Telegram Web Link
#MekelleUniversity

በ2016 ዓ.ም የተሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቅያ ፈተና ምክንያት የተቃረጠው ሰሚስተር ለማስጨረስ እና የ2017 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ለማስጀመር ዘንድ ሁለተኛ እና ከሁለተኛ ዓመት በላይ የሆኑ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መስከረም 04 - 05 /2017 ዓ.ም ባለው ግዜ ውስጥ በግቢ ተገኝተው ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

ሃገራዊ የስታቲስቲክስ ስልጠና በ ኣይናለም ግቢ, (MIT Campus) እየተሰጠ በመሆኑ የኣይናለም ግቢ (MIT Campus) ተማሪዎች ከላይ በተጠቀሰው ግዜ ሳይሆን መስከረም 11-12/ 2017ዓ.ም ወደ ግቢ ገብተው ሪፖርት እንዲያደርጉ ተብሏል።

በተካሄደው የሰላም ሚኒስቴር በጎ ኣድራጎት ዘመቻ ለመሳተፍ የኣንደኛ ዓመት የመጨረሻ ፈተና ያልወሰዱ ተማሪዎች ጥቅምት 06-07/ 2017 ዓ.ም በየግቢያቸው ሪፖርት እንዲያደርጉ ተብሏል። ሆኖም ግን ፈተናውን የወሰዱ (ያጠናቀቁ) የኣንደኛ ኣመት ተማሪዎች ጥቅምት 22-23/2017 ዓ.ም በየግቢያቸው ተገኝተው ሪፖርት እንዲያደረጉ ተብሏል።

የሪሜዳል ትምህርት መረሃግብር ሲከታተተሉ የነበሩ ተማሪዎች የ2017 ዓ. ም ኣዲስ ተማሪዎች ( Fresh Man) ቅበለ ጊዜ ወደፊት ስለሚገለጽ ከነሱ ጋር ይገባሉ ተብሏል።

@tikvahuniversity
የይሁኔ ወልዱ መታሰቢያ ደሴ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ያስፈተናቸውን ተማሪዎች በሙሉ አሳልፏል።

ትምህርት ቤቱ በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ያስፈተናቸው 65 ተማሪዎች ሁሉም ከ458 በላይ ውጤት አስመዝግበዋል፡፡

በትምህርት ቤቱ ከተፈተኑ 65 ተማሪዎች 45 ተማሪዎች ከ500 በላይ ነጥብ አስመዝግበዋል። ቀሪዎቹ 20 ተማሪዎች ከ458 እስከ 499 ነጥብ አምጥተዋል፡፡

በትምህርት ቤቱ የተመዘገበው ከፍተኛ ውጤት 574 ሲሆን፤ ዝቅተኛው ውጤት 458 እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ተማሪ ጌታቸው እያዩ 574 ነጥብ በማምጣት ከፍተኛውን ውጤት ማስመዝገቡን የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር በለጠ ኃይሌ ለአሚኮ ተናግረዋል።

@tikvahuniversity
#WolloUniversity

ወሎ ዩኒቨርሲቲ ለነባር መደበኛ ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል፡፡

በዚህም የሁሉም ነባር መደበኛ ተማሪዎች (ቅድመ-ምረቃ እና ድኅረ-ምረቃ) የ2017 ዓ.ም የመግቢያ ጊዜ መስከረም 10 እና 11/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

መስከረም 13/2017 ዓ.ም ትምህርት የሚጀመር መሆኑ ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
#DillaUniversity

ዲላ ዩኒቨርሲቲ ለሁሉም ነባር እና አዲስ ገቢ መደበኛ ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል።

በዚህም በዲላ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም የሁለተኛ ሴሚስተር ትምህርት ጀምራችሁ ሳታጠናቅቁ ከግቢ የወጣችሁ የ1ኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች በአካል ሪፖርት የማድረጊያ ቀናት መስከረም 6 እና 7/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የሌሎች ነባር የድኅረ ምረቃ እና የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት መስከረም 19 እና 20/2017 ዓ.ም እንደሆነ ተገልጿል።

በ2016 ዓ.ም በሪሚዲያል ፕሮግራም በዲላ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ እንዲሁም በ2017 ዓ.ም በፍሬሽማን ፕሮግራም በትምህርት ሚኒስቴር ዲላ ዩኒቨርሲቲ የምትመደቡ አዲስ ተማሪዎች ምዝገባ መስከረም 19 እና 20/2017 ዓ.ም ይከናወናል ተብሏል።

(የዩኒቨርሲቲው መልዕክት ከላይ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity
ቲክቫህ ለመላው ኢትዮጵያውያን በተለይም ለተማሪዎች ፣ መምህራን ፣ ከትምህርት ጋር ተያያዥ ስራዎች ላይ ለሚሰሩ ሠራተኞች በሙሉ አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የደስታ እና የስኬት እንዲሆን ይመኛል።

@tikvahuniversity
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ለመደበኛ ተማሪዎች ጥሪ አደርጓል።

የ2017 ዓ.ም አንደኛ ሴሚስቴር ምዝገባ/የተማሪዎች ቅበላ/ የሚካሄደዉ ከመስከረም 10 እስከ 11/2017 ዓ.ም መሆኑን ገልጿል።

@tikvahuniversity
የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ለመደበኛ ተማሪዎቹ ጥሪ አቅርቧል።

ነባር ቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሄደው መስከረም 27 እና 28/2017 ዓ.ም ሲሆን ትምህርት መስከረም 30/2017 ዓ.ም ይጀምራል።

ነባር የድህረ-ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት መስከረም 19 እና 20 ሲሆን መስከረም 23/2017 ዓ.ም ትምህርት የሚጀምር ይሆናል።

በ2016 ዓ.ም በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታቸውን የተከታተሉ የማለፊያ ውጤት ያመጡ እንዲሁም በ2017 ዓ.ም አዲስ በትምህርት ሚኒስቴር ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የሚመደቡ ፍሬሽማን ተማሪዎች ምዝገባ የሚከናወነው ጥቅምት 4 እና 5/2017 ዓ.ም ይከናወናል።

@tikvahuniversity
ዓዲግራት ዪኒቨርሲቲ በሳይንስ ሼርድ ካምፓስ ፕሮግራም ካስተማራቸውና በ2016 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ 21 ተማሪዎች 17ቱ (80.95 በመቶ) የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ማምጣታቸውን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@tikvahuniversity
የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ልዩ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ካስተማራቸውና በ2016 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ 57 ተማሪዎች 54ቱ (95 በመቶ) የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@tikvahuniversity
የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ልዩ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ካስተማራቸውና በ2016 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች 95.2 በመቶ የሚሆኑት የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ተማሪ ራጂ ተስፋዬ የትምህርት ቤቱን ከፍተኛ ውጤት ማለትም 568 ከ600 ማምጣቱ ተገልጿል።

@tikvahuniversity
#HarariEducationBureau

በ2016 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የተሻለ ውጤት በሀረሪ ክልል መመዝገቡን ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወቃል።

በሀረሪ ክልል ሁሉም ትምህርት ቤቶች ተማሪ ማሳለፍ መቻላቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ጌቱ ነገዎ ገልፀዋል።

ከዚህ ቀደም በክልሉ ሁለት ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪ ሳያሳልፉ መቅረታቸውን ያስታወሱት የቢሮው ኃላፊ፤ ዘንድሮ በክልሉ የሚገኙ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን አሳልፈዋል።

በ2015 ዓ.ም 7.1 በመቶ ተማሪዎች ማለፊያ ውጤት አስመዝግበው የነበረ ሲሆን፤ በ2016 ዓ.ም 13.3 በመቶ ተማሪዎች በክልሉ ማለፍ መቻላቸውን ጠቁመዋል።

በአገር አቀፍ ደረጃ ከተመዘገቡ ከፍተኛ ውጤቶች መካከል አራቱ በሀረሪ ክልል የተመዘገቡ መሆናቸውንም ገልፀዋል።

ይሁን እንጂ የተመዘገበው ውጤት አጥጋቢ አይደለም ያሉት ኃላፊው፤ በ2017 የትምህርት ዘመን የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የበለጠ ይሠራል ብለዋል።

@tikvahuniversity
#UniversityOfKabridahar

ቀብሪደሀር ዩኒቨርሲቲ ለነባር ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል።

በዚህም የ2ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ ነባር ተማሪዎች የ2017 ትምህርት ዘመን የመግቢያ ቀናት መስከረም 20 እና 21/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ላመጣችሁና በ2017 ዓ.ም ወደ ቀብሪደሀር ዩኒቨርሲቲ ለምትመደቡ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች በቅርቡ ጥሪ የሚደረግ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
#ASTU

አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለነባር መደበኛ ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል።

በዚህም የ2ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ ነባር መደበኛ የቅድመ እና የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች የ2017 ትምህርት ዘመን የምዝገባ ቀናት መስከረም 21 እና 22/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ትምህርት የሚጀመርበት ቀን መስከረም 23/2017 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል፡፡

በቅጣት ለመመዝገብ 👇
መስከረም 23 እና 24/2017 ዓ.ም

(የዩኒቨርሲቲው መልዕክት ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
#Update

የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና መርሐግብር

የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ከመስከረም 8-10/ 2017 ዓ.ም ይሰጣል።

የብቃት ምዘና ፈተናው መርሃሐግብር፦

መስከረም 8/2017 ዓ.ም
Medicine, Pharmacy, Anesthesia, Dental Medicine, Environmental Health, Psychiatric Nursing and Surgical Nursing.

መስከረም 9/2017 ዓ.ም
Medical Laboratory Science, Midwifery, Pediatric and Child Health Nursing, Medical Radiology Technology and Public Health.

መስከረም 10/2017 ዓ.ም
Nursing 

@tikvahuniversity
የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና የጥንቃቄ መልዕክት

የብቃት ምዘና ፈተናው ከመስከረም 8-10/ 2017 ዓ.ም ይሰጣል።

► እያንዳንዱ ተፈታኝ ከሚፈተንበት ቀን አንድ ቀን ቀደም ብሎ ጠዋት 3፡00 ሰዓት በመፈተኛ ጣቢያ በመገኘት ስለፈተናው አሰጣጥ ቅድመ ገለፃ መከታተል፣ የቅድመ ፈተና መለማመጃ ጥያቄዎችን መስራት እና የመፈተኛ ክፍሉን መለየት ይኖርበታል።

► በፈተናው ዕለት ተፈታኞች ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ (የቀበሌ መታወቂያ፣ ፓስፖርት፣ መንጃ ፍቃድ ወይም ሌላ በግልጽ የሚታይ ሕጋዊ መታወቂያ) ይዛችሁ መገኘት ይኖርባችኋል፡፡

► ምንም አይነት የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ (ስልክ፣ የእጅ ሰዓት፣ መነጽር (የተረጋገጠ የዕይታ ችግር ከሌለ በስተቀር)፣ ቦርሳ እና ሌሎች እቃዎች፣ ማጣቀሻዎች እንዲሁም ባዶ ወረቀት፣ ምግብ ወይም መጠጥ (የተረጋገጠ የጤና ችግር ከሌለ በስተቀር) ወደመፈተኛ ማዕከል ይዞ መግባት አይፈቀድም፡፡

► በፈተናው ወቅት ተመዛኞች በሁለቱም ክፍለ ጊዜ (ጠዋት እና ከሰዓት) አቴንዳንስ ላይ በአግባቡ መፈረም ይኖርባችኋል።

► ማንኛውም ተመዛኝ ወደ ፈተና ጣቢያ ሲሔድ ሲስተሙ የሚሰጠውን QR Code ያለው የፈተና መግቢያ (ስሊፕ) Print አድርጎ ካልያዘ ፈተናውን መውሰድ አይችልም፡፡

► የመፈተኛ ጣቢያ ኦንላይን በመረጣችሁት መሰረት ስም ዝርዝራችሁን https://drive.google.com/drive/folders/17QzuVtjm4Uh3yQhA-teNFt7PRDqBc0Ft?usp=sharing በመጫን መመልከት ይኖርባችኋል፡፡

► ተመዛኞች ስማቸው ከተጠቀሰበት ተቋም ውጪ ፈተናውን መውሰድ አትችሉም፡፡

► ጎንደር ዩኒቨርሲቲ (ቴዎድሮስ ካምፓስ) የመፈተኛ ጣቢያ የመረጣችሁ ተመዛኞች ወደ ዩኒቨርሲቲው ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የተዘዋወራችሁ መሆኑ ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
#SalaleUniversity

ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ለነባር መደበኛ ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል።

በዚህም 1ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናችሁ ነባር የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች የ2017 ትምህርት ዘመን የምዝገባ ቀናት መስከረም 20 እና 21/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

@tikvahuniversity
#የቴክኖ የአዲስ ዓመት ልዩ የበዓል ስጦታ!

የአዲስ ዓመት ልዩ ስጦታ ከቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ!
ከየትኛውም የቴክኖ ሱቅ የቴክኖ ስማርት ስልክን ሲገዙ አብሮዎት ካለ ወዳጅ ዘመድ ወይም ጓደኛ ጋር ፎቶ በመነሳት የማኅበራዊ ገፅዎት ላይ በመለጠፍ እና ብዙ ላይክ በማግኘት የዱባይ ደርሶ መልስ የቢዝነስ ክላስ የአውሮፕላን ትኬት፣ ላፕቶፖች፣ የቴክኖ ስማርት ስልኮች እና ገደብ አልባ የኢንተርኔት ፓኬጆችን ይሸለሙ፡፡

የውድድሩ መመሪያ
1. የቴክኖ ኢትዮጵያን ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ቲክቶክ ገፆችን ፎሎው ያድርጉ፡፡
2. የተነሱትን ፎቶ በመረጡት ማኅበራዊ ሚዲያ ሲለጥፉ የቴክኖ ኢትዮጵያን ገፅ ከፖስትዎት ጋር ታግ ያድርጉ፡፡ ብዙ ላይክ እና ኢንጌጅመንት ያገኘው ተሸላሚ ይሆናል፡፡

Tag ሲያደርጉን
ለ Facebook @ TecnoEt https://www.facebook.com/share/KpViroSyJgPe1bML/?mibextid=qi2Omg
ለ Instagram @ TecnoMobileEthiopia https://www.instagram.com/tecnomobileethiopia?igsh=cjdwdjQzbGlvaDV1
ለ TikTok @ TecnoEt
https://www.tiktok.com/@tecnoet?_t=8pQuOpSYlGP&_r=1 ሜንሽን ማድረግ እንዳይረሱ።
በተጨማሪም #TecnoEt2017 ኪወርድን መጠቀም እንዳይረሱ!
2024/10/01 19:23:56
Back to Top
HTML Embed Code: