Telegram Web Link
የግራፊክ ዲዛይን፣ ቪዲዮ ኤዲቲንግ፣ ሞሽን ግራፊክስ እና ዲጂታል ማርኬቲንግ ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን። 

👉 100% በተግባር የተደገፈ ስልጠና
👉 Advanced Graphics + Video Editing + Motion Graphics + Digital Marketing በአንድ ላይ
👉 ከ50 በላይ ፕሮጀክቶች ያሉት
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት

☎️    0906777799 / 0906777755

አድራሻ፦ ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: https://www.tg-me.com/sagetraininginstitute
TikTok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዓመትና ከዚያ በላይ ነባር መደበኛ ተማሪዎችን በመቀበል ላይ ይገኛል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ከመስከረም 20/2017 ዓ.ም ጀምሮ ነባር መደበኛ ተማሪዎቹን አቀባበል እየተቀበለ መሆኑን ተገልጿል፡፡

መደበኛ ትምህርት የመጀመሪያ ቀን መስከረም 23 ቀን 2017 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
በርካታ ዩኒቨርሲቲዎች በመደበኛ እና በተከታታይ መርሐግብር አዲስ የድኅረ ምረቃ አመልካቾችን ለመቀበል ያወጡትን ማስታወቂያ እያራዘሙ ነው።

አመልካቾች በትምህርት ሚኒስቴር የተሰጠውን ሀገር አቀፍ የድኅረ ምረቃ የመግቢያ ፈተና (NGAT) ማለፍ ይጠበቅባችኋል፡፡

(የተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች የድኅረ ምረቃ ፕሮግራም ማስታወቂያ ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
#የተሻሻለ

በ2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታችሁን ለመከታተል የመግቢያ ፈተና የወሰዳችሁ ተማሪዎች ውጤታችሁ ተለቋል፡፡

ፈተናውን የወሰዳችሁ ተማሪዎች ተከታዩን ሊንክ በመጠቀምና አድሚሽን ቁጥራችሁን በማስገባት ውጤታችሁን መመልከት የምትችሉ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ውጤት ለማየት 👇
https://aastu.ethernet.edu.et/

@tikvahuniversity
#Karvard_College
#ካርቫርድ_ኮሌጅ

🔔 በምዝገባ ላይ ነን!

ሙሉ ዕውቅና ባገኘንባቸው፦

Masters Programs
- MPH (General)
- MPH in Nutrition
Degree Programs
- Medical Radiology Technology
- Accounting & Finance
- Business Management
TVET Programs
- Medical Radiology
- Nursing
- Hardware & Networking Service
- Accounting & Finance
- Marketing & Sales Management
- Human Resource Management
Other Programs
- Remedial Program
- Short-term Training
- CPD Course

አድራሻ፦ አዲስ አበባ፣ ከፒያሳ ወደ ራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል በሚወስደው መንገድ፣ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት፣ ዳሞት ህንፃ

☎️ 0933686868 / 0903676869
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ስኬታማ የሆነው የልጃገረዶች አዳሪ ትምህርት ቤት

በክልሉ ሆሞሻ ወረዳ የሚገኘው 'ፋሮ የልጃገረዶች አዳሪ ትምህርት ቤት' ዘንድሮ ያስፈተናቸውን የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ ማሳለፍ መቻሉ ይታወቃል፡፡

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የትምህርት ዘርፉን ከሚደግፉ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች መካከል መሠረቱን በእንግሊዝ ያደረገው "ፋሮ ፋውንዴሽን" አንዱ ነው፡፡ ድርጅቱ በክልሉ አሶሳ ከተማ "ፋሮ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት" እንዲሁም ከአሶሳ 37 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው "ፋሮ ሆሞሻ የልጃገረዶች አዳሪ ትምህርት ቤትን" ያስተዳድራል፡፡

ፋውንዴሽኑ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካለፉት ስምንት ዓመታት ጀምሮ ትምህርት ቤት በመመስረት ጥራት ያለው ትምህርት ለተማሪዎች እያቀረበ ይገኛል፡፡ ፋውንዴሽኑ የፋሮ ሆሞሻ የልጃገረዶች አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን በ2012 ዓ.ም. አቋቁሟል፡፡

አዳሪ ትምህርት ቤቱ ለሦስተኛ ጊዜ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ተማሪዎችን ማስፈተኑን የሚገልጹት ኃላፊው፣ ዘንድሮ ለፈተና ያስቀመጣቸው 12 ተማሪዎች ሁሉም የማለፊያ ነጥብ በማምጣት ወደ ዩኒቨርሲቲ መግባታቸውን በፋሮ ፋውንዴሽን የኢትዮጵያ ትምህርት ዘርፍ ኃላፊ ሚኪያስ ሰሎሞን ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

የትምህርት ቤቱ ሴት ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲ ከገቡ በኋላ ትምህርታቸውን እስኪያጠናቅቁ ድረስ ድርጅቱ የምግብ፣ የአልባሳት እና የትራንስፖርት ወጪያቸውን ይሸፍናል፡፡ በተጨማሪም ከፍተኛ ነጥብ ላስመዘገቡ ተማሪዎች በውጭ አገራት ነፃ የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡ በዚህ ነፃ የትምህርት ዕድል ተጠቅመው በቱርክ እና በርዋንዳ ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ተማሪዎች መኖራቸውንም ኃላፊው ጠቅሰዋል፡፡ #ሪፖርተር

@tikvahuniversity
#MoH

ጤና ሚኒስቴር በፅሁፍ ከሚሰጠው የብቃት ምዘና ፈተና በተጨማሪ #የተግባር ተኮር የብቃት ምዘና ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ ሊሰጥ ነው፡፡

በዚህም ሰኔ 2016 ዓ.ም የተሰጠውን የመውጫ ፈተና አልፈው ዲግሪ ለያዙና የተግባር የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ በዝግጅት ላይ ለሚገኙ #የአንስቴዥያ ጤና ባለሙያዎች #የተግባር ተኮር የብቃት ምዘና ፈተና መስከረም 30/2017 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

ተፈታኞች ከሚፈተንበት ቀን አንድ ቀን ቀደም ብሎ ማለትም መስከረም 29/2017 ዓ.ም ጠዋት 3፡00 ሰዓት በመፈተኛ ጣቢያ በመገኘት ስለፈተናው አሰጣጥ ቅድመ ገለጻ (Orientation) መከታተል፤ የመፈተኛ ክፍሉን መለየት ይኖርባቸዋል።

ተፈታኞች በፈተናው ዕለት ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ (የቀበሌ መታወቂያ፣ ፓስፖርት፣ መንጃ ፍቃድ ወይም ሌላ በግልጽ የሚታይ ህጋዊ መታወቂያ) ይዛችሁ መገኘት ይኖርባችኋል፡፡ ምንም አይነት የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ (ስልክ፣ የእጅ ሰዓት፣ መነጽር (የተረጋገጠ የዕይታ ችግር ከሌለ በስተቀር)፣ ቦርሳ እና ሌሎች እቃዎች፣ ምንም አይነት ማጣቀሻዎች እንዲሁም ባዶ ወረቀቶች፣ ምግብ ወይም መጠጥ (የተረጋገጠ የጤና ችግር ከሌለ በስተቀር) ይዞ መግባት አይፈቀድም፡፡

ተመዛኞች ወደ ፈተና ጣቢያ ስትሔዱ ሲስተሙ የሚሰጣችሁን QR Code ያለው የፈተና መግቢያ /ስሊፕ/ Print አድርጋችሁ መያዝ ይኖርባችኋል፡፡ በፈተናው ወቅት አቴንዳንስ ላይ በአግባቡ መፈረም እንዳትዘነጉ ተብሏል፡፡

@tikvahuniversity
ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ተማሪዎች ቅዳሜ መስከረም 25/2017 ዓ.ም ያስመርቃል።

ተመራቂዎቹ በመደበኛ፣ በተከታታይ እና በክረምት መርሐግብር ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

@tikvahuniversity
📢 በሐዋሳ እና በድሬዳዋ ለምትገኙ ወጣቶች!

የመስራት የወጣቶች መማክርት ቡድን (M-YAG) አባል በመሆን ለለውጥ ድምፅ ሁኑ!

M-YAG ከቡድን በላይ ነው። በመስራት ፕሮግራም ውስጥ የወጣቶችን ድምፅ ለማሰማት የተዘጋጀ ሃይል ነው። እድሜአቸው ከ15 እስከ 35 የሆኑ ለመምራት፣ ለማነሳሳት እና በማኅበረሰቦቻቸው ላይ አዎንታዊ ተፅዕኖ ለማሳደር ዝግጁ የሆኑ ወጣቶችን እየፈለግን ነው!

በM-YAG በኩል በዋጋ ሊተመን የማይችል የግል እና ሙያዊ ክህሎቶችን ታገኛላችሁ፣ ጠንካራ አመራር ላይ ቁርጠኛ የሆነ ቡድን አካል ትሆናላችሁ።

ተፅዕኖ ለማሳደር ዝግጁ ከሆናችሁ እዚህ ይመዝገቡ፦ https://forms.gle/pd3JLtHM1u1fDD4D6

#MYAG #Mesirat #መስራት #Hawassa #ሐዋሳ #DireDawa #ድሬዳዋ
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በበይነመረብ (E-Learning) ማስተማር ሊጀመር ነው፡፡

በበየነ መረብ ትምህርት አሰጣጥ ዙሪያ የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ዘርፍ አመራሮች የምክክር ጉባኤ አካሒደዋል።

ዩኒቨርሲቲው በዚህ ዓመት የበይነ መረብ ትምህርት በተጠናከረ መልኩ እንደሚሰጥ ገልጿል።

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በሀገር አቀፍ ደረጃ ዘመናዊ የመልቲ ሚዲያ ስቱዲዮ ግንባታ ከተከናወነባቸው አምስት ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ ነው። ተቋሙ በቴክኖሎጂ የታገዘ የመረጃ ቋት ያለው መሆኑም ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የ 'ኢ-ለርኒግ' ማስጀመሪያ መርሐግብር አካሔደ።

መርሐግብሩ መንግስት በ2017 ዓ.ም የዲጂታል ትምህርት በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ለማስጀመር የያዘው ዕቅድ አካል ነው።

በዚህም ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ከትምህርት ሚኒስቴር እና ከአሪዞና ስቴት ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለ353 መምህራን እና ለ9,500 ተማሪዎች በ'ኢ-ለርኒግ' ፕሮግራም ላይ የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ጀምሯል።

የ e-SHE ፕሮግራም

e-SHE 'ኢ-ለርኒግ ከፍተኛ ትምህርትን ለማጎልበት' የአምስት ዓመት ፕሮጀክት ሲሆን በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዲጂታል ትምህርትን ተቋማዊ ለማድረግና ለማጎልበት ግብ ያደረገ ነው።

በፕሮጀክቱ የአምስት ዓመት ቆይታ 35 ሺህ መምህራን እና 800 ሺህ ተማሪዎች የዲጂታል ትምህርት አቅም ግንባታ ስልጠናዎችን እንደሚወስዱ ይጠበቃል።

@tikvahuniversity
#ሎርካን_ሜዲካል_ኮሌጅ

የበርካታ ዓመታት ልምድ ባላቸው ሐኪሞችና ምሁራን ባለቤትነት የሚመራው ሎርካን ሜዲካል ኮሌጅ ምዝገባ ጀምሯል❗️

BSc fields of study:
→ Doctor of Medicine
→ Doctor of Dental Medicine
→ Bachelor of Dental Science
→ Nursing

TVET Programs:
→ Dental Therapy
→ Nursing
→ Medical Laboratory
→ Pharmacy
→ Radiography

የ CPD ማዕከል አገልግሎት!

☎️ 0913398780 / 0911596059

🔔 በምዝገባ ላይ ነን!!

አድራሻ፦
CMC አደባባይ ከፀሐይ ሪል እስቴት ጀርባ ከ ICMC ጠቅላላ ሆስፒታል አጠገብ
Addis Ababa, CMC Square, behind Tsehay Real Estate, next to ICMC General Hospital

Facebook: https://www.facebook.com/Lorcanmedicalcollege
⚡️ቅመም MIFIን ገዝተን ፈጣን 4G ኢንተርኔት እንጠቀም! ከሳፋሪኮም ጋር አንድ ወደፊት⚡️
  
🔗 የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናውርድ፦ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom #SafaricomEthiopia #1Wedefit #Furtheraheadtogether
#ASTU

በ2017 ዓ.ም በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታችሁን ለመከታተል የመግቢያ ፈተና የወሰዳችሁ ተማሪዎች ውጤታችሁ ተለቋል፡፡

ፈተናውን የወሰዳችሁ ተማሪዎች ተከታዩን ሊንክ በመጠቀምና አድሚሽን ቁጥራችሁን በማስገባት ውጤታችሁን መመልከት የምትችሉ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ውጤት ለማየት 👇
http://stuoexam.astu.edu.et/

@tikvahuniversity
#ይመዝገቡ

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 2ኛ ዙር የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (GAT) የማመልከቻ ግዜ ቅዳሜ መስከረም 25/2017 ዓ.ም ያበቃል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለGAT ፈተና ለማመልከት 👇
https://portal.aau.edu.et

ለማመልከት፦

https://Portal.aau.edu.et ን ይክፈቱ።
► Exam Application የሚለውን ይጫኑ።
► Test Taker Registration ቅፅን ይሙሉ።
► ፓስፖርት መጠን ያለው ፎቶዎን ያስገቡ።
► Submit የሚለውን ይጫኑ።
► ሲስተሙ የሚሰጥዎትን ቁጥር ኮፒ ያድርጉ።
► የGAT ፈተና ክፍያ ብር 1000 በቴሌብር ይክፈሉ።
► የክፍያ ቲኬትዎን አውርደው ፕሪንት ይበሉ። የፈተና ቀን ወደመፈተኛ አዳራሽ ለመግባት ያስፈልግዎታል።

@tikvahuniversity
#AAU

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ ከሆነ በኋላ በራሱ የቅበላ ፖሊሲ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎችን ለመጀመሪያ ጊዜ ተቀብሏል፡፡

በዚህም ዩኒቨርሲቲው 5,300 የቅድመ ምረቃ ተማሪዎችን ለ2017 የትምህርት ዘመን መቀበሉ ታውቋል፡፡

2,660 በመንግስት ስፖንሰር የተደረጉ እና 2,640 የግል አመልካቾች መቀበሉን የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ጀይሉ ኡመር (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ከአጠቃላይ 11, 939 አመልካቾች በጥብቅ የምልመላ ሒደት 5,300 ተማሪዎችን የተቀበለ ሲሆን፤ ይህም 44 በመቶ የቅበላ መጠን እንደሆነ ምክትል ፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል፡፡

በራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲው የቅበላ ፖሊሲ መሰረት 15 በመቶ ለሴቶች፣ 5 በመቶ ለአካል ጉዳተኞች እና በእድገት ወደኋላ ለቀሩ አካባቢዎች ዕድል የተሰጠ ሲሆን፤ ለ200 ተማሪዎች ደግሞ ነፃ የትምህርት ዕድል መሰጠቱን ጠቁመዋል፡፡

@tikvahuniversity
#TVTI

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በሪሚዲያል ፕሮግራም የ12ኛ ክፍል ያጠናቀቁ ተማሪዎችን መቀበል ሊጀምር ነው።

ተቋሙ በ2017 ትምህርት ዘመን ሰልጣኞችን በስፋት ለመቀበል እንዲሠራ የኢንስቲትዩት ሴኔት ውሳኔ አሳልፏል።

በዚህም ተቋሙ ከዚህ ቀደም ሰልጣኖችን ከሚቀበልባቸው አማራጮች በተጨማሪ በሪሚዲያል ፕሮግራም የ12ኛ ክፍል ያጠናቀቁ ሰልጣኞችን እንደሚቀበል ተገልጿል።

የሰልጣኞች አቀባበል ትምህርት ሚኒስቴር በሚያስቀምጠው መመሪያ መሠረት ይተገበራል ተብሏል።

@tikvahuniversity
2024/10/03 10:55:55
Back to Top
HTML Embed Code: