Telegram Web Link
የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ውጤት መለቀቅን ተከትሎ በርካታ ዩኒቨርሲቲዎች አዲስ የድኅረ ምረቃ አመልካቾችን ለመቀበል ማስታወቂያ እያወጡ ይገኛሉ።

አመልካቾች በትምህርት ሚኒስቴር የተሰጠውን የመግቢያ ፈተና (NGAT) ማለፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡

(የተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች ያወጧቸው የጥሪ ማስታወቂያዎች ከላይ ተያይዘዋል፡፡)

@tikvahuniversity
#ክቡር_ኮሌጅ የአፍሪካ ቢዝነስ ስኩል አባልና ክህሎትን መሠረት ያደረገ ተግባራዊ የትምህርት አሰጣጥን የሚከተል ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ነው።

👉 በኢትዮጵያ ሙሉ ዕውቅና ያለው
👉 ከ18 ዓመት በላይ በትምህርት ኢንዱስትሪው የተሰማራ
👉 ምቹና ዘመናዊ በሆነ ስማርት የመማሪያ ክፍሎችና ግብዓቶች የተደራጀ

► በመጀመሪያ ዲግሪ
► በቴክኒክና ሙያ /TVET/ (level I-IV)
► የ12ኛ ክፍል የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) በቀን እና በማታ ተማሪዎችን ለመቀበል በምዝገባ ላይ ነን!

Website: https://kibur.net

አድራሻ፦ ጀሞ ሚካኤል ከአፍሪካ ህንፃ አጠገብ
☎️       0113854042 / 0904848586

Telegram: https://www.tg-me.com/kiburcollege
Facebook:  https://www.facebook.com/kiburcollege
በአዲስ አበባ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ለአምስት ዩኒቨርሲቲዎች የሚዲያ እና ተግባቦት መፅሐፍት ድጋፍ አድርጓል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ፣ ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ፣ ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ እና ወራቤ ዩኒቨርሲቲ የመፅሐፍት ድጋፍ የተደረገላቸው ዩኒቨርሲቲዎች ናቸው።

ድጋፉ በሀገሪቱ የሚዲያ ተቋማትና ጋዜጠኝነት እንዲጠናከር ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን ኤምባሲው ገልጿል።

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሙዚቃ ጥበባት ትምህርት ፕሮግራም በ2017 ዓ.ም በመደበኛው መርሐግብር የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር እንደሚጀምር አሳውቋል፡፡

በመሆኑም የ12ኛ ክፍል አጠናቃችሁ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጣችሁ፣ የሪሚዲያል ማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ እና ከተለያዩ ተቋሞች በስፖንሰር የመማር ፍላጎትና ተሰጥኦ ያላችሁ ተማሪዎች ከመስከረም 25/2017 ዓ.ም ጀምሮ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

የማመልከቻ ቦታ 👇
ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፔዳ ግቢ፣ የሲኒማና ቴአትር ጥበባት ትምህርት ክፍል

ለተጨማሪ መረጃ፦ 0918424663

@tikvahuniversity
#JigjigaUniversity

ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የ2ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ ነባር የቅድመ ምረቃ እና የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት መስከረም 22 እና 23/2017 ዓ.ም ሲሆን፤ ምዝገባ መስከረም 27 እና 28/2017 ዓ.ም እንደሚከናወን ገልጿል።

አዲስ በትምህርት ሚኒስቴር የምትመደቡ እና የሪሚዲያል ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች በሌላ ማስታወቂያ ጥሪ ይደረግላችኋል ተብሏል።

@tikvahuniversity
Empowering educators to utilize culturally relevant EdTech tools is crucial for engaging students and enhancing their learning experiences. Let's make education accessible for everyone. Discover how we can integrate local languages and cultural narratives into educational technology to create learning experiences that resonate with all Ethiopian students.

Tune in to Fana FM 98.1 on Monday, September 30th at 8:10pm for insights.

#EdTechMondays #EdTechMondaysEthiopia #Ethiopia #Africa #Education #EdTech #Tech #AddisAbaba #ICT #CulturallyResponsive #Inclusivelearning #CulturalRespect #EmpowerStudents #Inclusivelearning #Shega #mastercardfoundation
በ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስዳችሁ ወደ አርሲ ዩኒቨርሲቲ የምትመደቡ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ መረሐግብር ተማሪዎች፣ ዩኒቨርሲቲው የመግቢያ ቀናት ወደፊት እስከሚያሳውቅ በትዕግስት እንድትጠብቁ ጠይቋል።

@tikvahuniversity
አሶሳ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ለነበራችሁ እንዲሁም በ2017 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለምትመደቡ አዲስ የአቅም ማሻሻያ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲው አስካሁን ጥሪ አለማድረጉን ገልጿል።

በቀጣይ ጥሪ አስከሚደረግ በትዕግስት እንድትጠብቁ ዩኒቨርሲቲው ጠይቋል።

@tikvahuniversity
በ2017 የትምህርት ዘመን አዲስ የዩኒቨርሲቲዎች የቀን የምግብ በጀት ዋጋ ተመን ይፋ እንደሚደረግ ትምህርት ሚኒስቴር ባለፈው ሐምሌ መግለፁ ይታወቃል።

ይሁን እንጂ የ2017 ትምህርት ዘመን መጀመርንም ተከትሎ ዩኒቨርሲቲዎች አሁንም ቀድሞ በነበረው የበጀት አሰራር ተማሪዎቻቸውን እየመገቡ ይገኛሉ።

በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት የሰጡት የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ኮራ ጡሹኔ፣ የተሻሻለው አዲስ የበጀት አሰራር በቅርቡ ይለቀቃል ብለዋል።

"ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች አንድ አይነት የሜኑ በጀት ይሁን ወይስ በየአካባቢው የሚገኘውን ሀብት መሠረት ያደረገ በጀት ይሁን" በሚለው ላይ ውይይት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

ይሁን እንጂ የተሻሻለው አዲስ የሜኑ አሰራር በቅርቡ ይለቀቃል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፤ በዚህም የአንድ ተማሪ የቀን ወጪ ከ100 ብር በላይ እንደሚሆን ገልፀዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች በቀን አንድ ተማሪ ቁርስ፣ ምሳ እና እራት ለመመገብ በመንግሥት የሚመድብላቸው 22 ብር በጀት በቂ አለመሆኑን በተደጋጋሚ ያነሳሉ፡፡

ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ከተለያዩ በጀቶች በማዛወር በቀን እስከ 80 ብር በመመደብ ተማሪዎቻቸውን እየመገቡ እንደሚገኙ ይገልፃሉ፡፡

የዋጋ ትመናው ጊዜውን ያላገናዘበ በመሆኑ ማስተካከያ ሊደረግበት እንደሚገባ የተለያዩ አካላት ሲጠይቁ ይደመጣል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)፣ ጥናቶች "እስከ ነሐሴ 2016 ዓ.ም ድረስ ሥራዎች ተጠናቀው በአዲሱ የትምህርት ዘመን አዲስ የቀን ዋጋ ተመን ይፋ ይደረጋል" ብለው እንደነበር አይዘነጋም፡፡

@tikvahuniversity
ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የ2017 ትምህርት ዘመን መደበኛ ነባር የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜን አራዝሟል።

ምዝገባው ወደ መስከረም 30/2017 ዓ.ም እና ጥቅምት 1/2017 ዓ.ም መራዘሙን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

በ2017 ዓ.ም ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ለምትመደቡ አዲስ ገቢ ተማሪዎች እና በ2016 ዓ.ም በሪሚዲያል ፕሮግራም በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች ወደፊት ጥሪ ይደረግላችኋል ተብሏል።

@tikvahuniversity
#SamiTech

አዳዲስ ላፕቶፕች ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!!
@samcomptech

በጥራት፣ በብራንድ እና በባትሪ ቆይታ እጅግ አስተማማኝ የሆኑ ላፕቶፕች በተለያዩ ሞዴሎችና በፈለጉት ስክሪን መጠን ኮር እና ጀነሬሽን አሉን።

ላፕቶፕ ከመገዛትዎ በፊት ማወቅ ያለባቹሁን ወሳኝ ነገሮች እናስረዳዎታለን።

ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች፣ ለጌመሮች፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች ወ.ዘ.ተ ሁሉም አሉን! በላፕቶፖቻችን ጥራት አንደራደርም!

የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት ይሄን 👉 @samcomptech ተጭነው በቴሌግራም ማየት ይችላሉ።

@sww2844
0928442662 / 0940141114

https://maps.app.goo.gl/H3PM1NrTcQ4SWkK17
የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ውጤት መለቀቅን ተከትሎ በርካታ ዩኒቨርሲቲዎች አዲስ የድኅረ ምረቃ አመልካቾችን ለመቀበል ማስታወቂያ እያወጡ ይገኛሉ።

አምቦ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም ለሁለተኛ እና ለሦስተኛ ዲግሪ ፕሮግራም በቀን እና በተከታታይ መርሐግብር ለመከታተል የማመልከቻ ጊዜ እስከ መስከረም 20/2017 ዓ.ም መራዘሙን ገልጿል።

መቱ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በመደበኛ እና በሳምንት መጨረሻ ቀናት ትምህርት መርሐግብር የሁለተኛ እና የሦስተኛ ዲግሪ አመልካቾች እስከ መስከረም 25/2017 ዓ.ም ድረስ መመዝገብ ትችላላችሁ ብሏል።

አመልካቾች በትምህርት ሚኒስቴር የተሰጠውን ሀገር አቀፍ የድኅረ ምረቃ የመግቢያ ፈተና (NGAT) ማለፍ ይጠበቅባችኋል፡፡

@tikvahuniversity
የመውጫ ፈተና ለወደቁ ተማሪዎች ብቻ የሚሆን ቴምፖራሪ እንደሚዘጋጅ ተገለፀ።

የመውጫ ፈተና ወድቀው በድጋሜ መፈተን ለማይፈልጉ ተማሪዎች፣ ትምህርት ሚኒስቴር ዘንድሮው መፍትሔ እንደሚያስቀምጥ የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ኮራ ጡሹኔ ገልፀዋል።

በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት የሰጡት ሚኒስትር ዴኤታው፤ የመውጫ ፈተና ወድቀው በድጋሜ መፈተን ለማይፈልጉ ተማሪዎች የተማሩትን የሚገልፅ ቴምፖራሪ እንደሚዘጋጅ ጠቁመዋል።

የመውጫ ፈተና የወደቀ ተማሪ እንዴት ዓይነት ቴምፖራሪ እንደሚሰጠው እና ሥራ እየሠራ እንደገና መፈተን እንዲችል ሁኔታዎች ይመቻቻል ብለዋል።

@tikvahuniversity
2024/09/30 21:26:00
Back to Top
HTML Embed Code: