Telegram Web Link
#AddisAbabaUniversity

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም በማታ መርሐግብር የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት አመልካቾች ልታሟላቸው የሚገቡ ከላይ ተያይዟል።

https://portal.aau.edu.et ወይም www.aau.edu.et ላይ የተመለከቱትን ዝርዝር የማመልከቻ መስፈርቶች በማሟላት መመዝገብ ትችላላችሁ ተብሏል።

ምዝገባ የሚያበቃው 👇
መስከረም 8/2017 ዓ.ም

@tikvahuniversity
#AddisAbabaUniversity

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም #በቀን_መደበኛ መርሐግብር በመንግስት ስኮላርሽፕ እና በግል ከፍላችሁ የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት ለመማር የምታመለክቱ ዝርዝር መስፈርቶችን በማሟላት በ https://portal.aau.edu.et ወይም www.aau.edu.et ላይ መመዝገብ ትችላላችሁ ተብሏል።

አመልካቾች የዩኒቨርሲቲውን የመግቢያ ፈተና (UAT) እና ዩኒቨርሲቲው ያወጣዉን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባችኋል፡፡

ምዝገባ የሚያበቃው 👇
መስከረም 8/2017 ዓ.ም

@tikvahuniversity
የአምቦ ዩኒቨርሲቲ የመደበኛ እና ተከታታይ ፕሮግራም ተማሪዎች ምዝገባ ከመስከረም 27-28/2017 ዓ/ም እንደሆነ ተገልጿል።

@tikvahuniversity
#ጥቆማ
#AASTU #ASTU

በ2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ገብተው በአፕላይድ ሳይንስ እና በኢንጂነሪንግ የትምህርት ዘርፎች ትምህርታችሁን መከታተል ለምትፈልጉ ተቋማቱ መስፈርቶችን ይፋ አድርገዋል።

ዩኒቨርሲቲዎቹ በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ወስደው 50% እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችን ተጨማሪ የመግቢያ ፈተና በኦንላይን በመስጠት ይቀበላሉ።

የትምህርት መስኮች

ሁለቱም ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ ኢንጂነሪንግ እና የአፕላይድሳይንስ መስኮች አመልካቾችን ይቀበላሉ። (የትምህርት መስኮችን ዝርዝር ከላይ በተያያዘው ምስል ይመልከቱ።)

የምዝገባ ጊዜ፡-
ከመስከረም 6 እስከ 13/2017 ዓ.ም

አመልካቾች በ https://stuoexam.astu.edu.et ወይም www.aastu.edu.et / www.astu.edu.et ላይ መመዝገብ ትችላላችሁ፡፡

የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ወደፊት ይገልፃል።

ለምዝገባ እና ለመግቢያ ፈተና ምንም አይነት ክፍያ የማይጠየቅ መሆኑ ተገልጿል።

@tikvahuniversity
#ETA

የዕውቅና ፈቃድ ተሰጥቷችሁ እየሠራችሁ የምትገኙ እንዲሁም ለተለያዩ የመንግሥት ተቋማት ተጠሪ ሆናችሁ ነገር ግን በፈቃድ አሰጣጥ ስርዓት ውስጥ ሳታልፉ ትምህርትና ስልጠና እየሰጣችሁ ያላችሁ ተቋማት ከዛሬ መስከረም 7/2017 ዓ.ም ጀምሮ በባለሥልጣኑ ቅጥር ግቢ በመገኘት ዳግም ምዝገባ እንድታደርጉ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አሳስቧል።

በዳግም ምዝገባ ሂደት ውስጥ ያልገባ ተቋም በመምሪያው መሠረት ከባለሥልጣኑ የወሰደው የማስተማር ፈቃድ በገዛ ፈቃዱ እንዳቋረጠ ተቆጥሮ ፈቃዱ የሚነጠቅ መሆኑን ባለሥልጣኑ ገልጿል።

@tikvahuniversity
#WolkiteUniversity

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ነባር የቅድመ-ምረቃ እና የድኅረ-ምረቃ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜን ይፋ አድርጓል።

በ2016 ዓ.ም የአንደኛ ዓመት ሁለተኛ ሴምስተር ትምህርት ያጠናቀቃችሁ የ"Natural Science, Social Science and Pre-Engineering" ቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች ምዝገባ መስከረም 19/2017 ዓ.ም ይከናወናል ተብሏል።

የሁሉም ነባር አራተኛ ዓመትና ከዚያ በላይ የቅድመ-ምረቃ እንዲሁም ነባር የድኅረ-ምረቃ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ መስከረም 27 እና 28/2017 ዓ.ም መሆኑ ተመልክቷል።

በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተካታትላችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎች ምዝገባ የሚከናወነው በ2017 ዓ.ም አዲስ ከሚመደቡ የፍሬሽማን ፕሮግራም ተማሪዎች ጋር እንደሆነ ተገልጿል።

@tikvahuniversity
🤩 የተወዳዳሪዎች ጥበብ እንደጉድ እየጎረፈ ላይክ እያደረጋችሁ ድጋፋችሁን እያሳያችሁ ነው?

ራሳችሁ የዲጂታል ሙዚቃ ውድድርን ለመቀላቀል ከፈለጋችሁ፦

🎥 የአንድ ደቂቃ የራሳችን ሙዚቃ ቪዲዮ በTikTok ላይ እንፖስት
🏷 #1Wedefit እና #የምትኖሩበት ከተማ አድራሻ ማስገባት እንዳንረሳ
📲 የTikTok ድረገጽ @Safaricomet ታግ እናድርግ

እንዝፈን! እንፖስት! እናሸንፍ!

መልካም ዕድል!

#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#FurtherAheadTogether #DigitalMusicChallenge
ይሳተፉ!

ትምህርት ሚኒስቴር ባዘጋጀው 'የትምህርት መረጃ አሰተዳደር ስርዓት ረቂቅ መመሪያ' ላይ የገብዓትና አስተያየት መሰብሰቢያ መድረክ አዘጋጅቷል።

ሚኒስቴሩ በረቂቅ መመሪያው ላይ የውይይት መድረክ ነገ መሰከረም 8/2017 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ጀምሮ አራት ኪሎ በሚገኘው የመስሪያቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ በመገኘት ሰነዱን ለማዳበር የሚያስችል ግብዓት እንዲሰጡ ተጋብዘዋል።

@tikvahuniversity
በአማራ ክልል የ2017 ትምህርት ዘመን የመጀመሪያ ቀን ትምህርት ዛሬ ተጀምሯል፡፡

በክልሉ በዚህ ዓመት 7 ሚሊዮን ተማሪዎችን መዝግቦ ለማስተማር እየተሠራ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ እየሩስ መንግስቴ ገልፀዋል።

እስካሁን ባለው የምዝገባ ሒደት 24 በመቶ ተማሪዎች እንደተመዘገቡ ተናግረዋል፡፡

በቀጣይ ቀናት ሁሉም እድሚያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናትን ወደ ትምህርት ቤት እንዲሄዱ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ኃላፊዋ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

@tikvahuniversity
የ2017 ትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሒደት በተለያዩ ክልሎች ተጀምሯል።

የመማር ማስተማር ሒደቱ በኦሮሚያ፣ በትግራይ፣ በጋምቤላ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ በሐረሪ ክልል እና በድሬዳዋ አስተዳደር በይፋ ተጀምሯል።

@tikvahuniversity
2024/09/30 21:36:46
Back to Top
HTML Embed Code: