Telegram Web Link
የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ከመስከረም 8-10/ 2017 ዓ.ም ተሰጥቷል።

የብቃት ምዘና ፈተናው በ13 የጤና ሙያ መስኮች ለሦስት ተከታታይ ቀናት በተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተሰጥቷል።

ምስል፦ አክሱም ዩኒቨርሲቲ

@tikvahuniversity
#SPHMMC

ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌንየም ህክምና ኮሌጅ ለመጀመሪያ ጊዜ በከፍተኛ እንክብካቤ ህክምና የሰለጠኑ ሦስት ፌሎውስ Intensive Care Medicine Fellows (Intensivists) አስመርቋል።

የከፍተኛ እንክብካቤ ህክምና ፌሎውሺፕ ፕሮግራም መጀመር በሀገሪቱ የሚታየውን የዘርፉ ባለሙያዎች ፍላጎት ለማሟላት ጉልህ ድርሻ ይኖረዋል ተብሏል።

የፕሮግራሙ የመጀመሪያ ዙር ሦስት ተመራቂዎቹ በከፍተኛ እንክብካቤ ህክምና ትልቅ አበርክቶ ይኖራቸዋል ተብሏል።

@tikvahuniversity
#ESSS

የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይስን ሶሳይቲ በሥነ-ፈለክ፣ የሕዋ ምህንድስና እና የኤሮስፔስ ምህንድስና ዘርፍ ከአንደኛ ደረጃ እስከ ዩኒቨርሲቲ ላሉ ተማሪዎች ሲሰጥ የነበረውን ሥልጠና አጠናቋል።

ለዘጠኝ ቀናት በተሰጠው ስልጠና ከ250 በላይ ሠልጣኞች መሳተፋቸው ተገልጿል።

ሠልጣኞች የተማሩትን ቀድሞ ከነበራቸው የሳይንስ ዕውቀት ጋር በማጣመር በሥነ-ፈለክ፣ በሕዋ እና በኤሮስፔስ ምህንድስና የትምህርት ዓይነቶች ያዘጋጇቸውን ይዘቶች አቅርበዋል።

@tikvahuniversity
#ArbaMinchUniversity

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ነባር የቅድመ ምረቃ እና የድኅረ ምረቃ መደበኛ እና መደበኛ ያልሆኑ ፕሮግራሞች ተማሪዎች መግቢያ እሑድ መስከረም 19/2017 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡

በዕለቱ በየካምፓሶቻችሁ በመገኘት ሪፖርት እንድታደርጉ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

በቅጣት ምዝገባ መስከረም 20 እና 21/2017 ዓ.ም ብቻ ሲሆን፤ ትምህርት መስከረም 22/2017 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ነባር የ2015 እና የ2016 ባቾች እንዲሁም የሕክምናና ጤና ሳይንስ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ፕሮግራም ተማሪዎችን በቅርቡ መቀበሉ ይታወቃል፡፡

@tikvahuniversity
#MattuUniversity

መቱ ዩኒቨርሲቲ የነባር መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ መስከረም 20 እና 21/2017 ዓ.ም እንደሚከናወን አሳውቋል።

በመሆኑም በተጠቀሱት ቀናት በተቋሙ ሬጅስትራር ጽ/ቤት በአካል በመገኘት ሪፖርት አድርጉ ተብሏል። ትምህርት መስከረም 22/2017 ዓ.ም ይጀምራል።

አዲስ ገቢ የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች ምዝገባ የ NGAT ውጤት ከተገለፀ በኋላ ይከናወናል።

በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጣቹ ተማሪዎች፣ በ2017 ዓ.ም አዲስ ከሚመደቡ ተማሪዎች ጋር ጥሪ እንደሚደረግላችሁ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@tikvahuniversity
#AksumUniversity

ባሳለፍነውሳለፍነው ሳምንት መደበኛ ነባር ተማሪዎቹን የተቀበለው አክሱም ዩኒቨርሲቲ፣ በርካታ ተማሪዎች በተጠቀሱት ቀናት በአካል ያልተመዘገቡ ተጨማሪ የምዝገባ ጊዜ ሰጥቷል።

በዚህም በቅጣት ምዝገባ መስከረም 13/2017 ዓ.ም የሚከናወን መሆኑን ገልጿል።

በ2016 ዓ.ም በአክሱም ዩኒቨርሲቲ የሪሚድያል ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ቆይታችሁ ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች፣ በ2017 ዓ.ም አዲስ ከሚመደቡ ተማሪዎች ጋር ጥሪ እንደሚደረግ ተገልጿል።

@tikvahuniversity
መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ በባሌ ዞን ከሚገኙ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ 70 ተማሪዎች ሲሰጥ የቆየውን የስቴም ስልጠና አጠናቋል።

ስልጠናው ላለፉት ሁለት ወራት በዩኒቨርሲቲው የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስና እና ሂሳብ ማዕከል ተሰጥቷል።

@tikvahuniversity
በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ለግብርና መረጃ ናሙና ሰብሳቢዎች እና ተቆጣጣሪዎች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቋል፡፡

ስልጠናው በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚከናወን የግብርና መረጃ ናሙና የመሰብሰብ ፕሮጀክት፣ ሰብሳቢዎችን እና ተቆጣጣሪዎችን ለሥራው ብቁ ለማድረግ የተሰጠ ነው።

መንግሥት መሰል የግብርና ናሙና ቆጠራ ከ22 ዓመታት በፊት የሠራ ሲሆን፤ ለግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚ አስፈላጊ መረጃ ለመሰብሰብ የሚያስችል መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ስልጠናው በኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት፣ በትምህርት ሚኒስቴር፣ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና በዩኒቨርሲቲዎች ትብብር የተዘጋጀ ነበር፡፡

ምስል፦ አርባ ምንጭ፣ ወልቂጤ፣ ወልድያ እና አሶሳ ዩኒቨርሲቲዎች

@tikvahuniversity
ሰመራ ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዓመትና ከዚያ በላይ የዲግሪ ፕሮግራም የኤክስቴንሽን ተማሪዎች የ2017 ዓ.ም የአንደኛ ሴሚስተር ምዝገባ ከመስከረም 22 እስከ 24/2017 ዓ.ም ይከናወናል።

በቅጣት ምዝገባ ከመስከረም 27/2017 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 1/2017 ዓ.ም ይከናወናል ተብሏል።

@tikvahuniversity
#Update

የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ውጤት ይፋ ሆኗል።

በ2017 ዓ.ም የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች ለሚማሩ አመልካቾች የመግቢያ ፈተና ነሐሴ 30 እስከ ጳጉሜን 1/2016 ዓ.ም መሰጠቱ ይታወሳል።

የተፈታኞች ውጤት ዛሬ ይፉ ሆኗል። ተፈታኞች የምዝገባ ቁጥር / Username በማስገባት ውጤታችሁን በተከታዩ ሊንክ መመልከት ትችላላችሁ 👇

https://result.ethernet.edu.et/ngat_result

@tikvahuniversity
2024/10/04 03:22:39
Back to Top
HTML Embed Code: