ ብቻዬን ታግዬ ማሸነፍ አቅቶኛልና አቅም ሁነኝ እየሰማ ቃሉን የሚነጠቀውን መንገድ ዳር ልቤን ቃልህን ሸሽጎ የሚያበቅልና የሚያፈራውን ለምለም መሬት አድርግልኝ ሸክላህ እነሆኝ በፊትህ እንደገና ስራኝ" በለው እመነኝ በእርግጠኝነት ለዘላለሙ ያስጨነቀህን ፣የተጫወተብህን ፣ አቅምህን ጉልበትህን ፣ ጊዜህን ፣ዕድሜህን ፣ የበላብህን ክፉ ልማድ ሱስ እንቢ ብለህ የምታሸንፍበትን ኃይል ተጎናጽፈህ ትወጣለህ ግዴለህም ሞክረው ህያው አምላኬ ምስክሬ ነው ትለወጣለህ ።
ሰናይ ቀን !
ሊ/ዲ/ን መባጽዮን (ኢ/ር)
11/11/2015 ዓ/ም
ራጴ_ኢትዮጵያ
👇👇👇👇👇
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
⛪️የኢኦተቤክ አስተምህሮ ና ስርአትን የጠበቁ የትኞቹን መዝሙራት ማግኝት ይፈልጋሉ⁉️

👏 የቸብቸቦ መዝሙራት
          📖▓⇨→vido    ⇨ግጥም
🎻 የበገና መዝሙራት  
         📖▓⇨→vido     ⇨ግጥም
👑 የቅዱሳን መዝሙራት
          📖▓⇨→vido    ⇨ግጥም
⛪️ የንግስ መዝሙራት
          📖▓⇨→vido    ⇨ግጥም
🤲 የምስጋና  መዝሙራት
          📖▓⇨→vido    ⇨ግጥም
🙏 የንስሐ  መዝሙራት
         📖▓⇨→vido   ⇨ግጥም
💍 የሠርግ መዝሙራት
          📖▓⇨→avido   ⇨ግጥም
🌦 ወቅታዊ መዝሙራት
          📖▓⇨→vido    ⇨ግጥም
🇪🇹 ለአገር የተዘመሩ

          📖▓⇨→vido   ⇨ግጥም
          👇👇
https://youtu.be/74f62hDwSA4

          👇🏽ከእስልምና ወደ ክርስትና በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ በYOUTUBE👇🏽

         👇🏽🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔻👇🏽
   https://www.youtube.com/channel/UCy1JtUNzSqHW-91lAHXN-NA

           👆🏽🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔺‌‌👆🏽
+++ዝም ሲለን...+++
አንዳንዴ ደጁን እያንኳኳን አምላካችን ዝም ካለን ለበጎ ነው አንዛል ተስፋ አንቁረጥ እርሱም እንደሰው አልሰማኝም አንበል ጆሮን የሰጠ አይሰማም አይባልም እኛ እንኳ እሱ በሰጠን በውሰት ጆሮ እየሰማን ነው። በእርግጥም ይሰማል ግን እርሱ እንደሰው አይቸኩልምና ለእኛ የሚያስባትን ሀሳብ ያውቃልና ለጥቅማችን ዝም ይላል ኤር 29 :11 "ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ" እንዲል እኛን ከእኛ በላይ የሚያውቀን ጌታ የሚጎዳንንና የሚጠቅመንን ያውቃልና የምንለምነውን ሁሉ ወዲያው ላይሰጠን ይችላል አንድም ትዕግስትን ያስተምረን ዘንድ፣ አንድም ዕጹብ ድንቅ የሆነ በረከት ሊያሳፍሰን ሲል ዝም ይላል። ኤልሳቤጥን አስቡ ፣ሳራን አስቡ ፣ሀናና ኢያቄምን አስቡ የሳሙኤልን እናት ሀናን አስቡ እንደማንኛውም ሰዎች ዘር ለመተካት ልጅ ብቻ ነበር የሚለምኑት እርሱ ግን ከብዙ ዘመናት ዝምታው በኋላ ትውልድ የሚባረኩባቸውን ልጆች ለእያንዳንዳቸው ሰጣቸው።አስተውሉ ወገኖቼ አንዳንዴ ዝም ሲለን ማን ያውቃል ከእኛ አልፎ ለዓለም የሚበቃውን ለእኛ እያዘጋጀ አልያም የለመንነው የሚያጠፋን ከሆነ ለጥቅማችን ዝም ይላልና ዝምታውን እንደመልስ ተቀብለን በእምነታችን ጸንተን እንጠብቀው። ሁሉን የምታውቅ ሆይ ችኩሉ እኔነቴን አንተ አረጋጋው በአማኑኤል ስምህ አሜን🙏
28/11/2015 ዓ/ም
ሊ/ዲ/ን መብዓጽዮን (ኢ/ር)
👇👇👇👇👇👇
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
ጾሙን ከመጀመራችን በፊት ይህንን የእግዚአብሔር ሀሳብ በማስተዋል እናንብብ እና እንተግብር ክርስቶሳውያን

ይህን ሁሉ ዘመን እየጾምን ስለምንድነው መልስ ያጣነው?.... ይኸው መልሱ
👇👇👇👇👇👇👇
(ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ 58)
----------
3፤ ስለ ምን ጾምን፥ አንተም አልተመለከትኸንም? ሰውነታችንንስ ስለ ምን አዋረድን፥ አንተም አላወቅህም? ይላሉ። እነሆ፥ በጾማችሁ ቀን ፈቃዳችሁን ታደርጋላችሁ፥ ሠራተኞቻችሁንም ሁሉ ታስጨንቃላችሁ።

4፤ እነሆ፥ ለጥልና ለክርክር ትጾማላችሁ በግፍ ጡጫም ትማታላችሁ፤ ድምፃችሁንም ወደ ላይ ታሰሙ ዘንድ ዛሬ እንደምትጾሙት አትጾሙም።

5፤ እኔ የመረጥሁት ጾም ይህ ነውን? ሰውስ ነፍሱን የሚያዋርደው እንደዚህ ባለ ቀን ነውን? በውኑ ራሱን እንደ እንግጫ ዝቅ ያደርግ ዘንድ ማቅንና አመድንም በበታቹ ያነጥፍ ዘንድ ነውን? በውኑ ይህን ጾም፥ በእግዚአብሔርም ዘንድ የተወደደ ቀን ትለዋለህን?

መልስ የሚያሰጥ የተወደደ ጾም ምን ዓይነት ጾም ነው ?....አሁንም ይኸው መልሱ
👇👇👇👇👇👇
6፤ እኔስ የመረጥሁት ጾም ይህ አይደለምን? የበደልን እስራት ትፈቱ ዘንድ፥ የቀንበርንስ ጠፍር ትለቅቁ ዘንድ፥ የተገፉትንስ አርነት ትሰድዱ ዘንድ፥ ቀንበሩንስ ሁሉ ትሰብሩ ዘንድ አይደለምን?
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
(ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ 58)
----------
7፤ እንጀራህንስ ለተራበ ትቈርስ ዘንድ፥ ስደተኞቹን ድሆች ወደ ቤትህ ታገባ ዘንድ፥ የተራቈተውንስ ብታይ ታለብሰው ዘንድ፥ ከሥጋ ዘምድህ እንዳትሸሽግ አይደለምን?

8፤ የዚያን ጊዜ ብርሃንህ እንደ ንጋት ይበራል፥ ፈውስህም ፈጥኖ ይበቅላል፥ ጽድቅህም በፊትህ ይሄዳል፥ የእግዚአብሔርም ክብር በኋላህ ሆኖ ይጠብቅሃል።

9፤ የዚያን ጊዜ ትጠራለህ እግዚአብሔርም ይሰማሃል፤ ትጮኻለህ እርሱም። እነሆኝ ይላል። ከመካከልህ ቀንበርን ብታርቅ፥ ጣትህንም መጥቀስ ብትተው፥

10፤ ባታንጐራጕርም፥ ነፍስህንም ለተራበ ብታፈስስ፥ የተጨነቀውንም ነፍስ ብታጠግብ፥ ብርሃንህ በጨለማ ይወጣል ጨለማህም እንደ ቀትር ይሆናል።

11፤ እግዚአብሔርም ሁልጊዜ ይመራሃል፤ ነፍስህንም በመልካም ነገር ያጠግባል አጥንትህንም ያጠናል፤ አንተም እንደሚጠጣ ገነት፥ ውኃውም እንደማያቋርጥ ምንጭ ትሆናለህ።

12፤ ከዱሮ ዘመን የፈረሱት ስፍራዎች ይሠራሉ፥ የብዙ ትውልድም መሠረት ይታነጻል፤ አንተም። ሰባራውን ጠጋኝ፥ የመኖሪያ መንገድን አዳሽ ትባላለህ።

13፤ ፈቃድህን በተቀደሰው ቀኔ ከማድረግ እግርህን ከሰንበት ብትመልስ፥ ሰንበትንም ደስታ፥ እግዚአብሔርም የቀደሰውን ክቡር ብትለው፥ የገዛ መንገድህንም ከማድረግ ፈቃድህንም ከማግኘት ከንቱ ነገርንም ከመናገር ተከልክለህ ብታከብረው፥
" በዚያን ጊዜ በእግዚአብሔር ደስ ይልሃል፥ በምድርም ከፍታዎች ላይ አወጣሃለሁ፥ የአባትህንም የያዕቆብን ርስት አበላሃለሁ፤ የእግዚአብሔር አፍ ተናግሮአልና።
"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 58:14)
👆👆👆👆👆
ከላይ የተጻፈውን ከተገበርነው የበረከት ጾም ይሆንልናል እና ቀድመን ትዕዛዙን እናክብር
*ማስተዋል ይብዛልን* 🙏
👇👇👇👇👇👇
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
ቅድስት ሆይ !

በሔዋን ያዘኑ ባንቺ ካልተደሰቱ ይገርማል ። በሥጋ ድንግል በመሆንሽ በዚህ ብቻ አልተደነቅንም ። በኅሊናም ድንግል ነሽ ። ድንግል በክልኤ/በሁለት ወገን ድንግል ነሽና ለቅዱሱ ቅድስቲቱ አስፈልገሽዋል ። ሊቀ ካህናቱ ብቻ በዓመት አንድ ጊዜ የሚገባባት ያቺ ኅቱም መቅደስ ፣ ቅድስተ ቅዱሳን ትባላለች ። ሊቀ ካህናት ክርስቶስ ብቻ ያደረበት ያንቺ ማኅፀን ከዚያች መቅደስ ይበልጣል ። ከሊቀ ካህኑ ሌላ በዚያች መቅደስ የሚገባ ሰው በሞት ይቀጣል ። እሳተ መለኮት በተቀመጠበት ባንቺ ማኅፀንም ፍጡር ይቀመጥ ዘንድ አይቻለውም ። መጠን የሌለው ክብር ሳለሽ መጠን የሌለው መከራ ተቀበልሽ ። ክብሩ ባየለ ቍጥር መከራውም ብዙ ይሆናል ። ሁሉ ያንቺ ይሆን ሁሉን አጣሽ ። ልጅሽ ብቻ ሀብት እንዲሆንሽ “እፎ ቤተ ነዳይ ኀደረ ከመ ምስኪን” ተባለልሽ ።

ቅድስት ሆይ !

አንቺን የወደደ እግዚአብሔር አብ ቡሩክ ነው !
ካንቺ ሰው የሆነ እግዚአብሔር ወልድ ቡሩክ ነው !
ያጸናሽ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስም ቡሩክ ነው ። ለዘላለሙ አሜን
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
⛪️የኢኦተቤክ አስተምህሮ ና ስርአትን የጠበቁ የትኞቹን መዝሙራት ማግኝት ይፈልጋሉ⁉️

👏 የቸብቸቦ መዝሙራት
          📖▓⇨→vido    ⇨ግጥም
🎻 የበገና መዝሙራት  
         📖▓⇨→vido     ⇨ግጥም
👑 የቅዱሳን መዝሙራት
          📖▓⇨→vido    ⇨ግጥም
⛪️ የንግስ መዝሙራት
          📖▓⇨→vido    ⇨ግጥም
🤲 የምስጋና  መዝሙራት
          📖▓⇨→vido    ⇨ግጥም
🙏 የንስሐ  መዝሙራት
         📖▓⇨→vido   ⇨ግጥም
💍 የሠርግ መዝሙራት
          📖▓⇨→avido   ⇨ግጥም
🌦 ወቅታዊ መዝሙራት
          📖▓⇨→vido    ⇨ግጥም
🇪🇹 ለአገር የተዘመሩ

          📖▓⇨→vido   ⇨ግጥም
          👇👇
https://youtu.be/74f62hDwSA4

          👇🏽ከእስልምና ወደ ክርስትና በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ በYOUTUBE👇🏽

         👇🏽🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔻👇🏽
   https://www.youtube.com/channel/UCy1JtUNzSqHW-91lAHXN-NA

           👆🏽🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔺‌‌👆🏽
አለሁ !!!

ባሕረ ጥበባት በሆንከው ፣ ሁሉን እንደ መላህ በምታኖረው ባንተ አለሁ ። ደዌያትን በቃልህ ፣ አጋንንትን በሥልጣንህ በምትሸኘው ፤ ትላንትን ለመካስ ፣ ዛሬን ለማድረስ ፣ ነገን ለማውረስ አቅም ባለህ ባንተ አለሁ ። የሞትን አዋጅ በሕይወት ፣ የስቅላትን ደብዳቤ በሹመት በምትለውጠው ባንተ በመፍቀሬ ሰብእ/በሰው ወዳዱ ጌታ አለሁ ። የነበረው የነበረ እስከማይመስል ደብዛው ጠፍቷል ፣ ያለው የማያልፍ ይመስል ይሸልላል ። የሚታየው የማይታይ ሲሆን ፣ አፈር የላሰው እንጀራ ሲያገኝ ፣ ተስፋ ያጣው ቀን ሲወጣለት ባንተ ደስ ይለኛል ። እኔ ግን ባንተ አለሁ !

@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
++ አደራህን ሀገሬን ++
" የሁሉ ዓይን አንተን ተስፋ ያደርጋል፤ "
(መዝሙረ ዳዊት 145:15)

ሁሉ ወደ አንተ በማንጋጠጥ የዓይኑ አድራሻ ያደረገህ የማታሳፍረው የአገልጋዩ፣ የገበሬው ፣ የነጋዴው ፣ የተማሪው ፣ የሐኪሙ ፣ የጸሐፊው ፣ የአዛውንቱ ፣ የጎበዛዝቱ ፣ የሕጻናቱ ፣ የፍጥረቱ ሁሉ ተስፋ መፍቀሬ ሰብዕ (ሰው ወዳዱ) ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ተመስገን !

አቤቱ ያለፍንብህ ትናንትናችን ዛሬን ያየንብህ ብርሃናችን የነገም ተስፋችን አንተው ነህ!
ሰው ተስፋ ቢሰጥ ይረሳል አደራ ቢባል ይበላል የነገሩህን የማትረሳ የለመኑህን የማትነሳ አደራ የማትበላው መድኃኔአለም ሆይ ዘወትር እጆቿን ወደ አንተ የምትዘረጋው የሀገሬ ተስፋ አንተው ነህና በፍጹም ሰላምህ ትጎበኛት ለመኳንንቶቿ ማስተዋልን ታበዛ ዘንድ አደራ እንልሃለን አሁንም ተስፋችን አንተው ነህና ድል በሚነሳው ስምህ አሜን 🙏

ሊ/ዲ/ን መባጽዮን (ኢ/ር)
08/12/2015 ዓ/ም
ዲላ ኢትዮጵያ
👇👇👇👇👇👇
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
++ አደራህን ሀገሬን ++
" የሁሉ ዓይን አንተን ተስፋ ያደርጋል፤ "
(መዝሙረ ዳዊት 145:15)

ሁሉ ወደ አንተ በማንጋጠጥ የዓይኑ አድራሻ ያደረገህ የማታሳፍረው የአገልጋዩ፣ የገበሬው ፣ የነጋዴው ፣ የተማሪው ፣ የሐኪሙ ፣ የጸሐፊው ፣ የአዛውንቱ ፣ የጎበዛዝቱ ፣ የሕጻናቱ ፣ የፍጥረቱ ሁሉ ተስፋ መፍቀሬ ሰብዕ (ሰው ወዳዱ) ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ተመስገን !

አቤቱ ያለፍንብህ ትናንትናችን ዛሬን ያየንብህ ብርሃናችን የነገም ተስፋችን አንተው ነህ!
ሰው ተስፋ ቢሰጥ ይረሳል አደራ ቢባል ይበላል የነገሩህን የማትረሳ የለመኑህን የማትነሳ አደራ የማትበላው መድኃኔአለም ሆይ ዘወትር እጆቿን ወደ አንተ የምትዘረጋው የሀገሬ ተስፋ አንተው ነህና በፍጹም ሰላምህ ትጎበኛት ለመኳንንቶቿ ማስተዋልን ታበዛ ዘንድ አደራ እንልሃለን አሁንም ተስፋችን አንተው ነህና ድል በሚነሳው ስምህ አሜን 🙏

ሊ/ዲ/ን መባጽዮን (ኢ/ር)
08/12/2015 ዓ/ም
ዲላ ኢትዮጵያ
👇👇👇👇👇👇
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
"ለምን ያለቀኔ ልሙት? .... በቀኔ ይውሰደኝ እንጂ"

ዛሬ ነው ከሰዓት በኋላ የሆኑ ሰራተኞች ስራ ሰርተው በውላችን መሰረት ባለመስራታቸውና በሆኑ ምክንያቶች ጭቅጭቅ ተነስቶ ጸብ ካላነሳን ብለው "እምቧ ካራዮ" እያሉ ነው አንደኛው ግቶ ነው የመጣውና ሆዱ ያባውን ብቅሉ እያወጣለት የመጣለትን ሁሉ ይተፋል "እባካችሁ ነገ በጠዋት በቀና መንፈስ እንነጋገር" ተብለው ቢለመኑ ቢዘከሩ "አሻፈረን" ይሉ ጀመር ይባስ ብሎ አንደኛው (የጋተው) እየደጋገመ "ዛሬ ብሞትስ " እያለ ይፎክር ጀመር የቃሉ መደጋገም ሲገርመኝ "እንግዲህ ከሞት የሚቀር የለምና ሙታ !" አልኹት በዚህ ሰዓት የቅድሙ አይደለም በገነ(ተናደደ) ስካሩ እስኪለቀው እጅግ ተቆጣ መልሶ "እንዴት እንዲህ ትለኛለህ ለምን ያለቀኔ ልሙት? በቀኔ ልሙት እንጂ" እያለ በጥያቄ ያፋጥጠኝ ጀመር እኔም ጥያቄውን በጥያቄ "ምነው የምትሞትበትን ቀን ታውቃለህ እንዴ? ጌታ ቀንህን ነግሮሃል እንዴ?" ስለው በፍጥነት ረገበና ለደቂቃዎች ዝም አለ ከዚያም ይቅርታ ተባብለን ለነገ ተቀጣጥረን በሰላም ተለያየን።

ለደቂቃዎች ይህ ቃል በአዕምሮዬ ሲመላለስብኝ ላጋራችሁ ወደድኩኝ አዎ ብዙ ጊዜ በተለይ ሰው በድንገት ሲጠራ "ያለቀኑ ፣ ያለጊዜው ፣ ሞተ ምናም" እንላለን እንዴ ታሞ የሚሞት ብቻ በቀኑ የሚሞት በድንገት ደግሞ ሲሞት ያለቀኑ ሟች ያለው ማነው? መጽሐፍ ቅዱስ ግን እንዲህ ይለናል " ቀኒቱንና ሰዓቲቱን አታውቁምና እንግዲህ ንቁ።"
(የማቴዎስ ወንጌል 25:13) እንዲሁም
(የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 24)
----------
43፤ ያን ግን እወቁ፤ ባለቤት ከሌሊቱ በየትኛው ክፍል ሌባ እንዲመጣ ቢያውቅ ኖሮ፥ በነቃ ቤቱም ሊቈፈር ባልተወም ነበር።

44፤ ስለዚህ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፥ የሰው ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና። ስለዚህ ወገኖቼ ማናችንም የምንሞትበትን ቀን አናውቅምና ሁል ጊዜም በወንጌል በማመን፣ በንስሃ ተዘጋጅተን ልንኖር ይገባል።
ማስተዋል ይብዛልን 🙏
ሰናይ ጊዜ
ሊ/ዲ/ን መባጽዮን (ኢ/ር)
18/12/2015 ዓ/ም
👇👇👇👇👇👇
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
+ የብሽሽቅ ወንጌል +
ወገን ይህ የብሽሽቅ አገልግሎት መቼ ይሆን የሚያበቃው? እዛም እዚህም ቤት ሰው እውነት ብሎ የያዘውን ፣ የተረዳውን እውነት ብቻ በሥርዓቱ ለምን አያስኬደውም በዚህ የብሽሽቅ ስብከትስ ማንን ደስ ለማሰኘት ከማን ዘንድ ዋጋ ለማግኘት ነው? ማንንስ ለማጽናት ነው ለምንድነው ትውልዱ እንዲህ ልቅ የሆነው ?...... እንደው በቀና ልቦና አስቡት እስኪ ይኽች ልጅ ምን የቅድስት ቤተክርስቲያናችንን ስርዓት ባታውቅ እንኳ ቤተክርስቲያን እንደሆነ ግን ጠንቅቃ እያወቀች

1ኛ, ሰው ከራሱ ቤት ውጪ ግለሰብ ቤት እንኳ ሄዶ እንደፈለገ መሆን በሚታፈርበትና በማይቻልበት ሀገር እየኖረች የሰማይ ስርዓት በሚከናወንባት ታላቅና ትልቅ ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ ያውም ካሜራ ደግና እንዴት ልትጨፍር ቻለች ?
2ኛ , በሀገራችን ባህል በተለያዬ እንቅስቃሴና ሁኔታ የቀብር ስርዓት ይፈጸም ይሆናል ግን ቀብር ወጥቶ በደስታ እንቅስቃሴ ማድረግና መጨፈር ነውር ነው ካዘኑት ጋር እንድናዝን ከተደሰቱት ጋርም ሀሴት እንድናደርግ የሚያዝ መጽሐፍ ቅዱስ የምትናነብ ሆና እንዴት ቀብር ላይ ፈገግ እያለች ካሜራ ፊት ልትጨፍር ቻለች? ........ ሆን ብላ አብሽቆ ለመፈመስ ካልሆነ

ይህ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ትውልዱን የተጠናወተው ክፉ ነገር ትልቅ ትንሹ በየሚዲያው እየተነሳ እያቆሰለ "ይቅርታ ማሩኝ" ማለት ከዚያ ታዋቂ መሆን ደሞ በየቸርቹ በየአደባባዩ የሆነን አካባቢ የሚያስቆጣ ርዕስ እየተፈለገ መለፈፍና ማስጮኽ ማየት የተለመደ ሆኗል። .......በቃ ይብቃ ተው ይህች ቤ/ክ ውለታዋ ቢዘነጋ እንኳ ምን አደረገች ምንስ አጠፋች ? ደስ የማይል ዓመጽን የሚቀሰቅስ ነውና ይህ ዓይነቱ የብሽሽቅ ስብከት ይቅር በቃ !
ኧረ ጌታ ሆይ ቶሎ ናልን !
ሊ/ዲ/ን መባጽዮን (ኢ/ር)
Share ይደረግ

👇👇👇👇👇👇
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
+ የብሽሽቅ ወንጌል +
ወገን ይህ የብሽሽቅ አገልግሎት መቼ ይሆን የሚያበቃው? እዛም እዚህም ቤት ሰው እውነት ብሎ የያዘውን ፣ የተረዳውን እውነት ብቻ በሥርዓቱ ለምን አያስኬደውም በዚህ የብሽሽቅ ስብከትስ ማንን ደስ ለማሰኘት ከማን ዘንድ ዋጋ ለማግኘት ነው? ማንንስ ለማጽናት ነው ለምንድነው ትውልዱ እንዲህ ልቅ የሆነው ?...... እንደው በቀና ልቦና አስቡት እስኪ ይኽች ልጅ ምን የቅድስት ቤተክርስቲያናችንን ስርዓት ባታውቅ እንኳ ቤተክርስቲያን እንደሆነ ግን ጠንቅቃ እያወቀች

1ኛ, ሰው ከራሱ ቤት ውጪ ግለሰብ ቤት እንኳ ሄዶ እንደፈለገ መሆን በሚታፈርበትና በማይቻልበት ሀገር እየኖረች የሰማይ ስርዓት በሚከናወንባት ታላቅና ትልቅ ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ ያውም ካሜራ ደግና እንዴት ልትጨፍር ቻለች ?
2ኛ , በሀገራችን ባህል በተለያዬ እንቅስቃሴና ሁኔታ የቀብር ስርዓት ይፈጸም ይሆናል ግን ቀብር ወጥቶ በደስታ እንቅስቃሴ ማድረግና መጨፈር ነውር ነው ካዘኑት ጋር እንድናዝን ከተደሰቱት ጋርም ሀሴት እንድናደርግ የሚያዝ መጽሐፍ ቅዱስ የምትናነብ ሆና እንዴት ቀብር ላይ ፈገግ እያለች ካሜራ ፊት ልትጨፍር ቻለች? ........ ሆን ብላ አብሽቆ ለመፈመስ ካልሆነ

ይህ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ትውልዱን የተጠናወተው ክፉ ነገር ትልቅ ትንሹ በየሚዲያው እየተነሳ እያቆሰለ "ይቅርታ ማሩኝ" ማለት ከዚያ ታዋቂ መሆን ደሞ በየቸርቹ በየአደባባዩ የሆነን አካባቢ የሚያስቆጣ ርዕስ እየተፈለገ መለፈፍና ማስጮኽ ማየት የተለመደ ሆኗል። .......በቃ ይብቃ ተው ይህች ቤ/ክ ውለታዋ ቢዘነጋ እንኳ ምን አደረገች ምንስ አጠፋች ? ደስ የማይል ዓመጽን የሚቀሰቅስ ነውና ይህ ዓይነቱ የብሽሽቅ ስብከት ይቅር በቃ !
ኧረ ጌታ ሆይ ቶሎ ናልን !
ሊ/ዲ/ን መባጽዮን (ኢ/ር)
Share ይደረግ
@Yahiwenesei
" የእኛው መለያ ለእኛው እንግዳ ሆኖብን አስደነቀን"

ዛሬ አትሌቶቻችን የተቃቀፉት ፣ የተደጋገፉት በብሔራቸው ፣ በክልላቸው ፣ በጎሳቸው፣ በሰፈራቸው ምክንያት አይደለም እንደውም እንደ ጊዜው በሽታ ቢሆን ኖሮማ 3ቱም የተለያዩ ክልሎች ተወላጆች ነበሩ ግን ያደጋገፋቸው ፣ ያተቃቀፋቸው ፣ ያደመቃቸው፣ ኢትዮጵያዊነትና ኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው ዛሬ ትምህርት መውሰድ ለቻለ ሁሉ ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ ሩጫ ውድድር ነበር ብዙውን ተመልካች ዓይኑን በእንባ የመላ ፣ ዓለምን ያስደመመ ህብረት የታየበት ውድድር ! ይህ ነውና የናፈቀን የእኛው መለያ(አንድነታችን) ለእኛም እንግዳ ሆኖ አስደነቀን ! እናም አንድነታችን ይበጀናል !
ሊ/ዲ/ን መባጽዮን (ኢ/ር)
20/12/2015 ዓ/ም
ዲላ ኢትዮጵያ
👇👇👇👇👇👇
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
⛪️የኢኦተቤክ አስተምህሮ ና ስርአትን የጠበቁ የትኞቹን መዝሙራት ማግኝት ይፈልጋሉ⁉️

👏 የቸብቸቦ መዝሙራት
          📖▓⇨→vido    ⇨ግጥም
🎻 የበገና መዝሙራት  
         📖▓⇨→vido     ⇨ግጥም
👑 የቅዱሳን መዝሙራት
          📖▓⇨→vido    ⇨ግጥም
⛪️ የንግስ መዝሙራት
          📖▓⇨→vido    ⇨ግጥም
🤲 የምስጋና  መዝሙራት
          📖▓⇨→vido    ⇨ግጥም
🙏 የንስሐ  መዝሙራት
         📖▓⇨→vido   ⇨ግጥም
💍 የሠርግ መዝሙራት
          📖▓⇨→avido   ⇨ግጥም
🌦 ወቅታዊ መዝሙራት
          📖▓⇨→vido    ⇨ግጥም
🇪🇹 ለአገር የተዘመሩ

          📖▓⇨→vido   ⇨ግጥም
          👇👇
https://youtu.be/74f62hDwSA4

          👇🏽ከእስልምና ወደ ክርስትና በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ በYOUTUBE👇🏽

         👇🏽🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔻👇🏽
   https://www.youtube.com/channel/UCy1JtUNzSqHW-91lAHXN-NA

           👆🏽🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔺‌‌👆🏽
2024/11/16 07:27:24
Back to Top
HTML Embed Code: