Telegram Web Link
Forwarded from RHOBOTH Online shopping
የብሄር ብሄረሰቦች ተብሎ የተቋቋመው የጨበራ ሲኖዱስ እንዲፈርስ ተወስኗል፡፡
ሰልፉን ቤተ ክርስትያኒቱ ማድረግ ከፈለገች መቀጠል እንደምትችል ከስምምነት ላይ ተደርሷል!!
በህገወጥ መንገድ የተሾሙት 25 ጳጳሳት ቆብ እና መስቀላቸውን ያስረክባሉ። ሶስቱ አባቶች በይቅርታ ይመለሳሉ ተብሏል።
ዝርዝር መረጃ ከመግለጫው የምንሰማው ይሆናል።
#ሼር
@ORTODOX_MERJA
የመምህር ምህረት አሰፋ ቤት ተከቧል

ከሰዓታት በፊት በቀጥታ ስርጪት የቅዱስ ሲኖዶሱን መግለጫ እየተናገረ እና ምዕመኑን እያጽናና በነበረበት በመኖሪያ ቤቱ ሳለ በደንገት ሁለት ፓትሮል መኪና መጥቶ ቤቱን ከቦታል
ምንጪ ያሬድ (ያያ) ሁለቱም CHANNEL ተቀላቀሉ @ORTODOX_MERJA
@ORTODOX_MERJA2
Forwarded from RHOBOTH Online shopping
🩸 YouTube ገብታቹ የዛሬውን ቀጥታ ስርጭት መከታተል ለማትችሉ ከ3:10 ጀምሮ በዚሁ ቴሌግራም ቻናላችን እናስተላልፋለን።

🛎 3:10 ላይ ስንገባ መልዕክት እንዲደርሳቹ ከታች ያለውን ሊንክ ይንኩት

https://www.tg-me.com/Ortodox_Merja?voicechat
Forwarded from RHOBOTH Online shopping
ዛሬ 10k አንገባም አድ አድርጉ እንሰባሰብ አንድ እንሁን አድ ያድርጉ @ORTODOX_NANE2 @ORTODOX_NANE2
Forwarded from RHOBOTH Online shopping
ሰበር ዜና

ብፁዑ አቡነ ናትናኤል «መንግስት ቃሉን የማያከብር ከሆነ፣ በቤተክርስቲያን ድርድር ስለሌለ ምዕመናን ልጆቻችን በተጠንቀቅ በመቆም አይናቸውን ቤተክርስቲያን ላይ ጆሯቸውን ወደ ቅዱስ ሲኖዶስ አድርገው የአባቶችን ድምፅ ይጠብቁ» በማለት አሁን ቀጥታ እየተላለፈ ባለው መግለጫቸው አስጠነቀቁ!

ይሄ ነው የምንፈልገው!!! አዛምቱ!!!

@ORTODOX_MERJA
Forwarded from RHOBOTH Online shopping
እኛ ላዘንነው ከጎናችን መሆን ባትችሉ እንኳን ዝምታን ሳትመርጡ በንፁሀን ደም የተሳለቃችሁ ነጭ የለበሳችሁ ሁሉ የቤተክርስቲያንን መከፈል እና መፍረስ የተመኛችሁ ደስም የተሰኛችሁ ሁሉ እንድትፈርስም የአቅማችሁን የጣራችሁ በትንሽ ዳቦ የለወጣችሁ ነገን እጠግብ ብላችሁ ዛሬን በሰው ደም በሺህ አመታት ታሪክ ላይ የተረማመዳችሁ መሸሸጊያ ባጣችሁ ጊዜ ያስጠጋቻችሁን ቤተክርስትያን የገፋችሁ ሀገር ፊደል ቁጥር ቋንቋ ባህል ሰጥታችሁ ሰው ያረገቻችሁን ቤተክርስትያን ላይ ፊታችሁን ያዞራችሁ ሀዘንሽ የግልሽ ያላችሁ ልጆቿ ሲያለቅሱ ማቅ ስተለብስ በየSocial mediaw የተዘባበታችሁ ሀገርን ከነ ክብሯ ጠብቃ በጥቁር ህዝብ ታሪክ የሌለን ጥበብ ለዓለም ያበረከተችን ቤተክርስቲያን ሀዘንሽ ሀዘኔ አደለም ያላችሁ ሁሉ ታሪክሽ ተረት ነው እምነትሽም ጣዖት ነው ያላችሁ ሁሉ ስናዝን አይዟችሁ ያላላችሁ ሁሉ ከዚች ቀን አንስቶ እኔ አላውቃችሁም እናንተም የኔ ሰዎች አይደላችሁም፡፡ ፈጣሪም እምባዋን ቆጥሮ ፍርዱን በህይወት እያላችሁ ይስጣችሁ፡፡
አመሰግናለሁ ፡፡

YILIKAL GETU
@ORTODOX_MERJA
#በቤተ_እግዚአብሔር_ውስጥ_ለእላቂ_ጨርቅ_ለድቃቂ_ሳንቲም_ለሚያልፍ_መብል_ብቻ_እንደመመላለስ_ትልቅ_ኪሳራ_የለም !
#ምኩራብ
በቤተክርስቲያንናችን የዐቢይ ጾም 3ኛ ሳምንት ምኩራብ በመባል ይጠራል ይኸውም በዮሐ 2:12-ፍ በሚነበበው ወንጌል እንደተገለጸው ጌታችንንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓላማቸውን ዘንግተው የቤተእግዚአብሔርን ክብር ተላልፈው በምኩራብ ሲሸጡ ሲለውጡ የነበሩትን ነጋድያን ከቤቱ እንዳስወጣ የሚታሰብበት ሳምንት ነው ይህንንም ስያሜ የሰጠው ማህቶተ ቤ/ክ ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅ/ያሬድ ነው

አዎ ዛሬም የቤተክርስቲያን ራስ መድኃኔዓለም የሚመለከተን የማይመስለን አገልጋዮች አለን የአገልግሎታችንን አድራሻ ምድራዊ ገንዘብ ማካበትን ያደረግን የጸሎቱን ቤት የንግድ ማዕከል ያደረግን መንጋውን የዘነጋን ከመ ይሁዳ የሙዳዬ ምጽዋት ተቆጣጣሪዎች የሆንን
የመንፈስቅዱስን ተልዕኮ የዘነጋን ትውልድ ሲጠፋ ፣ ሲላሽቅ ህዝብ በሞት መንገድ ለመጓዝ ሲፋጠን ፣ምንመን ሲመናመን ፣ ቤተክርስቲያን ስትዘጋ ግድ የማይለን ባለ አደራዎች ጭንቀታችን የደመወዝ ጉዳይ የሆነብን እያንዳንዱ አገልግሎታችንን በምዕንዳን የምንለካ ፣ በገንዘብ ተደራድረን (ይህን ያክል ክፈሉኝ እያልን)ለአገልግሎት የምንንቀሳቀስ አገልጋዮች አለን "ቤቴ የጸሎት ፣ምስኪናን ከእኔ ጋር የሚገናኙበት፣ የምህረት ፊቴን የሚፈልጉበት ቤት ነው እንጂ የንግድ ቤት አይደለም" ይለናል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር "በእውነት ይህን አማናዊ ቃል በእዝነ ልቡናችን ሰምተን መንቃትና በንስሃ መመለስ ይሁንልን!
የቤቱ ቅንዓት የሚያንገበግባቸውን አገልጋዮች እግዚአብሔር ያብዛልን 🙏
26/06/2015
ሊቀ ዲ/ን መብዓጽዮን (ኢ/ር)
👇👇👇👇👇👇
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
  በዓቢይ ጾም 

🤔 የማንን የንስሐ መዝሙር
ማዳመጥ ይፈልጋሉ

💠  ለዐብይ ፆም ብዙ የንስሐ መዝሙሮችን
አዘጋጅተናል በመቀላቀል የፈለጉትን መርጠው
ያዳምጡ‼️

🌹➯ የይልማ ኃይሉ መዝሙር
🌹➯ የቴዎድሮስ ዮሴፍ መዝሙር
🌹➯ የዳግማዊ ደርቤ መዝሙር
🌹➯ የቀዳሜጸጋ መዝሙር
🌹➯ የኪነጥበብ መዝሙር
🌹➯ የቀሲስ ምንዴዬ ብርሀኑ
🌹➯ የቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
🌹➯ የዘማሪ አቤል መክብብ መዝሙር
🌹➯ የዘማሪ አርቲስት ይገረም ደጀኔ
🌹➯ የዘማሪ ገ/ዮሐንስን ገ/ፃዲቅ
🌹➯ የዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ
🌹➯ የዘማሪ ዲ/ን ሮቤል ማቲያስ
🌹➯ የዘማሪት ለምለም ከበደ መዝሙር
🌹➯ የዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
🌹➯ የዘማሪት አቦነሽ አድነው
🌹➯ የዘማሪት ትንቢት ቦጋለ
🌹➯ የዘማሪት ዶ/ር ሔለን ተስፋዬ

እነዚህንና የተለያዩ የንስሐ መዝሙር ያገኙበታል
🀄️🀄️ሉን።  ➲

መዝሙሮችን ለማግኘት ከስር
OPEN የሚለውን ይጫኑት። 👇

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
█  🔰 ✞  𝑶𝑷𝑬𝑵  ❖  𝑶𝑷𝑬𝑵  ✞ 🔰  █
█  🔰 ✞  𝑶𝑷𝑬𝑵  ❖  𝑶𝑷𝑬𝑵  ✞ 🔰  █
█  🔰 ✞  𝑶𝑷𝑬𝑵  ❖  𝑶𝑷𝑬𝑵  ✞ 🔰  █
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
Forwarded from RHOBOTH Online shopping
               †               

በሕገወጥ መንገድ የተሾሙት ግለሰቦች በምእራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ስም ሹመትና ዝውውር እያደረጉ እንደሆነ ተገለጸ፡፡

የካቲት 27 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

በሕገወጥ መንገድ የተሾሙት ግለሰቦች በመንግሥት ድጋፍ በምእራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት በአሉ አብያተ ክርስቲያናት ዝርፊያ መፈጸሙን መዘገባችን ይታወሳል ለዚህም ምንም አይነት እርምጃ በአለመወሰዱ ምክንያት አሁን ላይ ካህናትን በማፈናቀል እና የወረዳ ቤተ ክህነት የሥራ መደቦቸን የሀገር ስብከቱን ማሕተም በመጠቀም ሹመትና ዝውውር በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በዚህም የተነሳ የምእራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ በማለት በሚጠራው የሕገ ወጡ ቡድን አባል በሆነ ቄስ ታዳሳ ደሪቤ በተጻፈ ደብዳቤ የደብረ ንጉሥ መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን የስብከተ ወንጌል ኃላፊና ሒሳብ ሹም የነበሩትን ቄስ ሀሰቤ ታዳሳ በጡሎ እና ዶባ ቤተ ክህነት ወረዳዎች ተዛውረው በሥራ አስኪያጅነት እንዲሠሩ መሾሙን የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት ዘግቧል።

[ TMC ]

         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬

Share ያድርጉት @ORTODOX_MERJA
ዘማሪ ዲ/ን ፀጋዘአብ ይባላል
ከባለጸጋው ከሰማይ አምላክ የተቀበለውን መክሊት አትርፎ እስከነ ትርፉ(ፍሬው) "ይኸው በሰጠኸኝ መክሊት ዕልፍ አተረፍኩበት" ብሎ ሊያስረክበው የተሰጠውን አደራ በታማኝነት ለመወጣት እጅግ ተግቶ ቤ/ክ/ንን የሚያገለግል ትጉህ ወንድም ነው ።
ትጋቱ በመንፈሳዊ ሕይወቱ ብቻ አይደለም "ሰይፍ በክልኤ" እንደሚሉት አበው በሁለቱም በኩል የተሳለ ነውና በዓለማዊ ትምህርቱ በሰለጠነበት ሞያም ለሙያው ታምኖ በትጋት ሕዝብና ሀገሩን የሚያገለግል ትጉህ ሰራተኛም መሆኑን ከቅርብ የሥራ ባልደረቦቹ የሰማሁት ሀቅ ነው።
ላመነበት እውነት በጽናት የሚቆም ማስመሰል የሌለበት ፣ የዋህ ደግሞም ልባም ትንሽ ትልቁን አክባሪ በመልካምነት የተቃኘ ስብዕና ያለው ወንድማችን ነው። ታድያ ከሊቃውንት አባቶቻችን [ከጥሩ ምንጭ] የቀዳውን ጥሩ የሕይወት ውሃ በመልሕቅ ሚዲያ ባለሟቋረጥ እያፈሰሰልን ነው። ሁላችንም ወደዚህ ቻናል ጎራ በማለት ከውሃው እንጠጣና የተጠማች ነፍሳችንን አለምልመን መልሕቁን ይዘን ወደ ወደባችን እንሻገር እላለሁ።
https://youtu.be/y6sN0AJueuo
ትጉሁ ወንድሜ በነገር ሁሉ አምላክ መከናወንን ይስጥህ መልካሙ መሻትህ ይፈጸምልህ!
ይድረስ ለባለጊዜው......
‹‹ይህም ያልፋል›› ✝️

አንድ ንጉሥ አማካሪዎቹን ሰበሰበና እንዲህ ሲል አዘዛቸው፡፡ ‹‹ስከብርም ሆነ ስዋረድ፣ ሳገኝም ሆነ ሳጣ፣ የሁሉም የበላይ ስሆንም ሆነ የበታች፣ እጅግ ስደሰትም ሆነ ስከፋ፣ ድል ሳደርግም ሆነ ድል ስሆን፣ ዝናዬ ሲናኝም ሆነ ሲከስም፣ ያንን ነገር በሰላምና በጥበብ እንዳልፈው የሚያደርግ አንድ ዐረፍተ ነገር ስጡኝ፡፡ ላስታውሰው የምችል፣ መንገዱንም የሚመራኝ፣ ከልክ አልፌ እንዳልሄድ፣ ከልክ ወርጄም እንዳልወድቅ፣ የሚያደርግ አንድ ዐረፍተ ነገር አምጡልኝ፡፡ የተወሳሰብ ፍልስፍና አልፈልግም፣ ቀላልና ግልጽ የሆነውን እሻለሁ፡፡ ይህንን ሳትይዙ እንዳትመለሱ››
አማካሪዎቹ ከቤተ መንግሥቱ ወጥተው ለአራት ወራት ያህል መከሩ፡፡ አነሡ ጣሉ፤ በመጨረሻም የደረሱበትን ሐሳብ በብራና ጽፈው ወደ ንጉሡ ዘንድ መጡ፡፡ የተጠቀለለውንም ብራና ሰጡት፡፡

ንጉሡም ገለጠና አነበበው፡፡ እንዲህ ይል ነበር ‹‹ይህም ያልፋል››፡፡ ለምን? አላቸው ንጉሡ፡፡በየትኛውም የሥልጣንና የሀብት ከፍታ ላይ ብትሆን፣ በየትኛውም የዝናና የክብር ሠገነት ላይ ብትደላደል፣ ‹ይህም ያልፋል› ብለህ ካሰብክ ግፍ አትሠራም፣ ፍትሕ አታዛባም፣ ድኻ አትበድልም፣ ከልክህም አታልፍም፡፡ ራስህን ዘላለማዊ አድርገህ ካሰብክ፣ ጊዜ የማይቀየር ዓለምም የማትዞር ከመሰለህ ግን ራስህን ለማስተካከል እንኳን ጊዜ ሳታገኝ ነገሮች ይቀየሩና በሠራኸው ወኅኒ ትወረወራለህ፣ ባወጣኸው ሕግ ትቀጣለህ፣ በቆረጥከው ዱላ ትመታለህ፣ ባሳደግከው ውሻ ትነከሳለህ፡፡ ስለዚህ አሁን የተቀመጥክበትን ዙፋን፣ የምታንቀጠቅጥበትንም ሥልጣን፣ ‹ይህም እንኳን ያልፋል› ብለህ አስበው፡፡


ተቀናቃኞችህን ድል እንዳደረግክ፣ አገሩን ጠቅልለህ እንደያዝክ፣ ሁሉ በእጅህ ሁሉ በደጅህ እንደሆነ፣ በለስ እንደቀናህ፣አንደኛ እንደወጣህ፣ እንደ ተጨበጨበልህ ፣ እንደታፈርክና እንደተከበርክ፣ አትቀርም፡፡ ይህም በጊዜው ያልፋል፡፡ እነዚህ ዛሬ በዙሪያህ ሆነው የሚያፍሱልህ የሚያጎነብሱልህ፣ ሳታስነጥስ ይማርህ፣ ሳትወድቅ እኔን የሚሉህ፤ ሳይበርድህ ካልደረብንልህ ሳታዝን ካላለቀስንልህ የሚሉህ፤ ሳትጠራቸው አቤት፣ ሳትልካቸው ወዴት የሚሉህ፣ ይኼ ሁሉ ሲያልፍ ያልፋሉ፡፡

ካንተም በፊት ሌሎች ነበሩ፣ ካንተም በኋላ ሌሎች ይመጣሉ፡፡ ከፊትህ ሌላ ባይኖር ኖሮ ከኋላህ ሌላ ባልመጣም ነበር፡፡ በጊዜ ውስጥ ትናንት ዛሬና ነገ አሉ፡፡ ዛሬ ትናንት፣ ነገ ዛሬ እየሆኑ ያልፋሉ፡፡ አንተ ሌሎችን እንደተካህ ሁሉ የሚተካህም የግድ ይመጣል፡፡ አንተ ሌሎችን እንደረታህ ሁሉ የሚረታህም ነገ ይመጣል፡፡ አንተ ሌሎችን እንዳሠርክ ሁሉ የሚያሥርህም ነገ ይመጣል፡፡ አንተ እንደቀበርክ ሁሉ ቀባሪህም ነገ ይመጣል፡፡ እስኪ ለቀስተኞችን እይ፤ የዛሬ ቀባሪ ሁሉ ነገ በተራው ተቀባሪ ነው፡፡ ማንም ራሱን የሚቀብር የለም፡፡ ሌላውን እንደቀበረ ሁሉ እርሱን ሌላ ይቀብረዋል እንጂ፡፡ ‹ይህም ሁሉ ያልፋል› ብለህ ካሰብክ ሁሉን በልኩ፣ ሁሉን በደንቡ ታደርገዋለህ፡፡

የሌሎችን ታሪክ አጥፍተህ፣ የሌሎችን ሐውልት ሰብረህ፣ የሌሎችን ዋጋ አርክሰህ፣ የሌሎችን ስም ገድለህ መኖር ትችላለህ፤ ዐቅሙና ሥልጣኑ እስካለህ ድረስ፡፡ ነገር ግን ይህም ያልፋል፡፡ ያንተንም ታሪክ የሚያጠፋ፣ ያንተንም ሐውልት የሚሰብር፣ ያንተንም ስም የሚያጎድፍ፣ ያንተንም ዋጋ የሚያረክስ በተራው ይመጣል፡፡ የሚተካህን የምትፈጥረው ዛሬ በምታደርገው ተግባር ነው፡፡ ክፉ ከሆንክ ክፉ ይተካሃል፣ ርቱዕ ከሆንክ ርቱዕ ይተካሃል፡፡
ይኼ ሁሉ ዓለም አልፎ ብትወድቅ፣ ብትሰበር፣ ብትታሠር፣ ብትረሳ፣ ብትሰደድ፣ ብታጣ፣ ብትነጣ፣ ከላይ ወደታች እንዳየኸው ሁሉ ከታች ወደ ላይ የምታይበት ዘመን ቢመጣ፣ ያሰብከው ቀርቶ ያላሰብከው ቢሆን፣ ‹ይህም ያልፋል› ብለህ አስብ፡፡ ‹ይህም ያልፋል› ብለህ ካሰብክ ተሥፋ አትቆርጥም፣ ነፍስህ ሳትወጣ አትሞትም፣ ራስህን ለብስጭትና ንዴት፣ ለቁጣና ትካዜ አሳልፈህ አትሰጥም። የሥልጣን ጫፉ መውረድ እንደሆነው ሁሉ የውርደት ጫፉ ሥልጣን ነው፡፡ የብርሃን ጫፉ ጨለማ፣ የጨለማም ድንበሩ ብርሃን ነው፡፡ የበሽታ ጫፉ ጤና፣ የጤናም ጫፍ በሽታ ነው፡፡ ዓለም ቋሚ አይደለችም፡፡ ጊዜ ወደ ፊት ብቻ ነው የሚሄደው፡፡ እሥር ቤቱ ሲተከል የነበሩት አሁን የሉም፤ ስለዚህም አንተም እዚያ እሥር ቤት አትኖርም፡፡ ችግር ሲጀመር የነበሩት አሁን የሉም፤ አንተም ችግር ውስጥ የግድ አትሰምጥም፡፡ እንደሚያልፍ ካመንክ፡ ለማሳለፍ ትጥራለህ፡ እንደሚያልፍ ካላመንክ ግን ያለህበትን ትቀበለዋለህ፡፡...ይህም ያልፋል...!!!

~||~~~~~ሀቁ ይህ ነው አንተምጋ ያለው ያልፋል
👇👇👇👇👇👇
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
  በዓቢይ ጾም 

🤔 የማንን የንስሐ መዝሙር
ማዳመጥ ይፈልጋሉ

💠  ለዐብይ ፆም ብዙ የንስሐ መዝሙሮችን
አዘጋጅተናል በመቀላቀል የፈለጉትን መርጠው
ያዳምጡ‼️

🌹➯ የይልማ ኃይሉ መዝሙር
🌹➯ የቴዎድሮስ ዮሴፍ መዝሙር
🌹➯ የዳግማዊ ደርቤ መዝሙር
🌹➯ የቀዳሜጸጋ መዝሙር
🌹➯ የኪነጥበብ መዝሙር
🌹➯ የቀሲስ ምንዴዬ ብርሀኑ
🌹➯ የቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
🌹➯ የዘማሪ አቤል መክብብ መዝሙር
🌹➯ የዘማሪ አርቲስት ይገረም ደጀኔ
🌹➯ የዘማሪ ገ/ዮሐንስን ገ/ፃዲቅ
🌹➯ የዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ
🌹➯ የዘማሪ ዲ/ን ሮቤል ማቲያስ
🌹➯ የዘማሪት ለምለም ከበደ መዝሙር
🌹➯ የዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
🌹➯ የዘማሪት አቦነሽ አድነው
🌹➯ የዘማሪት ትንቢት ቦጋለ
🌹➯ የዘማሪት ዶ/ር ሔለን ተስፋዬ

እነዚህንና የተለያዩ የንስሐ መዝሙር ያገኙበታል
🀄️🀄️ሉን።  ➲

መዝሙሮችን ለማግኘት ከስር
OPEN የሚለውን ይጫኑት። 👇

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
█  🔰 ✞  𝑶𝑷𝑬𝑵  ❖  𝑶𝑷𝑬𝑵  ✞ 🔰  █
█  🔰 ✞  𝑶𝑷𝑬𝑵  ❖  𝑶𝑷𝑬𝑵  ✞ 🔰  █
█  🔰 ✞  𝑶𝑷𝑬𝑵  ❖  𝑶𝑷𝑬𝑵  ✞ 🔰  █
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
+ " ይባዕ አምላከ ምህረት
የምህረት አምላክ ይግባ"+

በኃጢአት ሸክም የጎበጥን፣ ዓለምንና በውስጡ ያሉትን በመውደድ ካቦ ተጠፍንገን የታሰርን ሰማይ አልታይ ያለን ፣ የልባችንን ዕልፍኝ በቂም፣ በበቀል፣በትዕቢት በበደል ቁልፍ ከርችመን ዕርጋታና ሰላም አጥተን በዓለም ባህር የምንናጥ ከልባችን ደጃፍ ቆሞ ራሱ ባበጃጀው ቤት ለመግባት የእኛን ፈቃድ የሚጠይቀውንና የሚያንኳኳውን ድምጽ እንስማ ፣ ግድ የለም እንክፈትለት በመኃልይ ዘሰሎሞን ላይ እንደተጠቀሰችው ሴት "እግሬን ታጥቤአለሁ ጫማዬንም አውልቄያለሁ ወደ መኝታየም ወጥቻለሁ ከእግዲህ አልወርድም" አንበል በዚያው ለዘላለሙ ማሸለብም አለና።

ግድ የለም ይዕባዕ ንጉሠ ስብሐት ፣ የሰላም አምላክ ይግባ እፍቀድለት ሊያስጨንቀን ያይደለ ካስጨነቀን መከራ ሊገላግለን ያንኳኳልና ፣ ሸክም ሊያበዛብን ያይደለ ሸክማችንን አርግፎ ዕረፍት ሊሆነን ፣ ሰላም ፣በረከቱን ሊያድለን ያንኳኳልና እንስማው ያኔ በውዳሴ ታጅቦ ወደ ኢየሩሳሌም የገባው ጌታ እፎይታ ወደ ናፈቀው ሕይወታችን ይግባ። የዘንባባ ዝንጣፊ ያይደለ የልባችንን ምንጣፍ እንዘርጋለት ፣ ከሚመላለሱብን ክፉ ሀሳቦች ይገላግለን "ዘንድ በልቤ ከተማ ተመላለስበት" እንበል "ንገስ በልቤ ዙፋን" እንበለው በኪሩብ ጀርባ ነግሶ የሚኖረው ልዑል ከሰማየ ሰማያት የወረደው እኛን አድራሻ አድርጎ ነውና ድንጋዮች ስንኳ አንደበት አውጥተው ከሚያመሰግኑለት የምስጋና ደቦ ሁኔታዎች አያጉድሉን "ሆሳዕና በአርያም ጌታ ሆይ ሀገራችንን ህዝባችንን አሁን አድን" እንበል ከልባችን ደጃፍ ቆሞ የሚያንኳኳው መድኃኒትን የሚያዝዝ ሳይሆን እራሱ የሞት መድኃኒቱ ነውና ደጃችን ይከፈት ይባዕ አምላከ ምህረት ያኔ ሁሉም መልካም ይሆናል።
01/07/2015
ሊ/ዲ/ን መብዓጽዮን (ኢ/ር)
ዲላ_ጪጩ
ኢትዮጵያ
👇👇👇👇👇👇
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
"ምክረ አይሁድ"
" እንግዲህ ከዚያ ቀን ጀምረው ሊገድሉት ተማከሩ።"
(የዮሐንስ ወንጌል 11:53)
በቤተክርስቲያናችን ሥርዓት መሰረት የዛሬው ዕለት ምክረ አይሁድ ተብሎ ይጠራል። ልብንና ኩላሊትን በሚመረምር ጌታ ሊገድለው በስውር የሚመክር እንዴት ያለ ምስኪን ነው ! አይሁድ የሞት መድኃኒቱን ንጹሁን ጌታ ፣ የሕይወት ምንጭ የሆነውን ፣ ገና ሳይጸነሱ የሚያውቃቸውን ፈጣሪ በሞት ሊቀጡት ተማከሩ ፣ አንደበት በሰጣቸው ላይ አንደበታቸውን ከፍተው የሞት ምክር መከሩበት እንዴት ያሳዝናሉ ! ....... ዛሬም እንዲሁ ነው ወገኖቼ ቸሩ አምላካችን በምህረቱ ጎብኝቶን ሳለ እርሱ በሰጠን ዕለትና ሰውነት ከጠላት ጋር እየመከርን ለኃጢአት ቀጠሮ የምንይዝ ፣ ለጭፈራ ፣ ለቂም ፣ለጥፋት ለበቀል ፣ለዝሙት ፣ ለዓለም ከንቱ ነገር ቀጠሮ የምንይዝ ካለን ከነዚያ አይሁድ በምን ተለየን ? እባክህን ሰው ሆይ የጌታህን በጎ በፈቃድ አስተውል በትዕዛዙም ሂድ !
ማስተዋል ይብዛልን🙏
04/08/2015
ሊ/ዲ/ን መብዓጽዮን (ኢ/ር)
ዲላ_ጪጩ
ኢትዮጵያ
👇👇👇👇👇👇
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
ወዳጄ ሆይ ትክክለኛው ትህትና በዕድሜ ፣ በባለጠግነት፣ በዝና ወይንም በልዩ ልዩ ነገር ለሚበልጡን ሰዎች የምናሳየው መታዘዝ ሳይሆን በሁሉ ነገር ለሚያንሱን ሰዎች የምንገልጠው የፍቅር ፣የከፍታ ሕይወት ነው። ይህን ደግሞ ከመምህረ ትህትና ከክርስቶስ ነው የተማርነው።"

በእውነት የእውነት ትሁታን ያድርገን🙏
05/08/2015 ዓ/ም
ሊ/ዲ/ን መብዓጽዮን (ኢ/ር)
ዲላ
ኢትዮጵያ
👇👇👇👇👇👇
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
"እንኳን ሰቀሉት"

"...በርባን ቢሰቀል ኢየሱስ ቀርቶ
ምን ይጠቅመናል ሽፍታ ሞቶ
እንኳን ኢየሱስን ሰቀሉት
የሞቱን መድኃኒት..."

👉ባለበገናው ሊቅ መሪጌታ ፍቅሩ ሳህሉ
ነፍሴን ያዳንኃት የሞት መድኃኒቱ ሆይ በሁለንተናዬ ክበር ተመስገን 🙏
ሊ/ዲ/ን መባጽዮን
05/08/2015
ራጴ
ኢትዮጵያ
https://www.tg-me.com/Yahiwenesei
2024/10/01 16:34:49
Back to Top
HTML Embed Code: