Telegram Web Link
#ማስታወሻ

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች #በመደበኛ እና #በሪሚዲያል ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች፣ የተቋም እና የትምህርት መስክ ምርጫችሁን በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እንድትሞሉ ትምህርት ሚኒስቴር ያራዘመው የመሙያ ጊዜ ነገ ጥቅምት 6/2017 ዓ.ም ይጠናቀቃል፡፡

የተቋም እና የትምህርት መስክ ምርጫችሁን በቀሩት ጊዚያት ይሙሉ!

@tikvahuniversity
💫 ከዳር እስከ ዳር አስተማማኙን ኔትወርካችንን እያሰፋን ነው! 👏

በፈጣኑ የሳፋሪኮም ኢንተርኔት አሁንም አንድ ወደፊት! አንድ ወደፊት እያልን እንገናኝ! የተመቸንን ሼር እናድርግ!👍ከወደድነው ❤️ጋር እንደልብ እንገናኝ!

አስተማማኙን ኔትወርክ ዛሬውኑ እንቀላቀል!

የቴሌግራም ቦታችንን https://www.tg-me.com/official_safaricomet_bot በመጠቀም የአየር ሰዓት ወይም ልዩ ልዩ ጥቅሎችን እንግዛ!

#MPESASafaricom #SafaricomEthiopia #1Wedefit #Furtheraheadtogether
የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ 34 የኅብረተሰብ ጤና ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡

ተማሪዎቹ ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ያለፉ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
#Update

ትምህርት ሚኒስቴር መስማት ለተሳናቸው የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የመቁረጫ ነጥብ ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህም በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ወስደው በመንግስት ተቋማት (ወጪያቸው ተሸፍኖ) የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል የመቁረጫ ነጥብ ያመጡ መስማት የተሳናቸው ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት እንደሚከተለው ይሆናል፦

► የተፈጥሮ እና የማኅበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከስድስት መቶ 192
► የተፈጥሮ እና የማኅበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከስድስት መቶ 186
በፕሪፓቶሪ ፕሮግራም የተፈጥሮ እና የማኅበራዊ ሳይንስ ወንድ ከሰባት መቶ 224
► በፕሪፓቶሪ ፕሮግራም የተፈጥሮ እና የማኅበራዊ ሳይንስ ሴት ከሰባት መቶ 217 እና ከዚያ በላይ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል፡፡

@tikvahuniversity
#AAU

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ2017 ዓ.ም የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች በፖርታል የማመልከቻ ጊዜ ሐሙስ ጥቅምት 7/2017 ዓ.ም ብቻ የሚከፈት መሆኑን አሳውቋል።

በመሆኑም የዶክመንታችሁን Hard Copy በተመሳሳይ ቀን ሐሙስ ጥቅምት 7/2017 ዓ.ም ከጠዋት 2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት 6 ኪሎ በሚገኘው ሬጅስትራር ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 203 እንድታስገቡ ተብሏል።

@tikvahuniversity
#AASTU #ASTU

አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በአማራ ክልል 2ኛ ዙር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች እንዲያመለክቱ ጥሪ አድርገዋል።

በአማራ ክልል በ2ኛ ዙር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስዳችሁ ትምህርት ሚኒስቴር ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያስቀመጠውን ዝቅተኛ የመቁረጫ ነጥብ 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ ተማሪዎች፣ በክልሉ ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት ሁለቱ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች በቅርቡ ያዘጋጁትን የመግቢያ ፈተና ሳትወስዱ የቀራችሁ፤ ነገር ግን ወደ ሁለቱ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች ለመግባት ፍላጎት ያላችሁ ተማሪዎች ከዛሬ ጥቅምት 5 እስከ 7/2017 ዓ.ም ድረስ ብቻ ከታች በተቀመጠው ሊንክ እንድትመዘገቡ ተብሏል።

የመመዝገቢያ ሊንክ 👇
http://stuoexam.astu.edu.et/

የመግቢያ ፈተናው በክልሉ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የፈተና ጣቢያዎች የሚሰጥ ሲሆን፤ የፈተናው ቀን በቀጣይ በሁለቱ ዩኒቨርሲቲዎች ይገለፃል ተብሏል፡፡

@tikvahuniversity
የትግራይ ክልል የትምህርት ዘርፍን መልሶ ለማቋቋም ከአምስት ቢሊዮን ዶላር በላይ ያስፈልጋል ተባለ፡፡

በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ከፍተኛ ውድመት እንደደረሰበት የተገለፀው የትግራይ ክልል፣ የትምህርት ዘርፍን ሙሉ ለሙሉ መልሶ እንዲያገግም ለማስቻል 5.65 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልገው ተነገረ።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ በጦርነቱ ምክንያት በትምህርት ቤቶች ላይ የደረሰውን የጉዳት መጠን ለመገምገም፣ በክልሉ ዋና ከተማ መቐለ እና በአምስት ዞኖች ውስጥ የሚገኙ 2,054 ትምህርት ቤቶች ላይ ጥናት አድርጓል፡፡

የጥናቱ ውጤት እንደሚጠቁመው በአጠቃላይ ከፊል ውድመት የደረሰባቸው 1,238 ትምህርት ቤቶች እንደሚገኙና ከእነዚህ በተጨማሪ 575 ትምህርት ቤቶች ደግሞ ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ተገልጿል፡፡ በትምህርት ቤቶች ሕንፃዎችና በትምህርት ግብዓቶች ላይ የደረሱ ውድመቶች እንዳሉበት በሰነዱ ተመላክቷል፡፡

በውይይቱ ተሳታፊ የነበሩ ማንነታቸው እንዳይገለፅ የጠየቁ የሪፖርተር ምንጮች እንደገለጹት፣ ከዚህ ባሻገር የትግራይ የትምህርት ዘርፉ ጉዳት ሌላው ገጽታ በጦርነቱ ምክንያት ከ10,000 በላይ መምህራን ሕይወታቸውን ማጣታቸው እንደሆነ በውይይቱ ላይ ተገልጿል፡፡

ጉዳዩን በተመለከተ ሪፖርተር ጋዜጣ ማብራሪያ የጠየቃቸው የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ዋና ኃላፊ ኪሮስ ጉዕሽ (ዶ/ር) ሙሉ ጥናቱ በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግ ጠቅሰው፣ ዝርዝር ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል። #ሪፖርተር

@tikvahuniversity
ትምህርት ሚኒስቴር ከማስተር ካርድ ፋውንዴሽን፣ ከአሪዞና ስቴት ዩኒቨርሲቲ፣ ከሻያሾኔ እና ከሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመሆን የኢ-ለርኒግ ከፍተኛ ትምህርትን ለማጎልበት (e-SHE) የተሰኘ የአምስት ዓመት ፕሮጀክት እየተገበረ ይገኛል።

በበይነ መረብ የሚሰጡ የስልጠና ዕድሎችን ለመጠቀም ተከታዩን ሊንክ በመጠቀም ይመዝገቡ 👇
https://courses.ethernet.edu.et/

@tikvahuniversity
#የሥራ_ቅጥር_ጥቆማ

ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የሥራ መስኮች አመልካቾችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

➤ የሥራ መደብ፦ በተለያዩ የሙያ መስኮች
➤ ተፈላጊ ባለሙያዎች ብዛት፦ 38
➤ የትምህርት ደረጃ፦ ከመጀመሪያ ዲግሪ ጀምሮ
➤ የሥራ ልምድ፦ አይጠይቅም
➤ የሥራ ቦታ፦ ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ
➤ የማመልከቻ ጊዜ፦ ከጥቅምት 4/2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት

የመመዝገቢያ አማራጭ፦
ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የብቃትና ሰው ሃብት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 4 ወይም በE-mail አድራሻ [email protected]

ተመዝጋቢዎች ለምዝገባ ስትሔዱ ከ8ኛ ክፍል ጀምሮ የተሟላ የትምህርት ማስረጃ ከማይመለስ ኮፒ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡ የፈተና ቀን ወደፊት በማስታወቂያ ይገለፃል ተብሏል፡፡

(ዩኒቨርሲቲው ያወጣው የቅጥር ማስታወቂያ ከላይ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity
በፀጥታ ችግር ምክንያት በሁለተኛ ዙር ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወሰዱ ደብረ ማርቆስ ከተማ የሚገኘው የክቡር ዶ/ር ሐዲስ ዓለማየሁ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት የወሰዱ ተማሪዎች ሁሉም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ማምጣታቸው ተገለፀ፡፡

ፈተናውን ከወሰዱ 33 ተማሪዎች መካከል 27 ተማሪዎች ከ500 በላይ ውጤት አስመዝግበዋል። ቀሪዎቹ ስድስት ተማሪዎችም የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸው ተገልጿል፡፡

ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ተማሪ ነፃነት መልካሙ በተፈጥሮ ሳይንስ መስክ በኢትዮጵያ 3ኛ የሚያደርገውን 570 ውጤት አስመዝግቧል። #አሚኮ

@tikvahuniversity
መስማት ለተሳናቸው የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የመቁረጫ ነጥብ

@tikvahuniversity
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የድኅረ ምረቃ ትምህርት አመልካቾች የምዝገባ ጊዜን እስከ ጥቅምት 29/2017 ዓ.ም ድረስ አራዝሟል፡፡

በዚህም አመልካቾች ለሁለተኛ ዲግሪ ትምህርት (በመደበኛ እና በተከታታይ መርሐግብር) እንዲሁም ለሦስተኛ ዲግሪ ትምህርት በተጠቀሰው ጊዜ ማመልከት ትችላላችሁ ተብሏል፡፡

በኦንላይን ለመመዝገብ👇
https://application.inu.edu.et/

@tikvahuniversity
ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የመደበኛ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜን በቅርቡ እንደሚያሳውቅ ገልጿል፡፡

በዩኒቨርሲቲው ማኅበራዊ ትስስር ገፆች በቅርቡጥሪ እንደሚደረግ የገለፀው ተቋሙ፤ እስከዛው ትክክለኛ ካልሆኑ የማኅበራዊ ትስስር ገፆች ከሚወጡ መረጃዎች እንዲጠበቁ ለተማሪዎቹ አስረድቷል፡፤

@tikvahuniversity
ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር እና በዩኒቨርሲቲው የተሰጠውን የሪሚዲያል ፈተና በተቋሙ የወሰዱ ተማሪዎች ውጤታቸውን ከዛሬ ጀምሮ ማየት እንደሚችሉ አሳውቋል፡፡

https://dku.edu.et/stud_result/index.php?con=2 ሊንክ በመጠቀምና በዩኒቨርሲቲው የተሰጣቹሁን Username በማስገባት ውጤታቹሁን ማየት የምትችሉ መሆኑን ዩኒቨርሲው ገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
#AASTU

አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በተከታታይ ትምህርት ፕሮግራም የመጀመሪያ ዲግሪ ለመማር በ Level IV/Diploma የትምህርት ደረጃ ላመለከቱ በመጀመሪያ ዲግሪ ለመቀጠል የመግቢያ ፈተና እሑድ ጥቅምት 10/2017 ዓ.ም ጠዋት 3፡00 ሰዓት እንደሚሰጥ ገልጿል፡፡

በ2017 ዓ.ም በተከታታይ የትምህርት ፕሮግራም በ Software Engineering እና በ Electrical & Computer Engineering የትምህርት መስኮች ላይ ብቻ በቂ አመልካቾች ስላመለከቱ ሁለቱ የትምህርት ክፍሎች ብቻ እንዲከፈቱ መወሰኑን ዩኒቨርሲቲው አስረድቷል፡፡

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity
ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታቸውን በተቋሙ ሲከታተሉ የነበሩና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤታቸውን ኦንላይን ማየት እንደሚችሉ ገልጿል፡፡

ተከታዩን ሊንክ በመጠቀም በዩኒቨርሲቲው የተሰጣቹሁን Username በማስገባት ውጤታቹሁን ማየት የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ውጤት ለማየት፦
https://www.slu.edu.et/remedial/index.php?fbclid=IwY2xjawF87TpleHRuA2FlbQIxMQABHRy6t7Qm6QrjVX6dWQXP2Tf7T0FetYe0oQW43itxh_NZSJnmtaVJjTZgQA_aem_MBlSF0PfU8yugqnKRa6sRQ

@tikvahuniversity
2024/11/06 00:15:33
Back to Top
HTML Embed Code: