Telegram Web Link
#HawassaUniversity

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም በመደበኛ የዲግሪ ፕሮግራም አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ኀዳር 9 እና 10/2017 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦
- የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በዋናው ግቢ
- የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ግቢ

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➭ የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
➭ ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➭ አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➭ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና ትራስ ጨርቅ፣
➭ የስፖርት ትጥቅ

@tikvahuniversity
#RayaUniversity

በ2017 ዓ.ም በራያ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ተማሪዎች እና በ2016 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው የማጠናከሪያ ትምህርት (Remedial Program) ወስዳችሁ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ህዳር 2 እና 3/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ትምህርት ህዳር 9/2017 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል፡፡

Note:
በ 2017 ዓ.ም ወደ ራያ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የሪሚዲያል ተማሪዎች በሌላ ማስታወቂያ ጥሪ እንደሚደረግላችሁ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

(የዩኒቨርሲቲው ጥሪ ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
💫 ከዳር እስከ ዳር አስተማማኙን ኔትወርካችንን እያሰፋን ወደ እናንተ እየቀረብን ነው! 🙌 ከአስተማማኙ ኔትወርካችን ጋር አሁንም በአብሮነት ወደፊት!

አስተማማኙን ኔትወርክ ዛሬውኑ እንቀላቀል!

የቴሌግራም ቦታችንን https://www.tg-me.com/official_safaricomet_bot በመጠቀም የአየር ሰዓት ወይም ልዩ ልዩ ጥቅሎችን እንግዛ!

#MPESASafaricom #SafaricomEthiopia
#1Wedefit #Furtheraheadtogether
ክቡር ኮሌጅ በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ወስደው የማለፊያ ነጥብ ያላሟሉ ተማሪዎች የአቅም ማሻሻያ መርሐግብር (Remedial Program) ለመስጠት ምዝገባ ጀምሯል!

👉 በትምህርት ሚኒስቴር የመግቢያ መስፈርት መሠረት
👉 በተጨማሪ የጥናትና የፈተና አወሳሰድ ክህሎት ስልጠናን ያካተተ
👉 የበይነ መረብ የፈተና አሰጣጥ ስልጠናን ያካተተ
👉 ትምህርቱ ብቃት ባላቸው መምህራን እንዲሁም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት አሰጣጥ ልምድ ባለው ተቋም በመታገዝ ይሰጣል፡፡

Website: https://kibur.edu.et
አድራሻ፦ ጀሞ ሚካኤል ከአፍሪካ ህንፃ አጠገብ
☎️ 0113854042 / 0904848586

https://www.tg-me.com/kiburcollege
#HaramyaUniversity

በ2017 ትምህርት ዘመን ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የፍሬሽማን ቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም ተማሪዎች እንዲሁም በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ጊዜ ከህዳር 9 እስከ 11/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ምዝገባ ለማድረግ የሚያስፈልጉ፦
- የ8ኛ ክፍል ካርድ፣
- ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት፣
- የ12ኛ ከፍል ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
- 6 ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ፣
- ብርድልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ መያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡

ከላይ የተዘረዘሩትን የትምህርት ማስረጃዎች እና ፎቶግራፍ ስካን አድርጋችሁ በሶፍት ኮፒ መያዝ ይኖርባችኋል፡፡

@tikvahuniversity
#OdaBultumUniversity

በ2016 ዓ.ም የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ፕሮግራም ስትከታተሉ ቆይታችሁ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ያስመዘገባችሁ እና በ2017 ዓ.ም ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ህዳር 4 እና 5/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ምዝገባ ለማድረግ የሚያስፈልጉ፦

- የ8ኛ ክፍል ስርትፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
- የ10ኛ እና 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
- ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
- አራት ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ፣
- አንሶላ፣ ትራስ ጨርቅ፣ ብርድ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ መያዝ ይኖርባችኋል፡፡

@tikvahuniversity
#AAU

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የብሪክስ+ ሀገራት ዩኒቨርሲቲዎች ማኅበር መስራች አባል ሆነ።

ማኅበሩ በዘጠኙ የብሪክስ+ ሀገራት ዩኒቨርሲቲዎች ጥምረት የተመሰረተ ሲሆን፤ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከመስራች ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አንዱ ሆኗል።

የብሪክስ+ ቡድንን ለመቀላቀል ፍላጎት ያላቸው የ 34 ሀገራት ዩኒቨርሲቲውዎችም የማኅበር አባል መሆናቸውን ከማኅበሩ ድረ-ገፅ ላይ የተገኘ መረጃ ያሳያል።

ዓለም አቀፍ ድጋፍ ማጠናከር፣ ልምድ ልውውጥ፣ የትምህርት ትብብርና ኔትወርኪንግ እንዲሁም ዓለም አቀፍ የአቅም ግንባታ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማጎልበት ማኅበሩ የሚያከናውናቸው ተግባራት ናቸው።

@tikvahuniversity
ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሜዲካል ኮሌጅ በኅብረተሰብ ጤና የማስተርስ ፕሮግራም (MPH) መደበኛ እና የእረፍት ቀናት አመልካቾች የመግቢያ ፈተና ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም ጠዋት 3:00 የሚሰጥ መሆኑን ገልጿል።

ለፈተና ስትሔዱ ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ መያዝ ያስፈልጋል።

የፈተና ቦታ፦
ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የአካዳሚክ ህንፃ

@tikvahuniversity
#JigjigaUniversity

ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም አዲስ ገቢ (1ኛ ዓመት) እና የሪሚዲያል ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት ከህዳር 4 እስከ 6/2017 ዓ.ም ድረስ መሆኑን አሳውቋል፡፡

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
-ከ8ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
- ስምንት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
- ብርድ ልብስ፣ አንሶላ እና የስፖርት ትጥቅ።

@tikvahuniversity
ልዩ የትምህርት ድጋፍ ዕድል ከፋዌ ኢትዮጵያ

ፋዌ ኢትዮጵያ ከማስተርካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር እድሚያቸው ከ 15 እስክ 25 የሆኑ ወጣቶችን በተለይም በዝቅተኛ ኢኮኖሚያዊ ደረጃ የሚገኙ ሴት እና የአካል ጉዳተኛ ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የከፍተኛ የትምህርት ዕድል ተጠቃሚ እንድትሆኑ ሲጋብዝ ታላቅ ደስታ ይሰማዋል፡፡

ዕድሉ ሁሉን አቀፍ የገንዘብ፣ የትምህርት እና ስልጠና እንዲሁም የማኅበራዊ ድጋፍን የሚያካትት ሲሆን፤ የትምህርት ድጋፉ የሚሰጠው በቴክኒክና ሙያ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ በሚሰጡ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስናና ተዛማጅ የትምህርት ዘርፎች (STEM) ኮርሶች ነው፡፡

ምዝገባው የሚካሔደው በአዲስ አበባ ጄኔራል ዊንጌት ፖሊቴክኒክ እና ተግባረ እድ ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች፣ በአዳማ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ፣ በሀዋሳ ፖሊቴክኒክ እና በሀዋሳ ተግባረ እድ ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች እንዲሁም በባህር ዳር ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በሚሰጡት መደበኛ የትምህርትና ስልጠና መርሐግብሮች ነው። አመልካቾች በ2014፣ 2015 ወይም 2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና የወሰዱ እና የ2017 ዓ.ም የቴክኒክና ሙያ መግቢያ ውጤት የሚያሟሉ መሆን አለባቸው፡፡

የማመልከቻ ቀናት ከጥቅምት 22-29/2017 ዓ.ም ባሉት የሥራ ቀናት ብቻ ይሆናል፡፡

ለበለጠ መረጃ፦
አዲስ አበባ 0911330024 / 0902662688
አዳማ 0911383055
ባህርዳር 0913042043
ሀዋሳ 0965679139
ድረ-ገፅ 👉 www.faweethiopia.org

ሴቶችን ማስተማር ህብረተሰብን ማስተማር ነው!

ምዝግባውም ሆነ የመረጣው ሒደተ ከማንኛውም ክፍያ ነጻ ነው።
#AAU

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የ2017 ትምህርት ዘመን ክፍያ ተመንን ይፋ አድርጓል።

በዩኒቨርሲቲው ሴኔት በፀደደቀ መመሪያ መሠረት አዲስ የማስተርስ እና የፒ.ኤች.ዲ. ፕግራሞች የክፍያ ተመን ከ2017 ዓ.ም የአንደኛ ሴሚስተር ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

በዚህም የማስተርስ እና የፒ.ኤች.ዲ. ፕሮግራሞች የምዝገባ ክፍያ ለኢትዮጵያውያን ብቻ በሴሚስተር ብር 300 መሆኑ ታውቋል፡፡

(የዩኒቨርሲቲው የክፍያዎች ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
#HaramayaUniversity

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የአንደኛ ዓመት የድኅረ-ምረቃ ተማሪዎች ኦንላይን ምዝገባ ጊዜ ከጥቅምት 28 እስከ ህዳር 3/2017 ዓ.ም መሆኑን ገልጿል።

በቅጣት ለመመዝገብ፦
ከህዳር 4-6/2017 ዓ.ም

Username እና Password ከሬጅስትራር ቢሮ በመውሰድ የኦንላይን ፖርታሉ ላይ መግባት ይችላሉ።

የኦንላይን ፖርታሉ የሚሠራው በዩኒቨርሲቲው ኔትወርክ ብቻ መሆኑ ተገልጿል።

(የምዝገባ ሒደቱ እና የሚያስፈልጉ ሰነዶች ዝርዝር መረጃ ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
#DireDawaUniversity

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ለተመደባችሁ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ መርሐግብር ተማሪዎች እንዲሁም በ2016 ዓ.ም በሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ህዳር 16 እና 17/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦

- የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ማስረጃ፣
- የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
- ስድስት 3X4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
- የመኝታ አልባሳት እና የስፖርት ትጥቅ።

Note:

በ2016 ዓ.ም አንደኛ ሴሚስቴር ጀምራችሁ በተለያዩ ምክንያቶች ዊዝድሮዋል በመሙለት ያቋረጣችሁ ተማሪዎች፥ የሞላችሁትን ቀሪ ፎርም ይዛችሁ መሔድ ይጠበቅባችኋል፡፡

የ2017 ዓ.ም አዲስ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ወደፊት እንደሚያሳውቅ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@tikvahuniversity
ልዩ የትምህርት ድጋፍ ዕድል ከፋዌ ኢትዮጵያ

ፋዌ ኢትዮጵያ ከማስተርካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር እድሚያቸው ከ 15 እስክ 25 የሆኑ ወጣቶችን በተለይም በዝቅተኛ ኢኮኖሚያዊ ደረጃ የሚገኙ ሴት እና የአካል ጉዳተኛ ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የከፍተኛ የትምህርት ዕድል ተጠቃሚ እንድትሆኑ ሲጋብዝ ታላቅ ደስታ ይሰማዋል፡፡

ዕድሉ ሁሉን አቀፍ የገንዘብ፣ የትምህርት እና ስልጠና እንዲሁም የማኅበራዊ ድጋፍን የሚያካትት ሲሆን፤ የትምህርት ድጋፉ የሚሰጠው በቴክኒክና ሙያ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ በሚሰጡ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስናና ተዛማጅ የትምህርት ዘርፎች (STEM) ኮርሶች ነው፡፡

ምዝገባው የሚካሔደው በአዲስ አበባ ጄኔራል ዊንጌት ፖሊቴክኒክ እና ተግባረ እድ ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች፣ በአዳማ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ፣ በሀዋሳ ፖሊቴክኒክ እና በሀዋሳ ተግባረ እድ ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች እንዲሁም በባህር ዳር ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በሚሰጡት መደበኛ የትምህርትና ስልጠና መርሐግብሮች ነው። አመልካቾች በ2014፣ 2015 ወይም 2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና የወሰዱ እና የ2017 ዓ.ም የቴክኒክና ሙያ መግቢያ ውጤት የሚያሟሉ መሆን አለባቸው፡፡

የማመልከቻ ቀናት ከጥቅምት 22-29/2017 ዓ.ም ባሉት የሥራ ቀናት ብቻ ይሆናል፡፡

ለበለጠ መረጃ፦
አዲስ አበባ 0911330024 / 0902662688
አዳማ 0911383055
ባህርዳር 0913042043
ሀዋሳ 0965679139
ድረ-ገፅ 👉 www.faweethiopia.org

ሴቶችን ማስተማር ህብረተሰብን ማስተማር ነው!

ምዝግባውም ሆነ የመረጣው ሒደተ ከማንኛውም ክፍያ ነጻ ነው።
2024/11/18 17:34:48
Back to Top
HTML Embed Code: